87834 civil procedure/ compromise agreement/ effect of compromise on third parties

 ተከራካሪ ወገኖች ለክርክራቸው ምክንያት ሊሆን የሚችለውን ጉዳይ ወይም ያከራከራቸውን ጉዳይ በእርቅ ስምምነት የጨረሱ እንደሆነ የእርቅ ስምምነቱ ግብ ተከራካሪዎቹ (ታራቂዎቹ) በግላቸው ያላቸውን መብትና ግዴታ እንደሁኔታው በማስተካከል ለክርክሩ መንስኤ የሆነውን ጉዳይ በስምምነት ማስቀረት ስለመሆኑና የእርቅ ስምምነቱ ውጤትና ተፈፃሚነቱ እርቁን ባደረጉት ተከራካሪ ወገኖች መካከል ብቻ ተገድቦ የሚቀር እንጂ የሌሎች 3ኛ ወገኖች መብትና ግዴታ ሁሉ በማካተት የ3ኛ ወገኖች መብትና ግዴታን አብሮ በእርቅ እንዳለቀ የሚያስቆጥር ስላለመሆኑ፣  የተከራካሪ ወገኖች የእርቅ ስምምነት በፍ/ቤት ትእዛዝ (ውሣኔ) መጽደቅና መመዝገብ መብቴን ወይም ጥቅሜን ይነካል በሚል 3ኛ ወገኖች የሚያቀርቡት የመቃወም አቤቱታ ህጋዊና ተቀባይነት ያለው ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 3311 የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 358

Download Cassation Decision