volume 16

volume 16

 • 92152 labor dispute/ scope of application of labor proclamation/

  የአዋጅ ቁጥር 377/96 የተፈፃሚነት ወሰን በአሠሪና ሠራተኛ መካከል በሚቋቋም በቅጥር ላይ የተመሰረተ የሥራ ግንኙነት ላይ ተፈጻሚነት የሚኖረው ቢሆንም፤ በአዋጁ በግልጽ በተደነገጉ ሌላ ሕግ በሚገዛቸው ግንኙነቶች ላይ ተፈጻሚነት የማይኖረው ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀፅ 3 Download Cassation Decision

 • 101271 civil service/ administrative decision/ administrative law/ civil service tribunal

  አግባብ ባለው የዩኒቨርስቲ አካል በተሰጠ አስተዳደራዊ ውሳኔ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ቅሬታ ሲኖራቸው የይግባኝ መብት ያላቸው ስለመሆኑ፤ ይግባኙን የማስተናገድ ስልጣን የፌደራል የመንግስት ሠራተኞች አስተዳደር ፍ/ቤት ስለመሆኑ፣ Download Cassation Decision

 • 85815 civil procedure/ preliminary objection/ when preliminary objection raised

  ይርጋ በተመለከተ የሚቀርብ መቃወሚያ ከመልስ ጋር መቅረብ ያለበት ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 234ሐእና 244ሠ Download Cassation Decision

 • 86398 civil procedure/ opposition/ procedure of oppostion

  የመቃወም አቤቱታ የሚመራው በመደበኛው የክርክር አመራር ሰርዓት ስለመሆኑ፡- - የመቃወም አቤቱታን የሚሰማው ፍ/ቤት ስላለው ስልጣን፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 222፣223፣234፣358፣359፣360(1) እና(2) Download Cassation Decision

 • 88446 tax law/ presumptive tax

  አንድ የግብር ውሳኔ በግምት ስለሚወሰንበት አግባብ የግብር ህግ አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀፅ 69 Download Cassation Decision

 • 89148 property law/ acquisistion of ownership/ acquisistion by prrescription

  የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለይዞታ የሆነ ሠው ባለማቋረጥ ለ 15 ዓመታት ግብር በስሙ መክፈሉ ከተረጋገጠ የዚሁ ንብረት ባለቤት መሆን ስለመቻሉ፣ የፍ/ህ/ቁ 1168(1) Download Cassation Decision

 • 90361 contract law /period of limitation

  በሕግ ተለይቶ የተወሰነ የይርጋ ጊዜ የመቋረጥ እና ያለመቋረጥ ጉዳይ አከራካሪ ነጥብ ሆኖ ሊነሳ የሚችለው የይርጋውን መቆጠር ያቋርጠዋል የተባለው ምክንያት የተከሰተው የይርጋው ጊዜ ከመሙላቱ በፊት በሆነ ጊዜ እንጂ የይርጋው ጊዜ የሞላ ወይም ያለፈ በሆነ ጊዜ ጭምር ስላለመሆኑ ፡- የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.1851 Download Cassation Decision

 • 90434 commerical law/ check/ background contract in connection with check

  ለቼኩ መሰጠት መሰረት የሆነውን ውል እና ለጉዳዩ አወሳሰን ተገቢነት ያለውን ህግ ሳይመለከቱና በተገቢው የክርክር አመራር ስርዓት ፍሬ ነገሩን ሳያጣሩ የሚሰጥ ዳኝነት ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ፣ Download Cassation Decision

 • 90570 labor dispute/ obligation of worker/ effect of non compliance of work instruction

  አንድ ሠራተኛ በስራ ውሉ እና በስራ ደንቡ መሠረት በአሰሪ የተሰጠውን ትዕዛዝ የመፈፀም ግዴታን አለመወጣቱ ስለሚያስከትለው ውጤት፣ በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ አንቀጽ 13(2)፣13(7) Download Cassation Decision

 • 90959 contract law/ donnation/ property law/ ownership

  በህግ ፊት የሚፀና ስጦታ ለማድረግ ሰጪው ስጦታ በተደረገበት ንብረት ላይ መብት ሊኖረው የሚገባ ስለመሆኑ፤የባልና የሚስት የጋራ በሆነ ንብረት ላይ አንደኛው ተጋቢ ብቻውን የሚያደርገው ስጦታ ዋጋ የሌለው ስለመሆኑ፣ Download Cassation Decision

 • 91329 civil procedure/ pleading/ particulars in statement of claim

  አንድ ክስ ሲቀርብ በክስ ማመልከቻው ላይ መገለፅ ከሚገባቸው ነገሮች መካከል አንዱ የክሱ ምክንያት እና ለክሱ ምክንያት የሆኑት ነገሮችና እነዚሁ የተፈጠሩበት ጊዜና ስፍራ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ8ዐ(2)፣213(1)፣216(1)፣222(1)(ረ) Download Cassation Decision

