volume 11

volume 11

 • 18495 labor dispute/ death/ severance pay

  ከሥራ ጋር ባልተገናኘ /ተፈጥሮአዊ/ ሞት ምክንያት የሥራ ውል ሲቋረጥ የሥራ ስንብት ክፍያ የማይከፈል ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 20869 labor dispute/ bonus payment/ profit of company

  የቦነስ ክፍያ ለሠራተኛ የሚከፈለው በሥራ ላይ ያለ ሰራተኛ ወደፊት በርትቶ እንዲሰራ ለማበረታታት ብቻ ሳይሆን በሥራ ላይ በነበረበት ወቅት የሰራው ሥራ ለአሰሪው ትርፋማ ውጤት በማስገኘቱ የትርፉ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል ጭምር ስለመሆኑ የቦነስ ክፍያ ተጠቃሚ ለመሆን ሠራተኛው ድርጅቱ /ተቋሙ/ ትርፋማ ውጤት ባስገኘበት ዓመት በሥራ ላይ የነበረና አስተዋጽኦ ያደረገ መሆን ያለበት ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 24643 extra contractual liability/ strict liability/ cars/ transfer of title of automobiles

  መኪና ወይም ባለሞተር ተሽከርካሪ ልዩ የምዝገባና የባለሀብትነት ስም ዝውውር የሚያስፈልገው ግዙፍነት ያለው ተንቀሳቃሽ ንብረት ስለመሆኑ የባለሞተር ተሽከርካሪ ባለቤትነት /ባለሃብትነት/ ወደ ሌላ ሰው ተላልፏል ሊባል የሚችልበት አግባብ መኪኖች እና ባለሞተር ተሽከርካሪዎች ከውል ውጪ በሆነ ግንኙነት ለሚያደርሱት ጉዳት በኃላፊነት ስለሚጠየቀው ወገን የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1186/1/ /2/, 2081/1/, 2082/2/, 2083/1/, 2267/2/, 2324/1/ አዋጅ ቁ. 256/60 አንቀጽ 6 አዋጅ ቁ. 468/97 አንቀጽ 21 ደንብ ቁ. 360/61 አንቀጽ 6 7/1/ /3/, 8, 11/1/ /2/, 42-45 Download Cassation Decision

 • 32282 Document authentication /private international law/ documents of foreign origin

  በውጭ አገር የተደረጉ ሰነዶች (foreign documents) በኢትዮጵያ ውስጥ ህጋዊ ተቀባይነት ሊያገኙ የሚችሉበት አግባብ አዋጅ ቁጥር 334/95 አንቀጽ 26/1/ Download Cassation Decision

 • 38117 extra contractual liability/ bodily injury/ minors/ damage assessment/ equity

  ለአካለ መጠን ያልደረሱ ህፃናት ላይ ከውል ውጪ በሆነ ግንኙነት ጉዳት ሲደርስ የጉዳት ካሣ መከፈል የሚገባው ስለመሆኑና የካሣ አወሳሰኑ ስሌት በገንዘብ ለመተመን የሚያዳግት የአካል ጉዳት በደረሰ ጊዜ ካሣ በርትዕ መወሰን ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2090, 2091, 2092/2/, 2095/2/ Download Cassation Decision

 • 40945 civil procedure/ execution of judgment/ plurality of judgment creditors

  በአንድ የፍርድ ባለዕዳ ላይ ከአንድ በላይ የሆኑ ባለገንዘቦች አፈፃፀም ሊቀጥል የሚችልበት አግባብ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 403, 378 Download Cassation Decision

 • 42824 property law/ sound pollution/ possessory action/business licensing

  የድምጽ ብክለት ተከስቷል ለማለት የሚቻለው የሚሰማው ድምጽ ከመጠን በማለፉ በሌሎች ላይ ሁከት የሚፈጥር መሆኑ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ የድምፅ ብክለት (Nuisance) ተፈጥሮብኛልና እንዲወገድ በሚል የሚቀርብ አቤቱታ በሁለት ዓመት ይርጋ ታግዷል ሊባል የማይችል ስለመሆኑ አንድ ሥራን ለመስራት የንግድ ፍቃድ የሰጠ አካል ሥራው የሚፈጥረው የድምጽ ረብሻ አለ በሚል የንግድ ፈቃዱን የሚሰረዝበት የህግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 43988 family law/ separation/ common property

  ጋብቻ ሳይፈርስ የትዳር ግንኙነቱን ትቶ የሄደ ተጋቢ ጋብቻውን ትቶ በሄደበት ወቅት የተፈራን ንብረት የጋብቻ ውጤት ነው በማለት የክፍያ ጥያቄ ሲያቀርብ በጋብቻ ወቅት የተፈራን ንብረት የጋራ ይሆናል በሚለው የህግ ግምት ተጠቃሚ ሊሆን የማይገባ ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 40/1/ Download Cassation Decision

 • 43996 tax law /custom duties/ contraband/ contraband carrying vehicles

  የጉምሩክ ባለስልጣን ኮንትሮባንድ እንደተፈፀመበት በበቂ ሁኔታ የጠረጠረውን ተሽከርካሪ በቁጥጥሩ ሥር አድርጐ ለሚያደርገው ማጣራት ለባለንብረቱ የተቋረጠ ጥቅም እንዲከፈል የማይጠየቅ ስለመሆኑ ባለስልጣኑ በቁጥጥሩ ሥር የሚያውላቸው ተሽከርካሪዎች የተያዙበትን ጉዳይ ለማጣራት ከሚያስፈልገው ተገቢና ምክንያታዊ ጊዜ በላይ የሆነ እንደሆነ የሚያስጠይቀው ስለመሆኑ በባለስልጣኑ ቁጥጥር ሥር የቆዩ ተሽከርካሪዎችን በተመለከተ የተቋረጠ ገቢ ይከፈለን በሚል አቤቱታ በቀረበ ጊዜ ፍርድ ቤት የተጠየቀውን ገቢ ህጋዊነት እና ትክክለኛነት በማረጋገጥ መወሰን ያለበት ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 44226 administrative law/ banking/ banking regulation/ board of directors

  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተሻሻለ አዲስ የባንክ ስራ ፈቃድና የዳይሬክተሮች እና የዋና ሥራ አስፈፃሚ ሹመትን አስመልክቶ የሚያወጣው መመሪያ ህጋዊ መሰረት ያላቸውና በተግባር ሊውሉ የሚገባ ስለመሆኑ መመሪያ ቁጥር ኤስቢቢ/39/ 2006 አንቀጽ 5.1.4 አንቀጽ 5.1.5 አዋጅ ቁ. 83/89 አዋጅ ቁ. 84/86 Download Cassation Decision

 • 44427 extra contractual liability/ fault/ bank manager

  Download Cassation Decision

 • 44804 cassation procedure/ fact / law/ weighing of evidence

  በአንድ በቀረበ ክርክር ላይ የተሰጠው ውሣኔ የቀረቡትን ማስረጃዎች ይዘት ወይም በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠውን ነጥብ ከሕጉ ጋር በአግባቡ ተዛምዶ አልታየም በሚል የሚቀርብ አቤቱታ የሕግ ነጥብ /ክርክር/ እንጂ የማስረጃ ምዘና ጉዳይ ነው ተብሎ በሰበር ችሎት ሊስተናገድ የሚችል አይደለም ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ የሰበር ችሎት በሥር ፍ/ቤቶች የቀረበን ማስረጃ ክብደትና ተዓማኒነት ለመመርመር በህግ ስልጣን ያልተሰጠው ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 45207 family law/ common property/ improvement on personal property

  ከጋብቻ በፊት በአንደኛው ተጋቢ የተፈራ ቤት በጋብቻ ወቅት እድሳት የተካሄደለት መሆኑ ብቻ ንብረቱን የባልና ሚስቱ የጋራ ሃብት የማያደርገው ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥ. 213/92 አንቀጽ 42/1/, 57 Download Cassation Decision

 • 45905 law of succession/ liquidation of succession/ recording of liquidation report/ civil procedure/ opposition

  የውርስ ሃብት አጣሪ ሪፖርት በፍ/ቤት መጽደቅ ውጤት በፍ/ቤት የፀደቀ የውርስ ሃብት አጣሪ ሪፖርትን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 358 አግባብ ተቃውሞ ሊቀርብበት ይገባል ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 46075 labor dispute/ scope of application of labor proclamation/ clubs

  በአዋጅ በተቋቋመ የት/ት ተቋም ውስጥ በሚገኝና በራሱ ገቢና በጀት የሚተዳደርና ሠራተኞችን ቀጥሮ በሚሠራ ክበብ ውስጥ የሚሠሩ ሠራተኞች ጋር በተያያዘ የሚነሱ ክርክሮች በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ሊስተናገድ የሚገባ ስለመሆኑ እና ተቋሙን ለማቋቋም የወጣው አዋጅ ተፈፃሚ ይሆናል ለማለት የማይችል ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አዋጅ ቁ. 515/96 አዋጅ ቁ. ደንብ ቁጥር 61/96 Download Cassation Decision

 • 46606 family law/ common property/ condominium house

  የኮንዶሚንየም ቤት ለማግኘት የተደረገ ምዝገባ ከጋብቻ በፊት ቢሆንም ዕጣ የወጣው ጋብቻ ፀንቶ ባለበት ጊዜ ከሆነ ተጋቢዎቹ የመካፈል መብት የሚያገኙ ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 46726 law of succession/ liquidation of succession/

  የውርስ ሃብት እንዲጣራ በሚል በንብረቱ ላይ የተሰጠው ትዕዛዝ ከሟች ጋር ህጋዊ ግንኙነት ባልነበረበት ሁኔታ ነው በሚል ክርክር በቀረበ ጊዜ ፍ/ቤቶች ይህንን እንደ ጭብጥ በመያዝ እልባት ሊሰጡበት የሚገባ ስለመሆኑ በዚህ ጉዳይ ላይ ፍ/ቤት የሚሰጠው ብይን ጊዜያዊ አገልግሎት እንዳለው ትዕዛዝ የሚወሰድ ስላለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 47139 property law /

  የማይንቀሳቀስ ንብረት ጋር በተያያዘ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ስመ ሃብት ይዞ መገኘት የንብረቱ ባለቤት አድርጐ የማያስቆጥር ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1195, 1196 Download Cassation Decision

 • 47201 family law/ contract of marriage/ divorce

  የጋብቻ ውል አስገዳጅ የህግ ድንጋጌን እስካልተቃረነ ድረስ በፍቺ ምክንያት የሚከተለውን የተጋቢዎች የንብረት ክፍፍል እልባት በመስጠት ረገድ ተፈፃሚ ሊሆን የሚገባ ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ. 213/92 አንቀጽ 42, 47, 73, 44 Download Cassation Decision

