criminal law

  • Criminal procedure

    Constitution

    Human right

    ...
  • በማስረጃ በተረጋገጠ የወንጀል ፍሬ ነገር መፈፀሙ የተረጋገጠው የወንጀል ተጠያቂነትን በሚያስከትለው የህግ ድንጋጌ መሰረት የጥፋተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ መሠጠት ያለበት ስለመሆኑ፡-

     

    የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል መንግስት የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 56/1995 አንቀጽ 98(2)(ሀ)

    ከአንድ በላይ ሰዎች በወንጀል ተሳታፊ በሚሆኑበት ጊዜ ለወንጀሉ ድርጊት ኃላፊ ናቸው የተባሉት ወንጀለኞች የእያንዳንዳቸውን ተሳትፎ ህጉ ባስቀመጠው የማስረጃ መለኪያ መሰረት መለየት ያለበት ስለመሆኑ-

    የወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ 141፣ የወ/ህ/ቁ. 40

    የሰ/መ/ቁ 97203

    Criminal law

    Sentencing

    Sentencing shall be according to law

    ...
  • ከዳኝነት ስራ ጋር ያልተያያዙ እና የአስተዳደር ስራ ሲያከናውኑ የሚፈፀሙ የወንጀል ጥፋቶች ዳኛውን ከተጠያቂነት የማያስቀሩ ስለመሆኑ፣

    የወ/ህ/ቁ. 402(1) እና (2)

    በትግራይ ክልል ዳኞች እና ሬጂስትራሮችን ለማስተዳደር ተሻሽሎ የወጣው ደንብ ቁጥር 1/2003

    ...
  • አንድ ሠው የአንድን ጉዳይ መከሰት በምክንያትነት በመግለጽ ከሌላ ሰው ገንዘብን ተበድሮ መውሰድ ተከስቷል የተባለው ጉዳይ ካለመከሰት ጋር በተገናኘ ተበዳሪው በእምነት ማጉደል ወንጀል ሊያስጠይቀው የሚችል ስላለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 675

    Download Cassation Decision

  • የማይንቀሳቀስ ንብረት የሸጠ ሰው ንብረቱን ከሌሎች ሰዎች ቁጥጥር ይዞታ ሥር ነፃ አድርጎ ፣የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ባለሀብትነት ለማስተላለፍ የሚያስችሉ አስፈላጊ ሰነዶች ለገዢ የማስረከብና የማይንቀሳቀሰዉን ንብረት የማይነካ የባለሀብትነት መብት ለገዥ ለማስተላለፍ አስፈላጊ የሆነ ተግባራትን የመፈጸም ግዴታ ያለበት ስለመሆኑ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2875፣ 2879(1)፣2281

    Download Cassation Decision

  • የRTD ችሎት መከላከያ የማቅረብ መብትን የማያስነፍግ ስለመሆኑ

     

     

    ዳኞች

    በአንድ የወንጀል ድርጊት በዋና ወንጀል አድራጊነት ወይም ግብረ አበርነት የተሳትፉ ተከሳሾች በግል ሁኔታዎች ሊኖር ከሚችለው ልዩነት በስተቀር ለተመሳሳይ የወንጀል አፈፃፀምና የወንጀል ተሳትፎ ተመጣጣኝና ተመሳሳይ ቅጣት ሊወሰን የሚገባ ስለመሆኑ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ስርዓት ቁጥር 196(1) ለሰበር ስርዓትም ተፈፃሚነት ያለውና ከተከሳሾች አንደኛው ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ውድቅ የሆነበትና አያስቀርብም የተባለን ተከሳሽ ጭምር ሊያካትት የሚገባ ስለመሆኑ፡- የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 25፣22 የወንጀል ሕግ አንቀጽ ፣4፣6 የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ 2/2006 አንቀፅ.3(2)

    Download Cassation Decision

  • ድርጊቱ ከተፈጸመ በኋላ የወጣ ህግ ለተከሳሹ ወይም ለተቀጣው ሰው ጠቃሚ ሆኖ በተገኘ ጊዜ ተፈጻሚነት ሊኖረው የሚገባው ድርጊቱ ከተፈጸመ በኋላ የወጣው ህግ ስለመሆኑ፣ በአዲሱ የጉሙሩክ አዋጅ ቁ. 859/2006 አንቀጽ 182 ስር የተመለከተው ድንጋጌ ተፈጻሚነት ሊኖረው የሚገባው ክርክር ካላስነሳው ጉዳይ በሌሎች ህጎች የተመለከቱት ድንጋጌዎች በማይነካ ሁኔታ ስለመሆኑ፣ የኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 22/2/ የኢፌድሪ የወንጀል ህግ ጠቅላላ ክፍል በአንቀጽ 6

    Download Cassation Decision

  • አንድ ሰው በሀሰት የተዘጋጀን ወይም የተለወጠን ሰነድ እያወቀ የተገለገለበት ካልሆነ በቀር የወንጀል ኃላፊነት የሌለበት ስለመሆኑ፣ የወ/ሕ/ቁ 378
  • ለሽብር ተግባር የሚያገለግል ንብረት ይዞ መገኘት ወንጀል ተፈፅሟል የሚባልበት አግባብ፤ በልዩ ሁኔታ በህግ የማስረዳት ሸክም ወደ ተከሳሽ ከዞረባቸው ወንጀሎች ውጭ ፤ ዓ/ህግ የሚያቀርበውን ክስ የወንጀል ደንጋጌውን የሚያቋቁሙት የህጋዊ ፣ግዙፋዊ እና ሞራላዊ ፍሬ ነገሮችን የማሰረዳት ሸክም የመወጣት ግዴታ ያለበት ሰለመሆኑ፤ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 141 ፣ የወ/ሕ/ቁ 23(2) ፤ የፀረ ሽብር አዋጅ ቁጥ 652

