Federal Court Case Tracker

 • የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ አፈፃፀም ጋር በተያያዘ የንግድ ድርጅት ሠራተኛ፣ ሥራ አስኪያጅ እንዲሁም ድርጅቱ በወንጀል ጉዳይ ክስ ቀርቦባቸው ኃላፊ ሊሆኑ የሚችሉበት አግባብ አዋጅ ቁ. 285/94 አንቀፅ 56(1)(3) አዋጅ ቁ. 6ዐ9/2ዐዐ1 አንቀፅ 5ዐ(ለ)(1) 22(1) የወንጀል ህግ አንቀፅ 23(3) 34(1)

  Download Cassation Decision

 • ወንጀልና የወንጀል ቅጣት የእያንዳንዱን ጥፋተኛ ግላዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ውሣኔ ሊሰጥባቸው የሚገባ ስለመሆኑ የጉምሩክ ህግን በመተላለፈ ጥፋተኛ የተባሉ ሰዎች /ተከሳሾች/ ላይ የሚጣለው የገንዘብ መቀጮ በእያንዳንዱ ጥፋተኛ ላይ ስለመሆኑ የወንጀል ህግ ቁ. 41, 32/1/ሀ/ አዋጅ ቁ. 60/89 አንቀጽ 73/1/ አዋጅ ቁ. 368/95 አንቀጽ 73/1/

  Download Cassation Decision

 • ከወንጀል ጉዳይ ጋር በተያያዘ ተከራካሪ ወገኖች የማስረዳት ሸክማቸውን ተወጥተዋል ለማለት የሚቻልበት አግባብ በፍ/ቤት ፊት ቃለ- መሃላ በመፈፀም የተሰጠ የምስክር ቃል እውነት ነው በሚል የሚወሰደው ግምት ሊፈርስ የሚችል ስለመሆኑ

  Download Cassation Decision

 • በሚያሽከረክረው መኪና ላይ ተሳፍሮ ሲሄድ የነበረ ሰው ወድቆ ለህልፈተ ህይወት የተዳረገበት ሾፌር በወንጀል ህግ ቁጥር 543/2/ ሊጠየቅ የሚችል ስለመሆኑ የወንጀል ህግ ቁጥር 543/2/

  Download Cassation Decision

 • ለዋስትና የተያዘ ገንዘብን የአስያዡን ማንነትን ማረጋገጥ እስከተቻለ ድረስ ገንዘቡን ያስያዘበት ደረሰኝ ኮፒን ያቀረበ እንኳን ቢሆን የተያዘው ገንዘብ መመለስ ያለበት ስለመሆኑ

  Download Cassation Decision

 • ከወንጀል ጉዳይ ጋር በተያያዘ ጥፋተኛ የተባለ ተከሳሽ የዘወትር ፀባይ መልካም የነበረ መሆኑ በተናጠል (በራሱ) ቅጣትን ለማቅለል የሚያስችል ስለመሆኑ የወንጀል ህግ ቁጥር 82(1) (ሀ)

  Download Cassation Decision

 • የንግድ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ የሆነ ሰው የድርጅቱን አስተዳደራዊ ሥራ ለሌላ ሰው የወከለ መሆኑ ድርጅቱ ያለተጨማሪ እሴት ታክስ ግብይት በመፈፀም ወንጀል ጥፋተኛ በተባለ ጊዜ ከሚቀርብበት የወንጀል ተጠያቂነት ነፃ የማያደርገው ስለመሆኑ

  Download Cassation Decision

 • ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖር ሰዎችን ወደ ውጪ አገር በመላክ ወንጀል የተከሰሰን ሰው ጥፋተኛ ነው ለማለት እና ቅጣት ለመጣል የሚቻልበት አግባብ የወንጀል ህግ ቁ. 598/1/ /2/

  Download Cassation Decision

 • በኃላፊነት ይዞት በሚገኝ ተሽከርካሪ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓትን በመተላለፍ ዕቃን ሲያጓጉዝ የተያዘ ሰው ሊጠየቅ ስለሚችልበት አግባብና ተፈፃሚ ስለሚሆነው የህግ ድንጋጌ አዋጅ ቁ.60/89 አንቀፅ አዋጅ ቁ.368/95 አንቀፅ 79,80(1), 81,64(4)74 ወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.113(2)

  Download Cassation Decision

 • አንድ ተከሳሽ በወንጀል ህግ ቁጥር 427/3/ መሰረት የሙስና ወንጀል ፈጽሟል በሚል ሊጠየቅ የሚችልበት አግባብ የወንጀል ህግ ቁጥር 427/1/, /3/

  Download Cassation Decision

 • በውጭ አገር መንግስት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን የማየት የዳኝነት ስልጣን ያለው የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 25/88 አንቀጽ 12/1/ የወንጀል ህግ ቁ. 263, 71

  Download Cassation Decision

 • በአሽከርካሪነት ሥራው ማድረግ የነበረበትን ጥንቃቄ ሳያደርግ ቀርቶ በሌላ ሰው ላይ የሞት አደጋ ያደረሰ ሰው በወንጀል ህግ ቁጥር 543/2/ የሚጠየቅ ስለመሆኑ የወንጀል ህግ ቁ. 543/1/, /2/, /3/, 59/1/ የወ/መ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ. 113

