volume 9
-
21214 federal courts/ concurrent power of regional courts/
ፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት መዋቅር ባልተዘረጋባቸው ክልሎች የክልል ጠቅላይ ፍ/ቤቶች የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤትን ወክለው/ተክተው/ ክርክሮችን ማስተናገድ ያለባቸው ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀፅ 139/1//ለ/,154/1/ 153 14ዐ Download Cassation Decision
-
31171 extra contractual liability/ liability of custom authority/
የጉምሩክ ባለሥልጣን ተግባር ህጋዊ ነው ሊባል የሚችለው በህጉ መሠረት ሊሟሉ የሚገቡትን ሁኔታዎች አሟልቶ ሲገኝ እንጂ በማናቸውም ጥርጣሬ ምክንያት የግለሰብን ንብረት በመያዝ ሊሆን የማይችል ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.6ዐ/89 አንቀጽ 6 58 አዋጅ ቁ. 368/95 አንቀጽ 2(28) የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 26(1) የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1193(1) (2) 2027 2035 2054 2118 Download Cassation Decision
-
31264 commercial law/ business/ rent of business/ subletting business
የንግድ መደብርን የተከራየ ወገን ይህንኑ የንግድ መደብር ለሌላ ሶስተኛ ወገን ያለአከራዩ ፈቃድ ማከራየት ስለመቻሉ የንግድ ህግ ቁጥር 145 Download Cassation Decision
-
31704 extra contractual liability/ liability of custom authority
የጉምሩክ ባለሥልጣን ያለአግባብ በቁጥጥሩ ሥር አድርጐ ለሚያቆየው ንብረት በባለንብረቱ ላይ ጉዳት የደረሰ እንደሆነ በኃላፊነት ሊያስጠይቀው የሚችል ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
31721 extra contractual liability/ vicarious liability/ minors
ለአካለ መጠን የደረሰ ሰው (ልጅ) ሃላፊነትን የሚያስከትል ሥራ የሰራ እንደሆነ ወላጆች በፍ/ብሔር በሃላፊነት ሊጠየቁ የማይችሉ ስለመሆናቸው የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2125 2124 Download Cassation Decision
-
31906 civil procedure/ jurisdiction /cause of action/ title deed
በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የይዞታ ማረጋገጫ ይሰጠኝ በሚል የሚቀርብ አቤቱታ በፍርድ ቤት ቀርቦ ዳኝነት ሊሰጥበት የሚችል ስላለመሆኑ Download Cassation Decision
-
33075 criminal law/ abuse of power/ faults by judges
የዳኝነትን ሥራ በማከናወን ወቅት የሚፈፀሙ ስህተቶች እና ጥፋቶች ሁሉ ዳኛን በሥልጣን ያለአግባብ መገልገል ወንጀል ሊያስጠይቁ የማይችሉ ስለመሆናቸው አዋጅ ቁ. 214/74 Download Cassation Decision
-
33201 extra contractual liability/ strict liability/
ማንም ሰው ሥራው በሚያደርሰው ጉዳት ምክንያት ጥፋት ባይኖርበትም ከውል ውጭ ሃላፊነት ሊከተልበት የሚችል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2ዐ66- 2ዐ89(2069(1)) Download Cassation Decision
-
33368 criminal procedure/ jurisdiction/ military courts
በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ በወታደርነት በማገልገል ላይ የሚገኙ የሠራዊት አባላት ጋር በተያያዘ የሚቀርቡ የወንጀል አቤቱታዎችን ለማስተናገድ ወታደራዊ ፍ/ቤቶች ስልጣን ያላቸው ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.27/88 አዋጅ ቁ. 343/94 አንቀፅ 2(9) 26(1) Download Cassation Decision
-
33470 commercial law/ business organizations / joint venture/ liquidation
የእሽሙር ማህበር መፍረስ በንብረት ክፍፍል ረገድ የሚያስከትለው ውጤት Download Cassation Decision
-
33841 civil procedure/ jurisdiction / Addis Ababa city court/ ownership
የከተማ ነክ ፍ/ቤቶች የቤት ባለቤትነት ክርክር የቀረበበትን ጉዳይ ለማየት ስልጣን የሌላቸው ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 361/95 አንቀጽ 41(1)(ረ) Download Cassation Decision
-
33954 commercial law/ business organizations/ liquidation
የንግድ ድርጅት በህግ አግባብ ለባለመብቶች ሊከፋፈል የሚችልበት ሁኔታ የንግድ ህግ ቁጥር 127 Download Cassation Decision
-
34314 extra contractual liability/ fatal accident/ compensation/ equity
ከውል ውጭ በሆነ ግንኙነት የሰው ህይወት የጠፋ እንደሆነና ለጉዳቱ መንስኤ (ምክንያት) የሆነው ወገን ሃላፊነት የተረጋገጠ ከሆነ በጠፋው የሰው ህይወት የተነሣ ጉዳት የደረሰበት ሰው የሞተው ሰው ምን ያህል ጥቅም ያስገኝለት እንደነበር ወይም ምን ያህል ተጨማሪ ዕድሜ ሊኖር እንደሚችል ያላስረዳ ቢሆንም እንኳን ፍ/ቤት የጉዳት ካሣውን በርትዕ ሊወስን የሚገባ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 21ዐ2 Download Cassation Decision
-
34440 civil procedure/ jurisdiction/ labor dispute/ scope of labor proclamation
የቅኔ መምህርነት ቀጥተኛ የሆነ መንፈሣዊ ሥራ በመሆኑ በሥራ ክርክር ችሎቶች ሊስተናገድ የሚችል ስላለመሆኑ Download Cassation Decision
-
34544 extra contractual liability/ fatal accident/ period of limitation
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 2143 ላይ የጉዳት ካሣን አስመልክቶ የቀረበው የይርጋ ድንጋጌ የሞት ጉዳትን የሚያካትት ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
34586 commercial law/ business/ good faith/ sale of business
በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1161 ላይ ግዙፍነት ያለው ተንቀሳቃሽ ነገር ጋር በተያያዘ በቅን ልቦና ዋጋ ሰጥቶ ስለመዋዋል የተመለከተው ድንጋጌ የንግድ መደብርን በተመለከተ ተፈፃሚ ሊሆን የሚችል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1161 የንግድ ሕግ ቁ. 124 Download Cassation Decision
-
34621 commercial law/ contract of carriage/ agency
በወኪል በኩል የሚፈፀም የመኪና ጭነት ውል በአስጫኙ እና በመኪናው ባለቤት መካከል እንደተደረገ የሚቆጠር ስለመሆኑ የንግድ ህግ ቁ. 566 እና የፍ/ብ/ሕ/ቁ 2251 Download Cassation Decision
-
34788 civil procedure/ jurisdiction /Addis Ababa city court
የአ.አ ከተማ ነክ ፍ/ቤቶች በከተማው አስተዳድር ሥር ካሉ ቤቶች ጋር በተያያዘ የሚነሱ ክርክሮችን ብቻ ለማየት ስልጣን ያላቸው ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
34945 commercial law/ business organizations/ private limited company
የጋራ ሀብት የሆነ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እንደሌላ ማናቸውም ንብረት ባለበት ሁኔታ በዓይነት ሊከፋፈል ወይም ደግሞ በሃራጅ ሊሸጥ የማይችል ስለመሆኑ የንግድ ህግ ቁ. 542 Download Cassation Decision
