Federal supreme court of Ethiopia cassation decisions

  • የመኪና ሽያጭ ውል መደረጉን (መኖሩን) ለማስረዳት ሊቀርብ ስለሚገባው የማስረጃ አይነት፣  የመኪና /ተሽከርካሪ/ ባለሀብትነት (ስመ ሀብት) እንዲተላለፍለት የሚጠይቅ ሰው ሊያቀርባቸው ስለሚገቡና ተቀባይነት ስላላቸው ማስረጃዎች አንድ ግዴታ እንዲፈፀምለት የሚጠይቅ ሰው የግዴታውን መኖር የማስረዳት ሸክም ያለበት ስለመሆኑ፣  አከራካሪ ሆኖ የቀረበን አንድ ፍሬ ነገር ማስረዳት ስለሚቻልበት የማስረጃ አይነት አግባብነት ባለው ህግ በተለይ የተቀመጠ ግለጽ ድንጋጌ እስከሌለ ድረስ ማናቸውንም ዓይነት ማስረጃ አቅርቦ ጉዳዩን ለማስረዳት ስለመቻሉ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ.1186(1),(2),2001(1) ስለ ተሽከርካሪ መለያ መመርመሪያና መመዝገቢያ አዋጅ ቁ.681/2002 አንቀጽ 6(3)(4)

    Download Cassation Decision

  • ከፍርድ አፈፃፀም ጋር በተገናኘ በአንድ በቀረበ የዋና ጉዳይ ክርክር ሒደት የእግድ ትዕዛዝ የተሰጠበት ንብረት በተመሳሳይ ተከራካሪ ወገኖች ጥያቄ በአፈፃፀም ደረጃ በተጠቃሹ ንብረት ላይ አፈፃፀም እንዲቀጥል በሚል የሚቀርብ አቤቱታ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ፣  ቀደም ሲል በዋና ጉዳይ ክርክር በፍ/ቤት ትእዛዝ እንዲታገድ የተደረገ መሆኑ የታወቀ ንብረት ላይ በድጋሚ በተመሳሳይ ንብረት ላይ መብትን ለማስከበር በሚል በሌላ ጊዜ በአፈፃፀም ደረጃ የሚቀርብ ጥያቄ ተገቢነት የሌለው ስለመሆኑ፣

    Download Cassation Decision

  • የስራ ውል የሚመሠረተው ማንኛወም ሰው ደመወዝ እየተከፈለው በአሰሪው መሪነት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ለተወሰነ ወይም ላልተወሠነ ጊዜ ወይም የተወሰነ ሥራ ለአሰሪው ለመስራት የተስማማ እንደሆነ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 2(3),

    Download Cassation Decision

  • በብድር የሚሰጥ ገንዘብ ላይ ተዋዋይ ወገኖች ሊያቋቁሙት ስለሚችሉት የወለድ ምጣኔ (መጠን)፣  የውል ግዴታውን ያልፈፀመ ወይም ያዘገየ ወገን ለሌላኛው ተዋዋይ ስለሚከፍለው የኪሣራ መጠን፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1803(2),1790(2),1800,2479(3),2488,2489

    Download Cassation Decision

  • ከንግድ ምዝገባ ፈቃድ ጋር በተገናኘ የሚነሱ የፍሬ ነገር ክርክሮችን የመደበኛ ፍ/ቤቶች አይተው ለመወሰን ስልጣን የሌላቸው ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 686/2002 አንቀጽ 61

    Download Cassation Decision

  • የፌዴራል መንግስት ጊዜያዊ (የኮንትራት) ሠራተኞች ቅጥር ጋር በተገናኘ በሠራተኛ እና በቀጣሪው መካከል የሚነሱ ክርክሮችን በተመለከተ የመደበኛ ፍ/ቤቶች ጉዳዩን በቀጥታ ክስም ሆነ በይግባኝ ለማስተናገድ ስልጣን ያላቸው ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ.515/99 አንቀጽ 22(3) ,2(1) የፌዴራል መንግስት ጊዜያዊ የኮንትራት ሰራተኞች ቅጥር አፈፃፀም መመሪያ

