• የመጀመሪያ ሚስት በንብረትዋ ላይ ስምምነት ባላደረገችበት ፤ባል ሁለተኛ ሚስት ሲያገባ መቃወሚያ አላቀረበችም በማለት በንብረትዋ ላይም ስምምነት አድርጋለች በማለት በመደምደም ፤ሁለተኛ ሚስት እኩል እንድትካፈል በማለት የሚሰጥ ውሳኔ ህጋዊ ስላለመሆኑ

  Download Cassation Decision

 • የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ነው የተባለ ንብረትን አፈፃፀምን በተመለከተ የንብረቱ ሕጋዊነት ላይ የሚመለከተው አስተዳደር አካል አግባብ ያለው ውሣኔ እስኪሰጥ ድረስ መሸጥ መለወጥ ባይቻልም ባለበት ሁኔታ የግራ ቀኙን እኩል ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ አግባብ በጋራ የሚያስተዳድሩበት ወይም ተከፋፍለው የሚጠቀሙበት ወይም አከራይተው ጥቅሙን እኩል የሚከፋፈሉበት ሁኔታ መመቻቸት ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ 386/2/

  Download Cassation Decision

 • አ ንድ የንግድ ቤት በኪራይ የተሰጠው በትዳር ግንኙነት ወይም በጋብቻ ውስጥ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ የንግድ ፈቃድ የተሰጠው ከትዳር ግንኙነት በፊት መሆኑ ብቻ የንግድ ሱቅ ከጋብቻ በፊት የተገኘ የግል ንብረት ነው ለማለት የማያስችል ስለመሆኑ፣

  Download Cassation Decision

 • ባ ል እና ሚስት በጋራ ሲጠቀሙበት የነበረ መሬት ጋብቻው በአንደኛው ተጋቢ ሞት የተቋረጠ ቢሆንም ሌላኛው ተጋቢ በሌላ ህጋዊ ምክንያት መብቱ እስካልተቋረጠ ድረስ ይዞታው በስሙ ተመዝግቦ ደብተር ለማግኘት እና በይዞታው ለመጠቀም የሚችል ስለመሆኑ፣ ሴቶች መሬትን በመጠቀም፤በማስተላለፍ፤በማስተዳደርና በመቆጣጠር ረገድ ከወንዶች ጋር እኩል መብት ያላቸዉ ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ድ.ሪ ሕ/መ አንቀጽ 35/7/፣ የኦሮሚያ የገጠር መሬት አዋጅ ቁ. 130/99 አንቀጽ 6/3/ እና ደንብ ቁጥር 151/2005 አንቀጽ 15

  Download Cassation Decision

 • የ ባልና ሚስት ንብረት ክፍፍልን በተመለከተ ለአፈፃፀም የቀረበ አከራካሪ የሆነ ቤት ሊካፈልም ሆነ ሊሸጥ የማይችል ሲሆን ሊካፈል የሚችለው በፕሮፖርሽን / በተነጻጻሪ ካርታ / ነው በማለት ባለሙያ አስተያየት በተሰጠበት ሁኔታ በዚሁ አግባብ ክፍፍሉ ሲደረግ የበለጠ ይዞታ የደረሰው ወገን ለሌላው ወገን ግምቱን እንዲከፍል በማድረግ መፈፀም የሚገባው እንጂ በፍርዱ በተቀመጠው ሌላ አማራጭ መሠረት ክፍፍሉ እንዲፈጸም ማድረግ የማይገባ ስለመሆኑ፡- የተሻሻለው የፌዴራል የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 91(1)እና(2)

  Download Cassation Decision

 • የባሌና ሚስት ፌቺ ተፇጽሞ የንብረት ክፌፌሌ እስከሚዯረግ ዴረስ በጋብቻ ውስጥ የተፇራ ንብረትም ሆነ ከዚህ ንብረት የሚገኝ ገቢ የጋራ ሆኖ የሚቆይ ስሇመሆኑ
  የተሻሻሇው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 89

  Download decision

 • የፍ/ብ/ህ/ቁ. 658 ተጋቢ ወገን ከሦስተኛ ወገን ጋር ያደረገውን ውል ለማፍረስ ምክንያት ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 658, 686

  Cassation Decision no. 28663

 • ከጋብቻ በፊት የግል የነበረን ንብረት መነሻ በማድረግ በጋብቻ ጊዜ በግብይት የተገኘ ንብረት የግል ሆኖ ሊቀጥል የሚችለው በፍ/ቤት ቀርቦ የፀደቀ እንደሆነ ብቻ ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 58(2) 57 62(2)

