Federal Court Case Tracker

 • አንድ ሠው ወንጀል አደረገ የሚባለው ህገ ወጥነቱ እና አስቀጪነቱ በህግ የተደነገገን ድርጊት ፈጽሞ የተገኘ እንደሆነ ስለመሆኑና አንድ ወንጀል ተደረገ የሚባለውም ወንጀሉን የሚያቋቁሙት ህጋዊ፣ ግዙፋዊና ሞራላዊ ፍሬ ነገሮች በአንድነት ተሟልተው ሲገኙ ስለመሆኑ፣  ማንም ሰው በዋና ወንጀል አድራጊነት ወንጀል እንዳደረገ ተቆጥሮ የሚቀጣው በቀጥታ ወይም በእጅ አዙር ወንጀሉን ያደረገ በሆነ ጊዜ ወይም ወንጀሉን እርሱ በቀጥታ ባያደርገውም እንኳን በሙላ አሳቡና አድራጐቱ በወንጀሉ ድርጊትና በሚሰጠው ውጤት ሙሉ ተካፋይ በመሆኑ ድርጊቱን የራሱ ያደረገ እንደሆነ ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 2፣23(1)፣ 32(1) የወ/መ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ. 111፣112፣141፣142

  Download Cassation Decision

 • አንድ የትራፊክ ባለሙያ የሚሰጠው ሙያዊ አስተያየት የማስረጃ ዋጋ
  የማይሰጠው አስተያየቱ ተገቢውን የሙያ ደንብ ተከትሎ ያልተሰጠና
  ያልቀረበ፣በጊዜውና በቦታው ከነበሩት የአይን ምስክሮች ቃል ጋር
  ተነፃፅሮ ሲታይ በመሰረታዊ ነጥቦች ላይ ልዩነት ያለበት መሆኑ
  ሲረጋገጥ እንጂ በጭፍጫፊ ነጥቦች ላይ ልዩነት ተከስቷል ተብሎ
  ሊሆን እንደማይገባ፣
  የልዩ አዋቂዎች ምስክሮች ቃላቸውን ገለልተኛ ሆነው መስጠት እንደ
  አለባቸውና ቃላቸው ያለበቂ ምክንያት ልዩ አዋቂ ያልሆኑ ሰዎች
  በሚሰጡት የምስክሮች ቃል ውድቅ መሆን የሌለበት መሆኑን
  ተቀባይነት ያላቸው የማስረጃ ህግ ደንቦች የሚያስገነዝቡ ስለመሆኑ
  የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 141፣142፣194
  የወንጀል ህግ ቁጥር 24፣59፣239(2)፣57፣543(2)

  ፈቃድ የሌላቸው የጦር መሳሪያዎችና ጥይቶችን በቤቱ ውስጥ አከማችቶ የተገኘ ሰው መሣሪያዎቹን ለመነገድ በሚል ሀሳብ የያዘ መሆኑ የተረጋገጠ ካልሆነ በስተቀር ግለሰቡ በወንጀል ተጠያቂ ሊሆን የሚገባው በወንጀል ህግ አንቀጽ 481(1)(ሀ) ሣይሆን በአንቀጽ 809(ሀ) ሥር በተመለከተው ድንጋጌ መሠረት ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 481(1)(ሀ), 809(ሀ)

  Download Cassation Decision

 • በወንጀል የተከሰሰ ሰው ጉዳዩን በሌለበት ለማየት ፍ/ቤቱ በመጀመሪያ
  ለተከሣሹ ህጉ ያስቀመጠውን ጥብቅ መስፈርት በተከተለ መልኩ
  በአግባቡ ጥሪ ሊያደርግለት የሚገባ ስለመሆኑ፣
  የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ቁጥር 161(1)(2) እና 162

  የሰ/መ/ቁ. 93577

   

  ህዳር 22 ቀን 2007 ዓ.ም.

