75788 civil procedure/ jurisdiction/ local jurisdiction/ execution of judgment/ procedure in execution of judgment

የፍ/ቤቶች የግዛት ስልጣን በዋነኛነት መሠረት የሚያደርገው ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ጉዳይ የተፈጠረበት ቦታ ለተከራካሪ ወገኖች የሚኖረውን አመቺነት ሲሆን የሥረ ነገር ስልጣን መሠረት የሚያደርገው ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ጉዳይ ይዘት፣ የተከራካሪ ወገኖችን መብትና ጥቅም ክብደትና መጠን እንዲሁም የጉዳዩን የውስብስብነት ደረጃ ስለመሆኑ፣  ፍርድን የማስፈፀም ጉዳይ በስረ ነገር ክርክር ተረጋግጠው የፍርድ ሀይል ያገኙትን የተከራካሪ ወገኖች መብቶችና ግዴታዎች በሥነ ሥርዓት ህጉ የተደነገገውን የአፈፃፀም ስርዓት ተከትለው እንዲፈፀሙ ከማድረግ ውጪ አዲስ መብትና ግዴታ የሚቋቋምበት ሂደት ስላለመሆኑና የማስፈፀም ስልጣን በመርህ ደረጃ የፍ/ቤቶች የሥረ ነገር ስልጣንን የሚከተል ስለመሆኑ፣  አስፈላጊ እና ተገቢ በሆኑ ሁኔታዎች ሥረ ነገሩን የወሰነ ፍ/ቤት በአፈፃፀም ጉዳዮችን በውክልና የሥረ ነገር ስልጣን ለሌለው ፍ/ቤት ሊያስተላልፍ ስለመቻሉ፡ አዋጅ ቁ. 25/88 አንቀጽ 5(2) የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 371, 372, 9, 10

Download Cassation Decision