Federal supreme court of Ethiopia cassation decisions

  • የመጥፋት ውሣኔ የተሰጠበት ሰው ቀደም ሲል ጋብቻ የነበረው እንደሆነ የጠፋው ሰው መመለስ በመጥፋት ውሣኔው የፈረሰውን ጋብቻ እንደገና ተመልሶ ህይወት እንዲዘራ (እንዲፀና) የማድረግ ውጤት አለው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣  በፍ/ቤት የተሰጠ የመጥፋት ውሣኔ መሻር በመጥፋት ውሣኔው መሠረት የፈረሰን ጋብቻ ከፈረሰበት ቀን ጀምሮ (ግለሰቡ ከተመለሰበት ቀን ጀምሮ) መልሶ እንዲቋቋም (እንዲፀና) ለማድረግ የሚያስችል ስላለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ.170,171

    Download Cassation Decision

  • አንድን ክርክር ለማስረዳት የቀረበን ማስረጃ ህጋዊነት አስመልክቶ የሚቀርብ ክርክር ሊቀርብና ታይቶ ሊወሰን የሚገባው በዚያው ዋናው ጉዳይ በቀረበበት ፍ/ቤት ስለመሆኑ፣

    Download Cassation Decision

  • የፍርድ አፈፃፀም ጥያቄ በህጉ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርቦ የባለዕዳው ንብረት እዳውን ለመሸፈን ባለመቻሉ በከፊል ተፈጽሞ ከቆየ በኋላ የፍርድ ባለመብት የባለዕዳውን ንብረት አፈላልጐ በማግኘት አፈፃፀሙን ለመቀጠል ሲፈልግ ይርጋ ሊቆጠር ስለሚችልበት አግባብ፣ አበዳሪ የሆነ ባንክ ከዕዳው አከፋፈል ጋር በተያያዘ በባለዕዳው ላይ የአፈፃፀም ክስ መስርቶ እንደ ፍርዱ ለመፈፀም የማይችል መሆኑ የተረጋገጠ ከሆነ በሌላ ጊዜ በባለዕዳው ንብረት ላይ በፍርድ ባለመብቱ የሚቀርበው የአፈፃፀም አቤቱታ ላይ ተፈፃሚ የሚሆነው የይርጋ ጊዜ መቆጠር ስለሚጀምርበት ጊዜ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 384, 329(2) አዋጅ ቁ. 97/90

  • የአላቂ ነገር ብድር ውል ጋር በተገናኘ፣ የመመለሻ ጊዜው በግልጽ ተለይቶ የተሰጠን የገንዘብ ብድር በተመለከተ አበዳሪው በውሉ የተመለከተው ጊዜ ካለፈ በኋላ ተበዳሪው የብድሩን ገንዘብ እንዲመለስ ማስጠንቀቂያ የመስጠት ግዴታ የሌለበት ስለመሆኑ፣  የብድሩ ገንዘብ መክፈያ ጊዜው በተወሰነ የብድር ውል ስምምነት ገንዘብ የተበደረ ወገን የመክፈያ ጊዜው ካለፈበት (ካበቃበት) ጊዜ ጀምሮ ወለድ ለመክፈል ስምምነት ያልተደረገ ቢሆንም፣ በድሩን ከነ ህጋዊ ወለዱ ለመክፈል የሚገደድ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ.2482(2)(3),2483, 2489(1),1676, 2478

    Download Cassation Decision

  • የአቃቤ ህግ ሙያን በሹመት የሚያከናውኑ ሰዎች ጋር በተገናኘ ቅጥር፣ ዝውውርና የደረጃ እድገትን አስመልክቶ የሚቀርብ አቤቱታን አይቶ ለመወሰን ስልጣን የተሰጠው አካል የአቃቤያነ ህግ አስተዳደር ጉባኤ ስለመሆኑና መደበኛ ፍ/ቤቶች ጉዳዩን ለማየት ስልጣን ያልተሰጣቸው ስለመሆኑ፣ ደንብ ቁ.24/99 አንቀጽ 46(3), 41, 44, 2 (4) አዋጅ 568/2000 አንቀጽ 2(7),3,10(1),4,5 የአ/አ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ ቁ.6/2000 አንቀጽ 2(5)(ሐ)

