volume 7
-
10489 civil procedure/ execution of judgment/ debtor government organ/ attaching government budget
በበጀት የሚተዳደር የመንግስት መስሪያ ቤት የፍርድ ባለዕዳ ሆኖ ሲገኝ ውሣኔውን ለማስፈፀም ለሌላ ጉዳይ በበጀት የተያዘውን እና የሰራተኛ ደመወዝን የሚያካትተውን ገንዘብ ከብሔራዊ ባንክ ወጪ ሆኖ እንዲከፈል ለማዘዝ ስላለመቻሉ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 404 Cassation Decision no. 10489
-
12719 contract law/ written contract/ intention of the parties
በሁለት ወገኖች መካከል የተፈረመ ሰነድን እንደ ህጋዊ ስምምነት ለመውሰድ የፈራሚ ወገኖችን ሃሳብና ፍላጐት መመርመር አስፈላጊ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1734, 1952/1/ Cassation Decision no. 12719
-
16218 banking/ foreclosure /pledge/ mortgage
ባንኮች ከሚሰጡት ብድር እና የመያዣ ውል ጋር በተያያዘ የሚነሱ ክርክሮች አዋጅ ቁ. 97/9ዐ”ን” ዓላማ እንዲሁም አዋጁን ለማስፈፀም በባንኮች የሚወጡትን የፎርክሎዥር መመሪያዎችና አግባብነት ያላቸውን ህግጋት ግምት ውስጥ በማስገባት እልባት ማግኘት ያለባቸው ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 97/90 አንቀጽ 3 እና 4, አዋጅ ቁ. 216/92 Cassation Decision no. 16218
- 16455 contract of sale
-
18380 contract law/ civil procedure/ cause of action/ contract of sale
ውል ይጽደቅልኝ በሚል ለፍ/ቤት የሚቀርብ አቤቱታ የክስ ምክንያት የሌለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 231/1//ሀ/ Cassation Decision no. 18380
-
18576 civil procedure/ execution of judgment/ liquidation of succession report
የውርስ ማጣራት ሪፖርት ከፀደቀ ወይም በፍ/ቤት ተቀባይነት ካገኘ በኋላም ቢሆን እንደ ፍርድ ተቆጥሮ በቀጥታ የአፈፃፀም አቤቱታ ሊቀርብበት ስላለመቻሉ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 944, 946, 956, 960, 996 Cassation Decision no. 18576
-
18809 tax law/ income tax/ car rental
በደንብ ቁጥር 75/1993 ኮምፒዮተርን ጨምሮ ከተለያዩ መሳሪያዎች ህንፃዎችና ሌሎች ዕቃዎች ኪራይ በሚገኝ ገቢ ላይ ግብር ለመሰብሰው የተደነገገው መኪናን በማከራየት የሚገኝን ገቢ የሚያካትት ስለመሆኑ ደንብ ቁጥር 75/93 አንቀጽ 2/9/ ደንብ ቁጥር 78/94 አንቀጽ 24/2/ /ሸ/ Cassation Decision no. 18809
-
19258 company law/ private limited company/ capital contribution
የተወሰነ ኃላፊነት ያለው የግል ማህበር መዋጮ መከፈል ያለበት ማህበሩ ሲቋቋም እንጂ ተቋቁሞ ሥራው ከተጀረ በኋላ ስላለመሆኑ Cassation Decision no. 19258
-
19283 banking/ foreclosure/ public auction
ባንክ ለሰጠው ብድር በመያዣነት እጁ ያስገባውን የተበዳሪ ንብረት በመጀመሪያም ሆነ በሁለተኛው የሃራጅ ጨረታ ለሽያጭ አቅርቦ ገዢ ያልተገኘ እንደሆነ ንብረቱን ሊያስቀር የሚችለው ለመጀመሪያው ጨረታ መነሻ በተሰጠው የዋጋ ግምት መሰረት ስለመሆኑ Cassation Decision no. 19283
-
20232 commercial law/ contract law/ negotiable instruments/
የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች የተዋዋይ ወገኖች መብትና ግዴታዎች የሚፈጠሩባቸውና የሚረጋገጡባቸው በመሆናቸው የውል ህግ መሰረታዊ ድንጋጌዎች መሟላታቸው አስፈላጊ ሁኔታ ስለመሆኑ የንግድ ህግ ቁ. 715, የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1706, 1679 Cassation Decision no. 20232