  Download Cassation Decision

 • የአንደኛው ተጋቢ ስምምነት ሣይኖር የጋራ የሆነ የማይንቀሣቀስ ንብረት በሌለኛው ተጋቢ የተሸጠ እንደሆን ስምምነቱን ያልሰጠው ተጋቢ ካወቀበት ቀን ጀምሮ በ 6 ወር ውስጥ እንዲሁም በማናቸውም ሁኔታ ደግሞ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ የሽያጭ ውሉ እንዲፈርስ ለመጠየት ስለመቻሉ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 69(2)

  Download Cassation Decision

 • በጋብቻ ውል ላይ ባልና ሚስት “መተዳደሪያችን” ነው በሚል ያመለከቷቸው ንብረቶች የጋራ ንብረት ተደርገው የሚቆጠሩ ስለመሆናቸው

  Download Cassation Decision

 • ጋብቻ ሳይፈርስ የትዳር ግንኙነቱን ትቶ የሄደ ተጋቢ ጋብቻውን ትቶ በሄደበት ወቅት የተፈራን ንብረት የጋብቻ ውጤት ነው በማለት የክፍያ ጥያቄ ሲያቀርብ በጋብቻ ወቅት የተፈራን ንብረት የጋራ ይሆናል በሚለው የህግ ግምት ተጠቃሚ ሊሆን የማይገባ ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 40/1/

  Download Cassation Decision

 • ከጋብቻ በፊት በአንደኛው ተጋቢ የተፈራ ቤት በጋብቻ ወቅት እድሳት የተካሄደለት መሆኑ ብቻ ንብረቱን የባልና ሚስቱ የጋራ ሃብት የማያደርገው ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥ. 213/92 አንቀጽ 42/1/, 57

  Download Cassation Decision

 • አንድ ወንድ ሁለት ሚስቶች ጋር ተጋብቶ በሚገኝ ጊዜ የንብረት ክፍፍል ሊደረግ የሚችልበት አግባብ የፌዴራል የተሻቫለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ. 213/92 አንቀጽ 102(1),86(1),62(1),63(1) የአማራ ብ/ክ/መ/የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 113(1),97(1),73(1),74(1)

  Download Cassation Decision

 • የኮንዶሚንየም ቤት ለማግኘት የተደረገ ምዝገባ ከጋብቻ በፊት ቢሆንም ዕጣ የወጣው ጋብቻ ፀንቶ ባለበት ጊዜ ከሆነ ተጋቢዎቹ የመካፈል መብት የሚያገኙ ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • በሁለት የተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ቤቶች የጋብቻ ፍቺን ተከትሎ ለባልና ሚስት ሊከፋፈሉ የሚችሉበት አግባብ

  Download Cassation Decision

 • ባል ሁለት ሚስቶችን በአንድ ጊዜ አግብቶ የሚኖር በሆነ ጊዜ በመካከላቸው የሚፈራ ንብረት ለተጋቢዎቹ ሊከፋፈል የሚችልበት አግባብ ሚስቶች ጋብቻ እንደተፈፀመ ከሚቆጠርበት ጊዜ ጀምሮ ከባል ጋር ያፈሩትን ሀብት ብቻ መካፈል ስለመቻላቸው

  Download Cassation Decision

 • በባልና ሚስት የጋራ ንብረት ላይ የተደረገ የሽያጭ ውል በሕጉ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ አለመፍረሱ ስለሚያስከትለው ውጤት

  Download Cassation Decision

 • ከኮንዶሚኒየም ቤት ባለቤትነት ጋር በተያያዘ ከጋብቻ በፊት በአንደኛ ተጋቢ በተደረገ ምዝገባ የተነሣ የቤት ዕጣው የወጣው ብሎም የቤት ሽያጭ ውል የተደረገው በጋብቻ ወቅት መሆኑ በተረጋገጠ ጊዜ ለቤቱ መገኘት ምክንያት የሆነው ተጋቢ ቤቱ የግል መሆን አለበት በሚል የሚያቀርበው ክርክር ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 62(2)

  Download Cassation Decision

 • ከጋብቻ በፊት አንደኛው ተጋቢ የግል መኖሪያ ቤት ኖሮት ከጋብቻ በኋላ ሌሎች ተጨማሪ ቤቶችና ግንባታዎች ተካሂደዋል በሚል ከጋብቻ በፊት በስሙ ተመዝግቦ የሚገኘው ቤት በጨረታ ተሸጦ ለተጋቢዎቹ እንዲካፈል በሚል የሚሰጥ ውሣኔ አግባብነት የሌለው ስለመሆኑ

  Download Cassation Decision

 • ከጋብቻ በሞት መፍረስ ጋር በተገናኘ የሚቀርብ የጋራ ንብረት ክፍፍል ጥያቄ ላይ ተፈፃሚ የሚሆነው ይርጋ መቆጠር የሚጀምረው ጋብቻው ከፈረሰበት ዕለት አንስቶ እንጂ ወራሽነት ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1846, 826/1/

  Download Cassation Decision

Page 2 of 3

 
 
 

Google Adsense