69797 contract law/ nonperformance of contract/ damage/ performance bond/ inflation

በተዋዋይ ወገኖች መካከል ውል ባለመፈፀሙ ምክንያት የጉዳት ኪሣራ እንዲከፈል በሚል ጥያቄ በቀረበ ጊዜ በውሉ ለዚሁ ዓላማ ተዋዋዮቹ ካመለከቱት የገንዘብ መጠን በላይ እንዲከፍል ለማስገደድ የማይቻል ስለመሆኑ፣  የመልካም ሥራ አፈፃፀም ቦንድ መሰረታዊ ዓላማ በውል የተመለከተው ጉዳይ እንደውሉ ስለመፈፀሙ (የሚፈፀም ስለመሆኑ) ለማረጋገጥ ስለመሆኑ፣  አንድን ዕቃ ማቅረብ ጋር በተያያዘ የተደረገ ውልን አስመልክቶ በአቅራቢው በኩል ከእቃው ዋጋ ጋር በተገናኘ በመንግስት የታወቀ የዋጋ ግሽበት መከሰቱ አቅራቢው ውሉን ሙሉ ለሙሉ ለማቋረጥ የሚያስችለው በቂ ምክንያት ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 3183(2),3188(1),1731,1734,1732,1889

Download Cassation Decision