Federal supreme court of Ethiopia cassation decisions

  • አንድን ሰው በመወከል በፍርድ ቤት ቀርቦ ለመሟገት በህጉ የተቀመጠውን የዝምድና ደረጃ ወይም በህጉ የተቀመጡትን መስፈርቶች የሚያሟላ የውክልና ስልጣን የሚያስፈልግ ስለመሆኑ፣ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/ 58(ሀ)፣63

    Download Cassation Decision

  • አንድ ሠው ወንጀል አደረገ የሚባለው ህገ ወጥነቱ እና አስቀጪነቱ በህግ የተደነገገን ድርጊት ፈጽሞ የተገኘ እንደሆነ ስለመሆኑና አንድ ወንጀል ተደረገ የሚባለውም ወንጀሉን የሚያቋቁሙት ህጋዊ፣ ግዙፋዊና ሞራላዊ ፍሬ ነገሮች በአንድነት ተሟልተው ሲገኙ ስለመሆኑ፣  ማንም ሰው በዋና ወንጀል አድራጊነት ወንጀል እንዳደረገ ተቆጥሮ የሚቀጣው በቀጥታ ወይም በእጅ አዙር ወንጀሉን ያደረገ በሆነ ጊዜ ወይም ወንጀሉን እርሱ በቀጥታ ባያደርገውም እንኳን በሙላ አሳቡና አድራጐቱ በወንጀሉ ድርጊትና በሚሰጠው ውጤት ሙሉ ተካፋይ በመሆኑ ድርጊቱን የራሱ ያደረገ እንደሆነ ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 2፣23(1)፣ 32(1) የወ/መ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ. 111፣112፣141፣142

    Download Cassation Decision

  • በፍርድ ቤት የተሰጠ ውሣኔ ሕጋዊ ባልሆነ እና ውሳኔውን ውጤት አልባ በሚያድርግ መልኩ ውድቅ ሊደረግ የሚችልበት አግባብ ስላለመኖሩ፣ የአስተዳደር አካል በባለቤትነት ማረጋገጫ ማስረጃ አሰጣጥ ላይ ፍጹም የሆነ አስተዳደራዊ ስልጣን ያለው ስላለመሆኑ፣ ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 378፣ 392 የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1195 እና 1196

    Download Cassation Decision

  • የማይገባውን ክፍያ የከፈለ ሰው ገንዘቡን ከከፈለበት ቀን አንሥቶ ሕጋዊ ወለድ እንዲከፈለው ለመጠየቅ የሚችለው፣ ገንዘቡን የተቀበለው ሰው እምነትን በሚያጓድል ሁኔታ ክፍያውን ተቀብሎት በሆነ ጊዜ ብቻ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሕ/ቁ/ 2164(2)

    Download Cassation Decision

  • ባለፎቶግራፍ ወይም ባለስዕሉ ካልፈቀደ በቀር የማንም ሰው ፎቶግራፍ ወይም ስዕል በህዝብ አደባባይ ሊለጠፍም ሆነ ሊባዛ ወይም ሊሸጥ የማይችል ስለመሆኑና ፎቶው ወይም ስዕሉ ጥቅም ላይ ለዋለበት የማስታወቂያ ሥራ ባለፎቶው ወይም ባለስዕሉ ካሣ ሊከፈለው የሚገባ ስለመሆኑ፣ ለባለ ፎቶው ወይም ለባለስዕሉ የሚከፈለውን የካሣ መጠን ድርጊቱን የፈፀመው ሰው በዚሁ ድርጊት ያገኘው ሀብት (ጥቅም) ተመዛዛኝ በሚሆንበት መጠን በዳኛች ሊወሰን ስለመቻሉ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ 28 29(2), 2142