- 20979 contract law
- 21411 criminal law
- 21531 contract law
-
22069 criminal law/ criminal intention/ homicide
በወንጀል ህግ የሃሳብ ክፍል የሚረጋገጠው ከወንጀል ድርጊት አፈፃፀሙ በመነሳት ስለመሆኑ የወ/መ/ህ/ቁ. 522 /1/ /ሀ/ Cassation Decision no. 22069
-
22448 civil procedure/ execution of judgment/ judgment creditor
ፍርድ እንዲፈፀም ለመጠየቅ ችሎታ ያለው ፍርድ የተፈረደለት ሰው /ወገን/ ብቻ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 378/1/ Cassation Decision no. 22448
-
22452 criminal law/ aggravated homicide
በወ/መ/ህ/ቁ. 522/1/ /ሀ/ ሥር የተመለከቱት የወንጀል ማቋቋሚያ ነጥቦች ለየራሳቸው የሚቆሙ ስለመሆናቸው የወ/መ/ህ/ቁ. 522/1/ /ሀ/ Cassation Decision no. 22452
-
22481 civil procedure/ execution of judgment/ public auction/ errors in auctioning
በሀራጅ ጨረታ የአሻሻጥ ስርዓት ላይ ”ግዙፍ የሆነ ጉድለት” ወይም ትክክለኛ ያልሆነ ተግባር እንደተፈፀመ ሊቆጠር የሚችልበት አግባብ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 422/3/, 428/5/, 455, 428/1/ Cassation Decision no. 22481
- 22514 criminal law
- 22530 insurance
-
22860 evidence law/ method of proof
አንድ ግዴታ መኖሩን ለማስረዳት ህጉ የተለየ ማስረጃ እንዲቀርብ ያዘዘ ካልሆነ በቀር ግዴታው መኖሩን በጽሁፍ፣ በምስክር፣ በህሊና ግምት በተከራካሪው ወገን እምነት ወይም በመሃላ ማስረዳት የሚቻል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2002 Cassation Decision no. 22860
-
22930 family law/ divorce/ debt of spouses
ባልና ሚስት በፍቺ ከተለያዩና የንብረት ክፍፍል ከተደረገ በኋላ ከአንደኛው ተጋቢ የግል ተግባር የሚመነጭ ዕዳ አፈፃፀም የተጠየቀው /የቀረበው/ ከፍቺ በኋላ እስከሆነ ድረስ ለዕዳው ምክንያት ከሆነው ተጋቢ ብቻ የሚጠየቅ ስለመሆኑ Cassation Decision no. 22930
-
23024 civil procedure/ thrid party intervention/ appeal
በጣልቃ ገብነት ተሳታፊ ሆኖ የፍርድ ተጠቃሚ የሆነ ወገን ዋና ተከራካሪ ከሆኑት ወገኖች መካከል በአንዱ አነሣሽነት ጉዳዩ በይግባኝ በሚታይበት ጊዜ በሥር ፍርድ ተጠቃሚ የሆነው ጣልቃ ገብ ባልተጠራበት ሁኔታ የሚሰጥ ውሣኔ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 40/5/”ን” የሚፃረር ስለመሆኑ Cassation Decision no. 23024
-
23322 law of succession/ liquidation of succession/ power of the liquidator
የውርስ ሀብት አጣሪ የንብረት ባለቤትነትን የመወሰን ስልጣን የሌለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 956 Cassation Decision no. 23322
-
23331 contract of sale/ invalidation
በህግ ፀንቶ ያለ የሽያጭ ውልን መሰረት በማድረግ የተገኘ መብት ውሉ ፈራሽ እስካልተደረገ ድረስ የሚቀጥል ስለመሆኑ Cassation Decision no. 23331
- 23389 company law
-
23609 labor dispute/ manager/ civil code
የስራ መሪ የሥራ ውል ያለአግባብ በተቋረጠ ጊዜ የስራ መሪው ሊያገኝ ስለሚገባው ልዩ ልዩ ክፍያዎች እና ጥቅማጥቅም የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2573, 2574/2/, 2570/2/, 2577, 2562 Cassation Decision no. 23609