-
35003 property law/ immovable property/ valuation of property
የማይንቀሳቀስ ንብረት ጋር በተገናኘ የንብረቱ ትክክለኛ ዋጋ ተደርጐ ሊወሰድ የሚገባው ንብረቱን ለመገንባት የወጣው ወጪ (BooK value) ብቻ ሣይሆን ንብረቱ በወቅቱ ለገበያ ቀርቦ ሊያወጣ የሚችለው ዋጋ ( market value) ጭምር ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
35034 extra contractual liability/ compensation/ equity/ future damage
ጉዳት መድረሱ የተረጋገጠ ከሆነና ጉዳቱ በተጐጂው የወደፊት ህይወት ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ሊያሳድር እንደሚችል ምክንያታዊ እርግጠኝነት ያለ እንደሆነ ካሣ ርትዕን መሠረት በማድረግ ሊወሰን የሚገባ ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
35391 public pension/
የጡረታ መዋጮ በመዘግየቱ ምክንያት በአዋጅ ቁ. 345/95 መሠረት ተጨማሪ ክፍያ ሊከፈል የሚችልበት አግባብ እና አዋጅ ቁ. 345/95 አንቀጽ 7(3) 52(1) 56 የጡረታ መዋጮ በ2 ዓመት ውስጥ እንደተከፈለ የህግ ግምት ሊወሰድበት የሚችል የክፍያ ዓይነት ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2ዐ24(ሠ) Download Cassation Decision
-
35657 civil procedure/ jurisdiction/ Addis Ababa city court/ liquidation of succession
የአዲስ አበባ ከተማ ነክ ፍርድ ቤቶች የውርስ አጣሪ የመሾም ሥልጣን ያልተሰጣቸው ስለመሆኑ እና በአዲስ አበባ መስተዳደር ውስጥ የውርስ አጣሪ ይሾምልኝ ጥያቄን የማየት የዳኝነት ሥልጣን የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 361/95 አንቀጽ 41(1) (ሸ) የፍ/ብ/ህ/ቁ. 996(1) Download Cassation Decision
-
35695 criminal law/ new criminal code
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ የተሻሻሉና የተለወጡ ሁኔታዎች ከነባሩ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ጋር በቀጥታ ተጣምረው ሥራ ላይ ሊውሉ የሚገባ ስለመሆኑ በወ/ሕ/ አንቀጽ 543(3) የተከሰሰ ሰው የዋስ መብት የሚከለከል ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
35697 criminal law/ evidence law/ evaluation of evidence
በወንጀል ጉዳይ የክስ ሂደት የዐቃቤ ህግ ማስረጃ ከነሙሉ ይዘቱ ሊመዘን የሚገባ ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
36013 property law/ immovable property/ mortgage/ banking
በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የመያዣ መብት ያለው ባንክ በንብረቱ ላይ ሊኖረው የሚችለው የመብት አድማስ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 3059/1/, 3088/1/, 3110/ሐ/ Download Cassation Decision
-
36320 property law/ immovable property/ ownership/ title deed/
የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነት ካርታ በማቅረብ ብቻ የሚረጋገጥ ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1195 Download Cassation Decision
-
36338 civil procedure/ jurisdiction /social courts/
የቀበሌ ማህበራዊ ፍ/ቤቶች ለክርክር መነሻ የሆነው ክስ በገንዘብ ሊተመን የማይችል የመብት ጥሰትን የተመለከተ በሆነ ጊዜ የሥረ ነገር የዳኝነት ሥልጣን የሌላቸው ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 361/95 አንቀጽ 5ዐ(1) 39 Download Cassation Decision
-
36638 property law/ without objection by landowner
ባለመሬቱ ሳይቃወም በሌላ ሰው መሬት ላይ ህንፃ የሰራ ሰው የህንፃው ባለሀብት ሊሆን የሚችልበት አግባብ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1179 Download Cassation Decision
-
36645 property law/ possession/ possessory action
አንድ ተከራካሪ ተገቢነት ያለው የሁከት ይወገድልኝ አቤቱታ አቅርቧል ለማለት ለክርክር መንስኤ የሆነው ንብረት በእጅ አድርጎ መገኘትና በዚሁ ንብረት ላይ በእውነት ለማዘዝ እንዲችል የንብረቱ አያያዝ ያልተጭበረበረና በማናቸውም መንገድ ህገ-ወጥ በሆነ ሁኔታ ያልተገኘ መሆን ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 114ዐ 1149(1) Download Cassation Decision
-
36677 civil procedure/ jurisdiction / sharia courts/ possessory action
የሸሪዓ ፍ/ቤቶች የይዞታ ክርክርን ማስተናገድ የማይችሉ ስለመሆናቸው Download Cassation Decision
-
36730 civil procedure /jurisdiction/ period of limitation/
ስልጣን ለሌለው የዳኝነት አካል ክስ ማቅረብና ክርክር ማካሔድ የይርጋ ጊዜን የሚያቋርጥ ስለመሆኑ ( ከዚህ ቀደም የሰበር ችሎት በተቃራኒው የሰጠው የህግ ትርጉም የተለወጠ ስለመሆኑ፡፡) አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀፅ 138 147 164(1) የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 9 23 (1) (ለ) 231 (1)(ለ) 278(3) የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1851 (ለ) 1852(1) አዋጅ ቁ. 454/97 አንቀፅ 2(4) Download Cassation Decision
-
36776 civil procedure/ framing of suit/ splitting of cause of action
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 216 መሠረት በድጋሚ ክስ እንዳይቀርብ ሊደረግ የሚችልበት አግባብ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 216(3) Download Cassation Decision
-
37016 labor dispute/ jurisdiction / collective labor dispute
ወደ ቀድሞ የሥራ መደብ እንድመለስና ለመደቡም የተሰጠው ልዩ ጭማሪ እንዲከፈለኝ ይወሰንልኝ በሚል የሚቀርብ ጥያቄ የወል ሥራ ክርክር ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ142(1) (ሀ) Download Cassation Decision
-
37050 criminal procedure/ legal representation/ public defence
በከባድ የወንጀል ጉዳይ የተከሰሱ እና በራሣቸው ወጪ ጠበቃ ለማቆም ያልቻሉ ግለሰቦች በተመለከተ ጉዳዩን የሚያየው ፍ/ቤት የግለሰቦችን በጠበቃ የመወከል ህገ-መንግሥታዊ መብት መከበሩን በቅድሚያ ማረጋገጥ ያለበት ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
37163 contract law/ administrative contract/ tender
የመንግሥት መሥሪያ ቤት በጨረታ አማካኝነት የሽያጭ ውል አካሄዷል ተብሎ ሊገደድ የሚችልበት አግባብ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1688(2) 3167(1) 1688(2) 3168 Download Cassation Decision
-
37184 evidence law/ judgment on criminal bench/ relevance
