• በወንጀል ተጠርጥሮ በህግ ከለላ ስር የሚገኝን ተጠርጣሪ በዋስትና የመለቀቅ ጥያቄ ባነሳ ጊዜ ተጠርጣሪው በከተማው ውስጥ ቋሚ የመኖሪያ /የመታወቂያ/ አድራሻ የለውም በማለት የዋስትና መብቱን መከልከል ህገ መንግስታዊ ስላለመሆኑ፣ አንቀጽ 19/6/፣ 25 እና የወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 69/ሀ/

  Download Cassation Decision

 • በ ትምህርት ደረጃው ከፍተኛ የሆነና በባህሪው ለህብረተሰብ አርአያ ሊሆን የሚገቡ ሰዎች ፍፁም ነውረኛ በሆነና ጨካኝነት በተሞላበት ሁኔታ የፈፀሙት ከባድ የወንጀል ድርጊት የወንጀል አፈጻጸሙን ከባድነት እና የወንጀለኛውን አደገኛነት የሚያሳይ በሆነ ጊዜ ወንጀለኛው ላይ የቀረበ የቀደመ የወንጀል ሪከርድ ያለመኖር ወንጀለኛው ጥሩ ፀባይ ወይም መልካም ፀባይ ያለው ነው የሚል ግምት ለመውሰድ የማያበቃ ስለመሆኑ፣ -የወ/ህ/ቁ. 184/1/ሀ/ እና ለ ቁ. 539 ቁ. 671/1/0/ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁ. 2/2006 የኢ.ፌ.ዲ.ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት በአንቀጽ 15 እና የወ/ህ/ቁ. 117

  Download Cassation Decision

 • በፍርድ ቤት የቀረበ ጉዳይ የክስ ምክንያት አለው ብሎ ለመወሰን የሚቻለው በክሱ ላይ የተገለፀው ነገር ቢረጋገጥ ከሳሹ የጠየቀውን ዳኝነት ለማግኘት ሕግ የሚፈቅድለት የሆነ እንደሆነ ስለመሆኑ፡- ማንኛውም ሰው በፍርድ ሊወሰን የሚገባውን ጉዳይ ለፍርድ ቤት ወይም ለሌላ በህግ የዳኝነት ስልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብ እና ውሳኔ ወይም ፍርድ የማግኘት መብት ያለው ስለመሆኑ፡- የኢፌድሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 37(1)

  Download Cassation Decision

 • በ ከተማ አስተዳደር ወይም በቀበሌ ያላግባብ የተያዘን የምርጫ ቤት ለማስመለስ የሚቀርብን ክስ የማየት ስልጣን በህግ ለሌላ የመንግስት አካል ባልተሰጠበት ሁኔታ መደበኛ ፍርድ ቤቶች የማየት ስልጣን ያላቸው ስለመሆኑ፡- ኢ.ፊ.ዲ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀጽ 37

  Download Cassation Decision

 • አንድ ተከሳሽ በሕግ አግባብ መጥሪያ የደረሰዉ እና እርሱ በሌለበት ዉሳኔ መሰጠቱን ማወቁን አግባብነት ባለዉ ማስረጃ ባልተረጋገጠበት  ሁኔታ በሌለሁበት የተሰጠዉ ፍርድ ተነስቶ የመከላከያ መልስ ላቅርብ በማለት የሚያቀርበውን አቤቱታ በህግ በተቀመጠው አንድ ወር ጊዜ ዉስጥ አልቀረበም በሚል ምክንያት ብቻ መከላከያ መልስና ክርክር አቅርቦ የመሰማትና ፍትሕ የማግኘት ሕገ መንግስታዊ መብት መንፈግ ያልተገባና ህጋዊነት የሌለው ስለመሆኑ፡- 

  የኢ.ፌ.ዴ.ሪ.ሕገ መንግስት አንቀጽ 37፣የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.78፣95 /2/

  Download here

 • አንድ ተከሳሽ በሕግ አግባብ መጥሪያ የደረሰዉ እና እርሱ በሌለበት ዉሳኔ መሰጠቱን ማወቁን አግባብነት ባለዉ ማስረጃ ባልተረጋገጠበት  ሁኔታ በሌለሁበት የተሰጠዉ ፍርድ ተነስቶ የመከላከያ መልስ ላቅርብ በማለት የሚያቀርበውን አቤቱታ በህግ በተቀመጠው አንድ ወር ጊዜ ዉስጥ አልቀረበም በሚል ምክንያት ብቻ መከላከያ መልስና ክርክር አቅርቦ የመሰማትና ፍትሕ የማግኘት ሕገ መንግስታዊ መብት መንፈግ ያልተገባና ህጋዊነት የሌለው ስለመሆኑ፡- 