-
23733 civil procedure/ execution of judgment/ partition of property/
ከንብረት ክፍፍል ጋር በተያያዘ በዋናው ጉዳይ አከራካሪ የሆነው ንብረት መካፈል ከተቻለ እንዲካፈል ካልሆነ ደግሞ በባለሙያ ተገምቶ እንዲካፈሉ በሚል የተሰጠን ፍርድ መነሻ በማድረግ የአፈፃፀም ችሎት /ፍ/ቤት/ ከተከራካሪ ወገኖች መካከል አንደኛው ግምቱን ከፍለው ንብረቱን እንዲያስቀሩ በሚል ትዕዛዝ ለመስጠት የማይችል ስለመሆኑ Cassation Decision no. 23733
-
23855 criminal law/ custom law violation/ confisication
የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ሳይፈፀምበት የመንግስት ቀረጥ ያልተከፈለበት መኪና ይዞ የተገኘ ግለሰብ በወንጀል ተከስሶ ጥፋተኛ ያልተባለ ቢሆንም ግለሰቡ ተገቢውን ቀረጥ ከፍሎ መኪናውን መረከብ አልያም ደግሞ መኪናው መወረስ ያለበት ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 60/89 አንቀጽ 74 አዋጅ ቁ. 388/95 አንቀጽ 80/3/ Cassation Decision no. 23855
- 23895 contract of sale
-
23989 civil procedure/ execution of judgment/ attaching immovable property
የማይንቀሳቀስ ንብረት ስመ ንብረት /ባለቤትነት/ ከሻጭ ወደ ገዥ ያለመዛወሩ ብቻ ሦስተኛ ወገኖች በሻጭ ላይ ሽያጭ የተካሄደበት ንብረት ላይ የጀመሩት አፈፃፀም እንዲቀጥል ለማስደረግ በቂ ሁኔታ ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2878 Cassation Decision no. 23989
-
24221 contract law/ rent/ subletting
ከኪራይ ቤቶች አስተዳደር ጋር የተደረገን የኪራይ ውል መሰረት በማድረግ የተያዘ ቤትን ያለአከራዩ ፍቃድ ለሌላ ወገን ማስተላለፍ ለኪራይ ውሉ መሰረዝ በቂ ምክንያት ስለመሆኑ Cassation Decision no. 24221
-
24278 criminal law/ special penal law/ breach of trust
በአዋጅ ቁ. 214/74 አንቀጽ 13/1/ መሠት የተከሰሰ ሰው ጥፋተኛ ሊባል የሚችለው እንዲጠብቃቸው በአደራ የተረከባቸውን ወይም በሥራው አጋጣሚና ምክንያት በእጁ የገቡትን ንብረቶች የወሰደው/የሰወረው/ ለራሱ ወይም ለሌላ ሰው ተገቢ ያልሆነ ብልጽግና ለማግኘት የሆነ እንደሆነ ስለመሆኑ Cassation Decision no. 24278
- 24554 contract of sale
-
24703 insurance/ contract law/ form of insurance contract
በህግ ተቀባይነት ያለው የኢንሹራንስ ውል የሚቋቋምበት አግባብ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1725, 1727 የንግድ ህግ ቁጥር 651, 654, 657 Cassation Decision no. 24703
- 24704 insurance
-
24974 contract law/ partial performance of contract/ cancellation
በውል ከተገባ ግዴታ አመዛኙ ክፍል ተፈፀመ ወይም/እና አይነተኛ የሆነ የውል መጣስ ተከስቷል ለማለት ባልተቻለ ጊዜ ውል እንዲሰረዝ ለመወሰን የማይቻል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1771,1784, 1785 Cassation Decision no. 24974
-
25031 civil procedure/ execution of judgment/ investigation of claims to attached property
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 418 መሰረት አቤቱታ ሊቀርብ የሚችልበት አግባብ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 358,418 Cassation Decision no. 25031