    Download Cassation Decision

  • በአንድ ወቅት የነበረን የተገነባ የመንገድ ደረጃ መነሻ (መሠረት) በማድረግ በመንገዱ ግራ ቀኝ አዋሣኝ በሆነ ይዞታ ላይ ተገቢውን ርቀት በመጠበቅ ንብረትን ያፈራ ሰው በሌላ ጊዜ የመንገዱ ደረጃ ከፍ እንዲል በመደረጉ የተነሣ በአዋሣኝ ይዞታው ላይ ግለሰቡ ያፈራቸው ንብረቶች ላይ ጉዳት የደረሰ እንደሆነ፣ ጉዳት ያደረሰው ወገን ካሣ የመክፈል ኃላፊነት ያለበት (የሚኖርበት) ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 65/1936 አንቀጽ 2(ሀ) አዋጅ ቁ. 66/1936 አንቀጽ 1(ለ) አዋጅ ቁ. 455/1997,የኤ.ፌዲሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 40(8)

    Download Cassation Decision

  • ፍ/ቤቶች በወንጀል ረገድ የሚሰጧቸው ማናቸውም ውሣኔ በወ/ህ/አ. 2 የተደነገገውን የህጋዊነት መርህ መሠረት በማድረግ መሆን ያለበት ስለመሆኑ፣ ፍ/ቤቶች በወንጀል ጉዳይ ንብረት ወይም ሀብት እንዲወረስ ወይም ለመንግስት ገቢ እንዲሆን በሚል ውሣኔ ለመስጠት የሚችሉት በወንጀል ህግ በግልጽ የተደነገገ ድንጋጌ የተመለከተ እንደሆነ ብቻ ስለመሆኑ፣  በወንጀል ጉዳይ አንድ ንብረት (ሀብት) እንዲወረስ ወይም ለመንግስት ገቢ እንዲሆን ሊወሠን የሚችለው ንብረቱ (ሀብቱ) አንድን ሰው ለወንጀል ሥራ እንዲያነሳሳ ወይም ወንጀሉን ለመስራት እንዲረዳው ወይም ደግሞ ወንጀሉን ለፈፀመበት ዋጋ እንዲሆነው የተሰጠው ወይም ሊሠጠው የታቀደን ማንኛውም ጥቅም የተመለከተ ንብረት (ሀብት) ስለመሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ ስለመሆኑ ወይም ንብረቱ (ሀብቱ) የወንጀል ድርጊቱን ለመፈፀም ያገለገለ ወይም ሊያገለግሉ የሚችሉ ወይም የወንጀል ተግባር ፍሬ የሆኑ ማናቸውም ነገሮች ጋር የተያያዘ ወይም የተመለከተ እንደሆነ ስለመሆኑ፣ የወ/ህ/አ. 98,100,140, 2(1) (2)

    Download Cassation Decision

  • የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ህጋዊነትና ተቀባይነት ጋር በተናኘ የምስክር ወረቀቱ ሊሰጥ የቻለው የንብረት ባለሀብትነት መብትን ከአንዱ ወገን ወደ ሌላው እንዴት መተላለፍ እንዳለበት በህጉ የተመለከተውን ደንብና ሥርዓት ሳይከተል ስለሆነ የንብረቱ ባለሀብት ስለመሆን የህግ ግምት መውሰጃ የሆነው የባለቤትነት የምስክር ወረቀት ቀሪ ነው፣ ሊሰረዝ ይገባል በማለት የሚቀርብ አቤቱታ በፍ/ቤት ሊረጋገጥ የሚችል የዳኝነት ጥያቄ እንጂ ጉዳዩ በፍርድ ሊያልቅ የሚችል አይደለም ለማለት የሚያስችል ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ.1195,1196፣Download Cassation Decision

  • በጋብቻ ወቅት በአንደኛው ተጋቢ ስም የተመዘገበና በጋብቻ ወቅት ዕጣው የወጣ የኮንዶሚንየም ቤት ላይ ያለ መብት የቤቱ ውል ከጋብቻ መፍረስ በኋላ የተፈፀመና ቅድሚያ ክፍያ የተከፈለ መሆኑ (የንብረት ክፍፍል እስካልተፈፀመ ድረስ) ንብረቱን የግል የሚያስብል ስላለመሆኑ

    Download Cassation Decision

  • በጋብቻ ወቅት በአንደኛው ተጋቢ ስም የተመዘገበና በጋብቻ ወቅት ዕጣው የወጣ የኮንዶሚንየም ቤት ላይ ያለ መብት የቤቱ ውል ከጋብቻ መፍረስ በኋላ የተፈፀመና ቅድሚያ ክፍያ የተከፈለ መሆኑ (የንብረት ክፍፍል እስካልተፈፀመ ድረስ) ንብረቱን የግል የሚያስብል ስላለመሆኑ