    Download Cassation Decision

  • አንድ በንግድ ሥራ የተሰማራ ሰው (ድርጅት) በተጨማሪ እሴት ታክስ ግብር ከፋይነት የመመዝገብ ግዴታ አለበት ለማለት የሚቻልበት እንዲሁም መመዝገብ ሲኖርበት ሳይመዘገብ ቀርቶ ግብር ሊጣልበት ስለሚችልበት አግባብ፣ አዋጅ ቁ.285/94 አንቀጽ 3(1)(3), 16(1)(ለ)

    Download Cassation Decision

  • አሠሪ ሠራተኛውን እንደ ሠራተኛ በመቀበል የሚሰራውን ሥራ ባልሰጠበት ሁኔታ ሠራተኛውን ከሥራ ገበታው ቀርቷል በሚል ያለ ማስጠንቀቂያ ለማሰናበት የማይችል ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 27(1) ለ

    Download Cassation Decision

  • አንድ የመንግስት መ/ቤት በሠራተኛው ተግባር በኃላፊነት ሊጠየቅ የሚችለው በሠራተኛው የተፈፀመው ጥፋት የሥራ ጥፋት ሆኖ ሲገኝ ስለመሆኑ፣  አንድ ጥፋት የሥራ ጥፋት ነው ተብሎ የሚወሰደው ጥፋት አድራጊው በጥፋቱ ላይ የወደቀው በቅን ልቦና በስልጣኑ ለሥራው ክፍል መልካም ያደረገ መስሎት የፈፀመው መሆኑ ሲረጋገጥ ስለመሆኑና ከዚህ ውጪ በሆነ ጉዳይ ግን ጥፋቱ እንደ ግል ጥፋት የሚቆጠር ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2126, 2127 (1)(2)(3)

    Download Cassation Decision

  • የማይንቀሣቀስ ንብረት (ቤት) ሽያጭ ውል ጋር በተገናኘ ሻጭ በውሉ መሠረት የቤቱን ስመ-ንብረት የሚመለከተው አካል ወደ ገዢው ለማዞር እንዲችል በሚመለከተው ክፍል ቀርቦ ተገቢውን እንዲፈፀም በማለት ገዥ የሚያቀርበው ክስ የክስ ምክንያት የለውም ሊባል የማይችል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 231(1)(ሀ), 33(2-3), 222, 224

    Download Cassation Decision

  • አንድ ሠራተኛ በሥራው አፈፃፀም ምዘና ደካማ ነው በማለት የሥራ ውሉን ለማቋረጥ የሚቻለው ምዘናውን ሠራተኛው በተቀጠረበትና በተመደበበት የሥራ አይነት (መስክ) ላይ በማድረግ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 42, 43(1)

    Download Cassation Decision

  • አንድ ሠራተኛ መብቱን ለማስከበር በአሰሪው ላይ በፍ/ቤት ክስ መመስረቱ ብቻ ከአሠሪው ጋር ለወደፊት የሻከረ ግንኙነት ይፈጥራል የማያስብልና የስራ ውሉ እንዳይቀጥል ለማድረግ የሚያስችል ምክንያት ስላለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 43(3)

    Download Cassation Decision

  • አንድ ተከሳሽ በሌለበት ጉዳዩ እንዲታይ ብይን መስጠቱ ፍርዱ ለከሣሽ በሚጠቅም መልኩ (መንገድ) የመወሰኑን ሁኔታ በአስገዳጅነት የሚያስከትል ነው ለማለት የማይችል ስለመሆኑ፣  የማህበር ሊቀመንበርን ከስልጣን ለማንሳት ስለሚቻልበት አግባብ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 70(ሀ)