- 25165 contract of sale
- 25287 law of succession
-
25863 banking/ foreclosure/ mortgage/ priority of creditors
ለባንክ በመያዣነት በተሰጠ የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የሚኖር የቀዳሚነት መብት የፍ/ብ/ህ/ቁ. 3088, 3052, 3081,3059 Cassation Decision no. 25863
-
25869 law of succession/ partition of property/ auction
የማይንቀሳቀስ ንብረት የጋራ ባለሀብት የሆኑ ሰዎች ንብረቱን በአይነት ለመከፋፈል ባልቻሉ ጊዜ ንብረቱ በሃራጅ ተሸጦ ገንዘቡን መካፈል ያለባቸው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1272, 1273 Cassation Decision no. 25869
-
25938 contract law/ rent/ form of rent contract
የኪራይ ውል የተለየ ፎርም መከተል እንዳለበት የሚያስገድድ የህግ ድንጋጌ የሌለ ስለመሆኑ እና በሁለት ተዋዋይ ወገኖች መካከል የሚፀና ውል /ህጋዊ ውጤት ያለው ውል/ ለመመስረት በሁለቱም መካከል ስምምነት መኖሩ ብቻ በቂ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1719/1/,1719-1930, 2898/3/ Cassation Decision no. 25938
-
26553 civil procedure/ execution of judgment/ attachment and sale of immovable property
የማይንቀሳቀስ ንብረት በሃራጅ በሚሸጥበት ጊዜ በሃራጅ እንዲሸጥ የሚወጣው ማስታወቂያ ለ3ዐ ቀናት መቆየት ያለበት ስለመሆኑ ንብረቱ በመያዣ የተያዘ እንደሆነም የመያዣው ልክ ምን ያህል እንደሆነ በጨረታ ማስታወቂያ ላይ መገለጽ ያለበት ስለመሆኑ ሽያጩ ባልተገባ መንገድ ተከናውኗል ከተባለም ጨረታው በድጋሚ መካሄድ ያለበት ስለመሆኑ በመያዣ የተያዘን ንብረት በሌላ ባለገንዘብ ጠያቂነት እንዲሸጥ ሊደረግ ስለመቻሉ Cassation Decision no. 26553
-
26996 contract law/ performance impossible/ reinstatement of parties
ውል የተደረገበት ጉዳይ ሊፈፀም የማይችል ሆኖ በተገኘ ጊዜ ተዋዋይ ወገኖችን ወደ ነበሩበት ቦታ የመመለስ ውጤት ያለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1715, 1815 Cassation Decision no. 26996
-
27349 contract law/ alternative dispute settlement/ power of court
ተዋዋይ ወገኖች በመካከላቸው የሚፈጠርን አለመግባባት በስምምነት ወይም ደግሞ በአስታራቂ አማካኝነት ለመፍታት የተስማሙ ከሆነ ይኼው ስምምነት ተፈፃሚ መሆን ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1765, 1731/1/ Cassation Decision no. 27349
-
27574 civil procedure/ execution of judgment/ arbitral award
በሽምግልና ጉባኤ አማካኝነት የተሰጠ ውሣኔ በፍ/ቤት ሊፈፀም የሚችል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 215/1/, 319/2/ Cassation Decision no. 27574
-
28019 civil procedure/ execution of judgment/ decree
ፍርድን በአግባቡ ውጤት ለመስጠት የአፈፃፀም ችሎት የፍርዱን ትክክለኛ ቃል እና መንፈስ መከተል ያለበት ስለመሆኑ Cassation Decision no. 28019
-
28025 contract law/ rent /rent for indefinite period of time
ላልተወሰነ ጊዜ የተደረገ የኪራይ ውል ለተከራዩ በሚሰጥ ማስታወቂያ በማናቸውም ጊዜ ሊቋረጥ የሚችል ስለመሆኑ እና የኪራይ ውሉን ለማቋረጥ/ለማፍረስ ለተከራዩ ማስታወቂያ /ማስጠንቀቂያ/ መስጠት አስገዳጅ ቅድመ ሁኔታ ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2966/1/ Cassation Decision no. 28025
