Federal Court Case Tracker

 • “በአዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 27 መሰረት አግባብ ያለው አካል በሕገወጥ መንገድ የተያዘን የከተማ ቦታን የማስለቀቂያ ትዕዛዝ መስጠት እና ካሣ መክፈል ሳያስፈልግ የሠባት የሥራ ቀናት የጽሑፍ ማሥጠንቀቂያ ብቻ ለባለይዞታው በአካል በመስጠት ወይም በቦታው በሰፈረው ንብረት ላይ በመለጠፍ የማስለቀቅ ሥልጣን ይኖረዋል” በማለት የተቀመጠው ሀሳብ በሕጋዊ መንገድ ለተያዙ የከተማ ቦታዎችን ለማስለቀቅ የተቀመጠውን የማስለቀቂያ ትዕዛዝ የመስጠት እና ካሣ የመክፈል ሥርዓት ማሟላት ሳያስፈልግ በሕገወጥ መንገድ የተያዘን የከተማ ቦታን ማስለቀቅ የሚቻልበትን ሥርዓት የሚደነግግ እንጂ የከተማ ቦታን ወሮ ለያዘ ሰው የወንጀል ሀላፊነትን የሚያስቀር ስላለመሆኑ
  አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 26(4)፣27 

  Download here

 • በወንጀል ጉዳይ ፍርድ ከተሰጠ በኋላ አዲስ የወጣ ህግ ተከሳሹን የሚጠቅም በሆነ ጊዜ ተከሳሹ አዲሱ ህግ ተፈፃሚ እንዲሆን አቤቱታ ባቀረበ ጊዜ አዲስ የወጣው ህግ ተፈፃሚ እንዲሆን መደረግ ያለበት ስለመሆኑና በዚሁ ጉዳይ አቤቱታ የቀረበበት ጉዳይ በባህሪው እንደመደበኛ የክርክር ጉዳይ የሚታይ ሳይሆን በቀረበ ጊዜ ሊስተናገድ የሚችል በመሆኑ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የቀረበ አቤቱታ ነው በማለት ተቀባይነት የለውም የማይባል ስለመሆኑ 

  የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 22(2)፣ የወ/ሕ/አንቀጽ 6 እና 9(1)፤ ዓለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ስምምነት አንቀጽ15/1/ 

  Download here

 • የአንድ ቼክ ሕጋዊነት ጥያቄ ባላስነሳበት ፤በዋናነት ደግሞ ቼኩ ተጽፎ እና ተፈርሞ መሰጠቱ ባልተካደበት ሁኔታ እንዲሁም ቼክ እንደቀረበ ክፍያ የሚፈጸምበት ሰነድ ከመሆኑ አንፃር በወንጀል ጉዳይ ያለው ተጠያቂነት ቼክ በወጣበት ወይም ለክፍያ ለቀረበበት ጊዜ በቂ ስንቅ መኖር ያለመኖሩን መሠረት ያደረገ እንጂ ለዋስትና የተሰጠ መሆን ያለመሆን በወንጀል ጉዳይ እንደ ሕጋዊ መከላከያ የሚወሰድ ስላለመሆኑ
  የወንጀል ሕግ አንቀጽ 693(1) 

  Download here

 • አንድ ምስክር በፖሊስ በወንጀል ምርመራ ወቅት የሚሰጠዉ ቃል እንደመደበኛዉ የዳኝነት አካል ወይም የዳኝነት ነክነትወይም መሰል /quasi-judicial/ ተቋም ቃለ መሃላ ፈጽሞ የሚሰጥ የምስክርነት ቃል ባለመሆኑ ምስክሩ በፖሊስ የምርመራ መዝገብ የሰጠው የምስክርነት ቃል ፍ/ቤት ቀርቦ በመለወጡ ምክንያት የሀሰት ቃል የትኛዉ እንደሆነ በትክክል በሌላ ማስረጃ ሳይረጋገጥ የምስክሩ ቃል መለያየት ብቻዉን በቂ ማስረጃ በማድረግ ምስክሩ በሀሰተኛ የምስክርነት ቃል መስጠት ወንጀል የሚጠየቅበት የህግ መሰረት ስላለመኖሩ
  የወንጀል ህግ አንቀጽ 453/2/