    Download Cassation Decision

  • የንግድ ማህበር ሒሣብ ከተጣራና ትርፍና ኪሣራው ተለይቶ ከቀረበ በኋላ የማህበር አባል (ባለአክሲዮን) የሆነ ሰው ከትርፍ ሊደርሰው የሚገባውን የድርሻ ክፍያ በመለየት ክፍያ እንዲፈፀምልኝ በማለት የሚያቀርብው ጥያቄ ህጋዊ ተቀባይነት ያለው ስለመሆኑ፣ የንግድ ህግ ቁጥር 211, 517, 518, 532(1)

    Download Cassation Decision

  • በወንጀል ጉዳይ ተከስሶ ጥፋተኛ የተባለ ሰው ላይ የሚወሰነው ቅጣት በቅጣት አወሣሠን መመሪያው የተሸፈነ እንደሆነ ቅጣቱ በመመሪያው አግባብ ሊወሰን የሚገባ ስለመሆኑ፣  በወ/ህ/አ 539(1)(ሀ) ድንጋጌ ክስ ቀርቦበት ጥፋተኛ የተባለ ሰው ለእያንዳንዱ የቅጣት ማቅለያ ምክንያት ሶስት እርከን ሊቀነስለት የሚገባ ስለመሆኑ፣ የወ/ህ/አ. 539(1)(ሀ) የፌ/ጠ/ፍ/ቤት የቅጣት አወሣሠን መመሪያ ቁ.1/2002 አንቀጽ 16(7)

    Download Cassation Decision

  • ኑዛዜ ፈራሽ ነው በሚል ስለሚቀርብ ክስ እና ክሱ ሊቀርብ ስለሚገባበት የጊዜ ገደብ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 973, 974

    Download Cassation Decision

  • የንግድ ቤትን ከመንግስት የተከራየ ተከራይ ከአከራዩ እውቅና ውጭ ለ3ኛ ወገን የንግድ ቤቱን ማስተላለፉ አከራዩ የመጀመሪያውን የኪራይ ውል ለማቋረጥ የሚያስችለው ስለመሆኑ፣ በዚሁ መሠረትም አከራዩ ቤቱን ለማስለቀቅ የሚያያደርግው እንቅስቃሴ ሁከት ሊባል የማይችል ስለመሆኑ፣ መመሪያ ቁጥር 4/2004 አንቀጽ 6 የፍ/ብ/ህ/ቁ.1140, 1149

    Download Cassation Decision

  • ሚስትነትን በተመለከተ የአመልካችን ማስረጃ ብቻ በመቀበል ሚስትነትን በማረጋገጥ በፍ/ቤት የሚሰጥ ማስረጃ (Declaratory Judgment) በማናቸውም ጊዜ ተዓማኒነትና ክብደት የሌለው ማስረጃ መሆኑን ለማሳየት ክርክር ሊቀርብበትና ተቃራኒ ማስረጃ ተሰምቶ ውድቅ ሊደረግ የሚችል እንጂ ማስረጃውን በተሰጠው ፍ/ቤት ተቃውም በማቅረብ ያልተሻረ በመሆኑ ተቀባይነት ያለው ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣

    Download Cassation Decision

  • ከውርስ ሀብት ክፍፍል ጥያቄ ጋር በተገናኘ መብቱን ለማስፈፀም ጠይቆ በአፈፃፀም በገባበት የዋስትና ግዴታ መሰረት ተጠያቂ ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1827(1)

    Download Cassation Decision

  • የሥራ ክርክር ችሎት አንድን ሠራተኛ ያለአግባብ የተሰናበተ ነው በሚል ውሣኔ ከተሰጠበት ቀን ወደኋላ ቀደም ብሎ ካለ ጊዜ ጀምሮ አሰሪው ወደ ሥራ እንዲመልስ በሚል ውሣኔ የሰጠ እንደሆነ ሠራተኛው ከተጠቀሰው ጊዜ ጀምሮ ውዝፍ ደመወዝ ለማግኘት መብት የሚኖረው ስለመሆኑ፣

    Download Cassation Decision