-
28154 civil procedure/ execution of judgment/ investigation of claims to attached property
በተያዘ ወይም በተከበረ ንብረት ላይ 3ኛ ወገኖች መብት ያቋቋምን ስለሆነ አፈፃፀም ሊቀጥል አይገባም በሚል አቤቱታ ያቀረቡ እንደሆነ ፍ/ቤት ተከራካሪ የሆኑ ወገኖች በአቤቱታው ላይ ያላቸውን ክርክር በቅድሚያ በመስማት መወሰን ያለበት ስለመሆኑ Cassation Decision no. 28154
- 28254 insurance
- 28362 civil procedure/ execution of judgment
-
28663 family law/ common property/ sale/ contract law
የፍ/ብ/ህ/ቁ. 658 ተጋቢ ወገን ከሦስተኛ ወገን ጋር ያደረገውን ውል ለማፍረስ ምክንያት ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 658, 686 Cassation Decision no. 28663
-
28923 company law/ public enterprises/ debt of privatized enterprises
የመንግስት የልማት ድርጅቶች ወደ ግል ይዞታ ከመቀየራቸው በፊት ያለባቸውን የዕዳ ክርክር በኃላፊነት ይዞ መከራከር ያለበት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ባላደራ ቦርድ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 208/1992 አንቀጽ 5/1/, 6/1/ /ሐ/, አዋጅ ቁ. 182/1992 Cassation Decision no. 28923
-
28952 criminal law/ criminal procedure/ withdrawal of charges
በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 122/2/ መሠረት ከሣሽ አቅርቦት የነበረውን ክስ ካነሣ በኋላ እንደገና ክሱን ለመቀጠል የሚችል ስለመሆኑ የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 122/2/, /5/ Cassation Decision no. 28952
-
29233 contract law/ form of contract/ invalidation/ reinstatement
በተዋዋይ ወገኖች መካከል የተደረገ ስምምነት በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1723 መሰረት የተሟላ አይደለም በሚል ውሣኔ ሲሰጥ ተዋዋይ የነበሩ ወገኖች በፍ/ብ/ህ/ቁ 1815 መሰረት ወደ ነበሩበት ቦታ እንዲመለሱ መወሰን ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1723, 1720/1/, 1815 Cassation Decision no. 29233
-
29269 civil procedure/ execution of judgment/ attachment/ priority of creditors
በፍርድ የተቋቋመ መያዣ ላይ ፍርዱ እንዲሰጥ ያደረገው ባለገንዘብ መያዣ በሆነው ንብረት ላይ የቀዳሚነት መብት ያለው ስለመሆኑ እና የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 403 ተፈፃሚነት የአንድ ፍርድ ባለዕዳ ንብረት በእርሱ ላይ የቀረቡትን ገንዘብ ጠያቂዎች ፍላጐት የሚያሟላ ሆኖ በተገኘ ጊዜ ክፍፍሉ ጋር በተገናኘ ስለመሆኑ Cassation Decision no. 29269
-
29325 criminal law/ criminal procedure/ trial in asentia
በወንጀል ክስ የቀረበበት ሰውን አስመልክቶ ጉዳዩ በሌለበት ነው የታየው ሊባል የሚችልበት አግባብ የወ/መ/ሥ/ሥ/ቁ. 161/1/ Cassation Decision no. 29325
-
29344 civil procedure/ execution of judgment/ decree
ውሣኔን የሚያስፈጽም ፍ/ቤት በውሣኔው መሰረት ከማስፈፀም ወጪ በአፈፃፀም ጊዜ ዋናውን ፍርድ ሊለውጥ የሚችልበት የህግ መሰረት የሌለ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 358, 418 Cassation Decision no. 29344
