በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 418 መሠረት የሚቀርብ አቤቱታ መደበኛውን የሙግት ሥነ- ሥርዓት ተከትሎ መከናወን ያለበት ስለመሆኑ፣ በፍርድ አፈፃፀም ደረጃ ንብረት እንዳይያዝ ወይም እንዳይከበር በሚል የመቃወሚያ አቤቱታ በቀረበ ግዜ ጉዳዩን የያዘው የአፈፃፀም ችሎት በንብረቱ ላይ ተቀዳሚ መብት አለኝ በሚል የቀረበውን የመቃወም አቤቱታ በመደበኛው የሙግት ሥነ-ሥርዓት ሂደት ክርክሩን በማስተናገድ ንብረቱ እንዲያዝ ወይም እንዲከበር የሚያደርግ ህጋዊና በቂ ምክንያት መኖር ያለመኖሩን በማስረጃ በማጣራት ለጉዳዩ እልባት መስጠት ያለበት ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 418, 419, 421