volume 10
-
29181 contract law/ loan contract/ banking/ presumption of payment/ evidence law
የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2ዐ26(1) ለባንኮችና ለደንበኞቻቸው መብት ልዩ ጥበቃ የሚያደርገው የፍ/ብ/ሀ/ቁ. 2473(2) ድንጋጌ ዋጋ በሚያሳጣ መንገድ ተፈፃሚ ሊሆን የማይገባ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2ዐ26(1) በባንኮችና በሌሎች አበዳሪ ተቋማት እና ደንበኞቻቸው መካከል ያለውን ግንኙነት በተመለከተ ተፈፃሚነት የሌለው የህግ ድንጋጌ ስለመሆኑ ባንኮች ለደንበኞቻቸው ያበደሩትን የብድር ወለድ ያልተከፈለ መሆኑን በሰው ምስክር፣ የሰነድና ሌላ ማስረጃ በማቅረብ በፍ/ብ/ህ/ቁ. 2ዐ24(1) ስር የተደነገገውን የህሊና ግምት ለማስተባበል የሚችሉ ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
34665 administrative law/ title deed/ Addis Ababa city
የአ.አ ከተማ መስተዳድር ምክር ቤት የሥራና ከተማ ልማት ቢሮ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነት ደብተርን ለመሰረዝ የሚያስችል ስልጣን ያለው ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
35758 contract law/ presumption of payment
በፍ/ብሔር ሕግ ቁጥር 2024/ረ/ መሰረት እንደተከፈለ ሊቆጠር የሚችለው በብድር የተሰጠ ገንዘብ ሳይሆን የተሰጠ ገንዘብ ላይ የሚታሰብ ወለድ ክፍያ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2024 Download Cassation Decision
-
38533 law of succession/ period of limitation
በውርስ ሕግ ውስጥ የተመለከቱ የይርጋ ድንጋጌዎች ሊተረጐሙ የሚችሉበት አግባብ የወራሽነት መብትን በሕግ በተመለከተ ጊዜ ውስጥ ያረጋገጡ ወራሾች የውርስ ንብረት ክፍፍል ጥያቄን በማናቸውም ጊዜ ማቅረብ የሚችሉ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 996,1000(1),1000(2),1060,1062 Download Cassation Decision
-
38544 family law/ common property/ contract of marriage
በጋብቻ ውል ላይ ባልና ሚስት “መተዳደሪያችን” ነው በሚል ያመለከቷቸው ንብረቶች የጋራ ንብረት ተደርገው የሚቆጠሩ ስለመሆናቸው Download Cassation Decision
-
38572 insurance/ banking/ loan/ mortgage/ insurance coverage
በብድር ለተሰጠ ገንዘብ በመያዣነት የተያዘ ንብረት መድን የተገባለት ሆኖ አደጋ የደረሰበት እንደሆነ አበዳሪው ንብረቱን በመያዣ የያዘበት ብድር ዋጋ ዋስትና ከተገባለት የገንዘብ መጠን ያነሰ እንኳን ቢሆን መድን ሰጪው እንዲከፍለው ሊጠይቅ የሚችል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2858 Download Cassation Decision
-
38681 contract law/ mortgage/ valid mortgage
የማይንቀሳቀስ ንብረት በመያዣ ተሰጥቷል ለማለት የሚቻልበት አግባብ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 3041,3052 Download Cassation Decision
-
39408 family law/ bigamy/ contract of marriage/ void ab initio
በጋብቻ ላይ የተደረገ ጋብቻ ከጅምሩ ውጤት አልባ ነው (void ab initio) ሊባል የሚችል ስላለመሆኑ የጋብቻ ውል ተጋቢዎች ንብረታቸውን በተመለከተ ጋብቻው የሚያስከትለውን ውጤት ስምምነት የሚያደርጉበት ሰነድ ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 42 44 33 1 Download Cassation Decision
-
39574 tax law/ income tax/ income from rent/ business/ value added tax (VAT)
የንግድ ቤቶችን የማከራየት እንቅስቃሴ ከታክስ ነፃ ከሆኑ ግብይቶች የማይመደብ ስለመሆኑ የንግድ ቤት ኪራይ የመክፈል ግዴታ ያለበት ወገን የተጨማሪ እሴት ታክስ መክፈል ያለበት ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 285/94 አንቀፅ 8 Download Cassation Decision
-
39601 extra contractual liability/ damage
የጉዳት ኪሣራ የሚከፈለው ጉዳት ስለመድረሱ ሲረጋገጥ ብቻ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2ዐ9ዐ 2ዐ91 Download Cassation Decision
-
39608 commercial law/ private limited company/ liability of manager
ኃላፊነቱ የተወሰነ የንግድ ማህበር ሥራ አስኪያጅ የሆኑ ሰዎች ማህበሩን ሲያስተዳድሩ በሰሩት ያልተገባ ስራ ምክንያት በኃላፊነት ሊጠየቁ የሚችሉበት አግባብ የንግድ ሕግ ቁጥር 580 Download Cassation Decision
-
39837 civil procedure/ execution of judgment/ family law/ debt of spouse
አንድ ተጋቢ በግሉ ያመጣው ዕዳ ከሌለኛው ተጋቢ የጋራ ንብረት እንዲከፈል የሚደረገው ዕዳውን ያመጣው ተጋቢ ዕዳውን ለመክፈል አለመቻሉ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ የደቡ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ እና የፌዴራል መንግስት የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ Download Cassation Decision
-
39902 insurance/ subrogation/ agreement for arbitration
መድን ሰጪ የሆነ ወገን በመድን ገቢው እግር በመተካት ባለዕዳ የሆነ ወገን ላይ ጥያቄ ባነሣ ጊዜ ባለዕዳው ከመድን ገቢው ጋር የሚፈጠር አለመግባባትን ከፍርድ ቤት ውጪ በሽምግልና ለመጨረስ የተስማማን በመሆኑ መድን ሰጪው በፍርድ ቤት ክስ መስርቶ ሊጠይቅ አይችልም በሚል የሚያቀርበው አቤቱታ የህግ መሠረት የሌለው ስለመሆኑ የንግድ ህግ ቁ. 683(1) Download Cassation Decision
-
40336 contract law/ contract of rent/ contract for indefinite period of time
ላልተወሰነ ጊዜ እንደተደረገ የሚቆጠር የኪራይ ውል አከራይ የሆነ ወገን ለተከራይ ማስታወቂያ በመስጠት ምክንያቱን መግለፅ ሳያስፈልገው የኪራይ ውሉን ሊያቋርጥ ስለመቻሉ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2966(1) Download Cassation Decision
-
40418 law of succession/ partition of succession/ period of limitation
የውርስ ሀብትድርሻ ክፍፍል ጥያቄ በይርጋ የሚታገድበት አግባብ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1080(3) Download Cassation Decision
-
40624 family law/ filliation/ paternity/ contestation of paternity
