መጥሪያ በጋዜጣ ጥሪ ሊደረግ የሚገባው ሌሎች አግባብነት ያላቸው የመጥሪያ አላላክ መንገዶች ቅደም ተከተላቸውን በጠበቀ መልኩ ከተከናወኑ በኋላ ስለመሆኑ መጥሪያ በአግባቡ ደርሷል ለማለት የሚላክለት ሰው ስም በተሟላ ሁኔታ ተገልጾ መላክ ያለበት ስለመሆኑ መጥሪያ በህጉ አግባብ እንዲደርሰው ሳይደረግ በሌለበት ጉዳዩ እንዲታይ ትዕዛዝ የተሰጠበት ወገን ትዕዛዙ እንዲነሳለት የሚያቀርበው አቤቱታ ተገቢነት ያለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 94-110, 7870/ሀ