constitution (cassation)

  • የሕግ ክርክሮችን በሰበር ማየት /ማስተናገድ/ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግስት ለፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የተሰጠ ስልጣን (power) ስለመሆኑ በግልግል ዳኝነት (arbitration) የታየ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ተዋዋይ ወገኖች የይግባኝ መብትን ለማስቀረት የሚያደርጉት ስምምነት ጉዳዩን በሰበር ችሎት ከመታየት የማያግድ ስለመሆኑ (ከዚሀ ቀደም በሰበር ችሎት የተሰጠው የሕግ ትርጉም የተለወጠ ስለመሆኑ፡፡) የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 80/3 (ሀ), አዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2 (4), አዋጅ ቁጥር 25/88, የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 350(2) 351 እና 356

    Download Cassation Decision

  • የፌዴሬሽን ምክር ቤት የኢፌዴሪ ህገ መንግስትን ለመተርጐም ባለው ስልጣን ተጠቅሞ የሚሰጠው ውሣኔ የመጨረሻና ጉዳዩ በሚመለከተታቸው አካላት መከበርና መፈፀም ያለበት ስለመሆኑ፣  የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ቦርድ የሚቀርብለትን አቤቱታ ህጋዊነት መርምሮ በመወሰን ሂደት ከፊል የዳኝነት ስልጣን ያለው አካል (quasi judicial body) እንደመሆኑ መጠን በህገ መንግስቱ የተጠበቁትን ፍትህ የማግኘት፣ የመሰማትና በእኩል ሚዛን የመታየት (የመዳኘት) መብት በሚያስከበር መልኩ ክርክሮችን ሊያስተናግድና ሊወስን የሚገባ ስለመሆኑ፣ የኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 62(1),37 አዋጅ ቁ. 251/93 አንቀጽ 3(1),56(1) አዋጅ ቁ. 87/86 አንቀጽ 8,9 የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 337, 336, 339

    Download Cassation Decision

  • በወንጀል ሕግ ቁጥር 543 እና 567 መሰረት አንድ ሰው በአንድ ጊዜ ሊጠየቅ ስለሚችልበት አግባብ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 543,567

    Download Cassation Decision

  • የፌዴራል ጉዳይን በውክልና ስልጣን ተመልክቶ በክልል ፍርድ ቤት ውሣኔ የተሰጠበትን ጉዳይ መሰረት በማድረግ የይግባኝ አቤቱታ ማቅረብ ስለሚቻልበት ሁኔታ /አግባብ/ የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመጀመሪያ ደረጃ በሚነሳ ክርክር ላይ እንደ ፌ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ብሎም በይግባኝ ደረጃ ባለ ክርክር ደግሞ እንደ ፌዴራል ይግባኝ ሰሚ ከፍተኛ ፍ/ቤት ሆኖ የፌዴራል ጉዳዮችን ለማስተናገድ የሚያስችል የውክልና ስልጣን ያለው ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 322/95 የተወሰኑ የክልል ጠቅላይ ፍ/ቤቶች በህገ መንግስቱ ተሰጥቷቸው የነበረውን የፌዴራል ጉዳዮችን በመጀመሪያ ደረጃ ስልጣናቸው የማስተናገድ የውክልና ስልጣንን ብቻ የሚያስቀር እንጂ በይግባኝ ያላቸውን ስልጣን ጭምር የሚያስቀር ስላለመሆኑ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80/2/, /5/ አዋጅ ቁ. 322/95

    Download Cassation Decision

  • የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት የክልል ጠቅላይ ፍ/ቤቶች ሰበር ችሎት በክልል ጉዳዮች ላይ የሰጡትንና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበትን ውሣኔ ለማረም ስልጣን ያለው ስለመሆኑ የሰበር ስርዓት በባህሪው ከይግባኝ ሥርዓት የተለየ ስለመሆኑና በሰበር ደረጃ ተጨማሪ ምስክሮችንና ማስረጃዎችን አስቀርቦ መስማትና የፍሬ ነገር ጉዳዮችን ተቀብሎ ማስተናገድ አግባብነት የሌለውና ህገ-ወጥ ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ህገመንግስት አንቀፅ 80(3)ለ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.343(1)