ፀንቶ ባለ ጋብቻ ውስጥ የተወለደ ልጅ አባት በጋብቻ ውስጥ ባል የሆነው ወገን ስለመሆኑና የዚህን ሰው አባትነት ለመቃወም የሚቻልበት አግባብ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 144 126 167 168 173 Download Cassation Decision
-
40947 contract law/ administrative contract/ tender bid/
ለጨረታ ማስከበሪያ በሚል የሚያዝ ገንዘብ ጨረታውን ባዘጋጀው አካል ሊወሰድ የሚችለው ተወዳዳሪው ጨረታውን ባሸነፈው መጠን ሆኖ በጨረታው መሠረት ውል ለመፈፀም ፈቃደኛ ያልሆነ እንደሆነ ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
41248 criminal law/ pardon/ criminal record
በወንጀል ጉዳይ ክስ ቀርቦ የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሣኔ ከተሰጠ በኋላ ወንጀለኛው በይቅርታ የተለቀቀ መሆኑ አስቀድሞ የተሰጠውን የጥፋተኝነት ውሣኔ እንዳልነበረ የሚያስቆጥር (በሪከርድነት እንዳይያዝ የሚያደረግ) ስላለመሆኑ የወንጀል ህግ ቁጥር Download Cassation Decision
-
41857 law of succession/ sale of property of inheritance/
Download Cassation Decision የጋራ የሆነን የውርስ ሀብት ከፍቃዱ ውጪ እንዲሸጥ የተደረገበት ወራሽ ከሽያጩ ዋጋ ድርሻውን ለማግኘት መብት ያለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1266 1ዐ6ዐ(1)
-
41893 contract law/ donation/ interpretation
የስጦታ ውል ሊተረጐም የሚገባው በውሉ ውስጥ የሚገኝን አንድ ሃረግ ነጥሎ በማውጣት ሳይሆን የውሉን አጠቃላይ ይዘት በመመልከት ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
42239 civil procedure/ constitution/ power of cassation/ power of federal supreme court/ agreement for arbitration
የሕግ ክርክሮችን በሰበር ማየት /ማስተናገድ/ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግስት ለፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የተሰጠ ስልጣን (power) ስለመሆኑ በግልግል ዳኝነት (arbitration) የታየ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ተዋዋይ ወገኖች የይግባኝ መብትን ለማስቀረት የሚያደርጉት ስምምነት ጉዳዩን በሰበር ችሎት ከመታየት የማያግድ ስለመሆኑ (ከዚሀ ቀደም በሰበር ችሎት የተሰጠው የሕግ ትርጉም የተለወጠ ስለመሆኑ፡፡) የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 80/3 (ሀ), አዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2 (4), አዋጅ ቁጥር 25/88, የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 350(2) 351 እና 356 Download Cassation Decision
-
42346 contract law/ donation/ period of limitation
የስጦታ ውል ገደብ ያለበት ወይም ግዴታ የተጣለበት እንደሆነ በውሉ ውስጥ የተመለከተው ግዴታ አልተፈፀመም በሚል ፈራሽ ሊሆን የሚችል ስለመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ. 244(1) ላይ የተመለከተው የይርጋ ድንጋጌ በስጦታ ውል ውስጥ የተመለከተ ግዴታ አልተፈፀመም በሚል ውሉ እንዲፈርስ ሲጠየቅ ተፈፃሚነት የሌለው ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
42482 law of succession/ will/ homologation of will/ ownership
ኑዛዜ በፍ/ቤት መፅደቁ በንብረት ላይ ያለ የባለቤትነት መብትን የሚያረጋግጥ ስላለመሆኑ Download Cassation Decision
-
42546 law of succession/ disinhersion
በተዘዋዋሪ መንገድ ተወላጅን ከውርስ ያለ በቂ ምክንያት መንቀል የማይቻል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 938,842,915 Download Cassation Decision
-
42569 family law/ filiation/ paternity
ልጅነት ሊረጋገጥ የሚችልበት አግባብ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 156 168 158 169 Download Cassation Decision
-
42648 family law/ filiation/ paternity
ልጅነትን በማረጋገጥ በፍ/ቤት የሚሰጥ ውሣኔ የህግ ግምት የሚፈጥር እንጂ አስገዳጅነት ያለው እና የመጨረሻ ማስረጃ ተደርጐ መወሰድ የሌለበት ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 154 155 156 Download Cassation Decision
-
42682 family law/ filiation/ patenity/ declaration of paternity by court
አባትነት በፍርድ ውሣኔ ሊታወቅ የሚችልበት አግባብ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 43 Download Cassation Decision
-
42682 family law/ filiation/ paternity
አባትነት በፍርድ ውሣኔ ሊታወቅ የሚችልበት አግባብ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 43 Download Cassation Decision
-
42691 contract law/ donation/ period of limitation
የስጦታ ውል ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ በሚቆጠሩ 1ዐ (አስር) ዓመታት ውስጥ ለአፈፃፀም ያልቀረበ እንደሆነ በይርጋ የሚታገድ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1676(1) 1845 Download Cassation Decision
-
42700 Contract law/ civil cases/ period of limitation/ calculation of period of limitation
የእቁብ ገንዘብ ይከፈለኝ ጥያቄ በይርጋ ደንብ የሚገዛ እንጂ በፍ/ብ/ህ/ቁ 2024 ሥር በተመለከተው የህሊና ግምት የሚሸፈን ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2024 Download Cassation Decision
-
42766 family law/ private property/ contract of marriage
ከጋብቻ በፊት የግል የነበረ ንብረት በተጋቢዎች የጋብቻ ውል መነሻነት የጋራ ሊሆን የሚችል ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
42861 property law/ possession/ possessory action
በሃይል ቤቴ ተይዞብኛል እንዲለቀቅልኝ በሚል የሚቀርብ አቤቱታ የሁከት ይወገድልኝ ክስ ነው ሊባል የሚችል ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1206,1149 Download Cassation Decision
-
42866 tax law/ refund