  የኢ.ፌ.ዴ.ሪ.ሕገ መንግስት አንቀጽ 37፣የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.78፣95 /2/

  Download here

 • ባ ል እና ሚስት በጋራ ሲጠቀሙበት የነበረ መሬት ጋብቻው በአንደኛው ተጋቢ ሞት የተቋረጠ ቢሆንም ሌላኛው ተጋቢ በሌላ ህጋዊ ምክንያት መብቱ እስካልተቋረጠ ድረስ ይዞታው በስሙ ተመዝግቦ ደብተር ለማግኘት እና በይዞታው ለመጠቀም የሚችል ስለመሆኑ፣ ሴቶች መሬትን በመጠቀም፤በማስተላለፍ፤በማስተዳደርና በመቆጣጠር ረገድ ከወንዶች ጋር እኩል መብት ያላቸዉ ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ድ.ሪ ሕ/መ አንቀጽ 35/7/፣ የኦሮሚያ የገጠር መሬት አዋጅ ቁ. 130/99 አንቀጽ 6/3/ እና ደንብ ቁጥር 151/2005 አንቀጽ 15

  Download Cassation Decision

 • ሰ በር ችሎቶች ሥነ ሥርዓታዊ የሆነ የህግ ጥያቄን ብቻ ለማየት ስልጣን እንዳላቸው ግንዛቤ በመውሰድ በአንድ ጉዳይ ላይ የተሰጠ ውሳኔ ስነ-ስርዓታዊ ሕጎችን መሰረት አድርጎ የተሰጠ መሆን ያለመሆኑን መመርመር አንጂ ከዚህ ውጪ መደበኛ ሕጎችን መሰረት አድርገው በሸሪዓ ፍርድ ቤት የተሰጠውን ውሳኔ ሊመረምሩ የሚችሉበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ፡- በኢ.ፌ.ዲ.ሪፐብሊክ ህገ መንግስት አንቀጽ 80(3(ሀ))፣ 80(3(ለ)) እና አዋጅ ቁጥር 53/94 እና አዋጅ ቁጥር 188/1992 አንቀጽ 6

  Download Cassation Decision

 • አ ንድ የመሬት ሽያጭ ውል ህገ ወጥ ውል መሆኑ በተረጋገጠበት ሁኔታ ገዥ ወገን በመሬቱ ላይ የሰራው ቤት በሻጭ ፈቃድ እንደተሰራ ተደርጎ የህግ ግምት የሚወሰድበት አግባብ የማይኖር ስለመሆኑ የኢፌድሪ ህ/መ አንቀፅ 40 (3) እና የፍ/ብ/ህ ቁጥር 1678 (ለ) እና 1716

  Download Cassation Decision

 • የከተማ ይዞታን የማስተዳደር ስልጣን በህግ አግባብ የተሰጠው አካል ስልጣንና ኃላፊነቱን በህግ አግባብ አልተወጣም የሚል ክርክር ያለው ወገን ጉዳዩን ለፍ/ቤት የማቅረብ መብት ያለው ስለመሆኑ
  የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 37፣ 40(3)(4)፣79(1) እና 78(4)

  Download here

 • በወንጀል ጉዳይ ፍርድ ከተሰጠ በኋላ አዲስ የወጣ ህግ ተከሳሹን የሚጠቅም በሆነ ጊዜ ተከሳሹ አዲሱ ህግ ተፈፃሚ እንዲሆን አቤቱታ ባቀረበ ጊዜ አዲስ የወጣው ህግ ተፈፃሚ እንዲሆን መደረግ ያለበት ስለመሆኑና በዚሁ ጉዳይ አቤቱታ የቀረበበት ጉዳይ በባህሪው እንደመደበኛ የክርክር ጉዳይ የሚታይ ሳይሆን በቀረበ ጊዜ ሊስተናገድ የሚችል በመሆኑ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የቀረበ አቤቱታ ነው በማለት ተቀባይነት የለውም የማይባል ስለመሆኑ 

  የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 22(2)፣ የወ/ሕ/አንቀጽ 6 እና 9(1)፤ ዓለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ስምምነት አንቀጽ15/1/ 

  Download here

 • አንድ ተከሳሽ የቀረበበትን ክስና ማስረጃ በመመርመር ተገቢውን ዝግጅት በማድረግ መልሱን አዘጋጅቶ እንዲያቀርብ የታዘዘው እና ቀጠሮ የተሰጠው ከ10 ቀን ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከሆነ የተከሳሹን የመከላከልና የመከራከር የመሰማት መብቱን የሚነፍግ በመሆኑ በቂ ጊዜ ተሰጥቶት የመከላከያ መልሱን እና ክርክሩን እንዲያቀርብ መደረግ ያለበት ስለመሆኑ
  ኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 37፣
  የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ.240[2] 