  ...
 • አንድ ሰው በቸልተኝነት ወንጀል ፈጽሟል ሊባል የሚችለው የድርጊቱን ውጤት እያወቀ ውጤቱ አይደርስም ከሚል መነሻ ድርጊቱን የፈፀመ እንደሆነ ወይም ድርጊቱ የወንጀል ውጤት የሚያስከትል መሆኑን ባያውቅም ውጤቱን ማወቅ ነበረበት ወይም ጥረት ቢያደርግ ማወቅ ይችል ነበረ ለማለት የሚቻል እንደሆነ ስለመሆኑ፣  አንድ ሰው የፈፀመው ድርጊት በቸልተኛነት ነው ለማለት በመስፈርትነት ሊወሰድ የሚገባው የድርጊቱ ፈፃሚ በድርጊቱና በውጤቱ መካከል ያለውን ግንኙነት አስመልክቶ ያለው ወይም ሊኖረው የሚገባው ግንዛቤ ስለመሆኑና ይህም የድርጊቱ ፈፃሚ የነበረው እውቀትና ግንዛቤ ወይም ሊኖረው የሚገባውን እውቀትና ግንዛቤ መመዘን ያለበት ከግለሰቡ እድሜ፣ ያለው የኑሮ ልምድ የትምህርት ደረጃ ሥራውና የማህበራዊ ኑሮ ደረጃውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 59(1), 543(2), 57

  Download Cassation Decision

 • በወንጀል ጉዳይ ፍርድ በሚሰጥበት ጊዜ ተከሳሹን ጥፋተኛ ሆኖ ያስገኘው ሕግ በፍርዱ ውስጥ መገለጽ እንደሚገባውና የጥፋተኝነት ውሳኔው የሚሰጥበት ድንጋጌ መፈጸሙ ከተረጋገጠው የወንጀል ፍሬ ነገር ጋር በጥንቃቄ መነጻጸር የሚገባው ስለመሆኑ፣ ወ/መ/ሕ/ስ/ስቁ. 149

  Download Cassation Decision

 • አንድ ተከሳሽ በሌለበት የተሰጠበት ውሣኔ እንዲነሳለት የሚያቀርበውን ማመልከቻ በመቀበል ከሚቻልባቸው ምክንያቶች አንዱ መጥሪያ ለተከሳሹ ያለመድረስ ጉዳይ ስለመሆኑ፣ የወ/መ/ሕ/ሥ/ ሥ/ቁ. 199ሀ

  Download Cassation Decision

 • አንድ በወንጀል ድርጊት ቅጣት የተጣለበትን ተከሳሽ ቅጣቱ እንዳይፈፀም ፍርድ ቤቱ ለማድረግ የሚችለው ጥፋተኛው በመልካም ጠባይ እንደሚመራ ፣ እንዲፈፅም የተሰጠውን ግዴታ እንደሚቀበል ፣ በሚቻለው መንገድ ሁሉ በጥፋቱ የደረሰውን ጉዳት እንደሚክስ ወይም ለተበዳዩ እንደሚከፍል እና ለዚሁ ጉዳይ በተወሰነ ጊዜ ውስጥ የፍርድ ቤቱን ወጪ እንደሚከፍል ማረጋገጫ ከሰጠ ስለመሆኑ፣ ከዚህም በተጨማሪ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛው ለገባበት ግዴታ አፈጻፀም መተማመኛ ዋስትና የሚጠይቅ ስለመሆኑ፣ አንቀጽ 197/1/ እና/2/

  Download Cassation Decision

 • አንድ ድርጅት ወንጀል እንዳደረገ የሚቆጠረው ከኃላፊዎች አንዱ ወይም ከሠራተኞች አንዱ ከድርጅቱ ጋር በተያያዘ ሁኔታ የድርጅቱን ጥቅም በሕገ ወጥ መንገድ ለማራመድ በማሰብ ወይም የድርጅቱን ሕጋዊ ግዴታ በመጣስ ወይም በመጠቀም በዋና ወንጀል አድራጊነት ወይም አነሳሽነት ወይም አባሪነት ወንጀል ሲፈጸም ብቻ ስለመሆኑ፣ የወ/ሕግ አንቀጽ 23 እና አንቀጽ 34/1/ ጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 93/1ሀ/ እና 93/2/