በብልጫ የተከፈለ የቀረጥ ገንዘብ ለባለገንዘቡ ሊመለስ የሚችልበት አግባብ አዋጅ ቁ. 6ዐ/89 አንቀፅ 53(1) 55 Download Cassation Decision
-
42897 contract law/ interpretation of contract
ውል በተዋዋይ ወገኖች መካከል ሊኖር የሚገባውን የቅንነትና የመተማመን ግንኙነት መሠረት በማድረግና ጉዳዮቹ ውስጥ ያለውን ልማዳዊ ሥርዓት በመከተል በቅን ልቦና ሊተረጐም የሚገባ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1732(1) Download Cassation Decision
-
42928 private international law/ judicial jurisdiction/ foreign company
በውጪ አገር ሕግ መሰረት የተቋቋመና በኢትዮጵያ ውስጥ ያልተመዘገበ የንግድ ድርጅት ከውል ውጪ በሆነ ግንኙነት በኢትዮጵያ ፍ/ቤት ቀርቦ ሊዳኝ የሚችል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 27(1), አዋጅ 25/88 አንቀጽ 11(2)(ሀ) Download Cassation Decision
-
42962 extra contractual liability/ damage/ no income/ equity
ከውል ውጪ በሆነ ግንኙነት ጉዳት የደረሰበት ሰው ጉዳቱ ከመድረሱ በፊት ገቢ ያልነበረው መሆኑ በርትዕ ሊከፈለው የሚገባውን ካሣ የሚያስቀር ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 21ዐ2 Download Cassation Decision
-
43069 law of succession/ will/ universal legatee/ disinhersion/
ጠቅላላ የኑዛዜ ወራሽ የሆነ ሰው እና ከህግ ውጪ ከውርስ የተነቀለ ያለኑዛዜ ወራሽ የውርስ ሃብትን ሊከፋፈሉ የሚችሉበት አግባብ የፍ/ብ/ህ/ቁ 939(3) 850 911(1) 912(1) Download Cassation Decision
-
43081 property law/ possession/ possessory action
በአንድ ቤት ውስጥ ሲኖር ያልነበረ ወይም ቤቱን በእጁ አድርጐ ሲያዝበት ያልነበረ ሰው የሚያነሣው የሁከት ይወገድልኝ ክስ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1149 Download Cassation Decision
-
43501 criminal law/ homicide/ self defense
ህጋዊ መካላከልን ከመጠን በማሳለፍ የተፈፀመ የሰው መግደል ተግባር በወንጀል ህግ ቁጥር 541(ሀ) የሚያስጠይቅ ስለመሆኑ የወንጀል ህግ ቁ. 54ዐ 541 Download Cassation Decision
-
43600 property law/ immovable property/ ownership
የማይንቀሳቀስ ንብረትን አስመልክቶ የሚቀርብ የመፋለም ክስ በይርጋ ቀሪ ነው (ቀሪ ሆኗል) ሊባል የሚችል ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ 1677 1845 1206 1188-1192 Download Cassation Decision
-
43636 contract law/ contract of sale/ cancellation of contract/ specific performance/ period of limitation
p>ከሽያጭ ውል ጋር በተገናኘ ሻጭ የሚያቀርበው የውል ይፍረስልኝ ክስ ገዥ ውል እንዲፈፀምልኝ በሚል ሊያቀርብ የሚችለው አቤቱታ ላይ የሚቆጠረውን የይርጋ ጊዜ የሚያቋርጥ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1845 1851 Download Cassation Decision
-
43781 administrative law/ directives/ banking/ national bank of Ethiopia
በአስፈፃሚ አካላት የሚወጡ የተለያዩ መመሪያዎች በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው የወጡ ወይም በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጁ አለመሆናቸው ህጋዊ ውጤት እንዳይኖራቸው የሚከለክል ስላለመሆኑ አዋጅን መሠረት በማድረግ የወጡ መመሪያዎችን የሚፃረር ድርጊት መፈፀም በኃላፊነት ሊያስጠይቅ የሚችል ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
43825 contract law/ form of contract/ nullity
ተከራካሪ ወገኖች ባላነሱበት ሁኔታ ፍ/ቤት የውል አፃፃፍ ሥርዓትን (ፎርማሊቲን) መሠረት በማድረግ በግራ ቀኝ ወገኖች መካከል የተካሄደን ውል ፈራሽ ነው በሚል የሚሰጠው ውሣኔ ተገቢነት የሌለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1723 1808(2) Download Cassation Decision
-
43843 extra contractual liability/ criminal proceeding/ effect of acquittal on civil suit
በወንጀል ጉዳይ ተከስሶ ጥፋት የሌለበት መሆን በራሱ በተመሳሳይ ጉዳይ በፍትሐብሔር ከቀረበ ክስ ነፃ ለመውጣት እንደ በቂና የመጨረሻ መስፈርት የሚወሰድ ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2149 Download Cassation Decision
-
43881 unlawful enrichment/ damage payment
በሌላ ሰው ድካም ወይም የሌላ ሰው ሃብት በሆነ ነገር በመገልገል በቂ ባልሆነ ምክንያት ጥቅም ያገኘ ሰው አላግባብ ጥቅም ባገኘበት መጠንና ባደረሰው ጉዳት መጠን ኪሣራ ሊከፍል የሚገባ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2162 Download Cassation Decision
-
43888 civil procedure/ execution of judgment/ law of succession/ public auction/ valuation
የውርስ ንብረት በጨረታ እንዲሸጥ ለማድረግ መነሻ ዋጋን ለመወሰን የሚቻልበት አግባብ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1083 1084 Download Cassation Decision
-
43912 civil procedure/ jurisdiction/ federal court jurisdiction/ federal registered companies
በፌዴራል መንግስት የተመዘገበ የንግድ ማህበር (ድርጅት) ጋር በተያያዘ የሚነሣ ክርክርን ለማስተናገድ ስልጣን የተሰጠው ለፌዴራል ፍ/ቤቶች ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 25/88 አንቀፅ 5(6) Download Cassation Decision
-
43992 civil procedure/ splitting of cause of action
ከሳሽ የሆነ ወገን ክስ ለማቅረብ ምክንያት የሆኑትን ሁሉ በአንድ ላይና በአንድ ጊዜ አጠቃሎ ለመክሰስ የሚችል (የሚገባው) የነበረ ቢሆንም ሊጠይቅ ይገባው ከነበረው ቀንሶ ያቀረበው በፍ/ቤት ፈቃድ የሆነ እንደሆነ የቀረው መብት ላይ በድጋሚ ክስ ለመመስረት የሚችል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 216(4) Download Cassation Decision
-
44025 law of succession/ period of limitation