- 29371 civil procedure/ execution of judgment
-
29375 banking/ mortgage/ improvment on property
የማይንቀሳቀስ ንብረት በመያዣነት ከተሰጠ በኋላ በማይንቀሳቀሰው ንብረት ላይ የሚደረግ ማናቸውም የማሻሻል ሥራ የመያዣ ውሉ አካል ተደርጐ የሚወሰድ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 3066 አዋጅ ቁ. 97/90 Cassation Decision no. 29375
-
29653 civil procedure/ execution of judgment/ judgment creditor
ዋናው ክርክር ገብቶ ተከራክሮ ውሣኔ ያላገኘ ተከራካሪ ወገን በአፈፃፀም ጊዜ ውሣኔ እንዲፈፀምለት ጥያቄ የሚያቀርብበት የህግ መሠረት የሌለ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 358, 418 Cassation Decision no. 29653
-
30158 law of succession/ constitution/ family immovables/ period of limitation
በፍ/ብ/ህጉ ውስጥ “ከዘር የወረደ ርስት” በሚል የተቀረበው አገላለጽ በህገ-መንግስቱ የተሻረ ወይም ተፈፃሚነት የሌለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1000/2/ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ-መንግስት አንቀጽ 40 Cassation Decision no. 30158
-
30298 law of person/ absence/ sale of property
የመጥፋት ውሣኔ የተሰጠበት ሰው ንብረቱ ወደ 3ኛ ወገን የተላለፈ በሆነ ጊዜ የንብረቱን ዋጋ የማግኘት መብት ያለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 171 Cassation Decision no. 30298
- 30894 contract/ rent
- 30991 law of succession
- 31223 contract of sale
- 31334 insurance
- 31482 contract of sale
-
31601 contract law/ rent/ civil procedure/ court fee
የኪራይ ውል ተቋርጦ ውዝፍ ኪራይ እንዲከፈለኝና ቤቱንም ልረከብ በሚል የሚጠየቅ ዳኝነት የኪራይ ገንዘብ የተጠየቀበትን ቤት ግምት ጭምር ታሳቢ ተደርጐ የዳኝነት ክፍያ ሊቀርብበት የሚገባ ስላለመሆኑ አዋጅ ቁ. 361/95, የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 227/2/, 226 Cassation Decision no. 31601
-
31634 contract law/ rent/ presumption of payment
መጠየቅ ከሚገባው ቀን ጀምሮ እስከ 2 ዓመት ድረስ ሳይከፈል የቀረ የኪራይ ዕዳ እንደተከፈለ የህግ ግምት ይወስድበታል ማለት ባለገንዘቡ /አከራዩ/ ክስ መስርቶም ቢሆን ዕዳውን ለማሰብሰብ የማይችል መሆኑን ለማመላከት እንጂ ተከራዩ /ባለዕዳው/ ግዴታውን እንደተወጣ የሚያስቆጥረው ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2024/መ/ Cassation Decision no. 31634
- 31640 contract of sale
- 31731 criminal law
-
31734 criminal law/ criminal procedure/ bail/ denial of bail
በወንጀል ተከሶ የተያዘ ሰው ዋስትና በጠየቀ ጊዜ ፍ/ቤት ተከሳሹ ተመልሶ ሊቀርብ አይችልም የሚል ግምት ለመውሰድና ዋስትናን ለመከልከል በቂ ምክንያት የሚያስፈልግ ስለመሆኑ የወ/መ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ. 67/ሀ/ Cassation Decision no. 31734
- 31917 contract law/ rent/
-
32222 contract law/ construction law/ contract of sale of immovables
ያልነበረ ቤትን ሠርቶ ለማስተላለፍ በሚል የሚደረግ ስምምነትን በተመለከተ Cassation Decision no. 32222
-
