ከወንጀል ጉዳይ ጋር በተገናኘ በወንጀል ጥፋተኛነቱ ተረጋግጦ የተጣለበትን ቅጣት ፈጽሞ ያጠናቀቀ ሰው በፍርድ ቤት መሰየም በግለሠቡ የጡረታ መብት ላይ ስለሚኖረው ውጤት በመሰየም ሊገኝ የሚችለው መብት ግለሰቡ ከመሰየሙ አስቀድሞ በቅጣት ቀሪ ሆኖበት የነበረውን መብት ሳይሆን ግለሰቡ ከተሰየመበት ጊዜ ጀምሮ ወደ ፊት ሊጠበቅለት የሚገባውን መብት በተመለከተ ብቻ ስለመሆኑ፣ የመንግስት ሰራተኛ የነበረና የጡረታ መብት ተጠቃሚ የሆነ ሠው በወንጀል ጉዳይ ተከስሶና ጥፋተኛነቱ ተረጋግጦ በፍ/ቤት ቢያንስ የ3 ዓመት ጽኑ እስራት ቅጣት የተወሰነበት በመሆኑ የጡረታ መብቱን እንዲያጣ የተደረገ ሠው ከቅጣቱ በኋላ በፍ/ቤት መሰየሙ አስቀድሞ በቅጣት ቀሪ ሆኖበት የነበረውን የጡረታ መብቱን መልሶ ለማግኘት የማያስችል ስለመሆኑ፣ የወ/ህ/አ. 231,235(1),232 አዋጅ ቁ. 209/55 አዋጅ ቁ. 5/67 አዋጅ ቁ.345/95 አንቀጽ 52/1/