 • 91493 civil procedure/ pleaders/ court representation by relatives

  አንድን ሰው በመወከል በፍርድ ቤት ቀርቦ ለመሟገት በህጉ የተቀመጠውን የዝምድና ደረጃ ወይም በህጉ የተቀመጡትን መስፈርቶች የሚያሟላ የውክልና ስልጣን የሚያስፈልግ ስለመሆኑ፣ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/ 58(ሀ)፣63 Download Cassation Decision

 • 91622 civil procedure/ exection of judgment/ property law/ title deed/ administrative law

  በፍርድ ቤት የተሰጠ ውሣኔ ሕጋዊ ባልሆነ እና ውሳኔውን ውጤት አልባ በሚያድርግ መልኩ ውድቅ ሊደረግ የሚችልበት አግባብ ስላለመኖሩ፣ የአስተዳደር አካል በባለቤትነት ማረጋገጫ ማስረጃ አሰጣጥ ላይ ፍጹም የሆነ አስተዳደራዊ ስልጣን ያለው ስላለመሆኑ፣ ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 378፣ 392 የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1195 እና 1196 Download Cassation Decision

 • 91643 unlawful enrichment/ undue payment/ interest/ breach of trust

  የማይገባውን ክፍያ የከፈለ ሰው ገንዘቡን ከከፈለበት ቀን አንሥቶ ሕጋዊ ወለድ እንዲከፈለው ለመጠየቅ የሚችለው፣ ገንዘቡን የተቀበለው ሰው እምነትን በሚያጓድል ሁኔታ ክፍያውን ተቀብሎት በሆነ ጊዜ ብቻ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሕ/ቁ/ 2164(2) Download Cassation Decision

 • 91745 civil procedure/ jurisdiction/ arbitration/ cooperatives/ constitution

  በህብረት ሥራ ማህበራትና በአባሎቻቸው ወይም በቀድሞ አባላቸው ወይም በህብረት ስራ ማህበር አባላት ወይም የቀድሞ አባላትና በማህበሩ አመራር መካከል የሚነሳ ክርክር በመጀመሪያ ደረጃ የሽምግልና ጉባኤው ውሳኔ ሳይሰጥበት ፍርድ ቤቶች ተቀብለው ዳኝነት ለማየትና ለመወሰን የማይችሉ ስለመሆኑ፣የኢ.ፌ.ዲ.ሬ ህገ መንግስት አንቀጽ 37፣ አንቀጽ 79(1) እና አዋጅ ቁጥር 147/91 አንቀጽ 49 Download Cassation Decision

 • 92035 civil procedure/ exection of judgment/ valuation of immovable property

  ለፍርድ ማስፈጸሚያ የቀረበን የማይንቀሳቀስ ንብረት ለመጀመሪያ የሐራጅ ሽያጭ የሚቀርብበትን የዋጋ ግምትን አስመልክቶ የተነሳ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን፣ፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 423(2)(ሀ) Download Cassation Decision

 • 92040 extra contractual liability/ mode of payment of damage/ pension age/ power of court

  የጉዳት ካሳ አከፋፈልን በተመለከተ በአንድ ጊዜ ሊሆን የሚችል መሆን ያለመሆኑን ለመወሰን ለፍርድ ቤቱ የተተወ ስለመሆኑ፣ በአንድ የግል ድርጅት ውስጥ ተቀጣሪ የሆነ ግለሰብ የአካል ጉዳት በሚደርስበት ወቅት የጉዳት ካሳው አሰላሉ የጡረታ መውጫ እድሜውን መሰረት ቢያደርግ ተገቢ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2154፣2090፣2091፣2095 አዋጅ.ቁ715/2003 Download Cassation Decision

 • 92043 civil procedure/ institution of a case/ appeal/ cross appeal/ procedure for corss appeal

  አንድ ክስ እንደቀረበ የሚቆጠረው ክስ የቀረበበት ጽሁፍ በፍ/ቤት በቀረበ ጊዜ በመሆኑ፡- የመስቀለኛ ይግባኝ ክርክር ስለሚመራበት የህግ አግባብ፣ በተከራካሪ ወገኖች መካከል የሚቀርብን መስቀለኛ ይግባኝን በተመለከተ በህግ በግልፅ የተቀመጠ ድንጋጌ ባለመኖሩ ምክንያት በመደበኛነት የተቀመጡት የስነ ስርዓት ድንጋጌዎች ተፈፃሚ መሆን ያለባቸው ስለመሆኑ፣መልስ ሠጪው ወገን የሚያቀርበው ይግባኝ ማመልከቻ ግልባጭ ለይግባኝ እንዲደርስ ሊደረግ የሚቻለው ይግባኙ ያልተሰረዘ ከሆነ ብቻ ስለመሆኑ፣ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 213(1) ፣337 ፣338 ፣ 340(2) Download Cassation Decision