    Download Cassation Decision

  • በህብረት ሥራ ማህበራትና በአባሎቻቸው ወይም በቀድሞ አባላቸው ወይም በህብረት ስራ ማህበር አባላት ወይም የቀድሞ አባላትና በማህበሩ አመራር መካከል የሚነሳ ክርክር በመጀመሪያ ደረጃ የሽምግልና ጉባኤው ውሳኔ ሳይሰጥበት ፍርድ ቤቶች ተቀብለው ዳኝነት ለማየትና ለመወሰን የማይችሉ ስለመሆኑ፣የኢ.ፌ.ዲ.ሬ ህገ መንግስት አንቀጽ 37፣ አንቀጽ 79(1) እና አዋጅ ቁጥር 147/91 አንቀጽ 49

    Download Cassation Decision

  • ሀሰተኛ ማስረጃ ለፍ/ቤት በመቅረቡ የተነሣ የተወሰነበት ተከራካሪ ወገን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 6(1)ን መሠረት በማድረግ ፍርዱ በድጋሚ እንዲታይለት አቤቱታ ባቀረበ ጊዜ ሀሰተኛ ማስረጃውን የሰጠው አካል በምን ምክንያት በህገ ወጥ ተግባር ሀሰተኛውን ማስረጃ ሊሰጥ እንደቻለ የማስረዳት ግዴታ ጭምር አለበት ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 6(1) የወንጀል ህግ አንቀጽ 403፣405

    Download Cassation Decision

  • ጥቅምን መሠረት ባላደረገ ሁኔታ ህፃናትን (እድሜው ለአካለ መጠን ያልደረሰ ሰውን) አሳፍሮ በመጓዝ ወቅት በደረሰ አደጋ ምክንያት በህፃናቱ ላይ ጉዳት የደረሰ እንደሆነ የተሽከርካሪው ባለቤትና በወቅቱ በተሽከርካሪው ሲገለገል የነበረ ወይም ሹፌሩ የጉዳት ካሣ የመክፈል ኃላፊነት የሚኖርባቸው ስለመሆኑ፣  የተሽከርካሪ ባለቤት የሆነ ሰው ጥቅም በሌላው ግንኙነት መነሻ በተሽከርካሪው ተሳፍሮ ሲጓዝ በነበረ ሰው ላይ ለሚደርስ የአደጋ ጉዳት ካሣ ለመክፈል የማይገደድ ቢሆንም ጉዳቱ የደረሰው ከፍተኛ ጥንቃቄና እንክብካቤ ሊደረግላቸው በሚገባ ህፃናት ላይ በሆነ ጊዜና ህፃናቱም ጥንቃቄ ባልተሞላበት ሁኔታ በተሽከርካሪው ላይ የተጫኑ (የተሣፈሩ) እንደሆነ የተሽከርካሪው ባለቤት የጉዳት ካሣ የመክፈል ኃላፊነት የሚኖርበት ስለመሆኑ፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 36(2), 15, 25 የህፃናት መብቶች ስምምነት አንቀጽ 3, 6(1) የአፍሪካ ህፃናት መብቶችና ደህንነት ቻርተር አንቀጽ 4(1), 5(1) የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2126(2), 2127, 2130 2131, 2089(2), 2081(1)

    Download Cassation Decision

  • ለፍርድ ማስፈጸሚያ የቀረበን የማይንቀሳቀስ ንብረት ለመጀመሪያ የሐራጅ ሽያጭ የሚቀርብበትን የዋጋ ግምትን አስመልክቶ የተነሳ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን፣ፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 423(2)(ሀ)

    Download Cassation Decision

  • የጉዳት ካሳ አከፋፈልን በተመለከተ በአንድ ጊዜ ሊሆን የሚችል መሆን ያለመሆኑን ለመወሰን ለፍርድ ቤቱ የተተወ ስለመሆኑ፣ በአንድ የግል ድርጅት ውስጥ ተቀጣሪ የሆነ ግለሰብ የአካል ጉዳት በሚደርስበት ወቅት የጉዳት ካሳው አሰላሉ የጡረታ መውጫ እድሜውን መሰረት ቢያደርግ ተገቢ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2154፣2090፣2091፣2095 አዋጅ.ቁ715/2003

