አንድ ሰው በቸልተኝነት ወንጀል ፈጽሟል ሊባል የሚችለው የድርጊቱን ውጤት እያወቀ ውጤቱ አይደርስም ከሚል መነሻ ድርጊቱን የፈፀመ እንደሆነ ወይም ድርጊቱ የወንጀል ውጤት የሚያስከትል መሆኑን ባያውቅም ውጤቱን ማወቅ ነበረበት ወይም ጥረት ቢያደርግ ማወቅ ይችል ነበረ ለማለት የሚቻል እንደሆነ ስለመሆኑ፣ አንድ ሰው የፈፀመው ድርጊት በቸልተኛነት ነው ለማለት በመስፈርትነት ሊወሰድ የሚገባው የድርጊቱ ፈፃሚ በድርጊቱና በውጤቱ መካከል ያለውን ግንኙነት አስመልክቶ ያለው ወይም ሊኖረው የሚገባው ግንዛቤ ስለመሆኑና ይህም የድርጊቱ ፈፃሚ የነበረው እውቀትና ግንዛቤ ወይም ሊኖረው የሚገባውን እውቀትና ግንዛቤ መመዘን ያለበት ከግለሰቡ እድሜ፣ ያለው የኑሮ ልምድ የትምህርት ደረጃ ሥራውና የማህበራዊ ኑሮ ደረጃውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 59(1), 543(2), 57