Federal supreme court of Ethiopia cassation decisions

  • የተሻሻለው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ከመውጣቱ በፊት በተፈፀመ ወንጀል ከተፈረደበት እና ሆኖም ግን ወንጀሉ በተፈፀመበት ጊዜ ስራ ላይ ከነበረው የቅጣት አወሳሰን ይልቅ የተሻሻለው መመሪያ ለተከሳሹ ቅጣትን የሚያቀልለትና ተከሳሹን የሚጠቅም ሆኖ ከተገኘ ይሄው የተሻሽለው መመሪያ ላይ ያለው ቅጣት የሚፈጽምበት ስለመሆኑ፣ የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ የወንጀል ህግ አተረጓጓም መርሆን መከተል ያለበት ስለመሆኑ፣ ወንጀል ህጉ ቁ 6

    Download Cassation Decision

  • አንድ ሰራተኛ የሥራ ውሉ በሚቋረጥበት ጊዜ በስሙ የሚቀመጠው የፕሮቪደንት ፈንድ ለእዳ ማስቻያ ሊሆን የሚችለው ሰራተኛው ዕዳ እንዳለበት ያመነ እንደመሆኑ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀፅ 59(1)

    Download Cassation Decision

  • አንድ ሰራተኛ በስራ ላይ እያለ የማጭበርበር ድርጊት በመፈፀሙ ምክንያት ያገኘው ጥቅም ባይኖርም፣ ወይም በሌላ ሰው ላይ ጉዳት ባያደርስም ወንጀልነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ የስራ ውሉን ያለማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ በቂ ስለመሆኑ፣ የአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 27(1(ሐ))

    Download Cassation Decision

  • የአፈጻጸም ጥያቄ የቀረበለት ፍርድ ቤት ለአፈጻጸሙ ተስማሚ በሆነ መንገድ ፍርድ እንዲፈጸም ትዕዛዝ የሚሰጠው የፍርድ ባለዕዳውን ጠርቶ ከመረመረው በኃላ እንደፍርዱ የማይፈጸምበት ምክንያት አለመኖሩን ካረጋገጠ በኃላ ስለመሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 207 እና 320(2) መሰረት በተሰጠው ትእዛዝ ላይ ቅሬታ አቅርቦ ነገር ግን ቅሬታው ተቀባይነት ቢያጣ የይግባኝ መብቱን (የይግባኝ ጊዜ ሊሰላበት) ስለሚችልበት አግባብ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 392 (1)

     

    የሰ/መ/ቁ. 95941

     

    ታህሳስ 7 ቀን 2008 ዓ.ም

    አንድ ሰው በድልድል ያገኘውን መሬት ሌላ ሰው ሊወስድበት የሚገባው በሕጉ የተመለከቱ ምክንያቶች ሲኖሩ ብቻ ሰለመሆኑ፣ የት/ብ/ክ/መንግስት የገጠር መሬት አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 136/2000 አንቀጽ 31፣5፣12፣14 እና 22 ደንብ ቁ. 48/2000 “ን” በደንብ ቁጥር 48/2000 14፣15፣16 አዋጅ ቁጥር 456/1997 በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሰት አንቀጽ 37፣40(3) እና 79

    Download Cassation Decision

  • ተሻሽሎ በቀረበው ክስ ላይ ግራ ቀኙ መልስ እንዲሰጡበት ሳይደረግ እና የመከላከያ መልሳቸውን ሳያቀርቡ ተሻሽሎ የቀረበውን ክስ መሰረት አድርጎ ፍርድ መስጠት ተገቢ ስላለመሆኑ፣ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 234(1)(ሠ)(መ)፣91(1)

    Download Cassation Decision

  • ተሻሽሎ በቀረበው ክስ ላይ ግራ ቀኙ መልስ እንዲሰጡበት ሳይደረግ እና የመከላከያ መልሳቸውን ሳያቀርቡ ተሻሽሎ የቀረበውን ክስ መሰረት አድርጎ ፍርድ መስጠት ተገቢ ስላለመሆኑ፣ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 234(1)(ሠ)(መ)፣91(1)

    Download Cassation Decision

  • በተከራካሪ ወገኖች በአንድ የመጨረሻ ውሳኔ ላይ የእርማት አቤቱታ ሊቀርብ የሚችለው ውሳኔ ያረፈበት ነጥብ ላይ ብቻ ስለመሆኑ፣ ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 208

