Federal Court Case Tracker

 • ለህፃን ልጅ ማሳደጊያ ቀለብ የመስጠት ግዴታ ያለበት ወላጅ፣ የሚከፍለውን የገንዘብ መጠን በተመለከተ ለመወሰን ግምት ውስጥ ሊገቡ ስለሚገባቸው ሁኔታዎች የተሻሻለው ፌዴራል የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 197 (2) ፣202

  Download Cassation Decision

 • በ ጋብቻ በተሳሰሩ ባልና ሚስት መካከል ከአንዱ ጋር የውል ግዴታ የገባ ሰው በዋናው ክርክር ሁለቱን አጣምሮ ሊከስ የሚችልበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ እንዲሁም ተዋዋይ በሆነው ተጋቢ ላይ የተሰጠ ውሳኔ የተጋቢዎች የጋራ እዳ ነው ወይስ የተወሰነበት ተጋቢ የግል እዳ ነው የሚለው ክርክር ሊነሳ የሚችለው በአፈጻጸም ወቅት እንጂ ሌላኛው ተጋቢ ሊከሰስም ሆነ ሊፈረድበት ስላለመቻሉ፡-

  Download Cassation Decision

 • የጉዳት ካሳ ጥያቄ ከጋብቻ ፍቺ ጋር ተያይዞ የቀረበ በሆነበት እና ጉዳቱም የደረሰው ከፍቺው ጋር ተያያዞ መሆኑ በተረጋገጠበት ሁኔታ ጥያቄው የባልና ሚስት ፍቺን ተከትሎ ከሚነሳ የንብረት ክፍፍል ጥያቄ ጋር በአንድ ላይ ሊስተናገድ አይችልም በሚል የሚሰጥ ውሳኔ ተገቢነት የሌለው ስለመሆኑ፡- የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 84Download Cassation Decision

 • አ ንድ የንግድ ቤት በኪራይ የተሰጠው በትዳር ግንኙነት ወይም በጋብቻ ውስጥ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ የንግድ ፈቃድ የተሰጠው ከትዳር ግንኙነት በፊት መሆኑ ብቻ የንግድ ሱቅ ከጋብቻ በፊት የተገኘ የግል ንብረት ነው ለማለት የማያስችል ስለመሆኑ፣

  Download Cassation Decision

 • በ ኦሮሚያ የቤተሰብ ህግ ጋብቻ በፍቺም ሆነ በሞት ምክንያት ሲፈርስ ንብረት የሚጣራበት አግባብ በውል ወይም በስምምነት ተለይቶ ባልተቀመጠበት ሁኔታ የባልና ሚስት ሀብት የሚጣራው በቤተሰብ ህጉ አንቀጽ 113 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት ስለመሆኑ፡- ኦሮሚያ የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 69/95 በአዋጅ ቁጥር 83/96 እንደተሻሻለው አንቀጽ 93

  Download Cassation Decision

 • ባ ል እና ሚስት በጋራ ሲጠቀሙበት የነበረ መሬት ጋብቻው በአንደኛው ተጋቢ ሞት የተቋረጠ ቢሆንም ሌላኛው ተጋቢ በሌላ ህጋዊ ምክንያት መብቱ እስካልተቋረጠ ድረስ ይዞታው በስሙ ተመዝግቦ ደብተር ለማግኘት እና በይዞታው ለመጠቀም የሚችል ስለመሆኑ፣ ሴቶች መሬትን በመጠቀም፤በማስተላለፍ፤በማስተዳደርና በመቆጣጠር ረገድ ከወንዶች ጋር እኩል መብት ያላቸዉ ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ድ.ሪ ሕ/መ አንቀጽ 35/7/፣ የኦሮሚያ የገጠር መሬት አዋጅ ቁ. 130/99 አንቀጽ 6/3/ እና ደንብ ቁጥር 151/2005 አንቀጽ 15

  Download Cassation Decision

 • የ ባልና ሚስት ንብረት ክፍፍልን በተመለከተ ለአፈፃፀም የቀረበ አከራካሪ የሆነ ቤት ሊካፈልም ሆነ ሊሸጥ የማይችል ሲሆን ሊካፈል የሚችለው በፕሮፖርሽን / በተነጻጻሪ ካርታ / ነው በማለት ባለሙያ አስተያየት በተሰጠበት ሁኔታ በዚሁ አግባብ ክፍፍሉ ሲደረግ የበለጠ ይዞታ የደረሰው ወገን ለሌላው ወገን ግምቱን እንዲከፍል በማድረግ መፈፀም የሚገባው እንጂ በፍርዱ በተቀመጠው ሌላ አማራጭ መሠረት ክፍፍሉ እንዲፈጸም ማድረግ የማይገባ ስለመሆኑ፡- የተሻሻለው የፌዴራል የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 91(1)እና(2)