 • 47201 law of succession/ petitio heriditatis/ period of limitation

  ወራሽ የሆነ ሰው ወራሽ ባልሆነ ሰው ላይ ንብረቴ ይለቀቅልኝ በሚል የሚያቀርበው ክስ /አቤቱታ/ ላይ ተፈፃሚ የሚሆነው ይርጋ የሚቆጠረው ወራሽነት ከተረጋገጠበት ቀን አንስቶ ሳይሆን ንብረቱ ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 47526 contract law/ construction contract/ form of contract

  የማይንቀሳቀስ ንብረት /ህንፃ/ ግንባታ ሥራ ጋር በተገናኘ ተፈፃሚ ስለሚሆኑ ድንጋጌዎች የሥራ ተቋራጭነት ውል ተፈጽሟል /አለ/ ለማለት የሚቻልበት አግባብ የግንባታ ሥራ ውል በልዩ ፎርም መደረግ ያለበት ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 47917 law of succession/ disinhersion/ will

  ተወላጅ የሆነ ሰው ከውርስ ተነቅሏል ሊባል የሚችለው ተናዛዡ ንብረቱን በጠቅላላ የኑዛዜ ስጦታ ለሌሎች ተወላጆች ወይም ሌሎች ሰዎች የሰጠ እንደሆነ ስለመሆኑ ሟች ያለው አንድ የታወቀ ንብረት ብቻ ሆኖ ይህንኑ ከተወላጆቹ መካከል አንዱን ወይም ሁሉንም ሳያካትት ለሌሎች ሰዎች በኑዛዜ የሰጠ እንደሆነ ተነቀልኩ የሚል ወገን ኑዛዜው ላይ ተቃውሞ ሊያነሳ የሚችል ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 48042 civil procedure/ execution of judgment/ attachment/ priority of creditors

  በዕዳ ምክንያት በፍ/ቤት የተከበረ ንብረት እንዲሸጥ በተደረገ ጊዜ ንብረቱን ያስከበረው ወገን የሚኖረው መብት ከሽያጭ ገንዘቡ ላይ የቀዳሚነት መብት ካላቸው ባለገንዘቦች የሚተርፍ ካለ መውሰድ ነው እንጂ ንብረቱን በሽያጭ ውል የተነሳ ባለቤት የሆነን ወገን መጠየቅ ወይም ንብረቱን የመከተል ስላለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 48086 property law / contract of rent/ expropriation

  አዋጅ ቁ. 47/67 ከመውጣቱ በፊት የተደረገ የመሬት ኪራይ ውል ህጋዊ አስገዳጅነት ሊኖረው የማይችል ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 47/67 Download Cassation Decision

 • 48217 property law/ right on land/ ownership/ constitution/ right to access to justice

  ቤትና ቦታዬን ያለአግባብ ተነጠቅሁ በሚል የሚቀርብ አቤቱታ በፍ/ቤት ታይቶ ፍርድ ሊሰጥበት የማይችል አስተዳደራዊ ጉዳይ ነው ሊባል የማይችል ስለመሆኑ ኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 37 የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 4 Download Cassation Decision

 • 48628 tax law / custom duty/ criminal law/ contraband/ contraband carrying vehicles/ confisication

  በጉምሩክ አዋጅ ቁ. 368/95 /እንደተሻሻለ/ አንቀጽ 74 ሥር ጥፋተኛ የተባለ ተከሳሽ ሊጣልበት ስለሚችለው የቅጣት አይነትና መጠን በኮንትሮባንድ ዕቃ ሲያጓጉዝ የተገኘ ተሽከርካሪ ሊወረስ የሚችልበት አግባብ አዋጅ ቁ. 60/89 አዋጅ ቁ. 368/95 አንቀጽ 64/4/, 74 Download Cassation Decision

 • 48945 labor dispute/ obligation of employer/ obligation of worker

  አንድ ሰራተኛ ለሥራ ከሚጠቀምበት መሳሪያ ብልሽት መከሰት ጋር በተገናኘ በኃላፊነት ሊጠየቅ የሚችለው አሰሪው ግዴታና ኃላፊነቱን በአግባቡ የተወጣ እንደሆነ ስለመሆኑ የአዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 12/1//ሀ/ Download Cassation Decision

 • 48997 civil procedure/ execution of judgment/ tax law/ priority of creditors/ Value Added Tax (VAT)

  ከግብር እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር በተያያዘ በአፈፃፀም ደረጃ የሚቀርብ የቀዳሚነት መብት ይከበርልኝ ጥያቄ የህግ መሰረት ያለውና ሊስተናገድ የሚገባ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 285/94 አንቀጽ 32/1/ አዋጅ ቁ. 286/94 አንቀጽ 80/1/ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 418 Download Cassation Decision

 • 49171 family law/ common property/

  በሁለት የተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ቤቶች የጋብቻ ፍቺን ተከትሎ ለባልና ሚስት ሊከፋፈሉ የሚችሉበት አግባብ Download Cassation Decision

 • 49200 property law/ land right/ constitution/

  መሬት በፍ/ብሔር ግንኙነት የተፈጠረን ዕዳ ለመክፈል ጥቅም ላይ ሊውል የማይችል ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 40/3/ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1678/2/ Download Cassation Decision

 • 49359 law of succession/ period of limitation

  የውርስ ሀብትን አስመልክቶ የሚቀርብ ክስ ላይ ተፈፃሚ የሚሆነው የይርጋ ገደብ በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1851/ለ/ መሰረት ሊቋረጥ የሚችልባቸው ሁኔታዎች ስለመኖራቸው የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1851 Download Cassation Decision

 • 49428 property law /sale of immovable property/ transfer of title/ administrative law/

  በህጋዊ መንገድ የማይንቀሳቀስ ንብረትን በሽያጭ ውል ያገኘ ገዢ የሚመለከተውን የአስተዳደር አካል የስም ዝውውር እንዲፈጽምለት በፍ/ቤት ለመክሰስ የሚችል ስለመሆኑ የሚመለከተው የአስተዳደር አካል በህግ የተሰጠውን ተግባርና ሃላፊነት ካልተወጣ ገዥ መብቱን ለማስከበር ክስ ማቅረብ የሚገባው በዚሁ የአስተዳደር አካል ላይ ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 49713 law of succession/ unworthiness/ disinhersion

  ከውርስ ጋር በተገናኘ በህግ ወራሽ የሆኑ ሰዎች ሟችን ለመውረስ ያልተገቡ ናቸው ሊባል የሚችልበት ሁኔታ ሟች በኑዛዜው ከውርስ ሊነቅላቸው ከሚችልበት ሁኔታ የተለየ ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 49831 law of succession/ will/ burden of proof

  የኑዛዜ መኖርን የማስረዳት ሸክም ስላለበት ወገንና ኑዛዜውን ለማስረዳት ሊቀርቡ ስለሚገቡ ማስረጃዎች የፍ/ብ/ህ/ቁ. 896, 897 Download Cassation Decision

 • 49985 property law /possessory action/ civil procedure/ court fee

  ፍ/ቤቶች በሚቀርቡላቸው አቤቱታዎች ላይ ህግን ተፈፃሚ ለማድረግ የቀረበውን የክስ አርእስት ብቻ ሳይሆን ይዘት ጭምር መመልከት የሚገባቸው ስለመሆኑ ከንብረት ባለቤትነት ጋር በተያያዘ በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1149/1/ መሰረት ሁከት የተፈጠረበት ሰው እንዲወገድለት ይዞታው የተወሰደበት ሰው ደግሞ እንዲመለስለት በሚል ዳኝነት የሚጠየቀው አቤቱታ የቀረበበት ንብረት ተገምቶ ተገቢው ዳኝነት ከተከፈለበት በኋላ ስለመሆኑና በጥቅሉ የተፈጠረ ሁከት እንዲወገድ (cessation of interference) እንደሆነ ተቆጥሮ ልክ አቤቱታቸው በገንዘብ የማይገመቱ አቤቱታዎች አይነት ሊስተናገድ የማይገባ ስለመሆኑና የይርጋ ደንብ ተፈፃሚ የማይሆን ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1149/2/ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 16, 226/3/ Download Cassation Decision

 • 50375 tax law / custom duties/ preinspection

  ከውጭ አገር ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ዕቃዎችን አስመልክቶ ስለሚካሄድ የቅድመ ጭነት ምርመራ ሥርዓት እና በዕቃው ላይ ስለሚከፈል ግብር /ታክስ/ አዋጅ ቁ. 173/91 አንቀጽ 6/1/, 4/1/ Download Cassation Decision

 • 50489 family law/ bigamy/ common property/ partition of common property

  ባል ሁለት ሚስቶችን በአንድ ጊዜ አግብቶ የሚኖር በሆነ ጊዜ በመካከላቸው የሚፈራ ንብረት ለተጋቢዎቹ ሊከፋፈል የሚችልበት አግባብ ሚስቶች ጋብቻ እንደተፈፀመ ከሚቆጠርበት ጊዜ ጀምሮ ከባል ጋር ያፈሩትን ሀብት ብቻ መካፈል ስለመቻላቸው Download Cassation Decision

 • 50580 family law/ irregular union/ proof of irregular union/ effect of irregular union

  ጋብቻ ሳይኖር እንደ ባልና ሚስት መኖርን ማስረዳት የሚቻልበት አግባብና ይሄው ግንኙነት በህግ ጥበቃ ያለው ነው ለማለት የሚቻልበት ሁኔታ ጋብቻ ሳይኖር እንደ ባልና ሚስት አብሮ የመኖር ግንኙነት በንብረት ረገድ ውጤት ሊያስከትል የሚችለው ግንኙነቱ ሦስት ዓመት እና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ የፀና ከሆነና በዚሁ ጊዜም የተፈራ ንብረት ያለ እንደሆነ ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 50810 property law / expropriation/ valuation/ compensation

  መንግስት አንድን የግል ንብረት ለህዝብ ጥቅም በሚወስድበት ጊዜ ሊከተለው ስለሚገባው ሥነ ሥርዓት ለህዝብ ጥቅም ሲባል ንብረቱ የተወሰደበት ሰው የተሰጠው ግምት ከንብረቱ ዋጋ ጋር ተመጣጣኝ አይደለም በሚል ለፍ/ቤት የሚቀርብ አቤቱታ በ3 ወር ጊዜ ውስጥ መቅረብ ያለበት ሰለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 50971 law of succession/ will/ blind person/ nullity

  ማየት የተሳናቸው ሰዎች የሚያደርጉት ኑዛዜ በውል አዋዋይ ፊት ካልሆነ በስተቀር አይፀናም ለማለት የሚያስችል የህግ መሰረት የሌለ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 881/3/, 1728/3/, 340, 343/2/ Download Cassation Decision