    Download Cassation Decision

  • አንድ ክስ እንደቀረበ የሚቆጠረው ክስ የቀረበበት ጽሁፍ በፍ/ቤት በቀረበ ጊዜ በመሆኑ፡- የመስቀለኛ ይግባኝ ክርክር ስለሚመራበት የህግ አግባብ፣ በተከራካሪ ወገኖች መካከል የሚቀርብን መስቀለኛ ይግባኝን በተመለከተ በህግ በግልፅ የተቀመጠ ድንጋጌ ባለመኖሩ ምክንያት በመደበኛነት የተቀመጡት የስነ ስርዓት ድንጋጌዎች ተፈፃሚ መሆን ያለባቸው ስለመሆኑ፣መልስ ሠጪው ወገን የሚያቀርበው ይግባኝ ማመልከቻ ግልባጭ ለይግባኝ እንዲደርስ ሊደረግ የሚቻለው ይግባኙ ያልተሰረዘ ከሆነ ብቻ ስለመሆኑ፣ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 213(1) ፣337 ፣338 ፣ 340(2)

    Download Cassation Decision

  • አንድ የትራፊክ ባለሙያ የሚሰጠው ሙያዊ አስተያየት የማስረጃ ዋጋ
    የማይሰጠው አስተያየቱ ተገቢውን የሙያ ደንብ ተከትሎ ያልተሰጠና
    ያልቀረበ፣በጊዜውና በቦታው ከነበሩት የአይን ምስክሮች ቃል ጋር
    ተነፃፅሮ ሲታይ በመሰረታዊ ነጥቦች ላይ ልዩነት ያለበት መሆኑ
    ሲረጋገጥ እንጂ በጭፍጫፊ ነጥቦች ላይ ልዩነት ተከስቷል ተብሎ
    ሊሆን እንደማይገባ፣
    የልዩ አዋቂዎች ምስክሮች ቃላቸውን ገለልተኛ ሆነው መስጠት እንደ
    አለባቸውና ቃላቸው ያለበቂ ምክንያት ልዩ አዋቂ ያልሆኑ ሰዎች
    በሚሰጡት የምስክሮች ቃል ውድቅ መሆን የሌለበት መሆኑን
    ተቀባይነት ያላቸው የማስረጃ ህግ ደንቦች የሚያስገነዝቡ ስለመሆኑ
    የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 141፣142፣194
    የወንጀል ህግ ቁጥር 24፣59፣239(2)፣57፣543(2)

    አንድ የትራፊክ ባለሙያ የሚሰጠው ሙያዊ አስተያየት የማስረጃ ዋጋ
    የማይሰጠው አስተያየቱ ተገቢውን የሙያ ደንብ ተከትሎ ያልተሰጠና
    ያልቀረበ፣በጊዜውና በቦታው ከነበሩት የአይን ምስክሮች ቃል ጋር
    ተነፃፅሮ ሲታይ በመሰረታዊ ነጥቦች ላይ ልዩነት ያለበት መሆኑ
    ሲረጋገጥ እንጂ በጭፍጫፊ ነጥቦች ላይ ልዩነት ተከስቷል ተብሎ
    ሊሆን እንደማይገባ፣
    የልዩ አዋቂዎች ምስክሮች ቃላቸውን ገለልተኛ ሆነው መስጠት እንደ
    አለባቸውና ቃላቸው ያለበቂ ምክንያት ልዩ አዋቂ ያልሆኑ ሰዎች
    በሚሰጡት የምስክሮች ቃል ውድቅ መሆን የሌለበት መሆኑን
    ተቀባይነት ያላቸው የማስረጃ ህግ ደንቦች የሚያስገነዝቡ ስለመሆኑ
    የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 141፣142፣194
    የወንጀል ህግ ቁጥር 24፣59፣239(2)፣57፣543(2)

    አንድ ፍርድ ሊፈጸም የሚገባው በፍርድ ባለእዳውና በሕግ አግባብ እንዳይያዙ ከሚጠቀሱት ንብረቶች/መብቶች ውጪ ባሉት የፍርድ ባለእዳ ንብረቶች /መብቶች ስለመሆኑ፣ በህግ አግባብ መብቱን ባስተላለፈ ንብረት ላይ የቀድሞ ባለቤት በድጋሜ ሽያጭ የሚፈጽምበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 378

