ሚስትነትን በተመለከተ የአመልካችን ማስረጃ ብቻ በመቀበል ሚስትነትን በማረጋገጥ በፍ/ቤት የሚሰጥ ማስረጃ (Declaratory Judgment) በማናቸውም ጊዜ ተዓማኒነትና ክብደት የሌለው ማስረጃ መሆኑን ለማሳየት ክርክር ሊቀርብበትና ተቃራኒ ማስረጃ ተሰምቶ ውድቅ ሊደረግ የሚችል እንጂ ማስረጃውን በተሰጠው ፍ/ቤት ተቃውም በማቅረብ ያልተሻረ በመሆኑ ተቀባይነት ያለው ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