 • 51034 contract law / contract of sale/ ownership

  አንድ ሰው የሌለውን ነገር ሸጦ በተገኘ ጊዜ ገዢው በህግ ሊያገኝ ስለሚገባው መፍትሔ በሌለ መብት መሥራት የማይቻል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2884/1/ /2/, 2282-2285, 1716 Download Cassation Decision

 • 51090 tax law / Value Added Tax (VAT)/ criminal law/ criminal liability of manager/

  የተጨማሪ እሴት ታክስ ህግን ተላልፏል በሚል በወንጀል የተከሰሰና ስራ አስኪያጅ የሆነ ሰው ድርጊቱ ሲፈፀም በቦታው አልነበረም ወይም አያውቅም በሚል ምክንያት ከወንጀል ኃላፊነት ነፃ ሊሆን የማይችል ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 285/94 አንቀጽ 56/1/ 55 አዋጅ ቁ. 609/209 አንቀጽ 22/1/ 50/ለ//1/ Download Cassation Decision

 • 52110 civil procedure/ execution of judgment/ appearance of parties

  በአፈፃፀም ደረጃ የሚገኝ ጉዳይ ጋር በተገናኘ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 78/1/ ያለው አግባብነት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 78 /1/ Download Cassation Decision

 • 52407 law of succession/ liquidation of succession/ period of limitation

  የውርስ ሀብት ይጣራልኝ በሚል የሚቀርብ አቤቱታ በሦስት ዓመት ይርጋ የሚታገድ ስለመሆኑ/ ከውርስ ሀብት ክርክር ጋር በተገናኘ ተፈፃሚ የሚሆነው የይርጋ ጊዜ መቆጠር የሚጀምረው ንብረቱ በእጅ ከተደረገበት ጊዜ እንጂ ስመሃብቱ ከተዛወረበት ጊዜ አንስቶ ስላለመሆኑ / Download Cassation Decision

 • 52496 property law / expropriation/ right on land/ compensation

  የመሬት ይዞታ ለህዝብ ጥቅም ሲባል በተወሰደ ጊዜ ካሣ የሚከፈለው በተወሰደው ይዞታ ላይ ንብረት የነበረ መሆኑ እንዲሁም ንብረቱን ለመተካት ከሚያስፈልገው ወጪ ጋር ተመጣጣኝነት ያለው መሆኑ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 401/96 አንቀጽ 9/1/, 10 አዋጅ ቁ. 455/97 Download Cassation Decision

 • 52530 cassation procedure/ change of previous precedent/ interpretation/ law of succession/ jurisdiction/ Addis Ababa court/ liquidation

  የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት በአንድ ወቅት በአንድ ጉዳይ /ጭብጥ/ ላይ የሰጠው የህግ ትርጉም እንደተለወጠ /እንደተሻሻለ/ ሊቆጠር የሚችለው በተመሳሳይ ጭብጥ ላይ በህግ አግባብ የተለየ ግልጽ ትርጉም በሰጠ ጊዜ ብቻ ስለመሆኑ የውርስ ይጣራልኝ አቤቱታ ተቀብሎ ማስተናገድ ብሎም የውርስ አጣሪ መሾም ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደ ፍርድ ቤቶች በህግ ስልጣን ያልተሰጣቸው ስለመሆኑ/ /የሰ/መ/ቁ. 35657፣ 42015፣51329 ይመለከቷል/ አዋጅ ቁ. 361/95 አንቀጽ 41 አዋጅ ቁ. 454/97 አንቀጽ 2/4/ Download Cassation Decision

 • 52569 family law/ public pension/ interruption of pension payment

  ባል/ሚስት በጡረታ መልክ የሚያገኘውን ክፍያ ሌላ ባል/ሚስት ባገባ ጊዜ የሚቋረጥ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 209/55 አንቀጽ 21 አዋጅ ቁ. 345/95 አንቀጽ 35/2/ Download Cassation Decision

 • 52595 extra contractual liability/ strict liability/ building/ contractor/ owner of building

  የህንፃ ተቋራጭ ሠራተኛ በመሆን በሚሠራው ህንፃ ላይ ሥራውን በማከናወን ላይ እያለ ከህንፃው ወድቆ ጉዳት የደረሰበት ሰው የሚሰራውን ህንፃ ባለቤት ከውል ውጭ የሆነ ግንኙነትን መሰረት በማድረግ የጉዳት ካሣ ሊጠይቅ የሚችልበት የህግ መሠረት የሌለ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2077 Download Cassation Decision

 • 53223 law of succession/ will/ contesting will/ period of limitation

  በኑዛዜ ላይ ስለሚቀርብ የመቃወም አቤቱታ እና ተፈፃሚነት ስላለው የይርጋ ደንብ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 973, 974 Download Cassation Decision

 • 53328 property law/ possession/ ownership/ period of limitation

  የይርጋ መርህ ክስን በተወሰነ የጊዜ ገደብ ቀሪ የሚሆንበትን አግባብ የሚመለከትና ንብረትን በመያዝ ወይም ባለይዞታ በመሆን የባለሀብትነት መብት ከሚገኝበት መርህ የሚለይ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1168, 1808 Download Cassation Decision

 • 53527 labor dispute/ execution of judgment/ period of limitation

  ከአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በፍ/ቤት የተሰጠ ፍርድ እንዲፈፀም የሚቀርብ አቤቱታ ፍርድ ከተሰጠበት ቀን አንስቶ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ የሚታገድ ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 53551 administrative law/ personality/ Kebele trust board

  የቀበሌ ባለአደራ ቦርድ ህጋዊ ሰውነት ያለው ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 361/95 አንቀጽ 14/1//ረ/, 66/1/ አዋጅ ቁ. 2/95 አንቀጽ 52 Download Cassation Decision

 • 53598 extra contractual liability/ damage assessment/ appeal

  ከውል ውጪ በሆነ ግንኙነት ፍ/ቤቶች የጉዳት ካሣን አስመልክቶ የሚሰጡት ውሣኔ በይግባኝ ሊለወጥ የሚችልበት አግባብ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2152, 2153 Download Cassation Decision

 • 53663 family law/ irregular union/ property law/ usufruct

  ከጋብቻ ውጭ እንደባልና ሚስት የሚኖሩ ሰዎች ግንኙነታቸው በንብረት ረገድ ያለውን ውጤት በተመለከተ በውል ሊወሰኑ ስለመቻላቸው በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ያለ አላባ የመጠቀም መብት ጥቅም ተቀባዩ ሲሞት የሚቋረጥና ለወራሾቹ የማይተላለፍ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1731, 1322/1/ Download Cassation Decision

 • 53749 tax law/ custom duties/ undue custom duty payment/ period of limitation

  በስህተት ለጉምሩክ የተከፈለ ቀረጥ ተመላሽ የሚደረገው ስህተቱ መኖሩን ባለስልጣን መ/ቤቱ ያወቀና ዕቃውም የጉምሩክ ስነ ስርዓትን አጠናቅቆ ወደ አገር ከገባበት ወይም ወደ ውጭ አገር ከተላከበት ቀን ጀምሮ ባለው 6 ወር ውስጥ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 368/95 አንቀጽ 15 Download Cassation Decision

 • 53814 family law/ common property/ immovable property/ improvements on property

  ከጋብቻ በፊት አንደኛው ተጋቢ የግል መኖሪያ ቤት ኖሮት ከጋብቻ በኋላ ሌሎች ተጨማሪ ቤቶችና ግንባታዎች ተካሂደዋል በሚል ከጋብቻ በፊት በስሙ ተመዝግቦ የሚገኘው ቤት በጨረታ ተሸጦ ለተጋቢዎቹ እንዲካፈል በሚል የሚሰጥ ውሣኔ አግባብነት የሌለው ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 53943 civil procedure/ execution of judgment/ summon of judgment debtor/ failure to appear/

  የአፈፃፀም ክስና መጥሪያው ደርሶት የፍርድ ባለዕዳ ሳይቀርብ በሚቀርበት ጊዜ ፍርድ ቤቶች የሚከተሉት ሥርዓት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 70/ሀ/“ን” ድንጋጌ መሰረት ያደረገ ስላለመሆኑ እና የተሰጠን ትዕዛዝም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 78 መሠረት ለማስነሳት የሚቻልበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 70/ሀ/, 78 Download Cassation Decision

 • 53985 labor dispute/ suspension/ collective agreement/ discipline breach

  የህብረት ስምምነት የሌለው አሰሪ ሰራተኛው የዲሲፕሊን ጉድለት ፈጽሟል የሚልበትን ጉዳይ ለማጣራትና ለመመርመር ሰራተኛውን ከአንድ ወር ላልበለጠ ጊዜ ለማገድ ስለመቻሉ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 27/4/ Download Cassation Decision

 • 54013 law of succession/ will/ public will/ finger print signature/ forensic analysis/ witnesses

  በፍ/ብ/ህ/ቁ. 881 መሰረት የተደረገ ግልጽ ኑዛዜ ላይ ያለን የተናዛዡ የጣት አሻራ በተመለከተ ክርክር በቀረበ ጊዜና በፎረንሲክ ምርመራ ለማረጋገጥ ካልተቻለ በኑዛዜው የተገኙ ምስክሮች ቀርበው እንዲመሰክሩ ማድረግ የሚገባ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 881, 1677/1/, 2007/2/, 897/1/, 896 Download Cassation Decision

 • 54021 extra contractual liability/ damage/ good faith

  ከውል ውጪ በሆነ ግንኙነት በመኪና ላይ ጉዳት በደረሰ ጊዜ የመኪናው ባለቤት በደረሰው ጉዳት የተነሳ ሊከተል የሚችለውን ኪሣራ ለመቀነስ ተገቢውን ጥረት የማድረግ ግዴታ ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2091, 2097/1/ /2/ Download Cassation Decision

 • 54024 family law/ filliation/paternity/ legal presumption/ birth in wedlock

  በጋብቻ ውስጥ የሚወለድ ልጅ አባት ባል እንደሆነ የህግ ግምት ሊወሰድ የሚችልበት አግባብ የዚህ የህግ ግምት የሚቋቋምበት አግባብ እና እንደ ማስረጃ ተወስዶ በፍ/ቤት እውቅና ሊያገኝ የሚገባ ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ. 213/92 አንቀጽ 126, 143 Download Cassation Decision