    Download Cassation Decision

  • የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ አመዘጋገብ ጋር በተያየዘ በተፈፀመ ስህተት ንብረቱን በመያዣ የያዘው ወገን የሚደርስበትን ጉዳትና ኪሣራ ኃላፊነቱን በአግባቡና በጥንቃቄ ባለመወጣት ስህተቱን የፈፀመው የሚመለከተው የአስተዳደር አካል ጉዳትና ኪሣራውን በመያዣ በተያዘው ንብረት ዋጋ መጠን ለመክፈል ኃላፊነት ያለበት ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ.1640(2), 3052, 3053(1),3081

    Download Cassation Decision

  • የፍ/ቤቶች የግዛት ስልጣን በዋነኛነት መሠረት የሚያደርገው ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ጉዳይ የተፈጠረበት ቦታ ለተከራካሪ ወገኖች የሚኖረውን አመቺነት ሲሆን የሥረ ነገር ስልጣን መሠረት የሚያደርገው ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ጉዳይ ይዘት፣ የተከራካሪ ወገኖችን መብትና ጥቅም ክብደትና መጠን እንዲሁም የጉዳዩን የውስብስብነት ደረጃ ስለመሆኑ፣  ፍርድን የማስፈፀም ጉዳይ በስረ ነገር ክርክር ተረጋግጠው የፍርድ ሀይል ያገኙትን የተከራካሪ ወገኖች መብቶችና ግዴታዎች በሥነ ሥርዓት ህጉ የተደነገገውን የአፈፃፀም ስርዓት ተከትለው እንዲፈፀሙ ከማድረግ ውጪ አዲስ መብትና ግዴታ የሚቋቋምበት ሂደት ስላለመሆኑና የማስፈፀም ስልጣን በመርህ ደረጃ የፍ/ቤቶች የሥረ ነገር ስልጣንን የሚከተል ስለመሆኑ፣  አስፈላጊ እና ተገቢ በሆኑ ሁኔታዎች ሥረ ነገሩን የወሰነ ፍ/ቤት በአፈፃፀም ጉዳዮችን በውክልና የሥረ ነገር ስልጣን ለሌለው ፍ/ቤት ሊያስተላልፍ ስለመቻሉ፡ አዋጅ ቁ. 25/88 አንቀጽ 5(2) የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 371, 372, 9, 10

    Download Cassation Decision

  • አንድ ኢትዮጵያዊ የሆነ የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማህበር ከውጭ ምንጭ በህጉ ከተመለከው የገንዘብ መጠን በላይ እንዲሰበሰብ ሊፈቅድ የማይችል ስለመሆኑ፡- አዋጅ ቁ. 621/2001 አንቀጽ2/2/፣3/4/፣14/5/፣14/2/፣6፣90፣111/2/፣112፣108፣110 ደንብ ቁጥር 168/2002 አንቀጽ 18/3/፣10/2/፣36

    Download Cassation Decision

  • አንድ ቀድሞ በመያዣ የተሰጠ የማይንቀሳቀስ ንብረት ካርታ ቁጥሩና የቤት ቁጥሩ ተለውጦ እንዲሁም ቀደም ሲል የነበረው ቤት ፈርሶ በቦታው ላይ አዲስ ቤት ተሠርቶና አዲስ ካርታና የቤት ቁጥር ተሰጥቶ በተገኘ ጊዜ አዲሱን ቤት በመያዣ የያዘ አበዳሪ ቀድሞ የነበረውን ቤት በመያዣ ከያዘው አበዳሪ የቅድሚያ መብት ያለው ስለመሆኑ፣ በፍ/ብ/ህ/ቁ. 3052, 3066

  • በወንጀል ጉዳይ የተከሰሰን ሰው የወንጀል ድርጊቱን ስለመፈፀሙ ለማስረዳት መቅረብ የሚገባው የማስረጃ አይነት ለጉዳዩ ቀጥተኛ ተዛማጅነት ያላቸው ፍሬ ነገሮች ለማስረዳት የሚችልና ድርጊቱ ሲፈፀም አይቻለሁ ወይም/እና ሰምቻለሁ የሚል ቀጥተኛ ማስረጃ ብቻ ነው ለማለት የሚያስችል የህግ መሠረት የሌለ ስለመሆኑ የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 137, 141, 149

  • አንድ የወንጀል ድርጊትን ማስረዳት ጋር በተያያዘ የአካባቢ ሁኔታ ማስረጃ (circumstantial evidence) በይዘቱ አንድ ክስተት ከመፈጠሩ በፊት፣ ክስተቱ ሲፈጠር ወይም ድርጊቱ ሲፈፀምና ክስተቱ ከተፈጠረ ወይም ድርጊቱ ከተፈፀመ በኋላ፣ ያሉትን አካባቢያዊ ሁኔታዎች የሚያሣይና የሚገልጽ በመሆኑ ህጋዊ ተቀባይነት ያለው ስለመሆኑ፣ የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 137(1)