 • 92290 civil procedure/ execution of judgment/ property of judgment debtor

  አንድ ፍርድ ሊፈጸም የሚገባው በፍርድ ባለእዳውና በሕግ አግባብ እንዳይያዙ ከሚጠቀሱት ንብረቶች/መብቶች ውጪ ባሉት የፍርድ ባለእዳ ንብረቶች /መብቶች ስለመሆኑ፣ በህግ አግባብ መብቱን ባስተላለፈ ንብረት ላይ የቀድሞ ባለቤት በድጋሜ ሽያጭ የሚፈጽምበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 378 Download Cassation Decision

 • 92302 labor dispute/ termination of contract of employment/ payments due/ period of limitation

  በአሰሪና ሰራተኛ መካከል ያለ የሥራ ግንኙነት በተቋረጠ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ የክፍያ ጥያቄ ያለበት አካል መብቱን ካልጠየቀ በይርጋ የሚታገድ መሆኑን፣ በተጨማሪነት ስድስት ወር ከሞላው(ካለፈው) በኃላ የሁለቱ የስራ ግንኙነት ቢቀጥል እንኳን አስቀድሞ የታገደውን የስንብት ክፍያ ጥያቄን ከአዋጁ ድንጋጌ ይዘት አኳያ የይርጋ ጊዜን ሊያቋርጥ የሚችል ስላለመሆኑ፣ አዋጅ 377 አንቀፅ 162(3)፣162(4) Download Cassation Decision

 • 92410 labor dispute/ waiver of right by worker/ void waiver

  በአሰሪና ሰራተኛ መካከል የሚፈጠር የስራ ግንኙነትን መነሻ በማድረግ ሰራተኛው በሕግ የተሰጠውን መብቱን ለመተው የሚያደርገው ስምምነት የህግ ውጤት የማይኖረው ስለመሆኑ፡- አዋጅ ቁጥር 377/1996 በአንቀጽ 25(1) Download Cassation Decision

 • 92423 labor dispute/ contract of employment/ good faith/ training and education

  -በአሰሪና ሰራተኛ መካከል በሚደረግ የውል ግንኙነት ተዋዋይ ወገኖች የገቡትን ግዴታ በቅንነት ይፈፅማሉ ተብሎ የሚገመት ስለመሆኑ፣ - በአሰሪውና ሰራተኛው መካከል በሚደረግ የሥልጠናና የት/ት ውል መሰረት አሰሪው የሚጠበቅበትን ድጋፍ ለሰራተኛው የማድረግ ግዴታ ያለበት ስለመሆኑ፣ የፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 1732፣አዋጅ ቁጥር 377/96 Download Cassation Decision

 • 92537 tax law/ custom duty/ contraband

  ህጋዊ ቀረጥ የተከፈለበት ዕቃ ህጋዊ የግምሩክ ስርዓት ካልተፈፀመበት ዕቃ ጋር ተቀላቅሎ ከተያዘ እና ከተወረሰ በህጋዊ መንገድ ዕቃው ሲገባ የተከፈለው ቀረጥ(tax) እንዲመለስለት የዕቃው ባለቤት የሚጠይቅበት የህግ ስርዓት ስላለመኖሩ፣ አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀፅ 104(3) Download Cassation Decision

 • 92903 civil procedure/ appeal/ procedure in case of reversal

  ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በሚሰጠው የፍርድ ውሳኔ የመጀመሪያውን ደረጃ ፍርድ ቤት ፍርድን ካሻሻለው ወይም የለወጠው እንደሆነ በትችቱ ላይ ለይግባኝ ባዩ የሚገባውን ዳኝነት ዘርዝሮ መግለፅ ያለበት ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 182(1)፣348(1) Download Cassation Decision

 • 93104 unlawful enrichment/ undue use of another's property

  አንድ ሰው የሌላውን ሰው የሥራ ድካም ወይም በሌላው ሰው ሀብት በመገልገል በቂ ባልሆነ ምክንያት ጥቅም ያገኘ እንደሆነ አላግባብ ባገኘው ጥቅም መጠን ለባለሀብቱ ወይም በጉልበቱ ለደከመው ሰው የመመለስና የመካስ ግዴታ ያለበት ስለመሆኑ፣ በፍ/ሕ/ቁ 2162፣2164(1) Download Cassation Decision

 • 93171 civil procedure/ change of venue/ closed civil case

  በውሳኔ በተቋጨ የክስ መዝገብ ላይ የክስ ይዛወርልኝ አቤቱታ ለማቅረብ የማይቻል ስለመሆኑ፣ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 31 Download Cassation Decision

 • 93220 civil procedure/ jurisdiction/ cassation procedure/ Addis Ababa city court

