Federal supreme court of Ethiopia cassation decisions

  • በአሰሪና ሰራተኛ መካከል በተነሳ ክርክር በመጀመሪያ ደረጃ የቀረበው ለክልል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ከሆነ ጉዳዩ በተነሳበት ክልል የሰበር ችሎት የተደራጀ እስከሆነ ድረስ በክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ሳይታይ እና ውሳኔው የመጨረሻ መሆኑ ሳይረጋገጥ በቀጥታ ለፌዴራል ጠ/ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቀርቦ ሊስተናገድ የሚችልበት ህጋዊ ምክንያት የሌለ ስለመሆኑ፣ በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 5(6)፣ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 138(1)፣

    Download Cassation Decision

  • ከሳሽ የጠየቀውን የካሳ ገንዘብ ተከሳሽ በግልጽ አለመካዱ የካሳውን መጠን ሙሉ ወይም በከፊል እንዳመነ የማያስቆጥር ስለመሆኑ፤ ሰዎች አንድ ሆነው በአንድ ጉዳይ ካሳ እንዲከፍሉ የተገደዱ እንደሆነ በአንድነት እያንዳንዳቸው ሀላፊ እንደሆኑና ለበደሉ ተግባር አነሳሽ በሆነው በዋና አድራጊው እና በተባባሪዎች መካከል ልዩነት የሚደረግ ስለመሆኑ፤ በፍ/ህ/ቁ 2155/1/ እና /2/ የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 83

    Download Cassation Decision

  • አንድ ተከሳሽ በሌለበት የተሰጠበት ውሣኔ እንዲነሳለት የሚያቀርበውን ማመልከቻ በመቀበል ከሚቻልባቸው ምክንያቶች አንዱ መጥሪያ ለተከሳሹ ያለመድረስ ጉዳይ ስለመሆኑ፣ የወ/መ/ሕ/ሥ/ ሥ/ቁ. 199ሀ

    Download Cassation Decision

  • አንድ ተከሳሽ በሌለበት የተሰጠበት ውሣኔ እንዲነሳለት የሚያቀርበውን ማመልከቻ በመቀበል ከሚቻልባቸው ምክንያቶች አንዱ መጥሪያ ለተከሳሹ ያለመድረስ ጉዳይ ስለመሆኑ፣ የወ/መ/ሕ/ሥ/ ሥ/ቁ. 199ሀ

    Download Cassation Decision

  • በአንድ ክርክር ችሎት በመታየት ላይ ያለን ጉዳይ በሌላ ችሎት ተያያዥነት ባለው ጉዳይ ውሳኔ ተሠጥቶ ከሆነ ጉዳዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት የተላለፈውን ውሳኔ በአግባቡ በማጤን በጭብጥነት ሊይዘው ስለሚችልበት አግባብ፡ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.247 እና 248

    Download Cassation Decision

  • -በፍርድ ቤት በሚደረግ ክርክር ስለዋናዎቹ ባለጉዳዮች በመሆን ሌሎች ሰዎች በተሟጋችነት ሊቀርቡ ስለሚችሉበት ስርዓት፣ በህጉ የተቀመጠውን መስፈርት አሟልቶ አለመገኘት የሚያስከትለው ህጋዊ ውጤት፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 57፣ 58(1)፣ 60፣61፣62፣ 63 እና 197(1)

    Download Cassation Decision

  • የውርስ ንብረት ክፍፍልን በተመለከተ በውርስ ህጉ የተመለከቱትን የውርስ ንብረት ክፍፍልን የሚገዙትን ድንጋጌዎች ይዘት መንፈስና አላማ የተከተለና ያገናዘበ መሆን ስላለበት፣ የፍ/ህ/ቁ 1079፣1082፣1083፣1086

