አንድ ሰው ለመንግስት ሊከፍል የሚገባውን ግብር ባለመክፈሉ በወንጀል ተግባር ሊጠየቅና ጥፋተኛ ተብሎ ሊቀጣ የሚችለው ግብሩን ላለመክፈል በማሰብና ግብር አስገቢው መ/ቤትም ንብረቶቹን በመያዝና በመሸጥ የግብር ገንዘቡን ገቢ እንዳያደርግ ለማድረግና ግብር የመክፈል ኃላፊነቱን ለማምለጥ ንብረቶቹን ለማሸሽ፣ የመሰወር ወይም ሌሎች ተገቢነት የሌላቸው ህገ ወጥ ተግባራትን በመፈፀም ግብርን ያልከፈለ መሆኑ ሲረጋገጥ እንጂ በሌሎች በህግ ተቀባይነት ባላቸው ምክንያቶች ግብሩን ለመክፈል ሳይችል የቀረ እንደሆነ ስላለመሆኑ፣ ማንኛውም ሰው በፍ/ብሔር ጉዳይ ያለበትን እዳ ለመክፈል ባለመቻሉ ምክንያት ብቻ በወንጀል ጉዳይ ጥፋተኛ ተብሎ ሊቀጣ የማይገባ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 285/94 አንቀጽ 49 አዋጅ ቁ. 286/94 አንቀጽ 96, 162 የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 13(2) ደንብ ቁጥር 78/94 ICCPR- አንቀጽ 11