የማይንቀሳቀስ ንብረት የመያዣ መብት ውጤት የሚኖረው ከተፃፈበት ቀን አንስቶ እስከ አስር ዓመት ድረስ ነው በሚል የተደነገገው ድንጋጌ የይርጋ የጊዜ ገደብን የሚደነግግ ሣይሆን የመያዣ ውሉ ቀሪ የሚሆንበት ወይም በህግ ውድቅ የሚደረግበት (Lapse of Mortgage Right) ስለመሆኑ፣ የማይንቀሳቀስ ንብረትን ለሰጠው ብድር በመያዣ የያዘ ባንክ በመያዣው ላይ ያለው መብቱ በይርጋ ቀሪ የሚሆነው የመያዣ ውሉ ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ አስር ዓመት ከማለፉ በፊት በመያዣ መብቱ መገልገል ያልጀመረ እንደሆነ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 3058 (1)(3)