  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰበር ሰሚ ችሎት ማስረጃ የመመዘን እና ፍሬ ጉዳይን የማጣራት ስልጣን የሌለው ስለመሆኑ፣ የአ.አ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 42(2) Download Cassation Decision

 • 93346 law of succession/ contract law/transfer of rent right

  ትዳር ያለው አንድ የመንግስት ቤት ተከራይ በሞት በተለየ ጊዜ የተከራይነት መብቱ ለሌላኛው ተጋቢ ሊተላለፍ የሚችለው አግባብነት ባለው መመሪያ ስለመሆኑ፣ Download Cassation Decision

 • 93358 civil service/ jurisdiction

  በመንግስት በጀት በከፊልም ሆነ በሙሉ የሚተዳደሩ መስሪያ ቤቶች ውስጥ የሚፈጠሩትን የመብት ጥያቄዎች መመራት ያለበት በመንግስት ሰራተኞች አዋጅ መሆን አለበት፡፡ -በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 3 (2)(ሠ) ፣ አዋጅ 515/1999 አንቀጽ 3 በአዋጅ 65ዐ/2ዐዐ1፣ ደንብ ቁጥር 214/2ዐዐ3 እና 21ዐ/2ዐዐ3 Download Cassation Decision

 • 93511 labor dispute/ termination of contract of employment/ termination by worker/ notice

  - አንድ የስራ ውል በሰራተኛው አነሳሽነት እንደነገሩ አግባብ በማስጠንቀቂያ ወይም ያለማስጠንቀቂያ ሊቋረጥ የሚችል ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 31 እና 32 Download Cassation Decision

 • 93532 labor dispute/ evidence law/ burden of proof/ back payment of salary

  -በፍትሐ ብሔር ክርክር አንድ ግዴታ እንዲፈጸምለት የሚጠይቅ ሰው የግዴታውን መኖር ማስረዳት እንደሚጠበቅበት እና በአንፃሩም ግዴታ ፍርስ ነው ወይም ተለውጧል የሚለው ወገንም ይህንኑ የማስረዳት ግዴታ ስለመሆኑ፣ ሠራተኛው በራሱ ጉድለት ባልሆነ ምክንያት ላልሰራው ስራ ደሞዝ ስለሚጠይቅበት አግባብ፣ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 በአንቀጽ 54(1)፣54(2) በፍ/ሕ/ቁ. 2001(1) እና(2) Download Cassation Decision

 • 93813 labor dispute /contract of employment for definite period/

  በአሰሪና ሰራተኛ መካከል በሚደረግ የስራ ግንኙነት የተነሳ ለተወሰነ ጊዜ ለፕሮጀክት ስራ መደብ የተቀጠረ ሠራተኛ ከአንድ የፕሮጀክት ወደ ሌላ የፕሮጅክት ስራ አዘዋውሮ ማሰራት በአሰሪውና ሰራተኛው መካከል ላልተወሰነ ጊዜ የስራ ግንኙነት ተፈጥሯል ለማለት የማያስችል ስለመሆኑ፣ አዋጅ. 377/96 አንቀፅ 30፣ አንቀፅ 10 Download Cassation Decision

 • 93828 labor dispute/ severance pay/ high salary

  አንድ ሰራተኛ ሲከፈለው የነበረው የደሞዝ መጠን ከፍተኛ መሆን የሥራ ስንብት ክፍያን ከመጠየቅ የሚያግደው ስላለመሆኑ፣ አዋጅ 377/1996 አንቀጽ 39 እና አዋጅ ቁጥር 494/1998 አንቀጽ 2(2)ሸ Download Cassation Decision

 • 93987 civil procedure/ oppostion/ procedure for opposition

  በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 358 መመዘኛ የሚያሟላ አቤቱታ አቅራቢ (ፍርድ ተቃዋሚ) የሚቃወመው ፍርድ በይግባኝ ያልተሻረ (ዋጋ ያለው) እና ያልተፈፀመ መሆን ያለበት ስለመሆኑ፣ Download Cassation Decision

 • 94070 criminal law/ criminal procedure/ guilty verdict

  በወንጀል ጉዳይ ፍርድ በሚሰጥበት ጊዜ ተከሳሹን ጥፋተኛ ሆኖ ያስገኘው ሕግ በፍርዱ ውስጥ መገለጽ እንደሚገባውና የጥፋተኝነት ውሳኔው የሚሰጥበት ድንጋጌ መፈጸሙ ከተረጋገጠው የወንጀል ፍሬ ነገር ጋር በጥንቃቄ መነጻጸር የሚገባው ስለመሆኑ፣ ወ/መ/ሕ/ስ/ስቁ. 149 Download Cassation Decision

