የግንባታና የኮንስትራክሽን ማዕድን ማውጣት ሥራ ጋር በተያያዘ በሚመለከተው የመንግስት አካል የተሰጠ የፀና ፈቃድ ሣይኖር ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የመግዛትና የመሸጥ ውል መፈፀም በወንጀል ተጠያቂነትን ሊያስከትል ስለመቻሉ ህገ ወጥ ወይም ወንጀል ስለመሆኑ የተደነገገ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የተደረጉ ውለታዎችን (ውሎችን) በህግ ኃይል እንዲፈፀሙ በሚል ለፍ/ቤት ጥያቄውን በቀረበ ጊዜ ዳኞች ጥያቄውን ውድቅ ማድረግ የሚገባቸው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ.1718, 1716 የወ/ህ/ቁ.353(1)(ለ) አዋጅ ቁ.52/85 አንቀፅ 53(5) ደንብ ቁ.182/86 አንቀፅ 39