  Download here

 • በፍ/ብ/ህጉ ውስጥ “ከዘር የወረደ ርስት” በሚል የተቀረበው አገላለጽ በህገ-መንግስቱ የተሻረ ወይም ተፈፃሚነት የሌለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1000/2/ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ-መንግስት አንቀጽ 40

  Cassation Decision no. 30158

 • የበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ በሰበር ችሎት የተሻረ ሲሆን በውሣኔው መብቱ የተነካ ወገን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 358 መሰረት ለሰበር ችሎት መቃወሚያ ማቅረብ የማይችል ስለመሆኑ፣ መብታቸው የተነካ ወገኖች ሊስተናገዱ ስለሚችሉበት አግባብ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 35ኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80(3)(ሀ) አዋጅ ቁ. 25/88 አንቀጽ 1

  Download Cassation Decision

 • አንድን ጉዳይ ተመልክቶ ዳኝነት ለመስጠት ሥልጣን የተሰጠው ለሌላ የዳኝነት አካል ከሆነ ፍ/ቤቶች ጉዳዮን የማየት ስልጣን የማይኖራቸው ስለመሆኑ የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ስልጣን ሥር የሚወድቅ አይደለም በሚል በኤጀንሲው የተረጋገጠ ጉዳይን ጉዳዩን የማየት ስልጣን ለሌላ የዳኝነት አካል የተሰጠ ነው በሚል ክርክር እስካልቀረበ ድረስ ፍ/ቤቶች ተቀብለው ማስተናገድ የሚችሉ ስለመሆናቸው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 37 የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 231/1//ለ/, 9/2/, 244/3/ እና 328/3/ አዋጅ ቁ. 110/87 አዋጅ ቁ. 47/67

  Download Cassation Decision

 • ከዘር የወረደ ርስት ነው በሚል የመሬት ባለቤት ለመሆን የሚቀርብ ክስ ህገ-መንግስታዊ ያልሆነና ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ

  Download Cassation Decision

 • ከፌዴራል መንግስት የልማት ድርጅት ሠራተኞች የሚሰበሰብ የሥራ ግብር ምንም እንኳን ሥራው የሚካሄደው በክልሎች ቢሆንም ወይም ሠራተኞቹ የክልል ነዋሪዎች ቢሆኑም ገቢ የሚደረገው ለፌዴራሉ መንግስት ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ-መንግስት አንቀጽ 96(3) አዋጅ ቁ. 33/85 አንቀጽ5(2)(ሐ) ደንብ ቁ. 109/96

  Download Cassation Decision

 • የሕግ ክርክሮችን በሰበር ማየት /ማስተናገድ/ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግስት ለፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የተሰጠ ስልጣን (power) ስለመሆኑ በግልግል ዳኝነት (arbitration) የታየ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ተዋዋይ ወገኖች የይግባኝ መብትን ለማስቀረት የሚያደርጉት ስምምነት ጉዳዩን በሰበር ችሎት ከመታየት የማያግድ ስለመሆኑ (ከዚሀ ቀደም በሰበር ችሎት የተሰጠው የሕግ ትርጉም የተለወጠ ስለመሆኑ፡፡) የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 80/3 (ሀ), አዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2 (4), አዋጅ ቁጥር 25/88, የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 350(2) 351 እና 356

  Download Cassation Decision

 • የፌዴሬሽን ምክር ቤት የኢፌዴሪ ህገ መንግስትን ለመተርጐም ባለው ስልጣን ተጠቅሞ የሚሰጠው ውሣኔ የመጨረሻና ጉዳዩ በሚመለከተታቸው አካላት መከበርና መፈፀም ያለበት ስለመሆኑ፣  የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ቦርድ የሚቀርብለትን አቤቱታ ህጋዊነት መርምሮ በመወሰን ሂደት ከፊል የዳኝነት ስልጣን ያለው አካል (quasi judicial body) እንደመሆኑ መጠን በህገ መንግስቱ የተጠበቁትን ፍትህ የማግኘት፣ የመሰማትና በእኩል ሚዛን የመታየት (የመዳኘት) መብት በሚያስከበር መልኩ ክርክሮችን ሊያስተናግድና ሊወስን የሚገባ ስለመሆኑ፣ የኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 62(1),37 አዋጅ ቁ. 251/93 አንቀጽ 3(1),56(1) አዋጅ ቁ. 87/86 አንቀጽ 8,9 የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 337, 336, 339

  Download Cassation Decision

 • በወንጀል ሕግ ቁጥር 543 እና 567 መሰረት አንድ ሰው በአንድ ጊዜ ሊጠየቅ ስለሚችልበት አግባብ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 543,567

  Download Cassation Decision

Page 2 of 4

 
 
 

Google Adsense