   

  የሰ//.94913

  የተሻሻለው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ከመውጣቱ በፊት በተፈፀመ ወንጀል ከተፈረደበት እና ሆኖም ግን ወንጀሉ በተፈፀመበት ጊዜ ስራ ላይ ከነበረው የቅጣት አወሳሰን ይልቅ የተሻሻለው መመሪያ ለተከሳሹ ቅጣትን የሚያቀልለትና ተከሳሹን የሚጠቅም ሆኖ ከተገኘ ይሄው የተሻሽለው መመሪያ ላይ ያለው ቅጣት የሚፈጽምበት ስለመሆኑ፣ የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ የወንጀል ህግ አተረጓጓም መርሆን መከተል ያለበት ስለመሆኑ፣ ወንጀል ህጉ ቁ 6

  Download Cassation Decision

 • አንድ ሰው በወንጀል ተከሶ በሌለበት የጥፋተኝነት ውሳኔ ከተሰጠ በኃላ ጥፋተኛ የተባለው ስው ቀርቦ በሌለበት የተሰጠውን ውሳኔ ለማስነሳት ሳይሆን በዋናው ጉዳይ ላይ በቀጥታ ይግባኝ ከጠየቀ በኃላ በሌለሁበት የተሰጠው ውሳኔ ይነሳልኝ ብሎ ቢያመለክት በፊት የጠየቀው ይግባኝ በህጉ ላይ የተቀመጠውን የ30 ቀን የጊዜ ገደብ የሚያቋርጥ ስለመሆኑ፣ የወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ.198

  Download Cassation Decision

 • የቲ.ኦቲ /ተርን ኦቨር ታክስ/ ተመዝጋቢ የሆነ ሰው በህግ ፊት እንደ መረጃ /ማስረጃ / ሊያቀርብባቸው የሚገቡ ደረሰኞች ከቫት በተቀበለው የቲ.ኦ.ቲ ደረሰኝ መሆን ያለበት ስለመሆኑ፣ /ታክስ የቲ.ኦቲ አዋጅ ቁጥር 285/194 አንቀጽ 21/
 • አንድ ሰው በአንድ አይነት የወንጀል አሳብ ወይም ቸልተኝነት የፈጸመው ወንጀል አንድን የሕግ ድንጋጌ ብቻ የሚጥስ ቢሆንም አንድ አይነት ጉዳት ያስከተለው ቁጥራቸው ከአንድ በላይ በሆነ ሰዎች መብት ወይም ጥቅም ላይ ሲሆን እንደተደራራቢ ወንጀሎች ሊቆጠር የሚገባ ስለመሆኑ፣ የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 27(1)፣6ዐ(ሀ) (ሐ) እና 598(1)

  Download Cassation Decision

 • በወንጀል ጉዳይ ጥፋተኛ የተባለ ሠው በቅጣት ማቅለያነት
  እንዲያዝለት ያቀረበውን ምክንያት በማስረጃ ማስደገፍ እንዲችል በቂ
  ጊዜ ባልተሠጠበት ሁኔታ በማስረጃ የተደገፈ አይደለም በሚል
  የማቅለያ ምክንያቱን ውድቅ በማድረግ የሚሠጥ የቅጣት ውሣኔ
  በወንጀል ህጉ እና በቅጣት አወሳሠን መመሪያው ሥለ ቅጣት
  አወሣሠን የተቀመጡትን ድንጋጌዎች መሠረት ያደረገ ነው ለማለት
  የሚቻል ስላለመሆኑ፣
  የወ/መ/ሥ/ሥርዓት 149/3//4/

  የሰ/መ/ቁ.96168 ህዳር 9 ቀን 2007 ዓ.ም.