    Download Cassation Decision

  • አንድ በወንጀል ድርጊት ቅጣት የተጣለበትን ተከሳሽ ቅጣቱ እንዳይፈፀም ፍርድ ቤቱ ለማድረግ የሚችለው ጥፋተኛው በመልካም ጠባይ እንደሚመራ ፣ እንዲፈፅም የተሰጠውን ግዴታ እንደሚቀበል ፣ በሚቻለው መንገድ ሁሉ በጥፋቱ የደረሰውን ጉዳት እንደሚክስ ወይም ለተበዳዩ እንደሚከፍል እና ለዚሁ ጉዳይ በተወሰነ ጊዜ ውስጥ የፍርድ ቤቱን ወጪ እንደሚከፍል ማረጋገጫ ከሰጠ ስለመሆኑ፣ ከዚህም በተጨማሪ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛው ለገባበት ግዴታ አፈጻፀም መተማመኛ ዋስትና የሚጠይቅ ስለመሆኑ፣ አንቀጽ 197/1/ እና/2/

    Download Cassation Decision

  • አንድ በወንጀል ድርጊት ቅጣት የተጣለበትን ተከሳሽ ቅጣቱ እንዳይፈፀም ፍርድ ቤቱ ለማድረግ የሚችለው ጥፋተኛው በመልካም ጠባይ እንደሚመራ ፣ እንዲፈፅም የተሰጠውን ግዴታ እንደሚቀበል ፣ በሚቻለው መንገድ ሁሉ በጥፋቱ የደረሰውን ጉዳት እንደሚክስ ወይም ለተበዳዩ እንደሚከፍል እና ለዚሁ ጉዳይ በተወሰነ ጊዜ ውስጥ የፍርድ ቤቱን ወጪ እንደሚከፍል ማረጋገጫ ከሰጠ ስለመሆኑ፣ ከዚህም በተጨማሪ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛው ለገባበት ግዴታ አፈጻፀም መተማመኛ ዋስትና የሚጠይቅ ስለመሆኑ፣ አንቀጽ 197/1/ እና/2/

    Download Cassation Decision

  • አንድ ንብረት ወይም ቤት የወቅቱ የገበያ ዋጋ ሊቆረጥ የሚችለው ከተቻለ በስምምነት ይህ ካልተቻለ ደግሞ ቤቱ ለጨረታ ቀርቦ በሚያወጣው ከፍተኛ ዋጋ መሰረት ስለመሆኑ፣

    Download Cassation Decision

  • የዋስትና ግዴታ ግልፅ መሆን ያለበት ስለመሆኑ ኃላፊነቱም ግዴታ ከተገባለት እዳ ወሰን ለማለፍ እንደማይችል እና እንዲሁም ይህ ለአፈፃፀሙ ግዴታ የተገባለት የእዳመጠን ወይም የገንዘብ ልክ በዋስትና ውሉ ካልተገለፀ ዋስትናው ፈራሽ ስለመሆኑ፣ ከዚህ በተጨማሪ ገና ለወደፊት ሊደርስ ለሚችል ግዴታ አፈፃፀምም ዋስ ለመሆን እንደሚችል ነገር ግን በግልፅ ለምን ያህል እዳ ተጠያቂ ሊሆን እንደሚችል በግልፅ በውሉ ላይ መስፈር ያለበት ስለመሆኑ፣ ፍ/ብ/ህ/ቁ 1922(2)(3)፣ 1925(1)

    Download Cassation Decision

  • -በሥራ ተከራካሪ ወገኖች ማንነት የፍርድ ቤቶችን ሥልጣን የክልል ወይም የፌዴራል ብሎ ለመወሰን እንደወሳኝ መለኪያ ሊወስድ የሚገባ ስላለመሆኑ፣ ኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 50፣ 51 እና 80 ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 14 እና 15፣አዋጅ ቁ.25/88አንቀፅ5

    Download Cassation Decision

  • ሁከት ፈጥረሀል ተብሎ የተከሰሰ ሰው ሁከት ፈጥረሀል በተባለበት ነገር ላይ በፍርድ የተረጋገጠ መብት ካለው ሁከት ፈጠረ ሊባል ስላለመቻሉ፣ የፍ/ህ/ቁ 1149(3)

    Download Cassation Decision

  • በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ በሠራተኛ ዕድገት ዝውውርና ሥልጠና በሚመለከት አሠሪው የሚወስዳቸው እርምጃዎች በፍርድ ሊታዩና ሊያልቁ የሚችሉ ጉዳዮች እንደሆኑ፣ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገመንግስት አንቀፅ 37፣ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 138፣142 ንዑስ አንቀጽ 1/ሰ/ እና ከአንቀጽ 147 ንዑስ አንቀጽ 1/ሀ/