 • 54121 private international law/ choice of law/ jurisdiction/ foreign company

  ለዳኝነት የቀረበው ጉዳይ በባህሪይው ከአንድ በላይ የሆኑ የህግ ስርዓቶችን ለጉዳዩ አወሳሰን የሚጋብዝና የየትኛው ሥርዓት ህግ ተመራጭ ሊሆን ይገባል የሚል ጥያቄን የሚያስነሳ እንደሆነ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመጀመሪያ ደረጃ የፍ/ብሔር ስልጣኑ ሊታይ የሚችል ስለመሆኑ ተዋዋይ ወገኖች በማናቸውም ሁኔታ የአገሪቱን ህግ ወደ ጐን በማድረግ ወይም በሚፃረር መልኩ ስምምነት ስላደረጉና ክርክር ስለተነሳ ብቻ አንድ ጉዳይ የግለሰብ ዓለም አቀፍ ህግ ጥያቄን/private international law issue/ የሚያስነሳ ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ በሚኒስትሮች ምክር ቤት በደንብ ካልተወሰነ በቀር አዋጅ ቁጥር 377/96 የውጭ አገር ድርጅት ሆኖ በኢትዮጵያ ተመዝግቦ በሚሰራ ድርጅት ላይ ተፈፃሚነት ያለው ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 54129 family law/ minors/ tutorship/ sale of immovable property

  አካለ መጠን ያልደረሰ ልጅ ሞግዚት የልጁ ንብረት የሆነን የማይንቀሳቀስ ንብረት በሽያጭ ለ3ኛ ወገን ለማስተላለፍ በህግ ስልጣን ያልተሰጠው ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 54203 tax law / criminal law/ custom duties/ duty free privilege

  ከቀረጥ ነፃ በሆነ መልኩ ለግል አገልግሎት እንዲውል የገባ መኪናን ለንግድ ማዋል በወንጀል ተጠያቂነትን የሚያስከትል ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 368/95 አንቀጽ 73/1/, 78 Download Cassation Decision

 • 54258 family law/ proof of marriage/ certificate of marriage/ registration before officer civil status

  የጋብቻ መኖርን አስመልክቶ ቀዳሚና ዋናው ማስረጃ የጋብቻ ምስክር ወረቀት ስለመሆኑ በማንኛውም ሥርዓት የተፈፀመ ጋብቻ በክብር መዝገብ ሹም ፊት ቀርቦ ሊመዘገብ የሚችልና በዚህ መልኩ የሚገኘው ሰነድ የጋብቻ መኖርን ለማረጋገጥ ብቃት ያለው ስለመሆኑ በዚሀ መልኩ በክብር መዝገብ ሹም ፊት የተመዘገበ ጋብቻ ውጤት አለው ለማለት የሚቻለው ምዝገባው ከተከናወነበት ጊዜ ጀምሮ ሳይሆን የጋብቻው ሥርዓት ከተፈፀመበት ዕለት አንስቶ ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 54326 labor dispute/ transfer/ collective agreement

  በህብረት ስምምነት ላይ ከተመለከቱ ሁኔታዎች ውጪ ሰራተኛን ያለአግባብ አዛውሮ የማሰራት ተግባር ህጋዊ ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 54385 law of succession/ will/ disinhersion

  ሟች ካለው ሀብት እጅግ አነስተኛ የሆነ መጠን ያለው ንብረት ለተወላጁ እንዲሰጠው የተናዘዘ እንደሆነ ተናዛዡ በተዘዋዋሪ መንገድ ተወላጁን እንደነቀለው የሚቆጠር ስለመሆኑ የሟች ኑዛዜ ጠቅላላ የኑዛዜ ስጦታ በሆነ ጊዜም የተነቀለ ተወላጅ ከኑዛዜ ተቀባዩ ጋር እኩል ሊካፈል የሚገባው ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 54451 labor dispute/ collective agreement/ registration of collective agreement

  Download Cassation Decision

 • 54518 unlawful enrichment/

  ከውል ውጭ የሌላ ሰው ሃብት የሆነን ነገር በመያዝ ለተገለገለበት ጊዜ ክፍያ እንዲከፈል በሚል የቀረበ አቤቱታ ጋር በተያየዘ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2024 ተፈፃሚነት የሌለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2024 Download Cassation Decision

 • 54567 civil procedure/ injunction/ violating injunction order

  በፍርድ ቤት የተሰጠ የእግድ ትዕዛዝ ፀንቶ ባለበት ወቅት እግድ የተሰጠበት ንብረት ተሸጦ በተገኘ ጊዜ የፍርድ ባለመብት የሆነ ወገን ሊኖረው ስለሚችለው መፍትሔ የፍርድ ቤትን የእግድ ትዕዛዝ አለማክበር /መጣስ/ ኃላፊነትን የሚያስከትል ተግባር ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 54827 family law/ minors/ tutorship/ sale of immovable property

  አካለ መጠን ያልደረሰ ሰው ሞግዚት የልጁ ሀብት የሆነን የማይንቀሳቀስ ንብረት ያለ ፍርድ ቤት ፈቃድ ለመሸጥ የማይችል ስለመሆኑ የኦ/ብ/ክ/መ/ የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ. 69/95 አዋጅ ቁ. 83/96 አንቀጽ 294, 316 የተሻሻለው የፌዴራል የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ. 213/92 አንቀጽ 277/1/, 292 Download Cassation Decision

 • 55081 civil procedure/ execution of judgment/ property law / ownership

  አንድ ሰው የንብረት ባለቤት የሚሆነው በጉልበቱ፣ በፈጠራ ችሎታው ወይም በገንዘቡ ንብረትን ያፈራ እነደሆነ ስለመሆኑ የፍርድ ባለዕዳ የሆነ ሰው ንብረቱ ለፍርድ ማስፈፀሚያነት እንዳይውል አስቦ አካለ መጠን ባልደረሰ ህፃን ልጁ ስም ማዞሩ ብቻ ከኃላፊነት ሊያድነው የሚያስችል ስላለመሆኑና ይህ በመሆኑም ሊፈፀም የሚችል ፍርድ የለም ሊባል የማይችል ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 55228 extra contractual liability/ strict liability/ driver/ car owner/ subrogation

  ባለሞተር ተሽከርካሪ ከሚያደርሰው ጉዳት ጋር በተያያዘ የመጨረሻው ኃላፊነት (ultimate liability) የሚወድቀው መኪናው ሲሽከረከር የነበረው ባለቤቱ በቀጠረው ሹፌር እንኳን ቢሆን በወቅቱ በመኪናው ሲገለገል የነበረው ሰው ላይ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2082/1/, 208/1/, 2083/1/ Download Cassation Decision

 • 55238 nationality/ Eritrea

  የኢትዮጵያን ዜግነት በመተው የኤርትራን ዜግነት መርጦ የያዘ ሰው “የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆነ የውጭ ዜጋ” ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 270/94 አንቀጽ 2/2/ ደንብ ቁ. 101/96 አንቀጽ 2/1/ Download Cassation Decision

 • 55648 law of succession/ will/ reserved share of heirs/ power of court

  ተናዛዥ የሆነ ሰው ተወላጁ የሆነ ሰው በውርስ ሊደርሰው ከሚገባው ድርሻ ከሩብ በላይ ጉዳት እንዲደርስበት ለማድረግ የሰጠው ምክንያት በቂ መሆን ያለመሆኑ በዳኞች ሊመረመር የሚገባው ስለመሆኑ “ስላልረዱኝ ወይም ስላልጠየቁኝ” የሚል ምክንያት በመስጠት ተወላጅን ሊደርሰው ከሚገባው የውርስ ድርሻ ሩብ በላይ ጉዳት እንዲደርስበት ለማድረግ የማይቻል ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 55731 labor dispute/ labor union/ right to establish labor union

  በአዋጅ ቁ. 377/96 መሰረት የሠራተኛ ማህበር ለማቋቋም የሚቻልበት አግባብ የሰራተኛ ማህበር ለማቋቋም መብት የተሰጣቸው በአዋጅ ቁ. 377/96 የሚተዳደሩ ሰራተኞች ብቻ ስለመሆናቸው አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 114, 115, 118, 2/4/, 113 የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 42/1/ /ሀ/, 31 Download Cassation Decision

 • 55794 finance/ Ikub/

  እጣው ከመድረሱ በፊት አባልነቱን ያቋረጠ የእቁብ አባል ለእቁብ የከፈለውን ገንዘብ ይመለስልኝ በሚል የኃላፊነት ጥያቄ ሊያቀርብባቸው ስለሚችሉ አካላት Download Cassation Decision

 • 56011 property law /condominium house/ sale of immovable property

  የኮንዶሚንየም ቤትን ዋጋ በአጠቃላይ የከፈለ የኮንዶሚንየም ቤት ባለቤት በፍርድ የተወሰነበት የሌላ ሰው ዕዳ ያለበት በሆነ ጊዜ ፍርድ ቤቶች ቤቱ በአፈፃፀም ተሸጦ ለዕዳው መክፈያነት እንዲውል ለማዘዝ የሚችሉ ስለመሆኑ የኮንዶሚንየም ቤት ባለሀብት የሆነ ሰው በራሱ ፈቃድ ቤቱን ለመሸጥ ለመለወጥ ወይም ለ3ኛ ወገን ለማስፈላለፍ የሚችለው ያለበትን የቤቱን ዋጋ አጠናቅቆ ከከፈለበት ጊዜ ጀምሮ አምስት ዓመት ካለፈ በኋላ ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 56157 family law/ conditions of marriage/ contract of marriage

  የጋብቻ ውል በአግባቡ ተደርጓል ሊባል የሚችልበት አግባብ የጋብቻ ውል በሚል በተጋቢዎች መካከል የሚደረግ ስምምነት ከነሙሉ ይዘቱ ሊታይና ተፈፃሚ ሊደረግ የሚገባ ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 56184 family law/ debt of spouses/ separation/ income

  በትዳር ወቅት የተወሰደ /በአንደኛው ተጋቢ/ ብድር ለትዳር ጥቅም እንደዋለ የሚገመት ስለመሆኑና ከዚህ በተቃራኒ የሚከራከር ተጋቢ ገንዘቡ ለትዳር ጥቅም ያልዋለ መሆኑን የማስረዳት ግዴታ ያለበት ስለመሆኑ ደመወዝ የተጋቢዎች የጋራ ሃብት ነው በሚል ሊወሰድ የሚችለው ተጋቢዎቹ በጋብቻ ባሉበት ወቅት የትዳርን ወጪ ከመሸፈን አኳያ መሆን ያለበት ስለመሆኑ ተጋቢዎች ከህጋዊ ፍቺ በፊት ተለያይተው በቆዩባቸው ግዜያት በግል ያገኙት ደመወዝ የጋራ ነው ለማለት የሚቻል ስላለመሆኑ በጋብቻ ወቅት የተወሰደና በፍቺ ወቅት ተከፍሎ ያላለቀ ዕዳ እንደ የጋራ ዕዳ የሚወሰድ ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 56934 administrative law/ right to hearing/ health professionals/

