የጡረታ አበል ተጠቃሚ የሆነ ሰው በሌላ የመንግስት ሥራ ተቀጥሮ ያለአግባብ የወሰደው የጡረታ አበል እንዲመለስ በሚል የሚቀርብ ጥያቄ በአሥር አመት ይርጋ የሚታገድ ስለመሆኑና የይርጋ ጊዜውም ግለሰቡ በሌላ የመንግስት ሥራ ከተቀጠረበት ጊዜ ጀምሮ የሚቆጠር ስለመሆኑ፣ አንድ የመንግስት ሠራተኛ ጡረታ ከወጣ በኋላ መልሶ ደመወዝ በሚያስገኝ የመንግስት ስራ ከተቀጠረ የቅጥሩ ሁኔታ በቋሚነትም ይሁን በጊዜያዊነት እንዲሁም ደመወዙ ከጡረታ አበሉ ያነሰ ሆነም አልሆነ ከደመወዙና ከጡረታ አበሉ አንዱን መምረጥ ያለበት ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ.345/95 አንቀጽ 46(1) (2) አዋጅ ቁ.209/55 አንቀጽ 30(2) የፍ/ብ/ህ/ቁ.1677(1)