    Download Cassation Decision

  • አንድ ሰው በወንጀል ተከሶ በሌለበት የጥፋተኝነት ውሳኔ ከተሰጠ በኃላ ጥፋተኛ የተባለው ስው ቀርቦ በሌለበት የተሰጠውን ውሳኔ ለማስነሳት ሳይሆን በዋናው ጉዳይ ላይ በቀጥታ ይግባኝ ከጠየቀ በኃላ በሌለሁበት የተሰጠው ውሳኔ ይነሳልኝ ብሎ ቢያመለክት በፊት የጠየቀው ይግባኝ በህጉ ላይ የተቀመጠውን የ30 ቀን የጊዜ ገደብ የሚያቋርጥ ስለመሆኑ፣ የወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ.198

    Download Cassation Decision

  • የመጓጓዣ ውልን መሰረት ያደረገ የካሳ ጥያቄ ሲቀርብ ጉዳዩ በየትኛው የህግ ማዕቀፍ እንደሚገዛ መለየት የይርጋውንም ሆነ የካሳ ስሌቱን በአግባቡ ለመዳኘት የሚያስችል ስለመሆኑ የን/ሕ/ቁጥር 587፣595 ፣597፣599 እና 603 የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2143፣ 2090

     

    የሰ/መ/ቁ. 95922

    መስከረም 26 ቀን 2008 ዓ.ም

     

     

    ዳኞች፡- አልማው ወሌ

    በክርክር ወቅት ጣልቃ ልግባ የሚለው ወገን በተከራካሪ ወገኖች መካከል ባለው ጉዳይ የሚሰጠው ውሳኔ የክርክሩ ተካፋይ ባይሆን በምን አግባብና መልኩ መብቱንና ጥቅሙን የሚጎዳ መሆኑንና አዲስ ክስ በማቅረብ ለማስቀረት የማይቻል መሆኑን የማስረዳት ግዴታ ያለበት ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 41(2)

    Download Cassation Decision

  • የቲ.ኦቲ /ተርን ኦቨር ታክስ/ ተመዝጋቢ የሆነ ሰው በህግ ፊት እንደ መረጃ /ማስረጃ / ሊያቀርብባቸው የሚገቡ ደረሰኞች ከቫት በተቀበለው የቲ.ኦ.ቲ ደረሰኝ መሆን ያለበት ስለመሆኑ፣ /ታክስ የቲ.ኦቲ አዋጅ ቁጥር 285/194 አንቀጽ 21/
  • የአባት ስም እንዲስተካከልልኝ በሚል የሚቀርብ አቤቱታ የክስ ምክንያት የለውም ሊባል የማይችል ስለመሆኑ፣  አንድ ሰው አንድ የቤተዘመድ ስምና አንድ ወይም ብዙ የግል ስሞችና የአባት ስም ሊኖረው ስለመቻሉና የአንድ ልጅ የአባት ስም የሚሆነው የአባቱ የግል ስም ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 231 (1)(ሀ) የፍ/ብ/ህ/ቁ. 32(1)፣ 36(1)

    Download Cassation Decision

  • በውል የተገባ አንድ ግዴታ መፈጸም ያለመፈጸሙን ለማጣራት የግራ ቀኙ ተዋዋይ ወገኖች የገቡት ግዴታ እና ያላቸው መብት የሚገልጽ የሰነድና የሰው ማስረጃ እንዲሁም የግዴታ ልዩ ባህርይ መሰረት በማድረግ ልምድን መዳሰስ የሚጠይቅ ስለመሆኑ ፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ 246፣247፣248 እና 249

     

    የሰ/መ/ቁ. 96041

     

    ጥቅምት 26 ቀን 2008 ዓ.ም

     

    አንድ ሰው በአንድ አይነት የወንጀል አሳብ ወይም ቸልተኝነት የፈጸመው ወንጀል አንድን የሕግ ድንጋጌ ብቻ የሚጥስ ቢሆንም አንድ አይነት ጉዳት ያስከተለው ቁጥራቸው ከአንድ በላይ በሆነ ሰዎች መብት ወይም ጥቅም ላይ ሲሆን እንደተደራራቢ ወንጀሎች ሊቆጠር የሚገባ ስለመሆኑ፣ የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 27(1)፣6ዐ(ሀ) (ሐ) እና 598(1)

