የዳግም ዳኝነት (Review of Judgment) ዓይነተኛ ዓላማ ተገቢ ሁኔታዎችና ፍሬ ነገሮች ተሟልተው መገኘታቸው ሲረጋገጥ በሀሰተኛ ማስረጃ፣ በመደለያና በመሰል ወንጀል ጠቀስ ድርጊቶች ምክንያት የተዛነፈን ፍትህ ወደ ነበረበት መመለስ ስለመሆኑ፣ የዳግም ዳኝነት ጥያቄ (አቤቱታ) ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ተግባራት የሚከናወንበት በመሆኑ ጥያቄው ለሰበር ችሎት በቀረበ ጊዜ ችሎት አቤቱታውን ፍሬ ነገር የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ስልጣን ላላቸው የስር ፍ/ቤቶች ሊመራውና ሊያስተላልፈው በሚገባ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 6(1)(ሀ)(ለ) አዋጅ ቁ. 25/88 አንቀጽ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80(3)(ሀ)