በወንጀል ጉዳይ የተሰጠ ውሣኔ በተመሳሳይ ጉዳይ በፍ/ብሔር ለቀረበው ክስ በማስረጃነት ለመወሰድ ብቃትና አግባብነት ያለው ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
37214 civil procedure/ execution of judgment/ suit to establish right to attached property
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 421 መሠረት ክስ ለመመስረት የሚቻልበት አግባብ Download Cassation Decision
-
37281 civil procedure/ jurisdiction / expropriation
በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሠረት ከተወረሱና በቀላጤ ከተያዙ ቤቶች ውጭ ያሉ ቤቶችን አስመልክቶ የሚነሣ የቤት ክርክር ጉዳዮችን ፍርድ ቤቶች ማየት የሚችሉ ስለመሆናቸው አዋጅ ቁ.47/67 አዋጅ ቁ. 11ዐ/87 Download Cassation Decision
-
37297 property law/ joint ownership of property/ priority of purchase
የጋራ ንብረትን ለመካፈል በሚደረግ ሽያጭ የጋራ ባለኃብት የሆነ ወገን የቅድሚያ ግዥ መብት ያለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1261(2) 1386 – 1409 Download Cassation Decision
-
37298 property law/ joint ownership of property/ mortgage/ priority of purchase
የጋራ ሀብት የሆነ ንብረት በመያዣ የተያዘ በመሆኑ የቅድሚያ መብት ያለ ቢሆንም የጋራ ባለሀብት የሆነ ወገን ንብረቱ በግልፅ ጨረታ ቀርቦ የሚያወጣውን ትክክለኛ የገበያ ዋጋ ግማሽ በመክፈል ማስቀረት የሚችል ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
37339 civil procedure/ jurisdiction /private international law/ property in foreign country
በውጭ አገር የሚገኝ ንብረትን አስመልክቶ የሚቀርብ ክርክርን የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ማስተናገድ ስለመቻሉ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ-መንግስት አንቀፅ 37 አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀፅ(4) Download Cassation Decision
-
37375 advocates/ licensing/
የጥብቅና ፈቃድን ለማግኘት በህጉ የተቀመጡት መስፈርቶች ራሣቸውን ችለው መታየት ያለባቸው ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 199/92 አንቀጽ 8(1) Download Cassation Decision
-
37799 commercial law/ contract of carriage/ transitor
የዕቃ አስተላላፊ አካል እንደ አጓዥ ሆኖ የሚቆጠረው ከወደብ የተረከበውን ዕቃ በራሱ ማጓጓዣ ካጓጓዘ ብቻ ስለመሆኑ ደንብ ቁ.37/9ዐ አንቀጽ 2(1) 3(6) (7) የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2251 የንግድ ህግ .ቁ. 683(3) Download Cassation Decision
-
37866 civil procedure/ jurisdiction / tax law/ tax appeal commission
የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ በመቀጮ እና ወለድ ላይ የሚቀርብ ይግባኝን አይቶ የመወሰን ስልጣን ያለው ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
38161 criminal law/ elements of crime
አንድ ወንጀል ተደረገ የሚባለው ወንጀሉ የሚቋቋምበት ህጋዊ፣ ግዙፍዊና፣ ሞራላዊ ፍሬ ነገሮች በአንድነት ተጣምረው ሲገኙ ብቻ ስለመሆኑ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 23/2 Download Cassation Decision
-
38169 civil procedure/ parties to suit/ standing
ንብረትነታቸው የመንግስት የሆኑ ቤቶችን በተመለከተ የኪራይ ቤቶች ኤጀንሲ መንግስትን ወክሎ የመከራከር መብት ያለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 33(2) Download Cassation Decision
-
38228 property law/ possession/ possessory action/ ownership
የሁከት ይወገድልኝ አቤቱታን ለማቅረብ አቤቱታ አቅራቢው ክርክር የቀረበበት ንብረት ባለሀብትነቱን ሳይሆን ባለይዞታነቱን ብቻ ማስረዳት ያለበት ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
38237 property law/ land law/ constitution
ከዘር የወረደ ርስት ነው በሚል የመሬት ባለቤት ለመሆን የሚቀርብ ክስ ህገ-መንግስታዊ ያልሆነና ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
38289 contract law/ contract of bailment
አደራ ተቀባይ የሆነ ወገን በአደራ የተቀበለውን ዕቃ መመለስ ያለበት ለአደራ ሰጪው ወይም ይቀበልልኝ ብሎ ላመለከተው ሰው ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
38457 extra contractual liability/ disinterested parties
በጥቅም ላይ ባልተመሰረተ ግንኙነት በመኪና ተሣፍሮ የሚሄድ ተሣፋሪ ላይ ለሚደርስ አደጋ የመኪናው ባለቤት ካሣ የመክፈል ሃላፊነት የማይኖርበት ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2089 Download Cassation Decision
-
38666 property law/ immovable property/ form of contract
ከህግ የሚመነጭ የማይንቀሣቀስ ንብረት ባለሀብትነትን አስመልክቶ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1723 ተፈፃሚነት የማይኖረው ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
38745 civil procedure/ res judicata/ family law/ divorce
ቀደም ብሎ የተሰጠን የፍች ውሣኔ ወደጐን በመተው አዲስ የተደረገን ጋብቻ ህገ ወጥ ነው ማለት የማይቻል ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
38794 alternative dispute settlement/ compromise and arbitral submission
አማራጭ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች ምንነት፣ የሚደረጉበት መንገድና ለአፈፃፀም የሚቀርቡበት አግባብ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 3318 3324 3325 3346 1731 የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 315 319 35ዐ 357 Download Cassation Decision
-
39085 civil procedure/ jurisdiction/ employees of custom authority
ከጉምሩክ ፖሊስ አባላት ጋር በተያያዘ የሚነሱ የሥራ ክርክሮችን ለማየት የሚያስችል ስልጣን ለመደበኛ የሥራ ክርክር ችሎቶች ያልተሰጠ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 368/96 አዋጅ ቁ. 6ዐ/89 አንቀጽ 8(2) መመሪያ ቁ.4/1996 Download Cassation Decision
-
39529 property law/ administrative law/ title deed
አስተዳደራዊ የሆኑ መስፈርቶች ባልተሟሉበት ሁኔታ ካርታ እንዲሰጥ የሚወሰን ውሣኔ ተገቢ ስላለመሆኑ Download Cassation Decision
-
39539 property law/ possession/ possessory action
የይዞታ መብት ፍፁም ስላለመሆኑ እና በህግ አግባብ ይዞታው የተወሰደበት ሰው ተገቢ የሆነ ካሣ የመጠየቅ መብት ያለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 114ዐ 1149(1) (2) አዋጅ ቁ. 7/1986 አንቀጽ 2(5) 21 22 24 23 በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ- መንግሥት አንቀጽ 4ዐ (8) አዋጅ ቁ. 455/1997 Download Cassation Decision