    Download Cassation Decision

  • በተከራካሪዎች ፈቃድ ላይ በተመሰረተ ሁኔታ በህግ ስልጣን ባላቸው የሸሪዓ ፍ/ቤቶች ክርክር ተካሂዶ በፍርድ ያለቀን ጉዳይ በተመለከተ እንደ አዲስ በመደበኛ ፍ/ቤት ክስ ሊቀርብ የማይችል ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.188/92 አንቀፅ 4(2), 5(4) የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 78(5), 34(5)

    Download Cassation Decision

  • በአንድ ጉዳይ ድጋሚ ክስ ወይም ድጋሚ ቅጣት (principle of double jeopardy) ክልክል ስለመሆኑ የተደነገገው መርህ ሊተረጐም ስለሚችልበት አግባብ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 23 የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.42(1)(ሀ)

    Download Cassation Decision

  • የክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ባለው የውክልና ስልጣኑ በዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የተሰጠን ውሣኔ የለወጠው ከሆነ ጉዳዩ ለፌዴራል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት ከመቅረቡ በፊት ለፌ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት መቅረብ ያለበት ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 80(3)(ሀ), (2)(4) አዋጅ ቁ.322/95 አዋጅ ቁ.25/88 አንቀፅ 9(2), 5(2)

    Download Cassation Decision

  • በወንጀል የተከሰሱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በግላቸው ጠበቃ ለማቆም የማይችሉ በሆነ ጊዜ በመንግስት ወጪ የጠበቃ ድጋፍና እርዳታ ሊያገኙ የሚችሉበት አግባብ፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 20(5) አዋጅ ቁ.27/88 አንቀፅ 35 አዋጅ ቁ.123/90 አዋጅ ቁ.27/885

    Download Cassation Decision

  • ሃይማኖታዊ ከሆኑ አለመግባባቶች ጋር በተያያዘ ፍ/ቤቶች የአምልኮት ሥርዓትን ሆነ ሃይማኖታዊ ህገ-ደንቦችን በመተርጐም ውሣኔ ለመስጠት የማይችሉ ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 11(1)(3), 37(1)

    Download Cassation Decision

  • የመሬት ይዞታና በመሬት የመጠቀም መብት ያለው ወገን በውል ለ3ኛ ወገን ሊያስተላልፍ ስለሚችለው የመብት አድማስ በመሬት የመጠቀም መብት የተላለፈለት ሰው በመሬቱ ላይ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረት ያፈራ እንደሆነ ንብረቱን አፍርሶ (ነቅሎ) የመውሰድ መብትን ብቻ ሊያገኝ የሚችል ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 40(3), (4) አዋጅ ቁ.456/97 የኦሮሚያ ብ/ክ/መ/አዋጅ ቁ.130/99 አንቀፅ 6

    Download Cassation Decision

  • የመሬት ባለ ይዞታ የሆነና በመሬቱ የመጠቀም መብት ያለው ሰው ለሁለት ዓመት ያህል መሬቱን በመተው ከአካባቢው ከጠፋ የመሬት ባለይዞታ የመሆንና በመሬቱ የመጠቀም መብቱ ቀሪ የሚሆን ስለመሆኑ በገጠር የእርሻ መሬት ላይ አርሶአደሮች ያላቸውን የይዞታና የመጠቀም መብት መደፈር ጋር በተያያዘ የሚነሣ ጥያቄ በ10 ዓመት ይርጋ የሚታገድ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.456/97 የኦሮሚያ ብ/ክ/መ/አዋጅ ቁ.130/99 የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 40(4) የፍ/ብ/ህ/ቁ 1677(1)(3), 1845

    Download Cassation Decision

  • ማንኛውም ሰው በወንጀል ህግና ሥርዓት መሠረት ተከስሶ የመጨረሻ በሆነ ውሣኔ ጥፋተኝነቱ በተረጋገጠበት ወይም በነፃ በተለቀቀበት ወንጀል እንደገና አይከሰስም ወይም አይቀጣም (Principle of Double Jeopardy) በሚል የሚታወቀው የወንጀል ህግ መርህ ሊተረጐምና ሥራ ላይ ሊውል የሚችልበት አግባብ፣ አንድ በወንጀል የተከሰሰ ሰው በድጋሚ የቀረበበትን የወንጀል ክስ በአንድ ጉዳይ በድጋሚ ያለመከሰስና ያለመቀጣት መብቴ ተጥሷል በሚል ክርክር ለማቅረብ ሊሟሉ ስለሚገቡ ህጋዊ መስፈርቶች፣ ዐቃቤ ህግ በአንድ ተከሳሽ ላይ የወንጀል ክስ ከማቀርቡ በፊት ተከሳሹ አንድ ወንጀል በመፈፀም ሀሣብ የሠራው አንድ የወንጀል ድርጊት ያስከተላቸውን ወይም ሊያስከትላቸው የሚችላቸውን ውጤቶች ሁለተናዊ በሆነ መንገድ በማገናዘብ አግባብነት ያላቸውን የህግ ድንጋጌዎች በመለየትና በመጥቀስ የወንጀል ክሱን በጥንቃቄ የማቅረብ ግዴታ ያለበት ስለመሆኑ፣ የወ/ህ/አ 2(5), 24(1) የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 130,131, 41, 111, 112 የኢ.ፌ.ዲ.ሪ.ህግ መንግስት አንቀጽ 23,13(2)