ከውርስ ሃብት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የውርስ ሃብቱን በእጅ አድርጐ በመገልገል ላይ ያለ ተከራካሪ የሆነ ወራሽ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ንብረት በጋራ ይዞ የቆየ ሰው ላይ የሚያነሳው የውርስ ጥያቄ በይርጋ ታግዷል ሊባል የሚችልበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
44101 family law/ adoption/ best interest of the child
የጉዲፈቻ ስምምነት የሕፃናትን ጥቅምት ለማስጠበቅ ሲባል ሊፈርስ የሚችል ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 195(2) Download Cassation Decision
-
44164 banking/ foreclosure/ right of bank
ባንክ በመያዣ መልክ የያዘውን የተበዳሪ ንብረት በአዋጅ ቁ. 97/9ዐ መሠረት በመሸጥ ላይ እያለ በሌላ በኩል ደግሞ በተበዳሪው ላይ በፍ/ቤት ክስ መስርቶ ዕዳው እንዲከፈለው ለመጠየቅ የሚችል ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
44235 criminal law/ constitution/ double jeopardy
በወንጀል ሕግ ቁጥር 543 እና 567 መሰረት አንድ ሰው በአንድ ጊዜ ሊጠየቅ ስለሚችልበት አግባብ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 543,567 Download Cassation Decision
-
44237 law of succession/ period of limitation
በውርስ ሕግ ውስጥ የተመለከቱ የይርጋ ድንጋጌዎች ሊተረጐሙ የሚችሉበት አግባብ የወራሽነት መብትን በሕግ በተመለከተ ጊዜ ውስጥ ያረጋገጡ ወራሾች የውርስ ንብረት ክፍፍል ጥያቄን በማናቸውም ጊዜ ማቅረብ የሚችሉ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 996,1000(1)1002,1060,1062 Download Cassation Decision
-
44520 property law/ intellectual property translation
አንድን መፅሐፍ ከተፃፈበት ቋንቋ ወደ ሌላ ቋንቋ የተረጐመ ሰው እንደ ድርሰት አመንጪ ተቆጥሮ የሞራልና የቁሣዊ ጉዳት ሊወሰንለት ስለመቻሉ አዋጅ ቁ.41ዐ/96 አንቀፅ 2(2) 6(1) Download Cassation Decision
-
44561 law of succession/family law/ insurance/ beneficiary of insurance/ right of spouse
ከውርስ ሃብት ክፍፍል ጋር በተያያዘ ተጠቃሚው በኢንሹራንስ ውል ላይ ባልተገለፀበት ጊዜ የሟች ባል ወይም ሚስት የኢንሹራንስ ገንዘቡን ከወራሾች ጋር ሊካፈሉ የሚችሉበት አግባብ የንግድ ህግ ቁጥር 705 701(1)(ሀ) የፍ/ብ/ህ/ቁ. 827 Download Cassation Decision
-
44588 labor dispute/ contract law/ liability of worker
በአሰሪና ሠራተኛ ክርክር ችሎት ሠራተኛው የፈፀመው ድርጊት ከሥራ ለማሰናበት በቂ አይደለም ተብሎ መወሰኑ አሰሪው በሠራተኛው ላይ በፍ/ብሔር ጉዳይ ሊያቀርብ የሚችለውን ክስ የሚያስቀር የመጨረሻ ፍርድ /ውሣኔ/ ስላለመሆኑ Download Cassation Decision
-
44612 family law/ filiation/ paternity
አባትነት በህግ አግባብ ሊታወቅ የሚችልባቸው ሁኔታዎች የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 126 1(1) (2),128(1) 130(2) 125 106(1), የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ-መንግስት አንቀፅ 35(2) Download Cassation Decision
-
44691 contract law/ contract of loan/ presumption of payment/ admission
አንድ ሰው ብድሩን አለመክፈሉን አምኖ በሚከራከርበት ሁኔታ የፍ/ብሔር ህግ ቁጥር 2024(ረ) ተፈፃሚነት የማይኖረው ስለመሆኑ 2024(ረ) ዋና ብድርን ሣይሆን ለብድር የሚከፈል ወለድን የሚመለከት ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
44800 contract law/ mortgage/ registration of mortgage/ validity
በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የመያዣ መብት ውጤት የሚኖረው ከተፃፈበት ቀን ጀምሮ እስከ አሥር ዓመት ድረስ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 3058 Download Cassation Decision
-
44862 criminal law/ custom duty law/ custom law violations/ contraband
የጉምሩክ አዋጅን በመተላለፍ ከሚፈፀም የወንጀል ድርጊት ጋር በተያያዘ የኮንትሮባንድ ተግባር ሃይልን በመጠቀም ወይም ከሌሎች ጋር በማበር የተፈፀመ እንደሆነ አዋጅ ቁ. 6ዐ/89 ተፈፃሚ ሊሆን የሚችል ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
45161 property law/ government owned houses/ expropriation/ jurisdiction
ለረጅም ጊዜ በመንግስት ቁጥጥር ሥር የነበረ ቤትን ይለቀቅልኝ በሚል አቤቱታ የሚያቀርብ ወገን ቤቱ በአዋጅ ቁጥር 47/67 የተፈቀደለት ስለመሆኑ ወይንም ከአዋጅ ውጪ ተወስዶብኛል የሚል ከሆነም ለሚመለከተው አካል ጥያቄውን አቅርቦ ውሳኔ አግኝቶ ባለመብትነቱን ሳያረጋግጥ የሚያቀርበው ክስ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 47/67 Download Cassation Decision
-
45202 family law/ debt of spouses/ nullity of loan contract/
በትዳር ወቅት የተወሰደ ብድር የአንደኛው ተጋቢ ፈቃድ የሌለበት ቢሆንም ፈቃዱን ያልሰጠው ተጋቢ የብድር ስምምነቱ እንዲፈርስ ያላደረገ እንደሆነ ወይም ደግሞ ለትዳር ጥቅም አለመዋሉን ማስረዳት ያልቻለ ከሆነ ለትዳር ጥቅም እንደዋለ የህግ ግምት የሚወሰድ ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 68(መ) Download Cassation Decision
-
45370 law of succession/ certificate of heir/ transfer of property
በተጭበረበረ መንገድ ወራሽነትን አሳውጆ የውርስ ንብረት አካል የሆነን ቤት ስመ ሃብት ወደ ራሱ አዙሮ የሚገኝ ሰው ጋር የሽያጭ ውል በተደረገ ጊዜ የሸያጭ ውሉ እንዲፈርስ በሚል ትክክለኛ ወራሾች የሚያቀርቡት ጥያቄ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ የፍብ/ህ/ቁ. 2882 2884 997 Download Cassation Decision
-
45422 contract law/ antichresis/ mortgage/ nullity
የወለድ አግድ ውል ህጋዊ ነው ሊባል የሚችለው የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ መቋቋምን የሚመለከቱ ድንጋጌዎችን በመከተል የተደረገ እንደሆነ ስለመሆኑና በዚህ መሰረት ያልተደረገ መሆኑ ውሉን ፈራሽ ሊያደርገው የሚችል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 3118,3045,3052 Download Cassation Decision
-
45545 contract law/ contract of sale/ price of sale/ evidence law/ delivery