 • 94102 labor dispute/ jurisdiction/ regional cassation bench/ federal cassation

  በአሰሪና ሰራተኛ መካከል በተነሳ ክርክር በመጀመሪያ ደረጃ የቀረበው ለክልል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ከሆነ ጉዳዩ በተነሳበት ክልል የሰበር ችሎት የተደራጀ እስከሆነ ድረስ በክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ሳይታይ እና ውሳኔው የመጨረሻ መሆኑ ሳይረጋገጥ በቀጥታ ለፌዴራል ጠ/ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቀርቦ ሊስተናገድ የሚችልበት ህጋዊ ምክንያት የሌለ ስለመሆኑ፣ በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 5(6)፣ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 138(1)፣ Download Cassation Decision

 • 94181 extra contractual liability/ civil procedure/ no denial/ plurality of plaintiffs

  ከሳሽ የጠየቀውን የካሳ ገንዘብ ተከሳሽ በግልጽ አለመካዱ የካሳውን መጠን ሙሉ ወይም በከፊል እንዳመነ የማያስቆጥር ስለመሆኑ፤ ሰዎች አንድ ሆነው በአንድ ጉዳይ ካሳ እንዲከፍሉ የተገደዱ እንደሆነ በአንድነት እያንዳንዳቸው ሀላፊ እንደሆኑና ለበደሉ ተግባር አነሳሽ በሆነው በዋና አድራጊው እና በተባባሪዎች መካከል ልዩነት የሚደረግ ስለመሆኑ፤ በፍ/ህ/ቁ 2155/1/ እና /2/ የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 83 Download Cassation Decision

 • 94227 criminal law/ criminal procedure/ trial in absentia

  አንድ ተከሳሽ በሌለበት የተሰጠበት ውሣኔ እንዲነሳለት የሚያቀርበውን ማመልከቻ በመቀበል ከሚቻልባቸው ምክንያቶች አንዱ መጥሪያ ለተከሳሹ ያለመድረስ ጉዳይ ስለመሆኑ፣ የወ/መ/ሕ/ሥ/ ሥ/ቁ. 199ሀ Download Cassation Decision

 • 94293 civil procedure/ pending case/ issue in dispute

  በአንድ ክርክር ችሎት በመታየት ላይ ያለን ጉዳይ በሌላ ችሎት ተያያዥነት ባለው ጉዳይ ውሳኔ ተሠጥቶ ከሆነ ጉዳዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት የተላለፈውን ውሳኔ በአግባቡ በማጤን በጭብጥነት ሊይዘው ስለሚችልበት አግባብ፡ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.247 እና 248 Download Cassation Decision

 • 94302 civil procedure/ pleaders/ representatives to a suit/ effect of improper representation

  -በፍርድ ቤት በሚደረግ ክርክር ስለዋናዎቹ ባለጉዳዮች በመሆን ሌሎች ሰዎች በተሟጋችነት ሊቀርቡ ስለሚችሉበት ስርዓት፣ በህጉ የተቀመጠውን መስፈርት አሟልቶ አለመገኘት የሚያስከትለው ህጋዊ ውጤት፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 57፣ 58(1)፣ 60፣61፣62፣ 63 እና 197(1) Download Cassation Decision

 • 94322 law of succession/ partition of succession property/

  የውርስ ንብረት ክፍፍልን በተመለከተ በውርስ ህጉ የተመለከቱትን የውርስ ንብረት ክፍፍልን የሚገዙትን ድንጋጌዎች ይዘት መንፈስና አላማ የተከተለና ያገናዘበ መሆን ስላለበት፣ የፍ/ህ/ቁ 1079፣1082፣1083፣1086 Download Cassation Decision

 • 94404 criminal law/ suspension of penalty/ gurantee

  አንድ በወንጀል ድርጊት ቅጣት የተጣለበትን ተከሳሽ ቅጣቱ እንዳይፈፀም ፍርድ ቤቱ ለማድረግ የሚችለው ጥፋተኛው በመልካም ጠባይ እንደሚመራ ፣ እንዲፈፅም የተሰጠውን ግዴታ እንደሚቀበል ፣ በሚቻለው መንገድ ሁሉ በጥፋቱ የደረሰውን ጉዳት እንደሚክስ ወይም ለተበዳዩ እንደሚከፍል እና ለዚሁ ጉዳይ በተወሰነ ጊዜ ውስጥ የፍርድ ቤቱን ወጪ እንደሚከፍል ማረጋገጫ ከሰጠ ስለመሆኑ፣ ከዚህም በተጨማሪ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛው ለገባበት ግዴታ አፈጻፀም መተማመኛ ዋስትና የሚጠይቅ ስለመሆኑ፣ አንቀጽ 197/1/ እና/2/ Download Cassation Decision

 • 94571 civil procedure/ exection of judgment/ valuation of immovable property

  አንድ ንብረት ወይም ቤት የወቅቱ የገበያ ዋጋ ሊቆረጥ የሚችለው ከተቻለ በስምምነት ይህ ካልተቻለ ደግሞ ቤቱ ለጨረታ ቀርቦ በሚያወጣው ከፍተኛ ዋጋ መሰረት ስለመሆኑ፣ Download Cassation Decision