32414 law of succession/ will/ nullity of will/ certificate of inheritance
ኑዛዜ ፈራሽ ነው ይባል በሚል የሚቀርብ ክስ እና የተሰጠ የወራሽነት የምስክር ወረቀት እንዲሰረዝ በሚል የሚቀርብ ተቃውሞ የተለያዩ ይዘትና ውጤት ያላቸው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 996/1/, 998/1/, 973, 996/2/ Cassation Decision no. 32414
-
32521 contract law/ rent / unlawful enrichment
የታወቀ የኪራይ ውል ግንኙነት ሳይኖር ወይም ባለቤት ሳይሆኑ በማይንቀሳቀስ ንብረት መገልገል የተገለገለውን ወገን በንብረቱ በበለፀገው መጠን ኃላፊ የሚያደርገው ስለመሆኑ Cassation Decision no. 32521
- 32899 contract of sale
-
33295 mortgage/ registration
የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ በማንኛቸውም ሰነድ ላይ የተመሰረተ ቢሆንም ከተፃፈበት ቀን አንስቶ የማይንቀሳቀሰው ንብረት በሚገኝበት አገር ባለው በማይንቀሳቀስ ርስተ መዝገብ ካልተፃፈ በቀር ምንም አይነት ውጤት የማያስገኝ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 3052, 3053,1605, 1607, 1606 Cassation Decision no. 33295
-
33760 commercial law/ business/ elements of business
የንግድ ድርጅት /መደብር/ ላይ ያለ መብት የድርጅቱ ንግድ የሚካሄድበትን ቤት የኪራይ መብት የሚያካትት ስለመሆኑ የንግድ ህግ ቁጥር 127 Cassation Decision no. 33760
-
34076 civil procedure/ local jurisdiction/ law of succession
የውርስ ሃብቶች በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ በሆነ ጊዜ የሚነሱ ክርክሮች የውርሱ ክፍያ በተጀመረበት ቦታ ለሚገኝ ፍ/ቤት የሚቀርቡና የሚስተናገዱ ስለመሆናቸው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 23 Cassation Decision no. 34076
-
34077 criminal law/ criminal procedure/ bail
በወንጀል የተከሰሰ ሰው የሚያነሳው የዋስትና ጥያቄ መታየት ያለበት ሊወሰንበት ከሚችለው ቅጣት አንፃር ስለመሆኑ Cassation Decision no. 34077
-
34280 criminal law/ suspension of penalty
በወንጀል ህግ ቅጣት ሊገደብ የሚችልበት አግባብ የወንጀል ህ/ቁ. 192,194 Cassation Decision no. 34280
-
34456 contract law/ rent / rent for indefinite period of time
ለተወሰነ ጊዜ የተደረገ የኪራይ ውል ውሉ የተደረገበት ጊዜ ካለቀና ውሉ ወደ ያልተወሰነ ጊዜ ከተቀየረ የኪራይ ውሉን በማናቸውም ጊዜ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ማቋረጥ የሚቻል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2966 Cassation Decision no. 34456
-
34521 criminal law/ sentencing/ mitigating circumstances
በወንጀል ህግ ቅጣትን በልዩ የህጉ ክፍል ከተወሰነው መነሻ ዝቅ አድርጐ በማቅለል ለመወሰን የሚቻልበት አግባብ የወ/ህ/ቁ. 184, 179 Cassation Decision no. 34521
-
35611 criminal law/ criminal procedure/ non appearance of complainant
በወንጀል ህግ ጉዳዩን ለመስማት በተቀጠረበት ዕለት አቤቱታ አቅራቢው ባልቀረበ ጊዜ አቤቱታው እንዲሰረዝ የሚደረገው አቤቱታ አቅራቢው ጉዳዩን በትጋት ያልተከታተለ ወይም በቸልተኘነት የተወው መሆኑ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ የወ/መ/ህ/ሥ/ Cassation Decision no. 35611