80343 labor dispute/ occupational accident/ extra contractual liability/ civil procedure/ res judicata

 አንድ ሠራተኛ በሥራ ላይ እያለ የደረሰበትን የአካል ጉዳት በተመለከተ የጉዳት ካሣ ክፍያ እንዲከፈለው ለመጠየቅ የሚችለው በአማራጭ አንድም በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጁ መሠረት አሰሪውን ያለጥፋት በሥራ ክርክር ችሎት ከሶ በመጠየቅ ወይም የአሰሪውን ጥፋት መነሻ በማድረግ የጉዳት ካሣ ክፍያ ከውል ውጪ ኃላፊነትን የተመለከቱ ድንጋጌዎችን መሠረት በማድረግ በፍ/ሔር ችሎት በአሠሪው ላይ ክስ ለማቅረብ የሚችል ስለመሆኑ፣  በሥራ ላይ ጉዳት የደረሰበት ሠራተኛ የጉዳት ካሣን ለመጠየቅ በህጉ የተመለከቱትን መብቶች በአግባቡና በትክክል ተገንዝቦ እንደ ጉዳቱ ሁኔታ፣ አይነትና አግባብነት በተሻለ ሁኔታ የሚጠቅመውን የመብት አድማስ አውቆ በመለየት ተገቢው መብቱ ከመነጨበት የህግ አግባብ አንፃር ክሱን ሊያቀርብ የሚገባ ስለመሆኑ፣  የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.5 ድንጋጌ ይዘት አድማሱ በግልጽ በተወሰኑ ጭብጦች ላይ ብቻ ሣይሆን በተከራካሪ ወገኖች ቢነሱ ኖሮ ሊወሰኑ ይችሉ የነበሩ ጭብጦችን ጭምር የሚያካትት ስለመሆኑ፣

Download Cassation Decision