• የጋብቻ ፍቺን በተመለከተ በፍ/ቤት የተሰጠ ውሣኔ ከሌለ በስተቀር የባልና ሚስት የጋራ ንብረትን አስመልክቶ የፍቺ ውጤት የሆነውን የክፍፍል ጥያቄ በፍ/ቤት ማቅረብ አይቻልም ለማለት የሚያስችል የህግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ.213/92 አንቀፅ 76

  Download Cassation Decision

 • ባልና ሚስት በፍቺ ወቅት የጋራ ንብረታቸውን ለመካፈል ስምምነት ላይ ያልደረሱ ከሆነና ንብረቱ በአይነት ሊካፈል የማይችል እንደሆነ ንብረቱ ተሸጦ የተገኘውን ዋጋ እኩል እንዲካፈሉ መደረግ ያለበት እንጂ በእጣ እንዲካፈሉ ሊወሰን የሚችልበት የህግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ. 213/92 አንቀጽ 103/1/

  Download Cassation Decision

 • ከባልና ሚስት የንብረት ክፍፍል ጋር በተገናኘ በአንደኛው ተጋቢ በውርስ የተገኙ ንብረቶች (ሀብቶች) ለልማት በሚል በመፍረሳቸው የተገኘ የካሳ ክፍያ በግብይት እንደተገኘ ተቆጥሮ የግል ስለመሆኑ በፍ/ቤት አልተረጋገጠም በሚል እንደ የጋራ ሀብት ሊቆጠር የማይችል ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ.213/92 አንቀፅ 58, 57

  Download Cassation Decision

 • ከባልና ሚስት የጋራ ንብረት ጋር በተገናኘ በጋብቻ ወቅት በአንደኛው ተጋቢ አማካኝነት ከባንክ ወጪ ተደርጐ ለ3ኛ ወገን የተላለፈ (የተሰጠ) ገንዘብ ለትዳር ጥቅም እንደዋለ የሚገመትበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ፣ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ.213/92 አንቀፅ 85-93

  Download Cassation Decision

 • የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ክፍፍል ጋር በተገናኘ አንድን የጋራ ንብረት በዓይነት ለመካፈል ተጋቢዎቹ ከስምምነት ላይ ለመድረስ ያልቻሉ እንደሆነና ሁለቱም የቅድሚያ ግዢ መብት ጥያቄ ያቀረቡ እንደሆነ ንብረቱ ለጨረታ ቀርቦ እንዲሸጥ በማድረግ ገንዘቡን መካፈል ያለባቸው ስለመሆኑ፣ የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ብ/መ/ የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ. 75/96 አንቀጽ 103(1)

  Download Cassation Decision

 • የኮንዶሚኒየም ቤትን በጋብቻ ወቅት እያሉ የደረሳቸው ባልና ሚስት የቤቱ ቅድመ ክፍያ በጋብቻ ወቅት ከተፈራ የጋራ ሀብት የተከፈለ እንደሆነና ቤቱን ለማሳመርና ለሌሎች ተያያዥ ወጪዎች ከጋራ ሀብቱ ወጪ በማድረግ ጥቅም ላይ በዋለበት ሁኔታ ጋብቻው በፍቺ የፈረሰ እንደሆነ ቤቱ ለተጋቢዎቹ፣ ሊከፋፈል ስለሚችልበት አግባብ፣ እንዲሁም በፍቺ ጊዜ እኩል መብት የሚኖራቸው ስለመሆኑ፣ የኢፌዲሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 35(1)  በህገ መንግስቱ የተረጋገጠላቸውን ቤተሰብ የመመስረት መብት በመጠቀም ጋብቻ የፈፀሙ ወንዶች እና ሴቶች በጋብቻው አፈፃፀም፣ በጋብቻው ዘመን

  Download Cassation Decision

 • በጋብቻ ወቅት በአንደኛው ተጋቢ ስም የተመዘገበና በጋብቻ ወቅት ዕጣው የወጣ የኮንዶሚንየም ቤት ላይ ያለ መብት የቤቱ ውል ከጋብቻ መፍረስ በኋላ የተፈፀመና ቅድሚያ ክፍያ የተከፈለ መሆኑ (የንብረት ክፍፍል እስካልተፈፀመ ድረስ) ንብረቱን የግል የሚያስብል ስላለመሆኑ

  Download Cassation Decision

Page 3 of 3

 
 
 

Google Adsense