ከእጅ በእጅ ሽያጭ ጋር በተያያዘ ገዢ የሸያጩን ዋጋ የከፈለበትን ደረሰኝ ይዞ መገኘቱ የገዛውን ንብረት እንደተረከበ የሚያሳይ የመጨረሻ (conclusive) ማስረጃ ነው ሊባል የማይቻል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2266 2278(1) እና (2) Download Cassation Decision
-
45559 contract law/ interest/ power of court
ፍ/ቤት ተከራካሪ ወገኖች ወለድን አስመልክቶ በውላቸው ካመለከቱት ሃሳብ ውጪ የራሱን ስሌት መሠረት በማድረግ ውሣኔ መስጠት ስላለመቻሉ የፍ/ብ/ህ/ቁ/. 1731 2478 Download Cassation Decision
-
45572 criminal law/ criminal procedure/ absence of witnesses/ withdrawal of charges/ period of limitation
በወንጀል ጉዳይ የቀረበ ክስ በዐቃቤ ህግ ምስክሮች ተሟልቶ አለመቅረብ የከሳሽ መዝገቡን የማንቀሳቀስ መብት ተጠብቆ መዘጋት በቀረበው ወንጀል ላይ ተፈፃሚ የሚሆነውን የይርጋ ጊዜ ተግባራዊ ከመሆን የሚያግደው ስላለመሆኑ Download Cassation Decision
-
45587 law of succession/ representation of heirs
የምትክ ወራሽነት ተጠቃሚዎችን ስለመለየት የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 842,843,844(3) Download Cassation Decision
-
45735 extra contractual liability/ vicarious liability/ liability of employer
ለተወሰነ ጊዜም ሆነ ላልተወሰነ ጊዜ የተቀጠረ ሠራተኛ ከውል ውጭ በሆነ ግንኙነት በሥራ ወቅት በሌሎች ሰዎች ላይ ለሚያደርሰው ጉዳት አሠሪ ኃላፊነት ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2130 2131 2132 Download Cassation Decision
-
45806 civil procedure/ jurisdiction/ Sharia courts/ intervention by third party
በሸሪአ ፍ/ቤት በሚካሄድ ክርክር ላይ ጣልቃ ገብቶ መከራከር በፍ/ቤቱ ለመዳኘት ስምምነትን እንደመስጠት የሚያስቆጥር ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 188(92) አንቀፅ 5(1) Download Cassation Decision
-
45819 family law/ maintenance obligation/ maintenance of child
የልጆች ቀለብ አከፋፈል ሁኔታ ጋር በተያያዘ ክፍያ ተግባራዊ ሊደረግ የሚችልበት አግባብ Download Cassation Decision
-
45882 tax law/ power of custom and revenue authority/ unpaid tax
የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ያልተከፈለን ቀሪ ቀረጥ ሊያስከፍል የሚችልበት አግባብ አዋጅ ቁ.6ዐ/89 አንቀፅ 57(1) 48 53(1) Download Cassation Decision
-
45927 criminal law/ homicide/ aggravated homicide
በግድያ ወንጀል የተከሰሰ ሰው የፈፀመው የግድያ ድርጊት በወንጀል ሕግ አንቀጽ 539(1) (ሀ) ሥር የሚያስጠይቅ ነው ሊባል የሚችልበት አግባብ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 539(1)(ሀ),84,86 Download Cassation Decision
-
46019 contract law/ Ikub/ presumption of payment/ period of limitation
የእቁብ ገንዘብ ይከፈለኝ ጥያቄ በይርጋ ደንብ የሚገዛ እንጂ በፍ/ብ/ህ/ቁ 2024 ሥር በተመለከተው የህሊና ግምት የሚሸፈን ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2024 Download Cassation Decision
-
46052 contract law/ land grant/ land lease/ nonperformance of contract
መዋዕለ ነዋይን በማፍሰስ ግንባታን ለማካሄድ የከተማ ቦታን ከመንግስት ተረክቦ ግንባታን በተገቢው ጊዜ ለማጠናቀቅ አለመቻል ሊያስከትል የሚችለው ውጤት የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ ደንብ ቁ. 41/97 አንቀፅ 8(3) የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ አዋጅ ቁ. 51/94 Download Cassation Decision
-
46143 civil procedure/ execution of judgment/ attachment/ ownership
አንድ ንብረት በፍርድ አፈፃፀም የተነሣ ሊያዝ የሚችለው በተሰጠው ፍርድ ባለዕዳ የሆነው ወገን ሃብት መሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
46189 criminal law/ fraudulent practice
አንድ ሰው የማታለል ተግባር ፈፅሟል በሚል በወንጀል ሊጠየቅ የሚችልበት አግባብ የወንጀል ህግ ቁጥር 692(1) Download Cassation Decision
-
46220 Administrative law/ land lease/ jurisdiction/
የከተማ ቦታ ያለአግባብ ተወስዶብኝ በሊዝ ለሌላ ተሰጥቷል በሚል የሚቀርብ አቤቱታ የቦታውን መውሰድ ውሣኔ ለሰጠው አካል በቅድሚያ መቅረብ ያለበት ስለመሆኑና በሚሰጠው ውሳኔ ቅሬታ ያለው ወገን ለቦታ ማስለቀቅ ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ማቅረብ ያለበትና ይኼው አካል የሚሰጠው ውሣኔ የመጨረሻ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 272/1994 Download Cassation Decision
-
46358 commercial law/ company law/ joint venture
የእሽሙር የሽርክና ማህበር ተመስርቷል ለማለት የሚቻልበት አግባብ በግለሰቦች መካከል በውል የሚፈጠር የሽርክና ማህበር የንግድ ሕግ በሚያዘው መሰረት አይነቱ ተለይቶ ተመዝግቦ የማይገኝ በሆነ ጊዜ እንደ የእሽሙር የሸርክና ማህበር ተደርጐ ሊወሰድ የሚችል ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
46394 contract law/ contract of rent/ termination of contract of rent/ government owned houses
ከቤት ኪራይ ውል ጋር በተያያዘ የኪራይ ውልን ለማቋረጥ በቂ ናቸው ሊባሉ የሚችሉ ተከራይ የሚፈፅማቸው የግንባታ አይነቶች የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2953 2954 1732 Download Cassation Decision
-
46490 family law/ minor/ power of guardian/ sale of property
ሞግዚት የሆነ ሰው በሞግዚትነት የሚያስተዳድራቸውን ልጆች ሀብት የሆነን ንብረት ለልጆቹ መልካም አስተዳደግ ሲል ሊሸጠው የሚችል ስለመሆኑ የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ ቤተሰብ ህግ አንቀፅ 292 Download Cassation Decision
-
46527 law of succession/ claim by heirs/ transfer of ownership/ property law
