የአንድ ደርጊት ወይም ግድፈት ወንጀልነት በህግ በግልጽ ተደንግጐ በማይገኝበት ሁኔታ የድርጊቱን ወይም የግድፈቱን ፈፃሚ በወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ የማይቻል ስለመሆኑ፣ በወንጀል ጉዳይ የሚቀርብ ክስ ስለ ድርጊቱና አፈፃፀሙ የሚሰጠው መግለጫ ድርጊቱን ወንጀል ከሚያደርገው ህግ አነጋገር በጣም የተቀራረበ መሆን የሚገባው ስለመሆኑ፣ በንግድ ሥራ ለተሰማሩ ወይም ሌሎች ሰዎች በግለሰብ ደረጃ መጠኑ በርካታ የሆነ ገንዘብን በተደጋጋሚ በብድር የመስጠት ተግባር በህግ የተከለከለ ወይም በወንጀል የሚያስቀጣ ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 2, 23(2), 3, 61 የወ/መ/ህ/ሥሥ/ቁ. 112 አዋጅ ቁጥር 83/86 አንቀጽ 59(1), (ሸ), 2(ሀ),