    Download Cassation Decision

  • አንድ ድርጅት ወንጀል እንዳደረገ የሚቆጠረው ከኃላፊዎች አንዱ ወይም ከሠራተኞች አንዱ ከድርጅቱ ጋር በተያያዘ ሁኔታ የድርጅቱን ጥቅም በሕገ ወጥ መንገድ ለማራመድ በማሰብ ወይም የድርጅቱን ሕጋዊ ግዴታ በመጣስ ወይም በመጠቀም በዋና ወንጀል አድራጊነት ወይም አነሳሽነት ወይም አባሪነት ወንጀል ሲፈጸም ብቻ ስለመሆኑ፣ የወ/ሕግ አንቀጽ 23 እና አንቀጽ 34/1/ ጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 93/1ሀ/ እና 93/2/

     

    የሰ//.94913

    የሥራ መሪ መብቱን ለማስከበር የሚችልበት የይርጋ ጊዜ አቆጣጠር፣ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1846

    Download Cassation Decision

  • ከጭብጥ አያያዝ ጋር በተገናኘ በአንድ ወገን ተቆጥሮ የቀረበን ማስረጃ ለጉዳዩ አግባብነት የለውም በሚል ወይም ህጋዊ ተቀባይነት ባለው ሌላ ምክንያት መሰማት አይገባውም የሚል ግልፅ ትእዛዝ ሳይሰጥበት የክርክሩ ጭብጥ በአንደኛው ወገን ማስረጃ ላይ ብቻ ተመስርቶ ውሳኔ እንዲያገኝ መደረጉ ተገቢ የክርክር አመራር ስርዓት ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 255፣257፣258፣259

    Download Cassation Decision

  • በአንድ ክርክር ሂደት ወደ ክርክሩ እንዲገባ የተደረገ ተከራካሪ ወገን ጉዳዩን የፌዴራል የሚያደርገው የነበረ ሁኖ እያለ ክሱን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤት ስልጣን ሳይኖረው ስረ ነገሩን አስተናግዶ ዳኝነት ከሰጠ በኋላ ይኼው ተከራካሪ ወገን በይግባኝ ደረጃ በነበረው ክርክር የተሠጠውን ዳኝነት ተቀብሎ ከወጣ በኋላ በሌሎች ጉዳዩን የፌዴራል ሊያደርጉ በማይችሉ ተከራካሪ ወገኞች መካከል የተሰጠው ውሳኔ ከመነሻውም የፌዴራል ጉዳይ ነው ብሎ መወሰን አግባብነት የሌለው ስለመሆኑ፣ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 43(1)፣ አዋጅ ቁ.25/88

    Download Cassation Decision

  • - የሥራ ውሉ ሊጠናቀቅ የአንድ ወር ጊዜ ብቻ የቀረው በሆነ ጊዜ አሰሪው የስራ ውሉ ከሚጠናቀቅበት የጊዜ ገደብ ከ1ወር በፊት የሥራ ውሉን ያቋረጠ እንደሆነ ሊከፍል የሚገባው የ1 ወር ደመወዝ ብቻ እንጂ የማስጠንቀቂያ ክፍያ እንዲከፍል የሚገደድበት ህጋዊ ምክንያት የሌለ ስለመሆኑ፤ አዋጅ ቁጥር377/96 አንቀፅ 43(4)(ሀ)፣36

    Download Cassation Decision

  • የተሻሻለው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ከመውጣቱ በፊት በተፈፀመ ወንጀል ከተፈረደበት እና ሆኖም ግን ወንጀሉ በተፈፀመበት ጊዜ ስራ ላይ ከነበረው የቅጣት አወሳሰን ይልቅ የተሻሻለው መመሪያ ለተከሳሹ ቅጣትን የሚያቀልለትና ተከሳሹን የሚጠቅም ሆኖ ከተገኘ ይሄው የተሻሽለው መመሪያ ላይ ያለው ቅጣት የሚፈጽምበት ስለመሆኑ፣ የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ የወንጀል ህግ አተረጓጓም መርሆን መከተል ያለበት ስለመሆኑ፣ ወንጀል ህጉ ቁ 6

    Download Cassation Decision