የወጪና ኪሣራ ክፍያ ጉዳይ ሊስተናገድ ሊወሰን የሚገባው በዋናው ጉዳይ ፍርድ (ውሣኔ) በተሰጠበት መዝገብ ስለመሆኑ፣ ወጪና ኪሣራ ክፍያን በተመለከተ ማን መክፈል እንዳለበት በዋናው ጉዳይ ላይ ተለይቶ ከተወሰነ በኋላ ምን ያህል መከፈል እንዳለበት በተመለከተ ደግሞ ዋናው ፍርድ ባረፈበት መዝገብ የወጪና ኪሣራ ዝርዝር ቀርቦ ሌላኛው ተከራካሪ ወገን ስለቀረበው የወጪና ኪሣራ አስፈላጊነት ስለመጠኑ እና በእርግጥም ወጪና ኪሣራ ስለመውጣቱ በተመለከተ የበኩሉን ክርክር ካቀረበ በኋላ የወጪና ኪሣራ ልኩ ሊወሰን የሚገባ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 183, 378, 462-464