 • 94837 contract law/ contract of surety/ form of surety/ limit of obligation/ voidable

  የዋስትና ግዴታ ግልፅ መሆን ያለበት ስለመሆኑ ኃላፊነቱም ግዴታ ከተገባለት እዳ ወሰን ለማለፍ እንደማይችል እና እንዲሁም ይህ ለአፈፃፀሙ ግዴታ የተገባለት የእዳመጠን ወይም የገንዘብ ልክ በዋስትና ውሉ ካልተገለፀ ዋስትናው ፈራሽ ስለመሆኑ፣ ከዚህ በተጨማሪ ገና ለወደፊት ሊደርስ ለሚችል ግዴታ አፈፃፀምም ዋስ ለመሆን እንደሚችል ነገር ግን በግልፅ ለምን ያህል እዳ ተጠያቂ ሊሆን እንደሚችል በግልፅ በውሉ ላይ መስፈር ያለበት ስለመሆኑ፣ ፍ/ብ/ህ/ቁ 1922(2)(3)፣ 1925(1) Download Cassation Decision

 • 94839 labor dispute/ jurisdiction/ jurisdiction of federal courts

  -በሥራ ተከራካሪ ወገኖች ማንነት የፍርድ ቤቶችን ሥልጣን የክልል ወይም የፌዴራል ብሎ ለመወሰን እንደወሳኝ መለኪያ ሊወስድ የሚገባ ስላለመሆኑ፣ ኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 50፣ 51 እና 80 ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 14 እና 15፣አዋጅ ቁ.25/88አንቀፅ5 Download Cassation Decision

 • 94869 property law/ possession/ possessory action/

  ሁከት ፈጥረሀል ተብሎ የተከሰሰ ሰው ሁከት ፈጥረሀል በተባለበት ነገር ላይ በፍርድ የተረጋገጠ መብት ካለው ሁከት ፈጠረ ሊባል ስላለመቻሉ፣ የፍ/ህ/ቁ 1149(3) Download Cassation Decision

 • 94889 labor dispute/ promotion/ transfer/ training/ individal labor dispute

  በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ በሠራተኛ ዕድገት ዝውውርና ሥልጠና በሚመለከት አሠሪው የሚወስዳቸው እርምጃዎች በፍርድ ሊታዩና ሊያልቁ የሚችሉ ጉዳዮች እንደሆኑ፣ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገመንግስት አንቀፅ 37፣ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 138፣142 ንዑስ አንቀጽ 1/ሰ/ እና ከአንቀጽ 147 ንዑስ አንቀጽ 1/ሀ/ Download Cassation Decision

 • 94931 labor dispute/manager/ period of limitation

  የሥራ መሪ መብቱን ለማስከበር የሚችልበት የይርጋ ጊዜ አቆጣጠር፣ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1846 Download Cassation Decision

 • 95026 civil procedure/ evidence law/ issue in dispute/relevance of evidence/ ruling on evidence

  ከጭብጥ አያያዝ ጋር በተገናኘ በአንድ ወገን ተቆጥሮ የቀረበን ማስረጃ ለጉዳዩ አግባብነት የለውም በሚል ወይም ህጋዊ ተቀባይነት ባለው ሌላ ምክንያት መሰማት አይገባውም የሚል ግልፅ ትእዛዝ ሳይሰጥበት የክርክሩ ጭብጥ በአንደኛው ወገን ማስረጃ ላይ ብቻ ተመስርቶ ውሳኔ እንዲያገኝ መደረጉ ተገቢ የክርክር አመራር ስርዓት ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 255፣257፣258፣259 Download Cassation Decision

 • 95033 civil procedure/ intervention by third party/ jurisdiction/ effect of intervention on jurisdiction

  በአንድ ክርክር ሂደት ወደ ክርክሩ እንዲገባ የተደረገ ተከራካሪ ወገን ጉዳዩን የፌዴራል የሚያደርገው የነበረ ሁኖ እያለ ክሱን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤት ስልጣን ሳይኖረው ስረ ነገሩን አስተናግዶ ዳኝነት ከሰጠ በኋላ ይኼው ተከራካሪ ወገን በይግባኝ ደረጃ በነበረው ክርክር የተሠጠውን ዳኝነት ተቀብሎ ከወጣ በኋላ በሌሎች ጉዳዩን የፌዴራል ሊያደርጉ በማይችሉ ተከራካሪ ወገኞች መካከል የተሰጠው ውሳኔ ከመነሻውም የፌዴራል ጉዳይ ነው ብሎ መወሰን አግባብነት የሌለው ስለመሆኑ፣ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 43(1)፣ አዋጅ ቁ.25/88 Download Cassation Decision