  Download here

 • አንድ ተከሳሽ በአንድ ቸልተኝነትና በአንድ ድርጊት በደረሱ ጉዳቶች በተደራራቢ ወንጀሎች ሲከሰስ ሌላ የተለየ ሀሳብና ድርጊት መኖሩ እስካልተረጋገጠ ድረስ አንዱን በቸልተኝነት ሌላዉን ደግሞ ሆን ተብሎ ታስቦ በተፈጸመ ወንጀል ጥፋተኛ የሚደረግበት አግባብ እና ቅጣትን በሚመለከት ተደራራቢ ወንጀሎች ተፈጽመዉ ሲገኙ ቅጣት ሊወሰን የሚገባዉ ለእያንዳንዱ ወንጀል መነሻ ቅጣት ከተያዘ በኃላ እነዚህን በመደመር ድምሩ የቅጣት መጠን የሚያርፍበትን ዝቅተኛ የቅጣት እርከን በመለየት ስለመሆኑ  የተሻሻለዉ የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 02/2006 አንቀጽ 22(1/ሀ)  

  Download here

 • በአንድ የወንጀል ክስ ማመልከቻ ላይ ተጠቅሶ የቀረበ ድንጋጌና የክሱ ፍሬነገር ዝርዝር ላይ በስህተት የተጠቀሰ ወይም ሳይጠቀስ የታለፈ መሠረታዊ ነገር መኖሩ ሳይረጋገጥ ከወዲሁ አንቀጽ ካልተለወጠ በሚል ምክንያት ክስ እንዲሻሻል ትእዛዝ መስጠትና ይህ ካልተፈጸመ በሚል የክሱን መዝገብ መዝጋቱ ክስ እንዲሻሻል የሚደረግብትን ህጋዊ አላማ ያላገናዘበ ስለመሆኑ 

  አንድ ተከሳሽ ላይ የቀረበ ክስ ሁለት ሆኖ 1ኛዉ ክስ ቀደም ሲል ፍርድ ቤት በሰጠው ትእዛዝ መሰረት ተሻሽሎ ባለመቅረቡ የሚዘጋ ቢሆን ሁለተኛዉ ክስ ላይ ያለምንም ህጋዊ ምክንያት ዉሳኔ ሳይሰጥ ማለፍ ሥነ-ሥርዓታዊ ስላለመሆኑ
  በወ/መ/ስ/ስ/ህግ ቁ/112፣113/2/፣119

  Download here

 • አንድ የአሽከርካሪነት ሙያ ያለዉ ሰዉ የትራፊክ ደህንነት ደንብን ተላልፎ በተሽከርካሪዉ የኋላ የዉጭ አካል ላይ ሰው አሳፍሮ ሲያሽከረክር ተሳፋሪው ለመዉረድ ሲል መዉደቁ ወይም ለመዉረድ ሲል ዘሎ በመዉደቁ ለደረሰበት ጉዳት አሽከርካሪውን በቸልተኝነት ተጠያቂ ከመሆን የማያስቀረው ስለመሆኑ
  የወ/ሕ/አንቀጽ 24፣ 59፣543(3)፣ በትራፊክ ደህንነት ደንብ ቁጥር 208/2003 አንቀጽ 36(1)