  Download Cassation Decision

 • የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍ/ቤቶች በአዋጅ ቁ. 67/89 ሥር የተደነገጉ የወንጀል ድርጊቶችን የተመለከቱ ክርክሮችን አይቶ ለመወሰን ስልጣን ያልተሰጣቸው ስለመሆኑ ያለ ንግድ ፈቃድ በመነገድ ወንጀል የተከሰሱ ሰዎችን በተመለከተ የቀረበ ክርክርን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍ/ቤቶች ለማየት ስልጣን ያልተሰጣቸው ስለመሆኑ ሺሻ ጋር በተገናኘ የሚፈፀሙ የደንብ መተላለፍ ወንጀሎችን አይቶ ለመወሰን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍ/ቤቶች ስልጣን የሌላቸው ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 67/89 አንቀጽ 46 አዋጅ ቁ. 361/95 አንቀጽ 41/2/, 52

  Download Cassation Decision

 • በግድያ ወንጀል የተከሰሰ ሰው የወንጀል ቁጥር 540 ወይም 541ን መሰረት በማድረግ ጥፋተኛ አድርጐ ለመወሰን የወንጀል ድርጊቱ አፈፃፀምን እንዲሁም መነሻ ሁኔታዎች በአግባቡ መመልከት የሚያስፈልግ ስለመሆኑ የወንጀል ህግ ቁጥር 78 ”ን” ተፈፃሚ ለማድረግ ሊሟሉ ስለሚገባቸው መስፈርቶች ህጋዊ መከላከልን በማለፍ የተፈፀመ የነፍስ ግድያ በወንጀል ህግ ቁጥር 541 የሚያስጠይቅ ስለመሆኑ የወንጀል ህግ ቁጥር 78, 540, 541

  Download Cassation Decision

 • በወንጀል ጉዳይ ተከሳሽ በሌለበት ፍርድ የተሰጠ እንደሆነ ፍርድ የተሰጠበት ተከሳሽ የሚያቀርበው የይግባኝ አቤቱታ ተቀባይነት ሊያገኝ የሚችልበት አግባብ በይግባኝ ደረጃ ክስ የቀረበበት ተከሳሽ ጉዳዩ በሌለበት ታይቶ የተሰጠ የጥፋተኝነት ፍርድ እንደመጨረሻ ውሣኔ ተቆጥሮ በሰበር እንዲታረም ለማድረግ የማይቻል ስለመሆኑ የወ/መ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ. 193/2/, 197-202, 160, 164, 163, 195/2/ /ሀ/ የወንጀል ህግ ቁ. 522, 526 አዋጅ ቁ. 25/88 አንቀጽ 9, 10 የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80/3/

  Download Cassation Decision

 • ዓቃቤ ህግ በወንጀል በተከሰሰ ሰው ላይ የሚያቀርበው የወንጀል ክስ የወንጀሉን ዝርዝር ሁኔታ መያዝ እንዳለበት በተለይም ተከሳሹ የተከሰሰበትን ወንጀል ለይቶ አውቆ መልስ ለመስጠት እንዲችል ክሱ ወንጀሉንና ሁኔታውን መግለጽ ያለበት ስለመሆኑ አንድ ሰው ከሌሎች ሰዎች ጋር የወንጀል ተካፋይ ሆኗል የሚባለው በወንጀሉ አፈፃፀም የግዙፍ ተግባር የሃሳብና የህግ ሁኔታዎችን መተላለፍ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ የወ/መ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ. 112 የወንጀል ህግ ቁ. 32/1/ 23/2

  Download Cassation Decision

 • በሙስና ወንጀል ተጠርጥሮ ክስ ከቀረበበት ሰው ጋር በተገናኘ በሚካሄድ የቅድመ ክስ ሂደት ጉዳዩን የሚያየው ፍ/ቤት እንደቀረበው የወንጀል አይነት በመመርመር ወደ ዋናው ክስ የመስማት ሂደት እንዲገባ በሚል ትዕዛዝ ሊሰጥ የሚችል ስለመሆኑ የወንጀል ህግ ቁ. 419 አዋጅ ቁ. 434/97 አንቀጽ 36/1//2/

  Download Cassation Decision

 • ዓቃቤ ሕግ ወንጀል ፈጽሟል በሚል የተጠረጠረና ምርመራ የተደረገበትን ሰው ተከሳሽ ከሚሆን ይልቅ ምስክር ቢሆን የተሻለ ነው ብሎ ካመነ ይህንኑ ለማድረግ የሚከለክለው ህግ የሌለ ስለመሆኑ

  Download Cassation Decision

 • አንድ ሰው በወር ደመወዝ ከሚያገኘው ገቢ ውጪ ሌላ ህጋዊ የገንዘብ ምንጭ እንዳለው ለማስረዳት ባልቻለበት ሁኔታ በሚሊዮን የሚቆጠር ሀብትና ንብረት ባለቤት መሆኑ ምንጩ ያልታወቀ ገንዘብ ይዞ በመገኘት የሙስና ወንጀል የሚያስጠይቀው ስለመሆኑ የወንጀል ህግ ቁ. 419

  Download Cassation Decision

 • የወንጀል እና የፍ/ብሔር ክሶች ተጣምረው ሊታዩ የሚችሉት በወንጀል ህግ ቁጥር 101 አግባብ ብቻ ስለመሆኑ የወንጀል ህግ ቁጥር 101

  Download Cassation Decision