የውርስ ንብረት በሆነ ቤት ላይ ድርሻ አለን የሚሉ ወገኖች ንብረቱን ህጋዊ የሆነ የባለቤትነት ማረጋገጫ ይዞ ከነበረ ሰው በመግዛት ስመ ሀብቱን ወደራሱ ስም አዛውሮ የሚገኝን ሰው ለመጠየቅ የማይችሉ ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
46613 family law/ irregular union/ proof of relationship
በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል እንደ ባልና ሚስት አብሮ የመኖር ሁኔታ ስለመኖሩ ለማስረዳት የሚችሉት በግንኙነቱ ውስጥ ያሉት ሰዎች ብቻ ናቸው ለማለት የሚያስችል የሕግ መሰረት የሌለ ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 98,99,106 Download Cassation Decision
-
46778 insurance/ period of limitation
የኢንሹራንስ ውልን መሠረት በማድረግ የሚቀርብ ክስ በሁለት ዓመት ይርጋ የሚታገድ ስለመሆኑ የንግድ ህግ ቁ. 674(1) 754(1) Download Cassation Decision
-
46808 insurance / liability of insurer
የመድን ሰጭ ኃላፊነት በመድን ውሉ ላይ ከተመለከተው የገንዘብ መጠን ሊበልጥ የማይችል ስለመሆኑ የንግድ ህግ ቁ. 665(2) Download Cassation Decision
-
46947 contract law/ contract of rent/ property law/ immovable property/ ownership
የኪራይ ውልን መሠረት በማድረግ ቤትን የያዘ ወገን የኪራይ ውሉን በቅድሚያ ሣያስፈርስ የባለቤትነት ጥያቄን መሠረት በማድረግ በኪራይ ውሉ አልገደድም በሚል የሚያቀርበው አቤቱታ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
47134 civil procedure/ jurisdiction/ Dire Dawa city court/ ownership
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፍ/ቤቶች በከተማው የሚገኝ ቤት ባለቤትነቱ የማን ነው ከሚል ጉዳይ ጋር ተያይዞ የሚነሣ ክርክርን ለማየት ስልጣን የሌላቸው ስለመሆኑ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁ. 416/19 አንቀፅ 33 Download Cassation Decision
-
47378 law of succession/ law of property/ ownership/ transfer
ከውርስ ጋር በተያያዘ በቤት ላይ ህጋዊ መብት የሌለው ሰው ሽያጭ አከናውኖ ሲገኝ ትክክለኛው ባለሃብት መብቱን ሊጠይቅ የሚችለው ተገቢውን ጥንቃቄ አድርጐ የገዛውን ገዥ ሣይሆን ሻጩን ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 997 2882 2884 1ዐ6ዐ(1) 1266 Download Cassation Decision
-
47487 law of succession/ will/ interpretation
ኑዛዜ ሊተረጐም የሚገባው ቃላቶቹና መልዕክቱ ግልፅ ሣይሆን ሲቀር ብቻ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ 810(2) Download Cassation Decision
-
47622 law of succession/ will/ reserved share of heirs/
ወራሽ የሆነ ወገን በውርስ ሃብት ክፍፍል ድርሻው ላይ ከሩብ የበለጠ ጉዳት የደረሰበት መሆኑን በመግለፅ አውራሽ ባደረገው ኑዛዜ መሠረት ክፍፍል እንዳይፈፀም መጠየቅ የሚችል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1123(1) Download Cassation Decision
-
47800 contract law/ contract of sale of immovable/ defect in object/ reinstatement of parties
ከሽያጭ ጋር በተያያዘ ውል ሲመሰረት ጉድለት የነበረበት መሆኑ ቢረጋገጥም ከውሉ መመስረት በኋላ በተሸጠው ንብረት ላይ ተዋዋይ ወገኖች ተጨማሪ ግንባታ ያካሄዱና ወደ ነበሩበት ለመመለስ አዳጋች ሁኔታ ያለ መሆኑ ከታመነ ውሉ ሊፀና የሚገባው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1817(1) Download Cassation Decision
-
47957 law of succession/ heirs by representation
የምትክ ወራሽነት ተጠቃሚዎችን ስለመለየት የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 842,843,844(3) Download Cassation Decision
-
47971 contract law/ surety/ validity
በፍ/ብሔር ጉዳይ ህጋዊ ጥበቃ ሊደረግለት የሚችል ዋስትና የሚደረግበት አግባብ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1922 Download Cassation Decision
-
48018 civil procedure/ local jurisdiction/ extra contractual liability
በሰዎች ወይም በሚንቀሳቀስ ሀብት ላይ ለደረሰ ጉዳት ካሣ ለማግኘት የሚቀርብ ክስን ለማስተናገድ የግዛት ክልል ሥልጣን ስለሚኖረው ፍ/ቤት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 27 Download Cassation Decision
-
48048 contract law/ contract of bailment/ period of limitation
አንድን ንብረት በአደራ ለማስተደደር (ለመጠበቅ) የተረከበ ወገን አደራ ሰጪው ንብረቱ እንዲመለስ በጠየቀው ጊዜ ወዲያውኑ መመለስ ያለበት ስለመሆኑ ንብረትን በአደራ የሰጠ ወገን ንብረቱ እንዲመለስለት ከመጠየቅ ጋር በተያያዘ በህግ የተቀመጠ የጊዜ ገደብ (ይርጋ)የሌለ ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
48094 contract law/ unlawful object/ nullity/ period of limitation
አንድ ውል ህግን የሚፃረር /የሚቃረን/ ነው በሚል እንዲፈርስ የሚቀርብ ጥያቄ በአሥር ዓመት ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ የሚታገድ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1845 Download Cassation Decision
-
48111 labor dispute/ labor board/ jurisdiction/ collective labor dispute/ promotion
የሥራ መደብ ወይም እድገት ይሰጠኝ በሚል የሚቀርብ አቤቱታ የወል የሥራ ክርክርን የሚመለከት ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
48269 contract law/ agency/ banking/ bank transfer
ባንክ በሐዋላ ለማድረስ የተቀበለውን ገንዘብ ለተገቢው ሰው አልደረሰም በሚል ኃላፊነት አለበት ሊባል የሚችለው ተገቢውን ጥንቃቄ እና የተለመደውን አሰራር ሳይከተል የቀረ እንደሆነ ወይም መጭበርበሩ የተረጋገጠ እንደሆነ ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
48358 contract law/ contract of rent/ turn over tax
ከኪራይ ውል ጋር በተያያዘ ተከራይ የሆነ ወገን የተርን ኦቨር ታክስ የመክፈል ግዴታ በህግ የተጣለበት እንደሆነ አከራይ የሆነው ወገን ይህንኑ ክፍያ ለመፈፀም ይቻል ዘንድ ተከራዩን ለመጠየቅ ስለመቻሉ አዋጅ ቁ. 308/95 አንቀፅ 2(3 5 7 8 9 12),6 Download Cassation Decision