 • 95392 labor dispute/ termination of contract of employment/ duration of contract/ notice/ salary payment

  - የሥራ ውሉ ሊጠናቀቅ የአንድ ወር ጊዜ ብቻ የቀረው በሆነ ጊዜ አሰሪው የስራ ውሉ ከሚጠናቀቅበት የጊዜ ገደብ ከ1ወር በፊት የሥራ ውሉን ያቋረጠ እንደሆነ ሊከፍል የሚገባው የ1 ወር ደመወዝ ብቻ እንጂ የማስጠንቀቂያ ክፍያ እንዲከፍል የሚገደድበት ህጋዊ ምክንያት የሌለ ስለመሆኑ፤ አዋጅ ቁጥር377/96 አንቀፅ 43(4)(ሀ)፣36 Download Cassation Decision

 • 95438 criminal law/ retroactive of criminal law/ favourable law

  የተሻሻለው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ከመውጣቱ በፊት በተፈፀመ ወንጀል ከተፈረደበት እና ሆኖም ግን ወንጀሉ በተፈፀመበት ጊዜ ስራ ላይ ከነበረው የቅጣት አወሳሰን ይልቅ የተሻሻለው መመሪያ ለተከሳሹ ቅጣትን የሚያቀልለትና ተከሳሹን የሚጠቅም ሆኖ ከተገኘ ይሄው የተሻሽለው መመሪያ ላይ ያለው ቅጣት የሚፈጽምበት ስለመሆኑ፣ የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ የወንጀል ህግ አተረጓጓም መርሆን መከተል ያለበት ስለመሆኑ፣ ወንጀል ህጉ ቁ 6 Download Cassation Decision

 • 95451 labor dispute/ provident fund/ set off/ debt of worker

  አንድ ሰራተኛ የሥራ ውሉ በሚቋረጥበት ጊዜ በስሙ የሚቀመጠው የፕሮቪደንት ፈንድ ለእዳ ማስቻያ ሊሆን የሚችለው ሰራተኛው ዕዳ እንዳለበት ያመነ እንደመሆኑ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀፅ 59(1) Download Cassation Decision

 • 95522 labor dispute/ termination of contract of employment/ notice/ fraud by worker

  አንድ ሰራተኛ በስራ ላይ እያለ የማጭበርበር ድርጊት በመፈፀሙ ምክንያት ያገኘው ጥቅም ባይኖርም፣ ወይም በሌላ ሰው ላይ ጉዳት ባያደርስም ወንጀልነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ የስራ ውሉን ያለማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ በቂ ስለመሆኑ፣ የአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 27(1(ሐ)) Download Cassation Decision

 • 95538 property law/ land law/ land allocation/ tigray land law

  አንድ ሰው በድልድል ያገኘውን መሬት ሌላ ሰው ሊወስድበት የሚገባው በሕጉ የተመለከቱ ምክንያቶች ሲኖሩ ብቻ ሰለመሆኑ፣ የት/ብ/ክ/መንግስት የገጠር መሬት አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 136/2000 አንቀጽ 31፣5፣12፣14 እና 22 ደንብ ቁ. 48/2000 “ን” በደንብ ቁጥር 48/2000 14፣15፣16 አዋጅ ቁጥር 456/1997 በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሰት አንቀጽ 37፣40(3) እና 79 Download Cassation Decision

 • 95620 civil procedure/ pleadings/ amendment of statement of claim/ procedure after amendment

  ተሻሽሎ በቀረበው ክስ ላይ ግራ ቀኙ መልስ እንዲሰጡበት ሳይደረግ እና የመከላከያ መልሳቸውን ሳያቀርቡ ተሻሽሎ የቀረበውን ክስ መሰረት አድርጎ ፍርድ መስጠት ተገቢ ስላለመሆኑ፣ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 234(1)(ሠ)(መ)፣91(1) Download Cassation Decision

 • 95649 civil procedure/ correction of error/

  በተከራካሪ ወገኖች በአንድ የመጨረሻ ውሳኔ ላይ የእርማት አቤቱታ ሊቀርብ የሚችለው ውሳኔ ያረፈበት ነጥብ ላይ ብቻ ስለመሆኑ፣ ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 208 Download Cassation Decision

 • 95875 criminal law/ criminal procedure/ trial in absentia/ appeal

  አንድ ሰው በወንጀል ተከሶ በሌለበት የጥፋተኝነት ውሳኔ ከተሰጠ በኃላ ጥፋተኛ የተባለው ስው ቀርቦ በሌለበት የተሰጠውን ውሳኔ ለማስነሳት ሳይሆን በዋናው ጉዳይ ላይ በቀጥታ ይግባኝ ከጠየቀ በኃላ በሌለሁበት የተሰጠው ውሳኔ ይነሳልኝ ብሎ ቢያመለክት በፊት የጠየቀው ይግባኝ በህጉ ላይ የተቀመጠውን የ30 ቀን የጊዜ ገደብ የሚያቋርጥ ስለመሆኑ፣ የወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ.198 Download Cassation Decision

