የውክልና ውል ሳይኖር ወኪል ነኝ በሚል የሚደረግ ውል ህጋዊ ውጤት አግኝቶ የሚፀናበት አግባብ ስላለመኖሩ፣ የውክልና ሥልጣኑ ከመሰጠቱ በፊት የተደረገ ውል ውክልና ከተሰጠ በኋላ ሊፀና ይችላል ለማለት የሚያስችል የህግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑና ወካይ የሆነ ሰው የወካዩን ድርጊት እንደተቀበለ ሊቆጠር የሚችለው በህግ የሚፀና የውክልና ውል ኖሮ ነገር ግን ወኪሉ ከተሰጠው ስልጣን በላይ ሰርቶ የተገኘ እንደሆነ ወይም የውክልና ስልጣኑ ካበቃ (ከተቋረጠ) በኋላ ወካዩን በመወከል የሰራቸውን ሥራዎች በተመለከተ ብቻ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2190, 1678 (ሐ),1719(2),1723