-
39581 civil procedure / extinction of cause of action
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 28ዐ መሠረት መዝገብ ሊዘጋ የሚችልበት አግባብ ተከራካሪ ወገኖች በአቤቱታቸው ዳኝነት የሚጠይቁበትን ፍሬ ነገር በአግባቡ ከገለፁ ትክክለኛውን የህግ ድንጋጌ አለመጥቀሳቸው መብታቸውን የሚያስቀር ስላለመሆኑ Download Cassation Decision
-
39722 criminal law/ criminal procedure/ appeal /leave to appeal
በተወሰነበት ፍርድ ላይ ይግባኝ እንደሚል ፍላጐቱን አሳውቆ እያለ ፍርዱን በሰጠው ፍርድ ቤት በኩል በተከሰተ መጓተት የይግባኝ ጊዜው ያለፈበት ፍርደኛ የሚያቀርበው የማስፈቀጃ አቤቱታ ተቀባይነት ያለው ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
39799 civil procedure/ third party intervention
የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 43 ሊተረጐም የሚችልበት አግባብ Download Cassation Decision
-
39853 civil procedure /evidence law/ additional evidence
በፍ/ብሔር ሥነ-ሥርዓት ህግ መሠረት ተጨማሪ ማስረጃ ሊቀርብ የሚችልበት አግባብ Download Cassation Decision
-
39940 property law/ possession/ possessory action
የሁከት ይወገድልኝ አቤቱታ የሚያቀርብ ወገን የሁከት ተግባር ፈጽሟል ከሚባለው ሰው የተሻለ የይዞታ መብት ያለው መሆኑን በቅድሚያ ማረጋገጥ ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 114ዐ 1149 Download Cassation Decision
-
40133 constitution/ tax law/ public enterprises
ከፌዴራል መንግስት የልማት ድርጅት ሠራተኞች የሚሰበሰብ የሥራ ግብር ምንም እንኳን ሥራው የሚካሄደው በክልሎች ቢሆንም ወይም ሠራተኞቹ የክልል ነዋሪዎች ቢሆኑም ገቢ የሚደረገው ለፌዴራሉ መንግስት ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ-መንግስት አንቀጽ 96(3) አዋጅ ቁ. 33/85 አንቀጽ5(2)(ሐ) ደንብ ቁ. 109/96 Download Cassation Decision
-
40229 civil procedure /third party intervention/ opposition
ጣልቃ በመግባት በክርክር ተሳታፊ ለመሆን ጠይቆ የተፈቀደለትና የጣልቃ ገብነት አቤቱታውን ለተከራካሪ ወገኖች ማድረስ ሲገባው ይህን ባለመፈፀሙ መብቱ ከተሰረዘበት በኋላ ፍ/ቤቱ በሰጠው ውሣኔ ላይ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 358 መሠረት የሚቀርብ አቤቱታ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 41 358 Download Cassation Decision
-
40529 labor dispute/ death of worker/ compensation to Dependant
በሞት ምክንያት የሥራ ውል ሲቋረጥ ለሠራተኛው ጥገኞች ስለሚከፈል ካሣ፣ ካሣው የሚከፈልበትና የሚሰላበት ሁኔታ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀፅ 11ዐ Download Cassation Decision
-
40752 civil procedure/ court fee
ግምቱ ከብር 1ዐ ዐዐዐ ብር በላይ ለሆነ የአፈፃፀም ክስ ሊከፈል የሚገባው ዳኝነት 25 ብር ብቻ ስለመሆኑ የህግ ክፍል ማስታወቂያ ቁ. 177/1945 አንቀጽ 2(ሠ) Download Cassation Decision
-
41385 labor dispute/ work force reduction/ termination of contract of employment
የግንባታ ዕቃዎች እጥረት አጋጥሟል በሚል የሚደረግ የሥራ ስንብት ህገ-ወጥ ነው ሊባል የሚችል ስላለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀፅ 26 28 3ዐ Download Cassation Decision
-
41526 civil procedure /cassation procedure/ fact and law
አቤቱታ የቀረበበት ጉዳይ ከማስረጃ ምዘና ጋር የተያያዘና የፍሬ ነገር ክርክር ላይ ያተኮረ እንደሆነ በሰበር ችሎት ሊስተናገድ የማይችል ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ-መንግስት አንቀፅ 8ዐ(3), አዋጅ ቁ. 25/88 አንቀፅ 1ዐ Download Cassation Decision
-
41608 civil procedure/ jurisdiction /social courts/ Addis Ababa city court
የቀበሌ ማህበራዊ ፍ/ቤቶችም ሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍ/ቤቶች የፍ/ብሔር ክርክር ጉዳዬችን ለማየት የሚያስችል ስልጣን በህግ ያልተሰጣቸው ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
41767 labor dispute/ working at two places/ fraud
አሰሪ በግልፅ ባልፈቀደበት ሁኔታ በሁለት ቦታ በተመሳሳይ ጊዜ መስራት ሠራተኛውን የማታለል ተግባር እንደፈፀመ የሚያስቆጥረው ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀፅ 27(1)(ሐ) Download Cassation Decision
-
42139 commercial law/ insurance/ liability of the insurer
ዕቃዎችን ለሚያጓጉዝ የጭነት መኪና የተገባ የመድን ዋስትና ጋር በተያያዘ በመኪናው ላይ ተሣፍሮ ሲሄድ ለነበረና አደጋ ለደረሰበት ሰው መድን ሰጪው የጉዳት ካሣ የመክፈል ኃላፊነት የሌለበት ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
42253 property law/ intellectual property/ copyright
አንድን የሥነ-ጥበብ(ኪነ-ጥበብ) ሥራ ያለባለቤቱ ፈቃድ ኦርጅናሉ ወይም ቅጅው ለህዝብ እንዲታይ ማድረግ የኮፒ ራይት ህግ ጥሰት የሚያስከትል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1791 1771(1) 1790 2090-2123 አዋጅ ቁ. 41ዐ/96 አንቀፅ 7 Download Cassation Decision
-
42309 commercial law/ insurance/ period of limitation
ኢንሹራንስ ሰጪ በውሉ መሠረት ከፈፀመ በኋላ በተሸሸገ ወይም በሀሰት ቃል የቀረበ ጉዳይ አጋጥሟል በሚል የሚያቀርበው አቤቱታ የተሸሸገውን ወይም በሐሰት የቀረበውን ቃል ካወቀበት ቀን ጀምሮ ባለው ሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ካላቀረበ በይርጋ የሚታገድ ስለመሆኑ የንግድ ህግ 674(1) (2) Download Cassation Decision
-
42361 labor dispute/ civil procedure/ relief requested/ reinstatement
የአሰሪና ሠራተኛ አዋጅን መሠረት አድርጐ ከሚቀርብ ክርክር ጋር በተገናኘ በግልፅ ዳኝነት ተጠይቆበት ውሣኔ ሣይሰጥ ከተጠየቁት ዳኝነት መካከል ወደ ሥራ የመመለስ ጉዳይ ላይ ብቻ ውሣኔ ከተሠጠና ሠራተኛው ወደ ሥራ መመለስ ሳይፈልግ ቢቀር ቀድሞ ዳኝነት በጠየቀባቸው ነገር ግን ውሣኔ ባላረፈባቸው ነጥቦች ላይ ዳኝነት ሊጠየቅ የሚችል ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀፅ 43(3) Download Cassation Decision
-
42703 criminal law/ negligent homicide/ accident
ከተሽከርካሪ ጋር በተያያዘ በድንገተኛ አደጋ ለሚከሰት የሰው ህይወት መጥፋት አሽከሪካሪው በቸልተኝነት ወንጀል በማድረግ ሊጠየቅ የማይችል ስለመሆኑ የወንጀል ህግ አንቀፅ 59(1) 543(2) እና (3)፣57 (2) Download Cassation Decision
-
42818 labor dispute/ part time job/ termination of contract of employment