    Download Cassation Decision

  • በአሰሪና ሰራተኛ መካከል ያለ የሥራ ግንኙነት በተቋረጠ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ የክፍያ ጥያቄ ያለበት አካል መብቱን ካልጠየቀ በይርጋ የሚታገድ መሆኑን፣ በተጨማሪነት ስድስት ወር ከሞላው(ካለፈው) በኃላ የሁለቱ የስራ ግንኙነት ቢቀጥል እንኳን አስቀድሞ የታገደውን የስንብት ክፍያ ጥያቄን ከአዋጁ ድንጋጌ ይዘት አኳያ የይርጋ ጊዜን ሊያቋርጥ የሚችል ስላለመሆኑ፣ አዋጅ 377 አንቀፅ 162(3)፣162(4)

    Download Cassation Decision

  • በአሰሪና ሰራተኛ መካከል የሚፈጠር የስራ ግንኙነትን መነሻ በማድረግ ሰራተኛው በሕግ የተሰጠውን መብቱን ለመተው የሚያደርገው ስምምነት የህግ ውጤት የማይኖረው ስለመሆኑ፡- አዋጅ ቁጥር 377/1996 በአንቀጽ 25(1)

    Download Cassation Decision

  • -በአሰሪና ሰራተኛ መካከል በሚደረግ የውል ግንኙነት ተዋዋይ ወገኖች የገቡትን ግዴታ በቅንነት ይፈፅማሉ ተብሎ የሚገመት ስለመሆኑ፣ - በአሰሪውና ሰራተኛው መካከል በሚደረግ የሥልጠናና የት/ት ውል መሰረት አሰሪው የሚጠበቅበትን ድጋፍ ለሰራተኛው የማድረግ ግዴታ ያለበት ስለመሆኑ፣ የፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 1732፣አዋጅ ቁጥር 377/96

    Download Cassation Decision

  • በችሎት በመገኘት ስልክን ማስጮህ ብሎም ፍርድ በሚነበብበት ጊዜ በችሎት ዳኛው ሥነ- ሥርዓት እንዲይዝ ሲነገረው ችሎቱ በሥነ-ሥርዓት ያናግረኝ በማለት ያልተገባ ባህሪ ማሣየት በችሎት መድፈር ወንጀል ሊያስቀጣ የሚችል ተግባር ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 481 የወንጀል ህግ ቁጥር 449(1)(ሀ)

    Download Cassation Decision

  • አንድን ሠራተኛ የሥራ መሪ ነው ለማለት የሚቻለው በህግ ወይም እንደ ድርጅቱ የሥራ ፀባይ በአሰሪው በተሰጠ የውክልና ስልጣን መሠረት የሥራ አመራር ፖሊሲዎችን የማውጣትና የማስፈፀም እንዲሁም በተጨማሪነት ወይም ይህንን ሣይጨምር ሠራተኛን የመቅጠር፣ የማዛወር፣ የማገድ፣ የመመደብ ወይም ሌሎች የሥነ-ሥርዓት እርምጃ የመውሰድ ተግባሮችን የሚያከናውን እንደሆነ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 3(2)(ሐ) አዋጅ ቁ. 494/98 አንቀጽ 2(1)(ሐ)

    Download Cassation Decision

  • ህጋዊ ቀረጥ የተከፈለበት ዕቃ ህጋዊ የግምሩክ ስርዓት ካልተፈፀመበት ዕቃ ጋር ተቀላቅሎ ከተያዘ እና ከተወረሰ በህጋዊ መንገድ ዕቃው ሲገባ የተከፈለው ቀረጥ(tax) እንዲመለስለት የዕቃው ባለቤት የሚጠይቅበት የህግ ስርዓት ስላለመኖሩ፣ አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀፅ 104(3)

    Download Cassation Decision