92020 extracontractual liability law/ contract of carriage/ accident/ liability/ constitution/ children

ጥቅምን መሠረት ባላደረገ ሁኔታ ህፃናትን (እድሜው ለአካለ መጠን ያልደረሰ ሰውን) አሳፍሮ በመጓዝ ወቅት በደረሰ አደጋ ምክንያት በህፃናቱ ላይ ጉዳት የደረሰ እንደሆነ የተሽከርካሪው ባለቤትና በወቅቱ በተሽከርካሪው ሲገለገል የነበረ ወይም ሹፌሩ የጉዳት ካሣ የመክፈል ኃላፊነት የሚኖርባቸው ስለመሆኑ፣  የተሽከርካሪ ባለቤት የሆነ ሰው ጥቅም በሌላው ግንኙነት መነሻ በተሽከርካሪው ተሳፍሮ ሲጓዝ በነበረ ሰው ላይ ለሚደርስ የአደጋ ጉዳት ካሣ ለመክፈል የማይገደድ ቢሆንም ጉዳቱ የደረሰው ከፍተኛ ጥንቃቄና እንክብካቤ ሊደረግላቸው በሚገባ ህፃናት ላይ በሆነ ጊዜና ህፃናቱም ጥንቃቄ ባልተሞላበት ሁኔታ በተሽከርካሪው ላይ የተጫኑ (የተሣፈሩ) እንደሆነ የተሽከርካሪው ባለቤት የጉዳት ካሣ የመክፈል ኃላፊነት የሚኖርበት ስለመሆኑ፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 36(2), 15, 25 የህፃናት መብቶች ስምምነት አንቀጽ 3, 6(1) የአፍሪካ ህፃናት መብቶችና ደህንነት ቻርተር አንቀጽ 4(1), 5(1) የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2126(2), 2127, 2130 2131, 2089(2), 2081(1)

Download Cassation Decision