ከጡረታ መብት አበል ተጠቃሚነት ጋር በተገናኘ የእድሜ አቆጣጠርና ውጤቱን በተመለከተ የሚቀርብ አቤቱታን አይቶ ለመወሰን ስልጣን ያለው የማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ተቋም ስለመሆኑና በውሣኔው ቅሬታ ያለው ወገን ለኤጀንሲው ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የይግባኝ አቤቱታ ለማቅረብ መብት ያለው ስለመሆኑ፣ በኤጀንሲው ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የሚሰጥ ውሣኔ በፍሬ ነገር ደረጃ የመጨረሻ ስለመሆኑና በውሣኔው ላይ መሠረታዊ የህግ ስህተት አለው በማለት አቤቱታ ያለው ሠራተኛ ቅሬታውን ለፌ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የማቅረብ መብት ያለው ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 714/2003 አንቀጽ 4(1),54(3),56(4) የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 343, 9, 231