    Download Cassation Decision

  • ከባልና ሚስት ጋብቻና ፍቺ ጉዳይ ጋር በተገናኘ የቀረበን ጉዳይ ስልጣን ያለውና ተከራካሪዎቹ ለመዳኘት ፈቃዳቸውን የገለፁለት የሽሪአ ፍ/ቤት ለመዳኘት ፈቃደኛ አለመሆኑን በመግለጽ መዝገቡን የዘጋው እንደሆነ መደበኛ ፍ/ቤት ጉዳዩን ማስተናገድ የሚገባው ስለመሆኑ፣ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. አንቀጽ 37(1), 34(5), 78(5),

    Download Cassation Decision

  • ተከሳሽ የቀረበበትን የወንጀል ክስ በተመለከተ በመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያነት ሊያቀርባቸው ስለሚችላቸው መከራከሪያዎች  ተከሳሽ በመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያነት የሚያቀርባቸው መቃወሚያዎች በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 130 ላይ የተመለከተቱት ጉዳዬች ጋር ብቻ በተገናኘ ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣  ማንኛውም ሰው የወንጀል ክስ ሲቀርብበት የተከሰሰበት የወንጀል ድርጊት በተፈፀመበት ጊዜ ድርጊቱን መፈፀሙ ወይም አለመፈፀሙ ወንጀል መሆኑ ካልተደነገገ በስተቀር ሊቀጣ የማይችልና ወንጀሉ በተፈፀመበት ጊዜ ተፈፃሚ በነበረው ህግ ከተመለከተው የቅጣት ጣሪያ በላይ ሊቀጣ የማይችል ስለመሆኑ፣  የወንጀል ህግ ወደ ኋላ ተመልሶ የማይሰራ ስለመሆኑና ዳኞች ወንጀሉ በተፈፀመበት ጊዜ ክስ የቀረበበት ድርጊት ወንጀል ስለመሆኑ የሚደነግገው ህግ ፀንቶ በሥራ ላይ ከመዋሉ በፊት መሆኑን ከተረዱ በማናቸውም ጊዜ አንስተው ውሣኔ ለመስጠት የሚችሉ ስለመሆኑ፣  ፍ/ቤቶች በዐ/ህግ የቀረበ የወንጀል ክስ በህገ-መንግስቱና በወንጀል ህጉ የሰብዓዊ መብቶችን ለማስከበር የተቀመጡ መርሆዎችና ድንጋጌዎችን የሚያሟሉ መሆን አለመሆኑን በመመርመር የመወሰን ግዴታ ያለባቸው ስለመሆኑ፣ የኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 5(2) ,13(1), 22(1 ) የወ/ህ/አ. (414/96)3,402,419,5(2) የወ/ህ/ቁ.(214/74) አለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ቃል ኪዳን ስምምነት (ICCPR) አንቀጽ 15(1) የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 130(2)(1)

    Download Cassation Decision

  • የኮንዶሚኒየም ቤትን በጋብቻ ወቅት እያሉ የደረሳቸው ባልና ሚስት የቤቱ ቅድመ ክፍያ በጋብቻ ወቅት ከተፈራ የጋራ ሀብት የተከፈለ እንደሆነና ቤቱን ለማሳመርና ለሌሎች ተያያዥ ወጪዎች ከጋራ ሀብቱ ወጪ በማድረግ ጥቅም ላይ በዋለበት ሁኔታ ጋብቻው በፍቺ የፈረሰ እንደሆነ ቤቱ ለተጋቢዎቹ፣ ሊከፋፈል ስለሚችልበት አግባብ፣ እንዲሁም በፍቺ ጊዜ እኩል መብት የሚኖራቸው ስለመሆኑ፣ የኢፌዲሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 35(1)  በህገ መንግስቱ የተረጋገጠላቸውን ቤተሰብ የመመስረት መብት በመጠቀም ጋብቻ የፈፀሙ ወንዶች እና ሴቶች በጋብቻው አፈፃፀም፣ በጋብቻው ዘመን