በትርፍ ሰዓት በሌላ መሥሪያ ቤት ሰርተሃል በሚል ሠራተኛን ያለማስጠንቀቂያ ለማሰናበት የሚያስችል የህግ ምክንያት የሌለ ስለመሆኑ አዋጅ 377/96 አንቀፅ 27 Download Cassation Decision
-
42871 civil procedure /review of judgment/ appeal
ዳኝነት በድጋሚ እንዲታይ በሚል የሚቀርብ አቤቱታ ላይ በተሰጠ ትእዛዝ/ብይን ላይ የይግባኝ አቤቱታ ለማቅረብ የማይቻል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 6(3)(4) Download Cassation Decision
-
42923 labor dispute/ termination of contract of employment/ failure to notify in writing
አሠሪ የሠራተኛውን የሥራ ውል ያቋረጠበትን ምክንያት በፅሁፍ አለመግለፁ ብቻ ስንብቱ ህገ- ወጥ ነው ለማለት የሚያስችል ስላለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀፅ 27(2) Download Cassation Decision
-
42985 labor dispute/ bankruptcy of enterprise/ termination of contract of employment/ notice
አንድ ድርጅት በመክሰሩ ወይም በሌላ ምክንያት ለዘለቄታው በመዘጋቱ የሥራ ውል ሲቋረጥ ሠራተኞች የስንብት ክፍያ ሊከፈላቸው የሚገባ ስለመሆኑ ድርጅት ለዘለቄታው እንዲቆም የሚያደርግ ሁኔታ ሲከሰት ማስጠንቀቂያ ለሠራተኞች መሰጠት ያለበት ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
43005 civil procedure /perjury/ summary punishment
ሐሰተኛ ቃል ተሰጥቷል በሚል ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 481 መሠረት የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሣኔ ሊሰጥ የሚችልበት አግባብ በአንድ የወንጀል ድርጊት ነፃ የተባለ ሰው እንደገና ሌላ ተጨማሪ ማስረጃ እንዲቀርብ ተደርጐ የሚቀጣበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
43160 labor dispute/ period of contract of employment/ definite/ indefinite
አንድ የሥራ ውል ለተወሰነ ጊዜ ወይም ለተወሰነ ሥራ የተደረገ ነው ሊባል የሚችልበት አግባብ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 9,10 Download Cassation Decision
-
43315 commercial law/ civil procedure/ summary procedure/ negotiable instruments/ check
ቼክን አስመልክቶ ክስ በቀረበ ጊዜ የተከሰሰው ወገን የቀረበበትን ክስ ለመከላከል እንዲፈቀድለት የሚያቀርበው ምክንያት ፈቃድ ሊያሰጥ የሚችል መሆን ያለመሆኑን አግባብነት ካላቸው ህግጋት አኳያ መታየት ያለበት ስለመሆኑ የንግድ ህግ ቁ. 717 የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 284 285 Download Cassation Decision
-
43331 civil procedure /preliminary objection/ appeal/ remand
የሥር ፍ/ቤት በመቃወሚያ ላይ የሰጠውን ውሣኔ የሚለውጥ ውሣኔ በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የተሰጠ እንደሆነ በግራ ቀኝ ወገኖችን በኩል የሚቀርቡ የፍሬ ነገር ክርክሮችንና ማስረጃ በአግባቡ ለመስማት ብሎም የተከራካሪዎችን ይግባኝ መብት ላለማጣበብ ሲባል ጉዳዩ ወደ ሥር ፍ/ቤት መመለስ ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 341(1) Download Cassation Decision
-
43410 civil procedure /non appearance of parties at first hearing
የቃል ክርክር እንዲሰማ በተቀጠረበት ዕለት ግራ ቀኝ የሆኑ ወገኖች ያልቀረቡ እንደሆነ መዝገቡ መዘጋት ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 69(2) Download Cassation Decision
-
43424 civil procedure/ mandatory joinder/ power of court
በክርክር የግድ ተካፋይ ሊሆኑ የሚገባቸው ወገኖች እና የፍ/ቤት ሚና የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 39 (1),40(2) Download Cassation Decision
-
43731 civil procedure /non appearance of parties/ ex parte suit
በሌለበት ጉዳዩ እንዲታይ ትዕዛዝ የተሰጠበት ተከራካሪ ወገን ፍ/ቤቱ ለጉዳዩ የመጨረሻ ውሣኔ ከመስጠቱ በፊት አቤቱታው ሊስተናገድ የሚችልበት አግባብ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 7ዐ(ሀ) 78 69 72 Download Cassation Decision
-
43821 civil procedure /review of judgment/ appeal
ዳኝነት እንደገና እንዲታይ (Review of judgment) በሚል የሚቀርብ አቤቱታ አስቀድሞ በተሰጠ ውሣኔ ላይ ይግባኝ የተባለበት ነው በሚል ምክንያት ብቻ ውድቅ ሊደረግ የማይገባ ስለመሆኑ (ከዚህ ቀደም በሰበር ችሎት የተሰጠው የሕግ ትርጉም የተለወጠ ስለመሆኑ) የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 6(1)(ሀ),(ለ) Download Cassation Decision
-
43845 civil procedure/ evidence law/ relevance of evidence
በተከራካሪ ወገኖች የሚቆጠሩ ማስረጃዎች ሳይሰሙ የሚቀሩት ለተያዘው ጉዳይ አግባብነት የሌላቸው መሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ ስለመሆኑ ፍ/ቤቶች ተከራካሪ ወገኖች የቆጠሩትን ማስረጃ ሳይሰሙ ወደ ጐን በመተው አቤቱታቸውን በበቂ ማስረጃ አላስረዱም በሚል የሚደርሱበት መደምደሚያ አግባብነት የሌለው ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
43875 civil procedure/ parties to a suit/ pleaders
መንግስታዊ የሆነ ተቋም በሚከሰስበትም ሆነ በሚከስበት ክርክር የሚቀርብ ሰነድ የኘሮቶኮል ቁጥር እንዲሁም ስለአቤቱታው ጽሁፍ ትክክለኛነት በሚመለከተው ኃላፊና በወኪሉ መፈረም ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 8ዐ 92 93 እና 92(3) Download Cassation Decision
-
44031 criminal law/ participation in crime
አንድ ተከሣሽ በተፈፀመ ወንጀል ላይ ተካፋይ ነበር ለማለት ተከሣሹ በሙሉ ፈቃዱና ዕውቀቱ በወንጀል ድርጊቱ ተሣታፊ የነበረ መሆኑ መረጋገጥ ያለበት ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 32 33 63ዐ 25 Download Cassation Decision
-
44218 labor dispute/ contract of employment for indefinite period of time
የሥራ ውል የተደረገው ለተወሰነ ጊዜ ወይም ሥራ ነው በሚል ክርክር በቀረበ ጊዜ ይህንኑ የማስረዳት ሸክም የሚኖር ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀፅ 9 Download Cassation Decision
-
44405 labor dispute/ payments due/ set off by employer
ሠራተኛ የተረከባቸውን ንብረቶች አላስረከበም ወይም አጉድሏል በሚል የሥራ ውሉ በተቋረጠ ጊዜ የሚጠይቃቸውን ተገቢ ክፍያዎች ሊጠይቅ አይችልም በሚል በአሠሪው የሚቀርብ ክርክር ተገቢነት የሌለው ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀፅ 36 37 38 Download Cassation Decision
-
44410 labor dispute/ severance pay/ termination of contract of employment by worker
ሥራውን በገዛ ፈቃዱ የሚለቅ ሰራተኛ የስንብት ክፍያ ለማግኘት የሚችለው ቢያንስ የ5 ዓመት አገልግሎት ያለው እንደሆነ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 494/98 አንቀጽ 2(ሸ) Download Cassation Decision