-
48617 criminal law/ criminal procedure/ appeal/ relief regarding sentencing
በሥር ፍ/ቤት የተሰጠ የቅጣት ውሣኔ ላይ አነሰ ወይም በዛ በሚል በግልፅ ይግባኝ ባልተጠየቀበት ሁኔታ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ቅጣትን ከፍ ወይም ዝቅ በማድረግ ውሣኔ ሊሰጥ የማይገባ ስለመሆኑ የወ/መ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ. 195(መ) Download Cassation Decision
-
48621 tax law/ tax appeal commission/ time for appeal
የግብር ይግባኝ ጉባኤ በሚሰጠው ውሳኔ ላይ ይግባኝ ለማቅረብ የተፈቀደው ጊዜና ስሌቱ አዋጅ ቁ. 285/94 አንቀጽ 43(1) Download Cassation Decision
-
48693 criminal law / custom duty law/ custom law violations
የጉምሩክ ሕግን በመተላለፍ ወንጀል ፈፅሟል በሚል የተጠረጠረ ሰው ክስ ሊቀርብበት የሚገባውና ጉዳዩ መታየት ያለበት በአዲሱ የወንጀል ህግ ሣይሆን በጉምሩክ አዋጆች መሠረት በማድረግ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 60/89 Download Cassation Decision
-
48698 insurance/ insurance coverage
ለአንድ ንብረት መድን የገባ ሰው በንብረቱ ላይ የደረሰው ጉዳት ሙሉ ውድመት ሊባል የሚችል ቢሆንም ካሣ ሊከፈለው የሚችለው ጉዳት በደረሰ ጊዜ ዕቃው ከሚያወጣው ዋጋ ሳይበልጥ ስለመሆኑ የንግድ ህግ ቁ. 678 Download Cassation Decision
-
48699 property law/ immovable property/ title deed/ ownership/ expropriation
የአዋጅ ቁጥር 47/67 በሥራ ላይ ከመዋሉ በፊት የተሰጠን ካርታ መሰረት በማድረግ ክሥ ለመመስረት የሚያስችል መብት ወይም ጥቅም የሌለ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 47/67 Download Cassation Decision
-
48783 property law/ servitutde/ damage and compensation
ከማይንቀሳቀስ ንብረት ጋር በተያያዘ የጉዳት ኪሣራን ጉዳት ለሚደርስበት ወገን በመክፈል የመንገድ መተላለፊያ ( servitude right) መብት ሊከበር የሚችል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1221 Download Cassation Decision
-
48850 criminal law/ value added tax (VAT)/ criminal liability of manager/ criminal liability of entity
የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ አፈፃፀም ጋር በተያያዘ የንግድ ድርጅት ሠራተኛ፣ ሥራ አስኪያጅ እንዲሁም ድርጅቱ በወንጀል ጉዳይ ክስ ቀርቦባቸው ኃላፊ ሊሆኑ የሚችሉበት አግባብ አዋጅ ቁ. 285/94 አንቀፅ 56(1)(3) አዋጅ ቁ. 6ዐ9/2ዐዐ1 አንቀፅ 5ዐ(ለ)(1) 22(1) የወንጀል ህግ አንቀፅ 23(3) 34(1) Download Cassation Decision
-
48967 contract law/ telephone contract/ expert testimony
የስልክ አገልግሎት ከማግኘት ጋር በተያያዘ በአገልግሎት የክፍያ መጠን ላይ በአገልግሎት ሰጪውና በአገልግሎት ተቀባዩ መካከል አለመግባባት በተፈጠረ ጊዜ የተጠየቀው የአገልግሎት ሒሳብ በእርግጥም ስልኩን በይዞታው ስር አድርጐ የሚጠቀምበት ወገን በተገለገለው መጠን የተመዘገበ ስለመሆኑ በባለሙያ እንዲጣራ በማድረግ እልባት መስጠት የሚያስፈልግ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1732 Download Cassation Decision
-
49152 labor dispute/ jurisdiction/ labor board/ collective labor dispute/
በአሰሪና ሰራተኛ ሕጉ እጅግ አስፈላጊ የህዝብ አገልግሎት ድርጅቶች ተብለው ከተዘረዘሩት ተቋማት ጋር ተያይዞ የሚቀርብ የሠራተኞች ደመወዝና ጥቅማጥቅም ጥያቄን የያዘ የውል የሥራ ክርክር ካልሆነ በስተቀር የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ለማስተናገድ የሥረ- ነገር ስልጣን የሌለው ስለመሆኑ መሰል ጉዳዬችን ለማየት በህግ ስልጣን የተሰጠው በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚሰየም ቦርድ ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
49326 contract law/ contract of sale/ form of contract/ reinstatement of parties
የሽያጭ ውል በህግ የተቀመጠውን የአፃፃፍ ሥርዓት ባለመከተሉ ፈራሽ ሲሆን ንብረት የመመለስ ግዴታ ያለበት ወገን ንብረቱን ለውጦ ወይም በንብረቱ ላይ ወጪ አውጥቶ ከሆነ ባወጣው ወጪ መጠን ሊጠይቅ የሚችል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1818 Download Cassation Decision
-
49453 contract law/ scholarship/ labor dispute/ damage
በአሰሪና ሠራተኛ መካከል በተደረገ ስምምነት መሠረት አሰሪው ሠራተኛው በውጭ አገር ትምህርቱን እንዲከታተል ለማስቻል የሚያስፈልጉ ወጭዎችን ደመወዝን ጨምሮ ለመክፈል ሠራተኛው ደግሞ ትምህርቱን ሲያጠናቅቅ አሠሪውን ለማገልገል ውል ገብቶ ሠራተኛው ግዴታውን ለመፈፀም ያልቻለ በሆነ ጊዜ አሠሪው የጉዳት ኪሣራ የመጠየቅ / የመከፈል/ መብት ያለው ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
49851 law of succession/ will/ document authentication office
ውል ለማዋዋል ስልጣን ባለው ባለስልጣን ፊት የሚደረግ ኑዛዜ በህግ የተቀመጠውን ፎርማሊቲ አሟልቷል ለማለት የሚቻልበት አግባብ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 882 Download Cassation Decision
-
49889 extra contractual liability/ liability of state/ revenue and custom authority/ damage
የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በሕግ የተሰጠውን ስልጣንና ተግባሩን በተገቢው ጊዜና ሁኔታ ባለማከናወኑ በሌላ ሰው ንብረት ላይ ለሚያደርሰው ጉዳት በኃላፊነት ሊጠየቅ የሚችል ስለመሆኑ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በሕግ በተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት መሰረት ግዴታውን ለመወጣት ሲንቀሳቀስ በቁጥጥሩ ሥር አድርጐት ከሚቆየው ንብረት ጋር በተያያዘ የተቋረጠ ጥቅም ወይም የጉዳት ካሣ ሊከፍል የሚችልበት የሕግ መሰረት የሌለ ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
49900 contract law/ donation/ fraud/ duress/ nullity