  በጤና ጥበቃ ሙያ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ከጤና ሥነ ምግባር ጉድለት ጋር በተያያዘ በጤና ባለሙያዎች መማክርት ጉባኤ ክስ በቀረበባቸው ጊዜ በተገቢው መንገድ መልስ የመስጠትና የመሰማት መብታቸው ሊጠበቅ የሚገባ ስለመሆኑ የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎችን መማክር ጉባኤ ማቋቋሚያ የሚንስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 76/94 አንቀጽ 16/1/ /2/ Download Cassation Decision

 • 57044 administrative law/ power of administrative authority/ construction permit/ damage

  የአስተዳደር አካል የሰጠው ውሣኔ ወይም የወሰደው እርምጃ ህገ ወጥ መሆኑን እስካረጋገጠ ድረስ ውሣኔውን ለማረም /እንዲስተካከል ለማድረግ/ ስለመቻሉ በተሳሳተ መንገድ በተሰጠ አስተዳደራዊ ውሣኔ ቅን ልቦና አድሮበት ለኪሣራ የተዳረገ ሰው ኪሣራ ለመጠየቅ ስለመቻሉ በስህተት በተሰጠ የግንባታ ፈቃድ ግንባታ ያካሄደ ሰው የአስተዳደር አካሉ ስህተቱን በማረም ግንባታው እንዲፈርስ መግለጫ በሰጠ ጊዜ የሚያቀርበው የሁከት ይወገድልኝ አቤቱታ የህግ መሰረት የሌለው ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 57045 property law / possessory action/ government houses/ law of succession

  ሟች ከቀበሌ ተከራይቶት የነበረን መኖሪያ ቤት ወራሽነትን በማረጋገጥ ብቻ በቤቱ ውስጥ የመኖር ህጋዊ መብት ሊገኝ የማይችል ስለመሆኑና ተቀባይነት ያለው የሁከት ይወገድልኝ አቤቱታ ሊቀርብ ስላለመቻሉ Download Cassation Decision

 • 57068 labor dispute/ occupational accident/ strict liability of employer

  በስራ ላይ ከሚደርስ ጉዳት ጋር በተያያዘ የአሰሪው ኃላፊነት በጥፋት ላይ ያልተመሰረተ (strict liability) ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 96, 97 Download Cassation Decision

 • 57100 tax law / priority of creditors/

  የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን አስቀድሞ በዋስትና ለሌላ ሰው ያልተሰጡ የግብር ከፋይ ንብረቶች ላይ የቀዳሚነት መብት ያለው ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 286/94 አንቀጽ 80/1/, 78/1/ Download Cassation Decision

 • 57114 law of succession/ period of limitiation/ minor

  ከውርስ ሃብት ጋር በተያያዘ ወራሽ የሆነና አካለመጠን ያልደረሰ ሰው ላይ የይርጋ ጊዜ ሊቆጠር የሚገባው አካለመጠን ከደረሰበት ወይም በመብቱ መጠቀም ከቻለበት ጊዜ አንስቶ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1845 Download Cassation Decision

 • 57243 tax law custom duties/ criminal law/ contraband/ contraband carrying vehicle

  የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ያልተፈፀመበት ዕቃን በማጓጓዝ የተያዘ ተሽከርካሪ እንዲወረስ ላይታዘዝ የሚችልበት አግባብ አዋጅ ቁ. 622/2001 አንቀጽ 104/3/ /ሀ/ አንቀጽ 91/1/ Download Cassation Decision

 • 57271 property law / expropriation/ compensation/ urban land/ civil procedure/ jurisdiction

  የከተማ መሬት ይዞታን እንዲለቅ የተደረገ ባለይዞታ በተወሰነለት የካሣ መጠን ላይ ካልተስማማ አቤቱታውን ማቅረብ ያለበት በከተማው አስተዳደር ሥር ለተቋቋመ የመሬት ነክ አቤቱታ ሰሚ አካል ስለመሆኑ እና በመደበኛ ፍ/ቤት ጉዳዩ ሊታይ የሚችለው በይግባኝ ብቻ ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 455/97 አንቀጽ 11/2/, /4/ Download Cassation Decision

 • 57337 labor dispute/ termination of contract of empolyment/ contract of employment for definite period of time

  ለተወሰነ ጊዜና ሥራ የተቀጠረ ሠራተኛ ጊዜው ደርሶ መሰናበቱ ምንም እንኳን ሌሎች ሠራተኞች በእሱ ምትክ የተቀጠሩ ቢሆንም ህገ ወጥ ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 57541 labor dispute/ termination of contract of employment/ burden of proof

  ከስራ ተሰናበትኩ በማለት አቤቱታ የሚያቀርብ ሠራተኛ በእርግጥም ስለመሰናበቱ አግባብነት ያላቸውን ማስረጃዎች በማቅረብ የማስረዳት ግዴታ ያለበት ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 57607 family law/ filliation/ paternity

  በጋብቻ ውስጥ የተወለድኩ በመሆኔ ልጅነቴ እንዲረጋገጥልኝ በሚል የሚቀርብ አቤቱታ ህጋዊ መሰረት ያለውና ፍ/ቤቶችም ተቀብለው በፍሬ ነገር ረገድ ሊጣሩ የሚገቡትን በማጣራት መወሰን ያለባቸው ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 37/1/ Download Cassation Decision

 • 57836 law of succession/ will/ disinhersion/ ownership

  ኑዛዜ አድራጊ “ስታመም አላስታመመኝም ” በሚል ምክንያት ተወላጅን በኑዛዜ ለመንቀል የሚያስችለው ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ ኑዛዜ በተደረገበት ንብረት ሟች መብት የሌለው በሆነ ጊዜ ሊከተል ስለሚችለው ውጤት Download Cassation Decision

 • 58008 criminal law/ criminal liability of coffee business regulation/ coffee

  የቡና ላኪነት ፈቃድ አውጥቶ በግብይት ሥራ ላይ የተሰማራ ሰው የቡና ጥራት ቁጥጥርና ግብይት አዋጅን ጥሷል በሚል በወንጀል ህግ አንቀጽ 34/1/ መሰረት ሊጠየቅ የሚችልበት አግባብ አዋጅ ቁ. 602/2000 አንቀጽ 14/3/, 15/3/ ደንብ ቁ. 159/2001 የግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስቴር መመሪያ Download Cassation Decision

 • 58009 civil procedure/ execution of judgment/ judgment debtor/ attachment/

  በክርክር ሂደት ተሳታፊ ያልነበረና ፍርድ ያልተሰጠበት ሰው ንብረት በፍርድ አፈፃፀም ሲያዝበት /በሃራጅ ሲሸጥበት/ ሊከተለው ስለሚገባው አካሄድ Download Cassation Decision

 • 58266 tax law / custom duties/ duty free previledges

  ከቀረጥ ነፃ፣ በቅናሽ ቀረጥ ወይም በጊዜያዊነት ከቀረጥ ነፃ የገባን ዕቃ ህግን በሚቃረን መልኩ የቀረጥ ነፃ መብቱ ከተሰጠበት ምክንያት ውጪ መጠቀም /ለሌላ ሰው አሳልፎ መስጠት/ የወንጀል ኃላፊነትን የሚያስከትል ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 60/89 አዋጅ ቁ. 368/95 አንቀጽ 73/1/ /ሀ/ /ለ/ /2/ Download Cassation Decision

 • 58338 law of succession/ disinhersion/ reserved share of heirs

  ከውርስ በዝምታ ወይም ያለበቂና ህጋዊ ምክንያት የተነቀለ የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ ከጠቅላላ የኑዛዜ ተጠቃሚ ጋር እኩል ወራሽ ሆኖ የሟችን የውርስ ሃብት ሊካፈል የሚገባ ስለመሆኑ “በህይወቴ ላይ ከፍተኛ ችግር ፈጥረውብኛል” የሚል ምክንያት በመስጠት ብቻ ተወላጅን ለመንቀል የማይቻል ስለመሆኑ ሟች ካለው ሃብት እጅግ አነስተኛ የሆነ ንብረት /ሀብት/ ለተወላጁ በኑዛዜ የሰጠ እንደሆነ በውጤት ደረጃ ተወላጁ የተነቀለ መሆኑን መገንዘብ የሚቻልና ተወላጁ ከሌሎች የጠቅላላ ኑዛዜ ተጠቃሚዎች ጋር እኩል መካፈል ያለበት ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 58822 criminal law/ criminal procedure/ exhibit/ appeal/ reversed judgment

  በወንጀል ድርጊት በኤግዚብትነት ተይዞ የነበረ ወርቅ ከተሸጠ በኋላ ጉዳዩ በይግባኝ ታይቶ የሥር ፍ/ቤት ውሣኔ ከተሻረ ሻጩ አካል የወርቁን ዋጋ መክፈል ያለበት በተሸጠበት ወቅት በነበረው ዋጋ ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 58920 extra contractual liability/ period of limitation

  ከውል ውጪ በሆነ ግንኙነት ተፈፃሚ ከሚሆነው የይርጋ ጊዜ ጋር በተገናኘ ለደረሰው ጉዳት ምክንያት የሆነው ድርጊት በወንጀል የሚያስቀጣና ጥፋት መሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ አጥፊው በወንጀል ጉዳይ ክስ ያልቀረበበትና ያልተቀጣ እንኳን ቢሆን በወንጀል ህጉ የተመለከተው የይርጋ ጊዜ ተፈፃሚ ሊደረግ የሚችል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2143 /1/ እና /2/ Download Cassation Decision

 • 59261 administrative law/ advocate licensing/ appeal procedure/

  የጥብቅና ፈቃድ ክልከላ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የሚቀርብ አቤቱታ ለሚመለከተው የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በይግባኝ ቀርቦ ታይቶ የሚወሰን እንጂ በቀጥታ ክልከላ እንዲወገድ በሚል ለፍ/ቤት አቤቱታ የሚቀርብበት ስላለመሆኑ አዋጅ ቁ. 199/92 አንቀጽ 29/1/ Download Cassation Decision

 • 59261 public pension/ power of social security agency/ marriage

  የማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ በህግ ከተጣለበት የጡረታ አበል የመክፈል ግዴታው ጋር በተያያዘ የአንድን ሰው ባልነት /ሚስትነት/ በማረጋገጥ የተሰጠ ውሣኔን የመቃወም መብት ያለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ህ/ቁ. 358 Download Cassation Decision

 • 59268 law of succession/ will/ witnesses to will/ contesting will

  ኑዛዜ ህጋዊ አይደለም እንዲሻር በሚል ተቃውሞ እስከቀረበ ድረስ በየትኛውም ህጋዊ መስፈርት መሰረት ፍ/ቤት ኑዛዜውን ውድቅ ሊያደርገው ስለመቻሉ በኑዛዜ ላይ የነበሩ ምስክሮች የሚሰጡት የምስክርነት ቃል ስለሚኖረው ዋጋ Download Cassation Decision