  Download here

 • የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ ለይግባኝ ማቅረቢያና ተያያዥ ጉዳዮች የጊዜ ገደብ ቢያስቀምጥም በመታየት ላይ ያለ መዝገብ መዘጋቱ አስፈላጊ ሆኖ ከተዘጋ በኃላ እንደገና መከፈቱ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በምን ያህል ጊዜ ዉስጥ አቤቱታ ሊቀርብበት እንደሚገባ በግልፅ ስላላስቀመጠ የጊዜ ገደቡ የሚወሰነው  የጉዳዩን ሁኔታዎችና የአቤቱታዉን ዓይነት በመመልከት እንጂ መዝገቡን ለማንቀሳቀስ የቀረበዉ አቤቱታ ከተወሰነ ጊዜ በኃላ የቀረበ ነው በማለት አቤቱታውን ውድቅ ማድረግ የይግባኝ ባዩን መብት የሚጣብብ ስለመሆኑ በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 22(2)፤በወ/ሕ/አንቀጽ 6፣ 9(1) 

  Download here

 • የዳኝነት ስራ አካሄድ ላይ በሚፈጸሙ ወንጀሎች በተለይም አንድ ችሎት በያዘዉ መዝገብ ላይ ችሎት መድፈርን በተመለከተ ወዲያዉኑ ቅጣት ሊወስን ስለሚችልበት አግባብ የወንጀል ህጉ አንቀጽ 449 ፣ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁ/480 እና 481 

  Download here

   

 • Cassation Decision no. 21411

 • በወንጀል ህግ የሃሳብ ክፍል የሚረጋገጠው ከወንጀል ድርጊት አፈፃፀሙ በመነሳት ስለመሆኑ የወ/መ/ህ/ቁ. 522 /1/ /ሀ/

  Cassation Decision no. 22069

 • በወ/መ/ህ/ቁ. 522/1/ /ሀ/ ሥር የተመለከቱት የወንጀል ማቋቋሚያ ነጥቦች ለየራሳቸው የሚቆሙ ስለመሆናቸው የወ/መ/ህ/ቁ. 522/1/ /ሀ/

  Cassation Decision no. 22452

 • Cassation Decision no. 22514

 • Cassation Decision no. 22514

 • በውጭ ሀገር ተመዝግቦ የህግ ሰውነት ያገኘ ኩባንያ በኢትዮጵያ የንግድ ምልክት ምዝገባ ጥያቄ አቅርቦ በሂደት ላይ ያለ መሆኑ በውጭ አገር ያገኘውን የህግ ሰውነት ቀሪ የሚያደርገው ስላለመሆኑ የንግድ ህግ ቁ. 1ዐዐ

  Cassation Decision no. 23628

 • የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ሳይፈፀምበት የመንግስት ቀረጥ ያልተከፈለበት መኪና ይዞ የተገኘ ግለሰብ በወንጀል ተከስሶ ጥፋተኛ ያልተባለ ቢሆንም ግለሰቡ ተገቢውን ቀረጥ ከፍሎ መኪናውን መረከብ አልያም ደግሞ መኪናው መወረስ ያለበት ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 60/89 አንቀጽ 74 አዋጅ ቁ. 388/95 አንቀጽ 80/3/

  Cassation Decision no. 23855

 • በአዋጅ ቁ. 214/74 አንቀጽ 13/1/ መሠት የተከሰሰ ሰው ጥፋተኛ ሊባል የሚችለው እንዲጠብቃቸው በአደራ የተረከባቸውን ወይም በሥራው አጋጣሚና ምክንያት በእጁ የገቡትን ንብረቶች የወሰደው/የሰወረው/ ለራሱ ወይም ለሌላ ሰው ተገቢ ያልሆነ ብልጽግና ለማግኘት የሆነ እንደሆነ ስለመሆኑ

  Cassation Decision no. 24278

 • በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 122/2/ መሠረት ከሣሽ አቅርቦት የነበረውን ክስ ካነሣ በኋላ እንደገና ክሱን ለመቀጠል የሚችል ስለመሆኑ የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 122/2/, /5/

  Cassation Decision no. 28952

 • በወንጀል ክስ የቀረበበት ሰውን አስመልክቶ ጉዳዩ በሌለበት ነው የታየው ሊባል የሚችልበት አግባብ የወ/መ/ሥ/ሥ/ቁ. 161/1/

  Cassation Decision no. 29325

 • Cassation Decision no. 31731