    Download Cassation Decision

  • በወንጀል የቅጣት አወሳሰን ጊዜ የቅጣት መነሻ ለማግኘት ቀላል
    የእስራት ቅጣትን ወደ ፅኑ እስራት መለወጥ የሚያሥፈልገው
    ወንጀለኛው ጥፋተኛ የተባለው በሁለት ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ
    ወንጀሎች ሲሆንና አንዱ ወንጀል በቀላል እስራት ሌላው ደግሞ በፅኑ
    እስራት የሚያስቀጣ በሆነ ጊዜ ብቻ ስለመሆኑ፡-
    የተሻሻለው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁ.2/2006
    የወ/ሕ/አንቀፅ 184(1(ለ))

    የሰ/መ/ቁ/103448

    ...

  • አንድ በወንጀል ተጠርጥሮ የተከሰሰ ሰው ቅጣት በሚያከብድ የህግ
    ድንጋጌ ስለተከሰስኩ ክሱ ይሻሻልልኝ በማለት ተቃውሞ ካቀረበ
    ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ፍ/ቤቱ የሚወስነው እንጂ ከጅምሩ ማስረጃ
    ሳይሰማ አቋም የሚወሰድበት እና ክሱ ይሻሻል ተብሎ የሚታዘዝ
    ስላለመሆኑ፣

    የሰ/መ/ቁ 103452 ቀን ጥር 19/2007 ዓ.ም

    ዳኞች፡-  አቶ አልማው ወሌ

    ህጉ በሚጠይቀው አግባብ ፈቃድ ሳያወጣ ወይም የጸና ፈቃድ ሳይኖረው ከቴሌኮሚኒኬሽን እውቅናና ፈቃድ ወጭ ሶፍትዌሮችን በመገልግል በኢንተርኔት ስልኮች ማስደወል ሊያስከትለው ስለሚችለው ኃላፊነት የቴሌኮሚኒኬሽን አዋጅ ቁጥር 49/1989 ለማሻሻል የወጣው አዋጅ ቁጥር 281/1994 አንቀጽ 13

     

    የሰ/መ/ቁ. 103940

    ቀን 24/05/2008 ዓ/ም

    ዳኞች፡-

    ...
  • አንድ ወንጀል ከመስራት ሃሳብ የሚመነጩ የተለያዩ ድርጊቶች አንድ
    ወንጀል ከመስራት ሃሳብ የሚመነጩ ናቸው በማለት ተጠቃለው እንደ
    አንድ ወንጀል እንዲተገበሩ ማድረግ የህጉን አግባብ የተከተለ
    ስላለመሆኑ፡-
    በፅኑ እስራትና በቀላል እስራት የሚያስቀጡ ወንጀሎች ተደራርበው
    ሲገኙ የቀላል እስራት ወደ ፅኑ እስራት እንደሚለወጥ፤ስሌቱም
    የሁለት ዓመት ቀላል እስራት እንደ አንድ ዓመት ፅኑ እስራት
    የሚቆጠር ስለመሆኑ፡-
    የወ/ሕ/ቁ/ 184 (1)(ለ)

    የሰ/መ/ቁ. 104715

    ...
  • በወንጀለኛ ህግ ቁጥር 627(2) መሰረት በክብረ ንህፅና ላይ የሚደረግ ድፍረት የተበዳይ ክብረ ንፅህና በጥቃቱ መገርሰስ ወይም አለመገርሰስ እንደ መስፈርት ሊቆጠር የሚገባው ስላለመሆኑ

     

    የሰ/መ/ቁ. 107166

    ቀን ጥቅምት 4/2008 ዓ.ም

     

     

    የጉምሩክ ወንጀል ጋር በተያያዘ ፤ተከሳሽ በወንጀሉ ጥፋተኛ ባይባልም ንብረቱ የሚወረሰው ሰለድርጊቱ አፈፃፀም ሁኔታ የሚያሰረዳ አጥጋቢ ማስረጃ መቅረቡን ፍ/ቤቱ አሳማኝ ሆኖ ሲያገኘው ስለመሆኑ ፤ አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀፅ 104 እና አዋጅ ቁጥር 859/2006

    Download Cassation Decision

  • በቀድሞ ህግ እንደ ወንጀል የሚቆጠር ድርጊት በአዲሱ ህግ የወንጀል ድርጊት መሆኑ ቀሪ ከሆነ ጉዳዩ በወንጀል የሚታይበት አግባብ ስላለመኖሩ በአዲሱ የገቢዎችና ጉምሩክ አዋጅ መሰረት ከቀረጥ በነፃ በገባ እቃ አላግባብ መገልገል የወንጀል ተጠያቂነት ሳይሆን አስተዳደራዊ ተጠያቂነት ብቻ የሚያስከትል ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ድ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 5(3) አዋጅ ቁ.622/2001 አንቀፅ 98(1)(ሀ)(ለ) የጉሙሩክ አዋጅ ቁ.859/2006 አንቀፅ 163(1)(ሀ)(ለ)
  • በወንጀል ክርክር ሂደት ፍ/ቤት በማስረጃ አቀራረብና አቀባበል ሂደቶች ውስጥ ሊኖረው(ሊያደርገው) ስለሚችለው ሚና የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 136(4)፣137፣138፣143(1)፣145፣194

     

    የሰ/መ/ቁ. 111498

     

    የካቲት 25 ቀን 2008 ዓ.ም

     

    Page 2 of 12