 • 59301 civil procedure/ execution of judgment/ staying execution/ appeal/

  ፍርድ የማይፈፀመው ፍርዱ በይግባኝ ስርዓት የተለወጠ እንደሆነ ወይም ፍርዱን ላለመፈፀም ህጋዊ ምክንያቶች ያሉ እንደሆነ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 378, 386 Download Cassation Decision

 • 59320 labor dispute/ suspension/ bonus payment/ backpayment

  አንድ ሰራተኛ በአሰሪው ታግዶ /የሥራ ውሉ ተቋርጦ/ በነበረበትና ባልሰራበት ዓመት አሰሪው ለሌሎች ሠራተኞች የከፈለውን የቦነስ ክፍያ ለመክፈል የማይገደድ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 43, 45/5/, 53 Download Cassation Decision

 • 59539 family law/ death of spouse/ common property/ period of limitation

  ከጋብቻ በሞት መፍረስ ጋር በተገናኘ የሚቀርብ የጋራ ንብረት ክፍፍል ጥያቄ ላይ ተፈፃሚ የሚሆነው ይርጋ መቆጠር የሚጀምረው ጋብቻው ከፈረሰበት ዕለት አንስቶ እንጂ ወራሽነት ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1846, 826/1/ Download Cassation Decision

 • 59579 labor dispute/ scope of application of labor proclamation

  በአዋጅ ቁ. 147/91 መሠረት በተቋቋመ ማህበር ውስጥ ላሉ ሰራተኞች አዋጅ ቁ. 377/96 ተፈፃሚ ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 59666 labor dispute/ attaching salary / collective agreement

  የሠራተኛ ደመወዝ ሊቀነስ የሚችለው በህግ፣ በህብረት ስምምነት፣ ወይም በሥራ ደንብ በተወሰነው መሰረት ወይም በፍ/ቤት ትዕዛዝ ብቻ ስለመሆኑ አሰሪ የሠራተኛን ደመወዝ በራሱ ውሣኔ ሊቀንስ፣ ሊይዝ ወይም የዕዳ ማቻቻያ ሊያደርግ የማይችል ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 59698 unlawful enrichment/ admission

  ንድ ሰው የሌላውን ሰው የሥራ ድካም ወይም በሌላው ሰው ሀብት በመገልገል በቂ ባልሆነ ምክንያት ጥቅም ያገኘ እንደሆነ አላግባብ ባገኘው ጥቅም መጠን ለባለሁብቱ ወይም በጉልበቱ ለደከመው ሰው የመካስ ግዴታ ያለበት ስለመሆኑ አንድ ሰው ባለዕዳ መሆኑን ያመነ እንደሆነ ዕዳው የታመነለት ሰው ባለዕዳው ዕዳውን ያመነበትን ምክንያት የማስረዳት /የማረጋገጥ/ ግዴታ የሌለበት ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 59711 tax law / tax appeal/ tax appeal commission

  በግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ውሣኔ ቅሬታ ያለው ግብር ከፋይ ይግባኙን ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት ለማቅረብ የሚችለው በጉባኤው የተወሰነበትን ግብር ይግባኝ ሙሉ በሙሉ ሲከፍል ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 286/94 አንቀጽ 112/4/ አዋጅ ቁ. 285/94 አንቀጽ 43/4/ Download Cassation Decision

 • 59851 tax law / Value Added tax (VAT)/ registration for VAT

  አንድ ግብር ከፋይ ለተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ግብር ከፋይነት ተመዘገበ የሚባለው በባለሥልጣኑ ከተመዘገበበት ዕለት ወይም ምዝገባው እንደሚፀና ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ ስለመሆኑ የተጨማሪ እሴት ታክስ ግብር ተመዝጋቢ የሆነ ሰው ከተመዘገበበት ዕለት ጀምሮ ለሚያደርገው ግብይት የተጨማሪ እሴት ታክስ ደረሰኝ ለተጠቃሚው ወዲያውኑ ያልሰጠ መሆኑ በወንጀል የሚያስጠይቀው ስለመሆኑ እውቅና ያልተሰጠው የሽያጭ መመዝገቢያ መጠቀም በወንጀል የሚያስጠይቅ ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 59906 labor dispute/ termination of contract of employment/ criminally charged worker

  የወንጀል ድርጊት ፈጽሟል በሚል በመጠርጠሩ የተነሳ ከሥራ ታግዶ የነበረና በኋላም የተሰናበት ሠራተኛ በወንጀል ተከስሶ ጥፋተኛ መሆኑ ተረጋግጦ የተሰጠ የፍ/ቤት ውሣኔ ያልቀረበ በመሆኑ ብቻ ስንብቱ ህገ ወጥ ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑና ጉዳዩን በማስተናገድ ላይ የሚገኝ ፍ/ቤት የሠራተኛውን ስንብት አግባብነት ለመወሰን ማናቸውንም ማስረጃ አስቀርቦ በመመልከት ለጉዳዩ እልባት መስጠት ያለበት ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 59979 property law/ constitution/ expropriation/ compensation/ period of limitation

  በህገ መንግስቱ አንቀጽ 40/8/ መሰረት ለተወሰደ ንብረት የሚጠየቅ ካሣ በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1143 እና 2143 በሁለት ዓመት ይርጋ የማይታገድ ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 60025 public pension/ pension increment

  በጡረታ የተገለለ ሰው በሌላ ሥራ ላይ በተቀጠረበት ጊዜ መንግስት ለጡረተኞች ያደረገውን የጡረታ ጭማሪ መሰረት በማድረግ አሰሪው የደመወዝ ጭማሪ እንዲያደርግለት የሚያቀርበው ጥያቄ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 60353 contract law/ interpretation / advocacy contract

  ጠበቃ የደንበኛውን ጉዳይ “እስከመጨረሻ ድረስ በመያዝ ለመከራከር” በሚል የሚያደርገው ስምምነት ጉዳዩ ሊያስኬድ የሚችል እስከሆነ ድረስ በአንድ ፍ/ቤት ሳይወሰን በይግባኝና በሰበር ደረጃ ሁሉ አገልግሎት የመስጠት ግዴታ የሚኖርበት ስለመሆኑ ጠበቃ ከደንበኛ ጋር ባለው ግንኙነት ደንበኛው ማድረግ ያለበትን ነገር ከህግ አንፃር የማስረዳትና ግልጽ የማድረግ ብሎም የማማከር ኀላፊነት ያለበት ቢሆንም በአንፃሩ አከራካሪ ጉዳይ በሌለበት ሁኔታ ክስና ክርክር ለማቅረብ የማይገደድ ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 60392 property law/ possessory action/ period of limitation

  ይዞታን አስመልክቶ ከሚነሳ የሁከት ይወገድልኝ አቤቱታ ጋር በተያያዘ ተፈፃሚ የሚሆነው የይርጋ ጊዜ መቆጠር ያለበት አቤቱታ አቅራቢው የይዞታ መብቱን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከሚመለከተው አካል ካገኘበት ቀን ጀምሮ እንጂ አቤቱታ የቀረበበት ድርጊት መፈፀም ከጀመረበት ዕለት አንስቶ ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1140, 1149, 1146/1/, 1144/2/ Download Cassation Decision

 • 60400 tax law/ custom duties/ criminal law/ contraband/

  አንድ ዕቃ /ንብረት/ ኮንትሮባንድ ነው ወይም የጉምሩክ ስርዓት ያልተፈፀመበት ነው በሚል በቁጥጥር ስር ሊውል የሚችልበት አግባብ የጉምሩክ ሥርዓት ያልተፈፀመበትን ዕቃ ወደ ጉምሩክ ክልል ማስገባት ወይም ከጉምሩክ ክልል ማስወጣት ዕቃው ኮንትሮባንድ እንዲባል የሚያደርግ ስለመሆኑና የኮንትሮባንድ ወንጀልን የሚያቋቁም ስለመሆኑ “የጉምሩክ ክልል” በሚል የተጠቀሰው ሃረግ አጠቃላይ የኢትዮጵያ የግዛት ክልልን የሚያመላክት ስለመሆኑ አዋጅ ቁ 622/2001 አንቀጽ 2/17/, 12/4/, 13/1/, 91/1/, 2/7/ Download Cassation Decision

 • 60464 labor dispute/ occupational accident/ extent of damage

  በሥራ ላይ ከሚደርስ ጉዳት ጋር በተያያዘ የጉዳቱን አይነትና መጠን መለየት የሚቻልበት አግባብ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 109/3/ /ሀ/ለ/ 101/2/ 100 96/1/ 99/1/ Download Cassation Decision

 • 60508 administrative law/ power of privatization agency

  የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ በህግ የተሰጠውን ስልጣን መሰረት በማድረግ አስቀድሞ የሰጠውን ውሣኔ በድጋሚ በማየት የተለየ ውሣኔ በሰጠ ጊዜ የተለወጠውን /የተሻረውን/ ውሣኔ መሰረት በማድረግ የተከናወኑ ተግባራትን ለማስተካከል ወይም የተከራካሪ ወገኖችን መብት ለማስተካከል ተገቢ የሆነ ትዕዛዝ ለመስጠት የሚችል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 349, 6 Download Cassation Decision

 • 60685 labor dispute/ private international law/ jurisdiction/ federal matter

  ከሥራ ክርክር ጋር በተገናኘ አሰሪና ሠራተኛው ያደረጉት የሥራ ቅጥር ውልን አስመልክቶ ክርክር ቢነሳ ጉዳዩን የሚገዛው ከኢትዮጵያ ሌላ /ውጭ/ የሆነ አገር ህግ መሆኑንና የሥራ ቦታውም ቢሆን ከኢትዮጵያ ውጪ እንዲሆን የተስማሙ እንደሆነ ጉዳዩ በአጠቃላይ የአለም አቀፍ የግለሰብ ህግ (private international law) ጥያቄን የሚያስነሳ በመሆኑ ጉዳዩን ለማየት ስልጣን ያለው ፍ/ቤት የትኛው ነው?፣ በየትኛው አገር ህግ መሰረት?፣ የመሳሰሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ስልጣን ያለው የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 25/88 አንቀጽ 11/2/ Download Cassation Decision

 • 60691 family law/ proof of marriage/ possession of status/ irregular union

  በሁለት ሰዎች መካከል የጋብቻ ሁኔታ መኖሩን ለማረጋገጥ የሚያዝ ጭብጥ በሁለቱ ሰዎች መካከል ከጋብቻ ውጪ እንደባልና ሚስት የመኖር ሁኔታ ስለመኖሩ ለማረጋገጥ በሚል ከሚያዘው ጭብጥ የተለየ ወይም አንድ አይነት ነው ሊባል የማይቻል ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ. 213/92 Download Cassation Decision

 • 60720 contract law / sale of immovable/ good faith/ ownership/ title deed/ document authentication

  የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል በቅን ልቦና የተደረገ ነው በሚል ምክንያት ብቻ በህግ ጥበቃ ሊደረግለት የማይችል ስለመሆኑ በህግ ፊት በማይፀና ሁኔታ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነት የምስክር ወረቀት የያዘ ሰው ይህንኑ ንብረት ለሌላ ሰው ለማስተላለፍ በውልና ማስረጃ ጽ/ቤት የሚያደርገው የሽያጭ ውል ህጋዊ ነው ሊባል የማይቻል ስለመሆኑ የማይንቀሳቀስ ንብረትን በሽያጭ ለ3ኛ ወገን ለማስተላለፍ መብት ከሌለው ሰው እያወቀ የሽያጭ ውል የፈፀመ ገዢ በቅን ልቦና የተደረገ ነው በሚል የሕግ ጥበቃ የሚደረግበት ምክንያት የሌለ ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 60725 family law/ contract of marriage/ modifying contract of marriage

  አስቀድሞ የተደረገን የጋብቻ ውል በማሻሻል የተደረገ የጋብቻ ውል ህጋዊ ተቀባይነት እንዲኖረው ፍ/ቤት ቀርቦ መጽደቅ ያለበት ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ. 213/92 አንቀጽ 47/1-3/ Download Cassation Decision

 • 61677 family law/ filliation/ paternity/ contesting paternity

  የልጅ አባት ነህ የተባለ ሰውን በተመለከተ የመካድ ክስ ሊቀርብ የሚችልበት አግባብ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ. 213/92 አንቀጽ 177/3/ Download Cassation Decision

 • 61788 family law/ divorce/ common property/ manner of partition

  ባልና ሚስት በፍቺ ወቅት የጋራ ንብረታቸውን ለመካፈል ስምምነት ላይ ያልደረሱ ከሆነና ንብረቱ በአይነት ሊካፈል የማይችል እንደሆነ ንብረቱ ተሸጦ የተገኘውን ዋጋ እኩል እንዲካፈሉ መደረግ ያለበት እንጂ በእጣ እንዲካፈሉ ሊወሰን የሚችልበት የህግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ. 213/92 አንቀጽ 103/1/ Download Cassation Decision

 • 61843 civil service/ appeal/

  የመንግስት ሰራተኞች አዋጅን መሰረት በማድረግ የሚነሳ ክርክር የሚስተናገድበት ህግና የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ይግባኝ ለማቅረብ ጊዜ ያለፈበትን አቤቱታ ተቀብሎ ለማስተናገድ የሚቻልበት የህግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 515/99 አንቀጽ 76/2/ አዋጅ ቁ. 6/2000 አንቀጽ Download Cassation Decision

 • 61872 Civil serivce/ public pension

  የመከላከያ ሰራዊት አባል ያልሆነ የመንግስት ሰራተኛ በፍቃዱ ሥራ በለቀቀ ጊዜ የስንብት ክፍያ ሊያገኝ የሚችልበት አግባብ የመንግስት ሰራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁ. 345/95 Download Cassation Decision

 • 62041 famy law/ filliation/ paternity/ DNA test

  አባትነት በፍርድ ሊነገር የሚችልባቸው ሁኔታዎች ላይ ሳይንሳዊ የደም ምርመራ (DNA test) በማስተባበያ ማስረጃነት ሊቀርብ የሚችል ስለመሆኑና ፍ/ቤቶች ተከራካሪ ወገኖች በዚህ ረገድ የሚያቀርቧቸውን አቤቱታዎች በአግባቡ ሊያስተናግዱ የሚገባ ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ. 213/92 አንቀጽ 144, 143 /ሠ/, 145 Download Cassation Decision

 • 62293 property law / expropriation/ compnesation

  ለህዝብ ጥቅም ሲባል በሚመለከተው የአስተዳደር አካል እንዲፈርስ መረጃ የደረሰው በመሆኑ ቤቱን ያፈረሰ ሰው የአስተዳደር አካሉ የዲዛይን ለውጥ አድርጐ ቤቱ ከፈረሰ በኋላ የግለሰቡን ይዞታ /ንብረት/ መፍረስ የማያስፈልግ መሆኑን መግለፁ ካሣ የመክፈል ግዴታውን ቀሪ የማያደርግ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 322/97 አዋጅ ቁ. 455/97 የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት art. 40/2/ Download Cassation Decision

 • 62370 labor dispute/ termination of contract of employment/ renewal of contract of employm

  ከሥራ ክርክር ጋር በተያያዘ ሠራተኞች እየሠሩ የሚገኙትን ሥራ በተመለከተ የሥራ ውል አላደሱም ወይም ለማደስ ፈቃደኛ አይደሉም በሚል ለማሰናበት የሚያስችል የህግ መሰረት የሌለ ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 62804 civil procedure/ execution of judgment/ power of execution bench

  ፍርድን የሚያስፈጽም የአፈፃፀም ችሎት የተሰጠውን ፍርድ በአግባቡ ለማስፈፀም ተስማሚ ነው ብሎ የገመተውን ትዕዛዝ ለመስጠት የሚያስችል ስልጣን ያለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 392/1/ Download Cassation Decision

 • 62858 contract law/ rent/ possession/ possessory action

  ተከራይ በይዞታው ያለውን የማይንቀሳቀስ ንብረት አከራይ ባለበት ዕዳ ምክንያት ባለገንዘብ የሆነ ወገን ንብረቱን መረከቡ በተከራዩ ላይ የሁከት ተግባር ፈጽሟል የማያስብል ስለመሆኑ የተከራዩ እና በንብረቱ ላይ መብት ያለው ባለገንዘብ የሚኖራቸው ተነፃፃሪ መብት Download Cassation Decision

 • 63042 contract law/ rent/ obligation of the lessor/ possession

  ተከራይ ለሆነ ወገን በተከራየው የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የባለቤትነት ወይም ሌላ መብት አለን በማይሉ 3ኛ ወገኖች አድራጐት ለሚነሳ ሁከት አከራይ ዋስትና እንዲሰጥ የማይገደድ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2914/1/, /2/, 2913/1/, /2/ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 158 Download Cassation Decision

 • 63195 family law/ filliation/ paternity/ DNA test/ civil procedure/ cost

  አባትነትን /ልጅነትን/ ከማረጋገጥ ጋር በተያያዘ በሚቀርብ አቤቱታና ክርክር የዲኤን.ኤ (DNA) ምርመራ እንዲደረግለት በመጠየቅ ክርክር የሚያቀርብ ወገን ለዚሁ የህክምና ማስረጃ የሚያስፈልገውን ወጪ የመሸፈን ግዴታ ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 259/1/ Download Cassation Decision

 • 63352 property law /expropriation/ compensation/

  ለህዝብ ጥቅም ሲባል ይዞታውን እንዲለቅ የተደረገ ሰው በመሬቱ ላይ የሰፈረውን ንብረት ለመተካት ከሚከፈለው ካሣ በተጨማሪ በይዞታው ላይ የነበረው ንብረት በመፍረሱ የተነሳ የተቋረጠ ገቢ /የታጠ ጥቅም/ ካሣ ሊከፈል የሚችልበት የህግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 455/97 አንቀጽ 2/1//ለ/, 7/1/2/ ደንብ ቁ. 135/99 Download Cassation Decision

 • 63635 labor dispute/ admission by employer/ period of limitation/

  ከአሰሪና ሠራተኛ ክርክር ጋር በተያያዘ አሰሪው ሠራተኛው የሚጠይቀውን የገንዘብ ክፍያ በማመን የፃፈው ደብዳቤ ሠራተኛው መብቱን ለማስከበር በሚያቀረበው የክፍያ ጥያቄ ላይ የሚቆጠረውን ይርጋ የሚያቋርጥ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 164/3/ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1852/1/ Download Cassation Decision

 • 63754 civil procedure/ execution of judgment/ detention of judgment debtor/ obstruction of execution of judgment

  በፍ/ብሔር ክርክር የተፈረደበት ሰው የፍርዱ አፈፃፀምን ለማሰናከል የተንቀሳቀሰ መሆኑ በተረጋገጠ ጊዜ እስከ ስድስት ወር በሚደርስ እስራት ሊቀጣ ስለመቻሉ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 389/1//ሀ//ለ/ Download Cassation Decision

 • 64079 labor dispute/unlawful termination of contract of employment/ reinstatement/ fault of worker

  አሰሪ ሠራተኛው ጥፋት እንደፈፀመ አውቆ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የማሰናበት እርምጃ አለመውሰዱ ስንብቱን ህገ ወጥ የሚያደርገው ቢሆንም ሠራተኛውን ወደ ሥራው እንዲመልስ ላይገደድ የሚችል ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 43/3/ Download Cassation Decision

 • 64354 civil procedure/ execution of judgment/ transfer of execution of judgment/ power of court

  ፍርድን የሰጠ ፍ/ቤት ፍርዱ እንዲፈፀምለት ለሌላ ፍ/ቤት የውክልና ስልጣን ስለሚሰጥበት አግባብና የፍርድ አስፈፃሚ ፍ/ቤት የስልጣን አድማስ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 371-455 Download Cassation Decision

 • 64590 extra contractual liability/ damage assessment/ equity

  በህክምና ጉድለት ሀላፊነት ሊከተል የሚችልበትና ካሣ የሚከፈልበት አግባብ የጉዳት ካሣን ለመወሰን የጉዳቱን ልክ በማስረጃ ለማረጋገጥ አዳጋች ሲሆን በርትዕ ለመወሰን የሚቻል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2090, 2102 Download Cassation Decision

 • 64734 labor dispute/ termination of contract of employment/ collective agreement

  በአሰሪና ሰራተኛ ስምምነት የሚዘጋጅ የህብረት ስምምነት ውስጥ የተካተቱ ሠራተኛን ያለማስጠንቀቂያ ከሥራ ለማሰናበት የሚያስችሉ ምክንያቶች ጥፋትን መሰረት ማድረግ ያለባቸው ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 27/1//ተ/ Download Cassation Decision

 • 64758 labor dispute/ bonus payment/ collective agreement

  አንድ ሠራተኛ ቦነስ ወይም ድጐማ ሊያገኝ የሚችለው ከአሰሪው ጋር በሚደረግ /በሚኖር/ ስምምነት እንጂ በህጉ አሠሪ ለሠራተኛው በቦነስ ድጐማ እንዲከፍል በአስገዳጅነት የተመለከተ ነገር የሌለ ስለመሆኑ የቦነስና ድጐማ አሰጣጥና አፈፃፀምን በተመለከተ በህብረት ስምምነት የተመለከተ ደንብና መመሪያ ተግባራዊ ሊደረግ የሚገባ ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 64819 tax law / custom duties/ criminal law/ contraband/ contraband carrying vehicles/ confiscation/