    Download Cassation Decision

  • አንድ ሰው በአንድ አይነት የወንጀል አሳብ ወይም ቸልተኝነት የፈጸመው ወንጀል አንድን የሕግ ድንጋጌ ብቻ የሚጥስ ቢሆንም አንድ አይነት ጉዳት ያስከተለው ቁጥራቸው ከአንድ በላይ በሆነ ሰዎች መብት ወይም ጥቅም ላይ ሲሆን እንደተደራራቢ ወንጀሎች ሊቆጠር የሚገባ ስለመሆኑ፣ የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 27(1)፣6ዐ(ሀ) (ሐ) እና 598(1)

    Download Cassation Decision

  • በወንጀል ጉዳይ ጥፋተኛ የተባለ ሠው በቅጣት ማቅለያነት
    እንዲያዝለት ያቀረበውን ምክንያት በማስረጃ ማስደገፍ እንዲችል በቂ
    ጊዜ ባልተሠጠበት ሁኔታ በማስረጃ የተደገፈ አይደለም በሚል
    የማቅለያ ምክንያቱን ውድቅ በማድረግ የሚሠጥ የቅጣት ውሣኔ
    በወንጀል ህጉ እና በቅጣት አወሳሠን መመሪያው ሥለ ቅጣት
    አወሣሠን የተቀመጡትን ድንጋጌዎች መሠረት ያደረገ ነው ለማለት
    የሚቻል ስላለመሆኑ፣
    የወ/መ/ሥ/ሥርዓት 149/3//4/

    የሰ/መ/ቁ.96168 ህዳር 9 ቀን 2007 ዓ.ም.

    በወንጀል ጉዳይ ጥፋተኛ የተባለ ሠው በቅጣት ማቅለያነት
    እንዲያዝለት ያቀረበውን ምክንያት በማስረጃ ማስደገፍ እንዲችል በቂ
    ጊዜ ባልተሠጠበት ሁኔታ በማስረጃ የተደገፈ አይደለም በሚል
    የማቅለያ ምክንያቱን ውድቅ በማድረግ የሚሠጥ የቅጣት ውሣኔ
    በወንጀል ህጉ እና በቅጣት አወሳሠን መመሪያው ሥለ ቅጣት
    አወሣሠን የተቀመጡትን ድንጋጌዎች መሠረት ያደረገ ነው ለማለት
    የሚቻል ስላለመሆኑ፣
    የወ/መ/ሥ/ሥርዓት 149/3//4/

    የሰ/መ/ቁ.96168 ህዳር 9 ቀን 2007 ዓ.ም.

    ከከተማው አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት የመቆጣጠር ስልጣን እና ተግባር ጋር እንዲሁም የከተማው አስተዳደር ከሚያስተዳድራቸው የመንግስት ቤቶች ጋር እና የከተማው አስተዳደር አካልም በተከሳሽነት በሚቀርብበት ጊዜ የስረ ነገር ስልጣን የከተማው ፍርድ ቤቶች ስለመሆኑ፣ በአንድ ክስ ውስጥ ብዙ አቤቱታዎች ቀርበው ከነዚሁ በከፊል ዋናውን ክስ የሚመለከቱ በከፊል ደግሞ ዋናውን ክስ መነሻ አድርገው ቅርንጫፍ ነገሮችን የሚመለከቱ በሆነ ጊዜ የፍርድ ቤቱ ስልጣን የሚወሰነው ከፍተኛ ግምት ያለውን አቤቱታ መሰረት አድርጎ በመከተል ስለመሆኑ፣ መመሪያ ቁጥር 4/2004 አዋጅ ቁጥር 361/1995 ፣ የተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ ቻርተር አንቀጽ 41(1) (ለ) እና (ረ) የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 17(2)

    Download Cassation Decision

  • አንድ ተጠርጣሪ ወይም ተከሳሽ በምርመራ ሒደትም ሆነ ክሱን
    ለሚሠማው ፍ/ቤት የሚሠጠው የእምነት ቃል ውጤት በራሱ በቃል
    ሠጪው ላይ ተወስኖ የሚቀር ከመሆኑ ውጪ ወንጀሉን
    አልፈፀምኩም ብሎ በሚከራከር ሌላ ተከሣሽ ላይ ህጋዊ ውጤት
    ሊያስከትል የማይችል ሥለመሆኑ፣
    የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ሥነ-ሥርዓት ቁጥር 27፣35 እና 134