  አንድ ተጠርጣሪ ወይም ተከሳሽ በምርመራ ሒደትም ሆነ ክሱን
  ለሚሠማው ፍ/ቤት የሚሠጠው የእምነት ቃል ውጤት በራሱ በቃል
  ሠጪው ላይ ተወስኖ የሚቀር ከመሆኑ ውጪ ወንጀሉን
  አልፈፀምኩም ብሎ በሚከራከር ሌላ ተከሣሽ ላይ ህጋዊ ውጤት
  ሊያስከትል የማይችል ሥለመሆኑ፣
  የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ሥነ-ሥርዓት ቁጥር 27፣35 እና 134

   

  ከስር ተከሳሾች መካከል ፍ/ቤት የሠጠው ውሣኔ ለአንዱየሚጠቅም
  በሆነ ጊዜና ይግባኝ ባዩ ጋር ተከሠውጥፋተኛ ተብለው የተቀጡ
  ሠዎች ይግባኝ ቢያቀርቡ ኖሮ በይግባኝ ሠሚው ፍቤት ውሣኔ
  ሊጠቅሙ ይችሉ የነበረ መሆኑ ከተረጋገጠ ይግባኝ ሠሚዉ ፍ/ቤት
  የሠጠው ውሣኔ ይግባኝ ላላቀረቡት ተከሳሾች ጭምር ተፈፃሚነት
  ሊኖረው የሚገባ ሥለመሆኑ፣
  የወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 196/1/ /ሀ/ /ለ/

  የሰ/

  ...
 • በተለያየ ጊዜና መዝገቦች የተለያዩ ቅጣቶች በአንድ ተከሳሽ ላይ በሚወሰንበት ጊዜ ተከሳሹ ይጣመርልኝ ብሎ በሚጠይቅበት ጊዜ ተደምረው የሚፈፀሙ ሲሆን የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች ግን እንደገና በድጋሚ የሚታዩበት የህግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑ፣ የወ/ህ/አንቀፅ 186(3)፣184(1)፣ 108(1)

  Download Cassation Decision

 • አንድ ተከሳሽ በክስ ማመልከቻ ላይ የተዘረዘረውን ወንጀል ለመስራቱ በሙሉ ያመነ እንደሆነ ጉዳዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት ተከሳሹ ጥፋተኛ ነኝ ብሏል ሲል በመዝገብ ካሰፈረ በኃላ በተከሳሹ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ መስጠት የሚገባው ስለመሆኑ፣ የወ/መ/ስ/ስ/ህ/አ 134(1)

  Download Cassation Decision

 • ከውል ግንኙነት ጋር በተያያዘ በህገ ወጥ መንገድ መብትን ማስከበር የወንጀል ተጠያቂነትን የሚያስከትል ስለመሆኑ፣ የወ/ህ/አንቀፅ 436(ለ)

  Download Cassation Decision

 • በአንድ ተከሳሽ ላይ ከቀረቡት ከአንድ በላይ ከሆኑት ክሶች መካከል
  ከፊሎች የሚወድቁት በፊዴራል ፍ/ቤት የስረ ነገር ስልጣን ስር
  ከፊሎቹ ደግሞ በክልል ፍርድ ቤት የስረ- ነገር ስልጣን ስር በሆነ
  ጊዜናበወንጀል ህግ ሥነ-ስርዓቱ የክስ አቀራረብ መርህ መሰረት
  በቀጥታም ሆነ በውክልና በፌደራል ፍ/ቤት ቀርበው እንዲታዩ
  ከተደረገ በሚሰጠው ውሳኔ ላይ የይግባኝ እና የሰበር ሥርዓታቸው
  በመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲቀርቡ እንደተደረገው ሁሉየፌደራል
  ፍ/ቤቶችን የይግባኝ እና የሰበር ሥርዓት ተከትለውና ተጠቃለው
  መታየትያለባቸው ስለመሆኑ።- ወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 109(3)፣116(2)
  አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀፅ 4(4)፣15(1)

  ...