  Download Cassation Decision

 • ከወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ጽ/ቤት ያሊገባ የሚሌ ማስረጃ መውሰዴ በራሱ በሁሇት ሰዎች መካካሌ የነበረውን የትዲር ሁኔታ ግንኙነት መኖሩን የሚያረጋግጠውን ማስረጃ የሚያስተባብሌ ስሊሇመሆኑ

  የተሻሻሇው የቤተሰብ ሔግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 94-97

  Download decision

 • በጋብቻ ውስጥ የተዯረገ የብዴር ውሌ ከአንዯኛው ተጋቢ እውቅና ውጪ የተዯረገና የጋራ እዲ መሆኑ ፌሬነገር የማጥራትና ማስረጃን የመመዘን መርህን በተከተሇ መንገዴ ተረጋግጦ መወሰን ያሇበት ስሇመሆኑ
  ፌ/ብ/ህግ ቁጥር 2472

  Download here

  • አባትነትን በሔግ ግምት ወይም በመቀበሌ መንገድች ሇመወሰን ክርክር ሲነሳ የባህሪ ወሳኝ ቅንጣት (DNA) ውጤት እንዯ መከሊከያ ማስረጃ እንዱቀርብ በሔጉ በግሌጽ የተቀመጠ ዴንጋጌ የላሇ በመሆኑ ፌርዴ ቤቶች በሔጉ የተረዘረጋውን ስርዒት ተከትሇውና ሇትክክሇኛ ፌትህ አሰጣጥ አስፇሊጊ መሆኑን ሲያምኑበት ተግባራዊ ሉያዯርጉት የሚችለ ስሇመሆኑ
  • የዘር የባህሪ ወሳኝ ቅጣት (DNA) ምርመራ ውጤት በሔጉ በተመሇከተው አግባብ በሔጋዊ ምክንያቶች ሇማስረጃነት የሚቀርብ እንጂ በሔግ የተቀመጠውን ግምት እናት ስሇካዯች ብቻ ሇማስረጃነት የሚቀርብ ማስረጃ ነው ተብል ዴምዲሜ የሚዯረስበት ስሊሇመሆኑ
   የአማራ ክሌሌ የቤተሰብ ሔግ አዋጅ ቁጥር 79/95

  Download decision

 • በመርህ ዯረጃ ጋብቻ በፌቺ እንዱፇርስ መጠየቅ የሚገባው ከባሌና ሚስቱ አንዯኛው ተጋቢ ወይም ሁሇቱም ቢሆንም በህግ አግባብ ተቀባይነት ያሇው ውክሌና ማስረጃ ጋር የሚቀርብ የፌቺ ጥያቄ ተቀባይነት ያሇው ስሇመሆኑ
  በፌ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.58፤ በፌ/ብ/ህ/ቁ.2199

  Download here

 • የባህሪ ወሳኝ ቅጣት ( DNA) ምርመራ አንዴ ሰው የሌጁ አባት ወይም እናት አይዯሇም ሇማሇት የሚቀርብ ማስተባባያ ማስረጃ ሉሆን የሚችሌ ቢሆንም የሚከናወነው አባትነትን በሚመሇከት የመካዴ ክስ ሇማቅረብ የሚያስችለ ቀዲሚ ሁኔታዎች ሲሟለ ስሇመሆኑ እና እናትነትን በተመሇከተም በቤተሰብ ህግ ከአንቀፅ 153 እስከ 166 ዴረስ የተዘረጋው ስርዒት የሚፇቅዴ ሁኖ በፌትሃ ብሓር ስነ ስርዒት ሔጉ የተመሇከቱትን የማስረጃ አቀራረብ ስርዒቶችን መሰረት በማዴረግ ሲቀርብ ስሇመሆኑ
  አዋጅ ቁጥር 213/1992 ከአንቀጽ 167-179

  Download here

 • ከባሌና ከሚስት ባንደ የተፇጸመውና ሇፌቺው ምክንያት ሆኖ የተገኘው ጥፊት በላሊው ተጋቢ ሊይ ጉዲት አስከትል ከተገኘ በዲዩ ሊዯረሰው ጉዲት ከጋራ ንብረት በካሳ መሌክ ያንዯኛውን ተጋቢ ዴርሻ አብዛኛውን ወይም ሙለውን በዯሌ ሇተፇጸመበት ወገን እንዱከፇሌ ሉወሰን የሚችሌ ስሇመሆኑ
  የኦሮሚያ ብሓራዊ ክሌሊዊ መንግሥት የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 69/95 እንዯተሻሻሇው አዋጅ ቁጥር 83/96 አንቀጽ 111፣117