-
44545 civil procedure/ appeal/ judgment on appeal
ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት የሥር ፍ/ቤትን ውሣኔ በመሻር በዋናው ጉዳይ ላይ የራሱን ውሣኔ ካሣለፈና የበላይ የሆነ ፍ/ቤት ደግሞ የይግባኝ ውሳኔውን ባለመቀበል የሥር ፍ/ቤትን ውሣኔ በደፈናው በማፅናት የሚሰጠው ውሣኔ የተከራካሪ ወገን የይግባኝ መብት የሚያጣብብና የሥነ-ሥርዓት ህግ ደንብን የሚጥስ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 341 342 343 Download Cassation Decision
-
44594 criminal law/ criminal procedure/ business
በወንጀል ድርጊት ተጠርጥሮ የተያዘ ሰው ንብረት የሆነ ንግድ መደብር ጋር በተገናኘ ፍ/ቤቶች የንግድ መደብሩን በውስጡ ከያዘው ሸቀጦች በመለየት (በመነጠል) የሚሰጡት ትዕዛዝ ተገቢነት የሌለው ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
44883 civil procedure/ execution of judgment/ banking/ mortage
የማይንቀሳቀስ ንብረትን ለሰጠው ብድር በመያዣነት የያዘ ባለገንዘብ ባንክ መብቱ በይርጋ እስካልታገደ ድረስ የያዘውን ንብረት በጨረታ ለመሸጥ የሚገደድበት ተለይቶ በህግ የተቀመጠ የጊዜ ገደብ የሌለ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 97/9ዐ አዋጅ ቁ. 216/92 አንቀፅ 2 የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሀ/ቁ. 394 - 449 Download Cassation Decision
-
44931 civil procedure/ error/ appeal procedure
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 2ዐ8 መሠረት በሥር ፍ/ቤት የተደረገ እርማትን መነሻ በማድረግ የይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት አስቀድሞ የሰጠውን ውሣኔ ለመለወጥ የሚያስችለው የህግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 208 209 320 (1) ,348(1) Download Cassation Decision
-
45038 civil procedure/ execution of judgment/ transfer of attached property to third party
የንብረት ክፍፍል እንዲደረግ በፍርድ ቤት ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ በውሳኔው ወቅት ንብረቱን በእጁ አድርጐ የሚገኘው ወገን የንብረቱን ስመ ሐብት ወደ ሌላ ሦስተኛ ወገን አዛውሮ ሲገኝ ፍርድ ቤቶች ሊከተሉት ስለሚገባው አካሔድ Download Cassation Decision
-
45170 labor dispute/ termination of contract of employment/ contract of employment
በክረምት ወቅት የማስተማር ሥራ እንዲሠራ የሚያዝ ግልፅ ደንብ ወይም መመሪያ የሌለ እንደሆነ ወይም አስተማሪው በክረምት ወራት ለማስተማር የገባው የውል ግዴታ (ስምምነት) በሌለ ጊዜ በክረምት ወቅት ሥራን ለመስራት ፈቃደኛ አልሆነም በሚል ከሥራ ሊሰናበት የማይችል ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀፅ 13(1) Download Cassation Decision
-
45247 civil procedure /cause of action
ፍ/ቤቶች የቀረበላቸው አቤቱታ የክስ ምክንያት አለው ወይም የለውም ብሎ ለመወሰን በክስ ላይ የተገለፀው ነገር ቢረጋገጥ ከሳሽ የሆነው ወገን የጠየቀውን ዳኝነት ለማግኘት ህግ ይፈቅድለታል ወይስ አይፈቅድለትም የሚለውን ጥያቄ መመርመር ያለባቸው ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
45371 civil procedure/ extinction of cause of action
ፍ/ቤቶች ለቀረበላቸው ክስ ምክንያት የሆነው ነገር መቋረጡን ወይም ጨርሶ መቅረቱን በክሱ ሂደት በማንኛውም ደረጃ በቂ በሆነ ማስረጃ በተገነዘቡ ጊዜ ክሱን ሊዘጉት የሚገባ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 280 Download Cassation Decision
-
45746 labor dispute/ termination of contract of employment/ period of limitation
ከሥራ ክርክር ጋር በተያያዘ አሰሪ ሠራተኛው የፈፀመውን ድርጊት መሠረት አድርጐ ለማሰናበት የሚችለው የሥራ ውሉን ለማቋረጥ ምክንያት የሆነው ነገር መከሰቱን ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ በሚቆጠሩ ሰላሳ ቀናት ውስጥ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀፅ 27(3) Download Cassation Decision
-
45839 civil procedure /review of judgment
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 6 መሠረት ውሣኔ ወይም ትዕዛዝ ለሰጠ ፍ/ቤት አቤቱታ ሊቀርብ የሚችልበት አግባብ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 6 Download Cassation Decision
-
45889 labor dispute/ power of employer
አሰሪ ሠራተኞቹን በማስተዳደር ረገድ የሚፈፅማቸውን ስህተቶች በራሱ አነሣሽነት ሊያርም የሚችል ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
45984 civil procedure /change of witnesses
ተከራካሪ ወገኖች በአቤቱታቸው ላይ የጠቀሷቸውን የሰው ማስረጃዎች ሊለውጡ (ሊቀይሩ) የሚችሉበት አግባብ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 223/2/,234 Download Cassation Decision
-
46276 labor dispute/ public pension/ severance pay
የጡረታ መብት ያለው እና መደበኛ የጡረታ ዕድሜው ደርሶ የተሰናበት ሰራተኛ የስንብት ክፍያ ለማግኘት መብት የሌለው ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 494/98 አንቀጽ 2/2(ሰ) እና (ሸ) Download Cassation Decision
-
46363 labor dispute/ occupational accident
አንድ አሰሪ በሥራ ላይ ጉዳት የደረሰበትን ሰራተኛ ወደ ውጭ አገር ልኮ ስለሚያሳክምበት አግባብ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 124,105 Download Cassation Decision
-
46382 criminal law/ sentencing/ suspension of penalty
በወንጀል ጉዳይ በእስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት ሰው የእስራት ቅጣቱን ሳይፈፀም በገደብ እንዲቆይ ወይም እንዲለቀቅ ሊደረግ የሚችለበት አግባብ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 82 192 194 Download Cassation Decision
-
47252 civil procedure /framing of issues
የክርክር ጭብጥ የሚመሰረተው ከሳሽ የሚያቀርበውን ክስና ማስረጃ በተከሳሽ የቀረበውን የመከላከያ መልስና ማስረጃ እንዲሁም ፍ/ቤቱ የቃል ምርመራ ሲያደርግ የሚያገኘውን ፍሬ ጉዳይ መሠረት በማድረግ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 241 248 Download Cassation Decision
-
47469 labor dispute/ public pension/ benefits
በጡረታ የተገለሉና ለተወሰነ ጊዜ የተቀጠሩ ሠራተኞች ቋሚ ሠራተኞች የሚያገኟቸውን ልዩ ልዩ ጥቅማጥቅሞችን የማግኘት መብት የሌላቸው ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀፅ 1ዐ Download Cassation Decision
-
