79465 civil procedure/ third party intervention/ third party defendant

በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.43 መሠረት ወደ ክርክር እንዲገባ የተደረገ 3ኛ ወገን በክርክሩ ሂደት ሊያነሣ ስለሚችለው የክርክር አይነትና አድማስ፣  3ኛው ወገን ሊያነሣ የሚችላቸው የክርክር ፈርጆች በአንድ በኩል ከተከሣሽ ጋር ሆኖ ድርሻ ክፍያ ወይም ስለተከሣሽ ሆኖ የካሣ ክፍያ የመክፈል ግዴታ ያለበት መሆኑን ተቀብሎ በተከሣሽ እግር ተተክቶ ተከሣሽ ለከሣሽ ኃላፊነት የማይኖርበት መሆኑን፣ ኃላፊነት አለበት የሚባል ቢሆን እንኳን ሊከፈል የሚገባው የካሣ ክፍያ መጠን ላይ ከከሣሽ ጋር ንጽጽር በማድረግ መሟገት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ድርሻ ወይም ካሣ ለመክፈል ለተከሣሽ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ግዴታ የለብኝም በማለት መከራከር ስለመሆናቸው፤  3ኛ ወገን ጣልቃ ገብ በክርክር ሂደቱ መሟገት የሚችለው ከተከሣሽ ጋር ብቻ ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣  የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 43 አስፈላጊነት ተከታታይ ክስ ሳይኖር ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች በአንድነት እንዲታዩ በማድረግ የኃላፊነት መጠኑን እንዲሁም ከፋዩን ወገን በመለየት የመጨረሻ እልባት ለመስጠት ስለመሆኑ፣  በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 43 መሠረት ጣልቃ የሚገባ ወገን ከመነሻውም ከተከሳሹ ጋር የህግ ወይም የውል ግንኙነት የለኝም በማለት ክርክር ያቀረበ እንደሆነ በመካሄድ ላይ ባለው ክርክር ተሣታፊ ሊደረግ የሚችልበት አግባብ የማይኖር ስለመሆኑና ይህን መሰል ክርክር ራሱን በቻለ ሌላ መዝገብ ታይቶ ሊወስን የሚገባ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 43(1),76 የፍ/ብ/ህ/ቁ.1896,1897,1908,1909 የንግድ ህግ ቁ.687,688,683

Download Cassation Decision