  የተሽከርካሪ ባለንብረትና ሹፌር በመሆን የኮንትሮባንድ ወንጀል በተሽከርካሪ በመታገዝ የተፈፀመ ስለመሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ የግለሰቡን የወንጀል ጥፋተኝነት ውሣኔ ተከትሎ ተሽከርካሪው እንዲወረስ ትዕዛዝ መሰጠት ያለበት ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 622/2001 አንቀጽ 91/2/, 2/1/ Download Cassation Decision

 • 64821 labor dispute/ promotion/ salary increment/ BPR

  የደረጃ እድገት በድርጅት ውስጥ በሥራ ላይ ባለ የእድገት አሰጣጥ ስርዓት እና ደንብ መሰረት የሚካሄድ ስለመሆኑ የደመወዝ ጭማሪ ሊገኝ የሚችለው በእድገት ወይም አሰሪው የደመወዝ ጭማሪ ማድረግ የሚችልበት አግባብ ኖሮት ሲጨመር ስለመሆኑ በመሠረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ (BPR) መሠረት የተደረገ የሥራ ምደባ የደመወዝ ጭማሪ የማያስገኝ ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 64988 labor dispute/ termination of contract of employment/ fault of worker

  ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያለውና በባለሃብትነት ሊያዝ የሚችልን የአሰሪ የሆነ ነገር ላይ ሠራተኛው ሆን ብሎም ሆነ በቸልተኝነት በማናቸውም ሁኔታ ጉዳት ያደረሰ መሆኑ በተረጋገጠ ጊዜ የሥራ ውሉን ለማቋረጥ በቂ ምክንያት ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 27/1/ሸ/ Download Cassation Decision

 • 65330 tax law / income tax/ employment tax/

  ማንኛውም ሰው በመቀጠር ምክንያት በሚያገኘው ማናቸውም ገቢ ላይ የገቢ ግብር የመክፈል ግዴታ ያለበት ስለመሆኑ በደረሰ የአካል ጉዳት ወይም በሞት አደጋ ምክንያት ከሚሰጥ የካሣ ክፍያ በስተቀር ሌሎች በማናቸውም ሁኔታ የሚከፈሉ የካሣ ክፍያዎች ከግብር ነፃ ናቸው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ ከሥራ መሰናበት ጋር በተገናኘ ለሰራተኞች የሚሰጥ የመልሶ ማቋቋሚያ የድጋፍ ክፍያ የሥራ ግብየሚከፈልበት ገቢ ነው ለማለት የሚያስችል የህግ መሰረት የሌለ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 286/94 አንቀጽ 10/1/, 2/10/, 1/11/ Download Cassation Decision

 • 65427 labor dispute/ public pension/ workers in public enterprise

  የጡረታ መብት ያለው የመንግስት ልማት ድርጅት ሠራተኛ ሊያገኝ ስለሚገባው ካሣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 9/1/ Download Cassation Decision

 • 65621 law of succession/ private international law/ place where succession opens/ foreign element

  ወደ ሌላ አገር ለሥራ በሄደበት ወቅት ህይወቱ ያለፈ ሰው ጋር በተያያዘ የግለሰቡ መደበኛ መኖሪያ ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ ውርሱ በኢትዮጵያ ውስጥ መከፈት ያለበት ስለመሆኑ የፍ/በ/ህ/ቁ. 826/1/ Download Cassation Decision

 • 65656 tax law / custom duties/ criminal law/ contraband/ confiscation

  በህግ አግባብ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት የተፈፀመበት ዕቃ/ንብረት/ የኮንትሮባንድ ዕቃን ለማሳለፍ በሽፋንነትና በከለላነት ያገለገለ መሆኑ በተረጋገጠ ጊዜ የጉምሩክ ባለስልጣን ይህን በሽፋንነትና በከለላነት ያገለገለውን ዕቃ ለመውረስ ስልጣን የተሰጠው ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 60/89 አንቀጽ 6/5/ 58/1/ /ለ/ 16-18 አዋጅ ቁ. 368/95 አንቀጽ 22 Download Cassation Decision

 • 65688 contract law/ mortgage/ property law/ transfer of immovable property/

  ለብድር በመያዣነት የተሰጠ የማይንቀሳቀስ ንብረት በመያዣ ውሉ መሰረት በህጉ አግባብ በዋስትና ከመያዙ በፊት በሽያጭ ለሦስተኛ ወገን ተላልፎና ስመ ሃብቱ ለገዢው ተላልፎ በተገኘ ጊዜ ሊኖር ስለሚችለው ውጤት የፍ/ብ/ህ/ቁ. 3051/2/ Download Cassation Decision

 • 66242 labor dispute/ payments due/ action for payment

  አንድ ሠራተኛ አሰሪው በአሰሪና ሠራተኛ ህጉ መሰረት ሊከፍለው የሚገባውና ያልከፈለው ክፍያ መኖሩን /እንዳለ/ በተረዳ ጊዜ አሰሪውን የመጠየቅ መብት ያለው ስለመሆኑ የአሰሪና ሠራተኛ ግንኙነት በቀጠለበት ሁኔታ ሠራተኛው በአንድ ወቅት ሊከፈለኝ /ሊጠበቅልኝ/ ይገባል በማለት ያቀረበው የመብት ወይም የክፍያ ጥያቄ በፍርድ ቤት ውድቅ መደረጉ በሌላ ጊዜ መብቱን ከመጠየቅ የሚያግደው ስላለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 12 የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 5, 216 Download Cassation Decision

 • 66306 labor dispute/ termination of contract of employment/ construction project

  የግንባታ ሥራ ተቋራጭ ድርጅት ከ3ኛ ወገን ጋር ባደረገው የግንባታ ሥራ ውል መነሻነት የቀጠረውን ሰራተኛ የግንባታ ሥራው ውል በመቋረጡ ምክንያት ማሰናበቱ ህገ ወጥ ነው ሊባል የማይችል ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 24/4/, 4/1/, 10, 9 Download Cassation Decision

 • 66727 law of succession/ liquidation of succession/ power of liquidator

  የውርስ ሃብት አጣሪ የሆነ ሰው የሟችን ንብረት በማጣራት ረገድ ሊኖረው የሚችለው የስልጣን አድማስ በወራሾች መካከል አንድን ንብረት በተመለከተ የውርሱ ሃብት አካል ስለመሆኑ ክርክር በተነሳ ጊዜ አጣሪው ግራ ቀኙ ያቀረቡትን ማስረጃ በሪፖርቱ ላይ በማስፈር ጉዳዩን ለሚመለከተው ፍ/ቤት ማቅረብ እንጂ ማስረጃዎቹን በራሱ መዝኖ አከራካሪው ንብረት የውርሱ ሃብት አካል ነው ወይም አይደለም በማለት ውሣኔ ለመስጠት ስልጣን የሌለው ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 66945 civil procedure/ change of venue/ jurisdiction/ power of regional courts

  የክስ ይዛወርልኝ (change of Venue) ጥያቄ ከተከራካሪ ወገኖች የሚነሳ ስለመሆኑና ፍ/ቤትም ጥያቄውን ሊያስተናግድ የሚችለው በህግ የተመለከቱት መስፈርቶች ተሟልተው ሲገኙ ብቻ ስለመሆኑ የክልል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤቶች ከሥራ ክርክር ጋር በተያያዘ የሚቀርቡ ክሶችን በመጀመሪያ ደረጃ ስልጣናቸው ለማስተናገድ የሚችሉ ስለመሆናቸው Download Cassation Decision

 • 66988 civil procedure/ execution of judgment/ transfer of execution of judgment/ power of court

  ፍርድን የሰጠ ፍርድ ቤት ፍርዱ በውክልና እንዲፈፀም ለሌላ ፍ/ቤት ትዕዛዝ ባስተላለፈ ጊዜ በውክልና ፍርድ ለማስፈፀም ስልጣን የተሰጠው ፍርድ ቤት ፍርድ ከሰጠው ፍርድ ቤት ማረጋገጫ እንዲላክለት ለመጠየቅ የሚችለው የፍርዱ ወይም የትዕዛዙ ግልባጭ ትክክለኛነት የሚያጠራጥር ስለመሆኑ በቂ ምክንያት ካለው ብቻ ስለመሆኑ ፍርድን በውክልና እንዲያስፈጽም ትዕዛዝ የደረሰው ፍርድ ቤት ስለፍርዱ ትክክለኛነት ወይም በግልባጮቹ ላይ ስለሰፈረው ነገር ሌላ መግለጫና ማብራሪያ ሳይጠይቅ በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ማስፈፀም ያለበት ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 67146 administrative law/ advocate licensing/ advocates code of conduct

  ጠበቃ የሆነ ሰው ደንበኛውን ወክሎ ለፍ/ቤት የሚያቀርበው አቤቱታ እውነት ስለመሆኑ በቅድሚያ የማረጋገጥ ግዴታ ያለበት ስለመሆኑ ማንኛውም ጠበቃ የህግ ሙያውን በሚያከናውንበት ጊዜ ሁሉ ለደንበኛው፣ ለሌሎች የህግ ባለሙያዎች፣ ለተከራካሪ ወገኖች፣ ለፍርድ ቤት፣ ለሙያው ብሎም በአጠቃላይ ለህብረተሰቡ ኃላፊነቱን በቅንነት፣ በታማኝነት እና በእውነተኛነት የመወጣት ግዴታ ያለበት ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 67280 administrative law/ advocate licensing

  በፌዴራል ፍ/ቤቶች በጥብቅና ለመስራት የሙያ ፈቃድ የሚሰጥበት አግባብ Download Cassation Decision

 • 67973 contract of carriage/ car accident/ liability of carrier

  የትራንስፖርት አገልግሎት በሚሰጥ ተሽከርካሪ ተሳፋሪ በመሆን ሲጓዙ ለሚደርስ ጉዳት አጓዡ ከኃላፊነት ነፃ ሊሆን የሚችልባቸው ልዩ ሁኔታዎች፣ ኃላፊ በሆነ ጊዜ የኃላፊነቱ መጠን እንዲሁም አጓዡ በህግ ከተደነገገው የጉዳት ካሣ መጠን በላይ በኃላፊነት ሊጠየቅ የሚችልባቸው ሁኔታዎች የንግድ ህግ ቁ. 595, 596, 599, 588, 597 የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2130, 2092, 2091 Download Cassation Decision

 • 97904 extra contractual liability/ strict liability/ dangerous activities/ high voltage electricity/ fault of vicitm

  የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የዘረጋቸው የኤሌክትሪክ መስመር ገመዶች ለሚያደርሱት ጉዳት ከኀላፊነት ነፃ ሊሆን የሚችለው ጉዳቱ የደረሰው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በተጐጂው ጥፋት መሆኑን በማስረዳት ብቻ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2086/2/ Download Cassation Decision

 
 
 

Google Adsense