75387 Criminal law/ principle of legality/ confiscation of property

ፍ/ቤቶች በወንጀል ረገድ የሚሰጧቸው ማናቸውም ውሣኔ በወ/ህ/አ. 2 የተደነገገውን የህጋዊነት መርህ መሠረት በማድረግ መሆን ያለበት ስለመሆኑ፣ ፍ/ቤቶች በወንጀል ጉዳይ ንብረት ወይም ሀብት እንዲወረስ ወይም ለመንግስት ገቢ እንዲሆን በሚል ውሣኔ ለመስጠት የሚችሉት በወንጀል ህግ በግልጽ የተደነገገ ድንጋጌ የተመለከተ እንደሆነ ብቻ ስለመሆኑ፣  በወንጀል ጉዳይ አንድ ንብረት (ሀብት) እንዲወረስ ወይም ለመንግስት ገቢ እንዲሆን ሊወሠን የሚችለው ንብረቱ (ሀብቱ) አንድን ሰው ለወንጀል ሥራ እንዲያነሳሳ ወይም ወንጀሉን ለመስራት እንዲረዳው ወይም ደግሞ ወንጀሉን ለፈፀመበት ዋጋ እንዲሆነው የተሰጠው ወይም ሊሠጠው የታቀደን ማንኛውም ጥቅም የተመለከተ ንብረት (ሀብት) ስለመሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ ስለመሆኑ ወይም ንብረቱ (ሀብቱ) የወንጀል ድርጊቱን ለመፈፀም ያገለገለ ወይም ሊያገለግሉ የሚችሉ ወይም የወንጀል ተግባር ፍሬ የሆኑ ማናቸውም ነገሮች ጋር የተያያዘ ወይም የተመለከተ እንደሆነ ስለመሆኑ፣ የወ/ህ/አ. 98,100,140, 2(1) (2)

Download Cassation Decision