    Download Cassation Decision

  • በአንድ ወቅት የነበረን የተገነባ የመንገድ ደረጃ መነሻ (መሠረት) በማድረግ በመንገዱ ግራ ቀኝ አዋሣኝ በሆነ ይዞታ ላይ ተገቢውን ርቀት በመጠበቅ ንብረትን ያፈራ ሰው በሌላ ጊዜ የመንገዱ ደረጃ ከፍ እንዲል በመደረጉ የተነሣ በአዋሣኝ ይዞታው ላይ ግለሰቡ ያፈራቸው ንብረቶች ላይ ጉዳት የደረሰ እንደሆነ፣ ጉዳት ያደረሰው ወገን ካሣ የመክፈል ኃላፊነት ያለበት (የሚኖርበት) ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 65/1936 አንቀጽ 2(ሀ) አዋጅ ቁ. 66/1936 አንቀጽ 1(ለ) አዋጅ ቁ. 455/1997,የኤ.ፌዲሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 40(8)

    Download Cassation Decision

  • አንድ ሰው በፍ/ቤት ክስ አቅርቦ ለማስወሰን የሚችለው ከህግ የመነጨ መብት ያለው መሆኑን በክሱ ውስጥ በዝርዝር በፍሬ ነገር ደረጃ ማመልከት የቻለ እንደሆነ ብቻ ስለመሆኑ፣  ሀይማኖታዊ (መንፈሣዊ) ትምህርት ለመስጠትና ለማሰልጠን በሚል ከሚቋቁሙ ተቋማት ጋር በተገናኘ በተማሪነት ማን እንደሚመለመል፣ ምን ምን መስፈርቶች ሊሟሉ እንደሚገባ፣ የመሰፈርቶቹ መሟላትና አለመሟላት እንዲሁም በተቋሙ ትምህርት የሚከታተሉ ተማሪዎች ከትምህርት አቀባበል ሂደት ወቅት ሊገልጿቸው ስለሚገቡ የዲሲፕሊን ጉዳዬች ወዘተ በሀይማኖት ተቋማቱ የሚወሰን ስለመሆኑና ከዚህ ጋር በተያያዘ የሚቀርቡ ክርክሮችን መደበኛ ፍ/ቤቶች አይቶ ለመወሰን ስልጣን ያልተሰጣቸው ስለመሆኑ፣  የግለሰብ ፍትህ የማግኘት መብት በፍ/ቤቶች ተግባራዊ ሊደረግ የሚችለው በፍርድ ሊያልቁ የሚባቸው ጉዳዬችን በተመለከተ ብቻ ስለመሆኑ፣ የኢፌዲሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 37

    Download Cassation Decision

  • አንድን ጉዳይ አስመልክቶ በፍርድ ሊወሰን የሚገባው እስከሆነና ጉዳዩን ለማየት በህግ በግልጽ የዳኝነት ስልጣን የተሰጠው ሌላ አካል እስከሌለ ድረስ ጉዳዩ በቀጥታ በፍ/ቤት ቀርቦ ሊስተናገድና ውሣኔ ሊሰጥበት የሚችልና የሚገባ ስለመሆኑ፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 37(1), 79(1) የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 4

    Download Cassation Decision

  • የግል ድርጅት ሠራተኞች የጡረታ መብት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የሚቀርብ ክርክርን ለማየት ስልጣን ያለው አካል የግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ስለመሆኑ፣  የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት በህግ የዳኝነት ስልጣን የተሰጣቸው አካላት የቀረበላቸውን ጉዳይ በህጉ አግባብ ያስተናገዱና ውሣኔ የሰጡ መሆኑን የማረጋገጥና የመቆጣጣር ኃላፊነትና ስልጣን ያለው ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.9,231 አዋጅ ቁ. 25/88 አንቀጽ 10(22) አዋጅ ቁ. 454/97 አንቀጽ 2(1) የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80(3)(ሀ) አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 142, 147 አዋጅ ቁ. 345/95 አዋጅ ቁ. 209/55 አዋጅ ቁ. 715/2003

    Download Cassation Decision

Page 3 of 4