  Download here

 • የባሌና ሚስት ፌቺ ተፇጽሞ የንብረት ክፌፌሌ እስከሚዯረግ ዴረስ በጋብቻ ውስጥ የተፇራ ንብረትም ሆነ ከዚህ ንብረት የሚገኝ ገቢ የጋራ ሆኖ የሚቆይ ስሇመሆኑ
  የተሻሻሇው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 89

  Download decision

 • የኮንደምኒየም ቤት እጣ ከጋብቻ በፊት ወጥቶ የኮንዶሚኒየም ቤቱ የሽያጭ ውል የተፈረመው ወይም የተደረገው በጋብቻ ውስጥ በሆነበት ሁኔታ ለቤቱ የተከፈለው ገንዘብ ምንጭ የሆነው ወገን የግሉ መሆኑን ካላስረዳ በስተቀር ቤቱ የአንደኛው ተጋቢ የግል ንብረት ነው ሊባል የሚችልበት ህጋዊ ምክንያት የሌለ ስለመሆኑ
  የፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ህግ ቁጥር 255

  Download

 • በልጅ ቀለብ አወሳሰን ጊዜ የከፋዩን የተጣራ የገቢ መጠን በማጣራት ተገቢ ነው የሚባለው የቀለብ ገንዘብ መጠን መወሰን የሚገባው ስለመሆኑ
  የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህገ መንግስት በአንቀጽ 36(2)፣አዋጅ ቁጥር 213/1992 የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 113

  Download

 • በፍርድ ቤት የጸደቀ የጉዲፈቻ ውል ስምምነት በወሳኝ ኩነት ምዝገባ ፅ/ቤት ተመዝግቦ የጉዲፈቻ ሰርተፍኬት ስለሚሰጥበት አግባብ
  አዋጅ ቁጥር 760/2004 አንቀፅ 70(2)፣ መመሪያ ቁጥር 7/2010 አንቀፅ 43(3) 

  Download

 • የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የዉጭ ዜጎች የሀገሪቷን ባህል፣ቋንቋ፣እሴት እንደማያዉቁ የዉጭ ሀገር ጉዲፈቻ አድራጊዎች በጉዲፈቻ የሚወስዱትን ኢትዮጵያዊ ሕፃን የሀገሩን ባህል፣ወግ ፣ልማድና በማህብረሰቡ እሴት ታንፆ እንዳያድግ ተፅዕኖ በማድረግ፣ፍቅር በመንፈግ ለስነ-ልቦናዊና ማሕበራዊ ችግር ያጋልጧቸዋል ብሎ በማሰብ የኢትዮጵያዊያን ዳያስፖራዎች በሀገር እድገት እና ብልጽግና እንዲሁም ለወገኖቻቸዉ ኑሮ መሻሻል ያላቸዉን ሚና ባለመገንዘብ ኢትዮጵያውያንን በጉዲፈቻ እንዳይወስዱ መከልከል አግባብነት የሌለው ስለመሆኑ
  የሕፃናት መብት ኮንቬንሺን አንቀጽ 20 ፤የአፍሪካ ሕፃናት መብቶችና ደህነት ቻርተር አንቀጽ 24(ለ)፣24(ረ) ፤ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 36(5)፤ አዋጅ ቁጥር 1070/2010 መቅድም (preamble)፤ ከተሻሻለዉ የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 193፣ 194(3)(መ) ፤ የዉጭ ዜጎችን በትዉልድ ሀገራቸዉ ተጠቃሚ ለማድረግ የወጣዉ አዋጅ ቁጥር 270/1994 አንቀፅ 5 እና 6 

  Download

 • ባልና ሚስት በፍቺ ከተለያዩና የንብረት ክፍፍል ከተደረገ በኋላ ከአንደኛው ተጋቢ የግል ተግባር የሚመነጭ ዕዳ አፈፃፀም የተጠየቀው /የቀረበው/ ከፍቺ በኋላ እስከሆነ ድረስ ለዕዳው ምክንያት ከሆነው ተጋቢ ብቻ የሚጠየቅ ስለመሆኑ

  Cassation Decision no. 22930

 • የፍ/ብ/ህ/ቁ. 658 ተጋቢ ወገን ከሦስተኛ ወገን ጋር ያደረገውን ውል ለማፍረስ ምክንያት ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 658, 686

  Cassation Decision no. 28663