አንድ የስጦታ ውል በኃይል ወይም በተንኮል ተግባር ተደርጓል በሚል ስለሚፈርስበት አግባብ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2442(3),1698,1699,1704,1706 Download Cassation Decision
-
50225 extra contractual liability/ fatal accident/ damage/ age of claimant
ከውል ውጪ በሆነ ግንኙነት ህይወቱ ካለፈ ሰው ጋር በተገናኘ የሚከፈለው የጉዳት ካሣ መብቱን የሚጠይቀው ሰው ዕድሜ ከአስራ ስምንት ዓመት በላይ በመሆኑ የተነሣ ብቻ ካሳው ሊከፈለው አይገባም ለማለት የሚያስችል የሕግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2095/1/ Download Cassation Decision
-
50440 contract law/ agency/ conflict of interest
ወኪል የሆነ ሰው የውክልና ሥራውን በሚሰራበት ጊዜ የራሱን ወይም ከራሱ ጋር ቤተሰባዊ ወይም ሌላ ጥብቅ ግንኙነትና ትስስር ያለው ሰውና የወካዩ ጥቅም ሊጋጭ የሚችልበት አጋጣሚ እንዳይፈጠር መከላከል ያለበት ወይም በተፈጠረ ጊዜ አስቀድሞ ለወካዩ ማሳወቅ ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2187(1)2198 2208 2209 Download Cassation Decision
-
50836 law of succession/ will/ certificate of inheritance/ liquidation of succession
በፍ/ቤት የተሰጠ የኑዛዜ ወራሽነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የውርስ ሃብት ማጣራት ሳይደረግ የተሰጠ ነው በሚል ምክንያት ብቻ ሊሰረዝ የሚችልበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
50901 law of succession/ will/ heir by law/ reserved share/
በኑዛዜ የውርስ ሀብት ክፍፍል መደረግ ጋር በተያያዘ ወራሽ የሆነ ወገን ሊደርሰው ከሚገባው የውርስ ሀብት መጠን ከአንድ አራተኛ በታች እንዲደርሰው የተደረገ መሆኑ ካልተረጋገጠ በስተቀር ኑዛዜውን እንዲፀና በማድረግ የተናዛዡን ፍላጐት ማክበርና መጠበቅ የሚያስፈልግ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 910 913 1123(1) Download Cassation Decision
-
51295 family law/ common property/ sale of immovable property/ nullity/ period of limitation
በባልና ሚስት የጋራ ንብረት ላይ የተደረገ የሽያጭ ውል በሕጉ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ አለመፍረሱ ስለሚያስከትለው ውጤት Download Cassation Decision
-
51706 criminal law/ criminal procedure/ evidence law/ burden of proof
ከወንጀል ጉዳይ ጋር በተያያዘ ተከራካሪ ወገኖች የማስረዳት ሸክማቸውን ተወጥተዋል ለማለት የሚቻልበት አግባብ በፍ/ቤት ፊት ቃለ- መሃላ በመፈፀም የተሰጠ የምስክር ቃል እውነት ነው በሚል የሚወሰደው ግምት ሊፈርስ የሚችል ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
51866 civil procedure/ relief requested
በተከራካሪ ወገኖች ዳኝነት የተጠየቀበትን ጉዳይ ፍ/ቤቶች በግልፅ በመቀበል ወይም ባለመቀበል ወሣኔ ሊሰጡበት የሚገባ ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
51893 family law/ property law/ common property/ condominium houses
ከኮንዶሚኒየም ቤት ባለቤትነት ጋር በተያያዘ ከጋብቻ በፊት በአንደኛ ተጋቢ በተደረገ ምዝገባ የተነሣ የቤት ዕጣው የወጣው ብሎም የቤት ሽያጭ ውል የተደረገው በጋብቻ ወቅት መሆኑ በተረጋገጠ ጊዜ ለቤቱ መገኘት ምክንያት የሆነው ተጋቢ ቤቱ የግል መሆን አለበት በሚል የሚያቀርበው ክርክር ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 62(2) Download Cassation Decision
-
52041 civil procedure/Material jurisdiction/ social courts/
የክርክሩ የገንዘብ መጠን ከ5000 ብር በታች የሆነ ጉዳይን በሙሉ ተቀብሎ ለማስተናገድ የአዲስ አበባ ከተማ ማህበራዊ ፍ/ቤቶች በሕግ ስልጣን ያልተሰጣቸው ስለመሆኑ የሥረ-ነገር ሥልጣን በሕግ ባልተሰጠው የዳኝነት አካል (ፍ/ቤት) የተሰጠ ፍርድ የማይፀና ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
52600 labor dispute/ promotion/ jurisdiction/ individual labor dispute/ collective labor dispute
በውድድር አሸንፌ ያገኘሁትን የሥራ መደብ እድገት ይሰጠኝ በሚል የሚቀርብ የሥራ ክርክር የግል የሥራ ክርክር በመሆኑ በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ቦርድ የሚታይ ሰላለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 Download Cassation Decision
-
52691 family law/ adoption/ nullity of adoption contract
የጉዲፈቻ ውል እንዲፈርስ ሊደረግ የሚችልበት አግባብ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 195(1) (2) Download Cassation Decision
-
52910 insurance/ renewal of insurance contract
አስቀድሞ የተደረገ ነገር ግን ባለመታደሱ ምክንያት የተቋረጠ (ያበቃ)ን የመድን ውል መሠረት በማድረግ ሊጠየቅ የሚችል የጉዳት ካሣ ስላለመኖሩ የንግድ ህግ ቁ. 666(2) እና (3) Download Cassation Decision
-
53279 law of succession/ will/ burden of proof
ኑዛዜ መኖሩን የማስረዳት ሸክም (ግዴታ) የተጠቃሚዎች ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 896,897 Download Cassation Decision
-
53459 criminal procedure/ bail bond
ለዋስትና የተያዘ ገንዘብን የአስያዡን ማንነትን ማረጋገጥ እስከተቻለ ድረስ ገንዘቡን ያስያዘበት ደረሰኝ ኮፒን ያቀረበ እንኳን ቢሆን የተያዘው ገንዘብ መመለስ ያለበት ስለመሆኑ Download Cassation Decision
-
53612 criminal law/ mitigating circumstances
ከወንጀል ጉዳይ ጋር በተያያዘ ጥፋተኛ የተባለ ተከሳሽ የዘወትር ፀባይ መልካም የነበረ መሆኑ በተናጠል (በራሱ) ቅጣትን ለማቅለል የሚያስችል ስለመሆኑ የወንጀል ህግ ቁጥር 82(1) (ሀ) Download Cassation Decision
-
54061 criminal law/ tax law/ Value Added Tax (VAT)/criminal liability of manager
የንግድ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ የሆነ ሰው የድርጅቱን አስተዳደራዊ ሥራ ለሌላ ሰው የወከለ መሆኑ ድርጅቱ ያለተጨማሪ እሴት ታክስ ግብይት በመፈፀም ወንጀል ጥፋተኛ በተባለ ጊዜ ከሚቀርብበት የወንጀል ተጠያቂነት ነፃ የማያደርገው ስለመሆኑ Download Cassation Decision