በህግ የተቀመጠው የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ካለፈ በኋላ የይግባኝ አቤቱታ ለማቅረብ እንዲፈቀድ የሚቀርብ አቤቱታ ሊስተናገድ የሚችልበት አግባብ ይግባኙ በጊዜው ሊቀርብ ያልቻለው የባለጉዳዩ ጠበቃ፣ነገረፈጅ ወይም ወኪል የሆነው ሰው ባለመቅረቡ ወይም ከነዚህ ሰዎች ጋር በተያያዘ በተከሰተ ጉድለት መሆኑ ከታወቀ የማስፈቀጃ አቤቱታው በበቂ ምክንያት የተደረገ ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 326/2/ /1/ 323/2/ 325