47535 labor dispute/ suspension/ collective agreement
አንድ ሠራተኛ በሥራ ላይ ከሚፈፅመው ጥፋት ጋር በተያያዘ ከሥራ ታግዶ ሊቆይ ስለሚችልበት ሁኔታ በህብረት ስምምነት ሊወሰን የሚችል ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 Download Cassation Decision
-
47551 civil procedure /evidence law/ evidence to prove fact
አንድን ፍሬ ነገር ለማስረዳት ተለይቶ የተመለከተ ማስረጃ እንዲቀርብ ህጉ ካላስገደደ በቀር ይህንን ፍሬ ነገር በማንኛውም የማስረጃ ዓይነት ማስረዳት የሚቻል ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
47784 labor dispute/ contract law/ period of limitation
በሥራ ክርክር ጉዳይ በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1853 ላይ የተመለከተው ድንጋጌ ተፈፃሚ ሊሆን የሚችልበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 164(3) የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1853 1852 Download Cassation Decision
-
47806 labor dispute/ scope of labor proclamation/ religious institutions
በክርስትና ሃይማኖት ተቋም ውስጥ በዲያቆንነት ሥራ ከማገልገል ጋር በተያያዘ የሚቀርቡ የሥራ ክርክር ጉዳዮች በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ መሠረት ሊስተናገዱ የማይችሉ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 Download Cassation Decision
-
47807 labor dispute/ occupational accident
በአሠሪና ሠራተኛ ሕጉ “በሥራ ላይ የሚደርስ ጉዳት” ወይም “በስራ ምክንያት የሚመጣ በሽታ” በሚል የተቀመጠው ሐረግ ሊተረጐም የሚችልበት አግባብ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 95/2/,97,96 Download Cassation Decision
-
47825 labor dispute/ termination of contract of employment/ bonus/ salary increment
ሠራተኞችን ለማበረታታት በሚል የሚደረግ የደመወዝ (ጥቅማጥቅም) ጭማሪን መሠረት በማድረግ ጭማሪውን የሚፈቅደው መመሪያ ከመውጣቱ በፊት የሥራ ውሉ የተቋረጠ ሠራተኛ የሚጠይቀው መብት የሌለ ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
48237 civil procedure/ court contempt
የፍ/ቤትን ክብርንና የዳኝነት ሥርዓቱን መልካም አመራር ለማስጠበቅ ሲባል የማንኛውም ችሎት ሰብሳቢ ዳኛ በችሎት ውስጥ በሚገኝ ማንኛውም ሰው ላይ ቅጣት ሊወሰን የሚችልበት አግባብ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 480 Download Cassation Decision
-
48476 labor dispute/ termination of contract of employment/ debt of worker/ certificate of experience or clearnce
የሥራ ውል በተቋረጠ ጊዜ አሰሪው ከሠራተኛው በህግ አግባብ የሚፈልገው/ የሚጠይቀው ዕዳ ያለ እንደሆነ ለሠራተኛው የሥራ ልምድ ምስክር ወረቀት ከመስጠት ባሻገር የሥራ መልቀቂያ (ክሊራንስ) ለመስጠት የማይገደድ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 515/99 አንቀፅ 78 (1) 87 Download Cassation Decision
-
48632 civil procedure /non denial/ admission
በግልፅ ያልተካደ ፍሬ ነገር እንደታመነ ይቆጠራል የሚለው የሥነ- ሥርዓት ህግ ድንጋጌ ተፈፃሚ የሚሆነው ተከሳሽ ቀርቦ ክርክሩን ባሰማ ጊዜ ስለመሆኑና ድንጋጌው የካሣ ጥያቄ ጋር በተያያዘ ተፈፃሚነት የሌለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 235(2) 83 Download Cassation Decision
-
48648 labor dispute/ contract of employment for definite period of time
በአሰሪና ሰራተኛ በኩል በአጠቃላይ ለፕሮጀክት ሥራ በሚል የተደረገ የሥራ ውል በአሰሪና ሰራተኛ ሕጉ አንቀጽ 10(1)(ሀ) መሰረት የተደረገ እንደሆነ ተደርጐ የሚወሰድ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 10(1)(ሀ) Download Cassation Decision
-
49057 labor dispute/ termination of contract of employment/ notice
በአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ መሠረት የሥራ ግንኙነት በአንቀፅ 3ዐ መሠረት ሲቋረጥ አሰሪ ማስጠንቀቂያ የመስጠት ግዴታ የሌለበት ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀፅ 3ዐ 28(2) Download Cassation Decision
-
49273 labor dispute/ occupational accident/ disability
ሠራተኛ በሥራ ላይ እያለ የሚደርስበትን ጉዳት ዘላቂ ሙሉ የአካል ጉዳት ወይም ዘላቂ ከፊል የአካል ጉዳት በማለት ለመለየት የሚቻልበት አግባብ Download Cassation Decision
-
49660 civil procedure /evidence law/ hearing of witnesses
ክስ የቀረበበት ወገን ክሱን ለማስተባበል የሚቆጥራቸው ማስረጃዎችን ተቀብሎ አለመስማት የመከላከል ህጋዊ መብትን የሚያጣበብ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ5 223 234 137 249 256 Download Cassation Decision
-
49750 labor dispute/ collective agreement/ fault by worker
የአሰሪና ሰራተኛ ሕጉ አሰሪና ሰራተኛ ስምምነት ሊያደርጉባቸው የሚችሉበት ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ጥፋትንና ጥቅምን በተመለከተ የተለያየ አቋም የያዘ ስለመሆኑ አሰሪና ሠራተኛ በህብረት ስምምነታቸው ውስጥ ያለማስጠንቀቂያ ከሥራ ሊያሰናብት የሚችል ጥፋት በሚል የተስማሙበት ድንጋጌ ተፈፃሚ ሊሆን የሚገባ ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
49797 labor dispute/ termination of contract of employment/ notice for termination
አሠሪ የሠራተኛውን የሥራ ውል ያቋረጠበትን ምክንያት በፅሁፍ አለመግለፁ ብቻ ስንብቱ ህገ- ወጥ ነው ለማለት የሚያስችል ስላለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀፅ 27(2) Download Cassation Decision
-
49857 civil procedure /joinder of defendants/
ሁለት ሰዎች ተጣምረው በተከሰሱ ጊዜ አንደኛው ወገን ጉዳዩ በሌለበት ከታየ በኋላ ወደ ክርክሩ እንዲገባ የተፈቀደለት እንደሆነ ሌላኛው ተከሳሽ አስቀድሞ ያነሳቸውን መቃወሚያዎች በድጋሚ ልታነሣና ልትከራከር አትችልም ሊባል የሚችልበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 5 Download Cassation Decision
-
49931 labor dispute/ unlawful termination/ reinstatement
ከሥራ ክርክር ጋር በተያያዘ ከሠራተኛው ጋር ያለው ግንኙነት ሠራተኛው ወደ ሥራ ቢመለስ ችግር ውስጥ እንደሚወድቅ በአሠሪው ስለተገለፀ ብቻ ሠራተኛው ካሣ ተከፍሎት እንዲሰናበት በሚል የሚሰጥ ውሣኔ ተገቢነት የሌለው ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 43/3/ Download Cassation Decision
-
49958 labor dispute/ termination of contract of employment without notice/ brawl at work place
የጠብ አጫሪነት ኃይለ ቃልና ዛቻ አዘል ንግግር በሥራ ቦታ ላይ ማድረግ ያለማስጠንቀቂያ ከሥራ የሚያሰናብት ጥፋት ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀፅ 27(1)(ረ Download Cassation Decision
-
50009 labor dispute/ fraud committed by worker
በአሰሪና ሠራተኛ ህጉ ውስጥ “እንደ ጥፋቱ ክብደት በሥራው ላይ የማታለል ወይም የማጭበርበር ተግባር መፈፀም” በሚል የቀረበው አባባል (አነጋገር) ሊተረጐም የሚችልበት አግባብ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀፅ 27(1)(ሐ) Download Cassation Decision
-
50022 civil procedure/ summon procedure
ክስ የቀረበለት ፍ/ቤት ወደ ጉዳዩ ሥረ-ነገር ገብቶ ተከሳሽ የሆነን ወገን በሌለበት ባለዕዳ የሚያደርግ ውሣኔ ከመስጠቱ በፊት ተከሳሹ በአግባቡ ስለመጠራቱ ማረጋገጥ ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 97 95(3) Download Cassation Decision
-
50148 civil procedure/ execution of judgment
አንድ ሰው በአፈፃፀም ሊገደድ የሚችለው በህግ አግባብ የተፈረደ ፍርድ ሲኖር ብቻ ስለመሆኑ በግልፅ ፍርድ ያላረፈበት ጉዳይ ጋር በተያያዘ ሊፈፀም የሚችል ፍርድ የሌለ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 378 Download Cassation Decision
-
50182 labor dispute/ civil procedure/ cause of action/ reinstatement
በድርጅት ውስጥ የተከሰተ ተጨባጭ ችግርን ለመቅረፍና የድርጅቱን ትርፋማነት ለማስቀጠል በሚል በተመሳሳይ ሙያና ደረጃ ላይ ካሉ ሠራተኞች መካከል ተለይቼ ወደ ሌላ የሥራ መደብ ስለተዛወርኩኝ እንድመለስ ይወሰንልኝ በማለት የሚቀርብ አቤቱታ የክስ ምክንያት የሌለው ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
50205 labor dispute/ contract of employment/ termination of contract of employment
አሠሪና ሠራተኛ የሥራ ውል መቋረጥ ጋር በተያያዘ በሥራ ውሉ ላይ የሚያመለክቱት ሁኔታ የአሰሪና ሠራተኛ ህጉን እስካልተፃረረ ድረስ ተግባራዊ ሊደረግ የሚገባ ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
50376 civil procedure /summon procedure/ mode of service
በፍ/ብሔር ጉዳይ ተከሣሽ ለሆነ ወገን ከፍ/ቤት የሚላከውን መጥሪያ ለተከሳሹ ሊደርስ የሚችልበትን የተሻለ አማራጭ መንገድ በመለየት ሊላክ የሚገባ ስለመሆኑ የመኖሪያ አድራሻው በግልፅ ለሚታወቅ ተከሳሽ ፍ/ቤቱ የሚልከውን መጥሪያ በፍ/ቤቱ ቅጥር ግቢ ብቻ እንዲለጠፍ በማድረግ ተከሳሹ አልቀረበም በሚል በሌለበት ጉዳዩ እዲታይ የሚሰጥ ውሣኔ ተገቢነት የሌለው ስለመሆኑ መጥሪያ በአግባቡ እንዲደርሰው ያልተደረገ ተከሳሽ በሌለበት ታይቶ የተሰጠበት ውሣኔ እንዲነሣለት የሚያቀርበው አቤቱታ ተገቢነት ያለው ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
50838 labor dispute/ structural change of enterprise/ right of employer/ assignment
የድርጅት መዋቅራዊ ለውጥ ያደረገ ተቋም በአሰሪና ሠራተኛ ህጉ መሠረት ሠራተኞቹን አዲስ በሚያወጣው የሥራ መደብ ላይ ተመርኩዞ የሥራ ምደባ ሊያከናውን የሚችል ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀፅ 28 Download Cassation Decision
-
50923 labor dispute/ private international law/ scope of application of labor proclamation
ከአሰሪና ሠራተኛ ግንኙነት ጋር በተገናኘ ሁለቱ ወገኖች አዋጅ ቁ. 377/96 “ን” ወደ ጐን በማድረግ በሌላ አገር ህግ ለመዳኘት ስምምነት ያደረጉ በመሆኑ ብቻ ጉዳዩ የግለሰብ አለም አቀፍ ህግ ጥያቄን ያስነሳል በሚል በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሊስተናገድ የማይገባ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 የውጭ አገር ድርጅት ሆኖ በኢትዮጵያ ተመዝግቦ በሚሰራ የበጐ አድራጐት ድርጅት ላይ ተፈፃሚነት ያለው ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
51912 labor dispute/ period of limitation/ calculation of period of limitation
ከሥራ ክርክር ጋር በተያያዘ የሚነሣው የይርጋ የጊዜ ገደብ የሚሰላው የሥራ ቀናትን ብቻ በማስላት ስላለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀፅ 163(2) Download Cassation Decision
-
52459 labor dispute/ termination of contract of employment/ annual leave
በማናቸውም ምክንያት የሥራ ውል ሲቋረጥ ሠራተኛው ያልወሰደው የዓመት እረፍት ፈቃድ በገንዘብ ተለውጦ ሊከፈል የሚገባ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀፅ 77(5) 24(2) Download Cassation Decision
-
52525 civil procedure / res judicata
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 5(1) መሠረት በድጋሚ ክስ ማቅረብ የማይቻለው በቀደመው ክርክር የተያዘው ጭብጥና የፍሬ ነገር ክርክር ተመሳሳይ መሆኑና የተከራካሪ ወገኖች አንድነት በመኖሩ ብቻ ሣይሆን በፍሬ ጉዳዩ ላይ የመጨረሻ ፍርድ የተሰጠ መሆኑ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 5 Download Cassation Decision
-
52752 civil procedure /compromise agreement
ተከራካሪ ወገኖች ጉዳያቸውን በእርቅ ለመጨረስ የተሰማሙና ይሄንኑም ስምምነት ለፍ/ቤት በማቅረብ ያስፀደቁ በሆነ ጊዜ ስምምነቱ እንደ ፍርድ ቤት ውሣኔ ተቆጥሮ መፈፀም ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 277 Download Cassation Decision
-
53064 labor dispute/ execution of judgment/ reinstatement/ compensation in lieu of reinstatement
ወደ ሥራ እንዲመለስ ፍርድ የተሰጠ እንደሆነና በአሰሪው ችግርም ሆነ በሠራተኛው ፍላጐት በፍርዱ መሠረት ወደ ሥራ ለመመለስ ሠራተኛው ያልፈለገ ከሆነ ሠራተኛው የአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ በምትክነት በሰጠው መብት መሠረት በመመለሱ ፈንታ ካሣ እንዲከፈለው አፈፃፀሙን ለያዘው ችሎት ጥያቄውን ባቀረበ ጊዜ ሊስተናገድ የሚገባው ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀፅ 43(3) Download Cassation Decision
-
53358 labor dispute/ interpretation/ right of employer to terminate contract of employment
በአሰሪና ሠራተኛ ህጉ ‹‹… ውሉ የሚቋረጥበት ምክንያት መከሰቱን ካወቀበት…›› በሚል የተመለከተው ሃረግ ሊተረጐም የሚችልበት አግባብ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀፅ 27(3) Download Cassation Decision
-
55189 labor dispute/ unlawful termination of contract of employment/ reinstatement/ industrial peace
በአሰሪ የተፈፀመው የሥራ ስንብት ህገ- ወጥ ቢሆንም ከሥራ ግንኙነቱ ፀባይ የተነሣ ከፍተኛ ችግር የሚፈጠር በሆነ ጊዜ ሠራተኛውን ወደ ሥራ ከመመለስ ይልቅ ካሣ ተከፍሎት እንዲሰናበት ማድረግ ተገቢ ስለመሆኑ የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ አንቀፅ 43(3) በአንድ በኩል የሠራተኛን የሥራ ዋስትና በሌላ በኩል ደግሞ የኢንዱስትሪን ሰላም በማመዛዘን ትርጉም ሊሰጠው የሚገባ ስለመሆኑ Download Cassation Decision