 • 95934 civil procedure/ intervention by third party/ interest in suit

  በክርክር ወቅት ጣልቃ ልግባ የሚለው ወገን በተከራካሪ ወገኖች መካከል ባለው ጉዳይ የሚሰጠው ውሳኔ የክርክሩ ተካፋይ ባይሆን በምን አግባብና መልኩ መብቱንና ጥቅሙን የሚጎዳ መሆኑንና አዲስ ክስ በማቅረብ ለማስቀረት የማይቻል መሆኑን የማስረዳት ግዴታ ያለበት ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 41(2) Download Cassation Decision

 • 96078 criminal law/ concurrence of offence/ mens rea/ moral ingredient

  አንድ ሰው በአንድ አይነት የወንጀል አሳብ ወይም ቸልተኝነት የፈጸመው ወንጀል አንድን የሕግ ድንጋጌ ብቻ የሚጥስ ቢሆንም አንድ አይነት ጉዳት ያስከተለው ቁጥራቸው ከአንድ በላይ በሆነ ሰዎች መብት ወይም ጥቅም ላይ ሲሆን እንደተደራራቢ ወንጀሎች ሊቆጠር የሚገባ ስለመሆኑ፣ የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 27(1)፣6ዐ(ሀ) (ሐ) እና 598(1) Download Cassation Decision

 • 96216 civil procedure/ jurisdiction/ government houses/ Addis Ababa city court

  ከከተማው አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት የመቆጣጠር ስልጣን እና ተግባር ጋር እንዲሁም የከተማው አስተዳደር ከሚያስተዳድራቸው የመንግስት ቤቶች ጋር እና የከተማው አስተዳደር አካልም በተከሳሽነት በሚቀርብበት ጊዜ የስረ ነገር ስልጣን የከተማው ፍርድ ቤቶች ስለመሆኑ፣ በአንድ ክስ ውስጥ ብዙ አቤቱታዎች ቀርበው ከነዚሁ በከፊል ዋናውን ክስ የሚመለከቱ በከፊል ደግሞ ዋናውን ክስ መነሻ አድርገው ቅርንጫፍ ነገሮችን የሚመለከቱ በሆነ ጊዜ የፍርድ ቤቱ ስልጣን የሚወሰነው ከፍተኛ ግምት ያለውን አቤቱታ መሰረት አድርጎ በመከተል ስለመሆኑ፣ መመሪያ ቁጥር 4/2004 አዋጅ ቁጥር 361/1995 ፣ የተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ ቻርተር አንቀጽ 41(1) (ለ) እና (ረ) የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 17(2) Download Cassation Decision

 • 96458 labor dispute/ termination of contract of employment/ payments due/ period of limitation

  የሥራ ውል በመቋረጡ ምክንያት በሰራተኛውም ሆነ በአሰሪው የሚቀርብ ማንኛውም የክፍያ ጥያቄ ሥራ ውሉ በተቋረጠ በ6 ወር ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ የሚታገድ ስለመሆኑ፣ የጳጉሜ ቀናት በይርጋ ቀናት የማይካተቱ ስመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 162(4)፣የፍ/ሕ/ቁ. 1860(3) Download Cassation Decision

 • 96503 criminal law/ criminal procedure/ consolidation of cases/ sentencing / concurrence

  በተለያየ ጊዜና መዝገቦች የተለያዩ ቅጣቶች በአንድ ተከሳሽ ላይ በሚወሰንበት ጊዜ ተከሳሹ ይጣመርልኝ ብሎ በሚጠይቅበት ጊዜ ተደምረው የሚፈፀሙ ሲሆን የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች ግን እንደገና በድጋሚ የሚታዩበት የህግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑ፣ የወ/ህ/አንቀፅ 186(3)፣184(1)፣ 108(1) Download Cassation Decision

 • 96954 criminal law/ criminal procedure/ plea guilty/ admission/ guilty verdict

  አንድ ተከሳሽ በክስ ማመልከቻ ላይ የተዘረዘረውን ወንጀል ለመስራቱ በሙሉ ያመነ እንደሆነ ጉዳዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት ተከሳሹ ጥፋተኛ ነኝ ብሏል ሲል በመዝገብ ካሰፈረ በኃላ በተከሳሹ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ መስጠት የሚገባው ስለመሆኑ፣ የወ/መ/ስ/ስ/ህ/አ 134(1) Download Cassation Decision

 • 97206 civil procedure/ exection of judgment/ priority of creditors

  አንድ የፍርድ ባለገንዘብ በፍርድ ባለዕዳ ንብረት ላይ በህግ፣በውል ወይም በፍ/ቤት ትዕዛዝ የቀደምትነት መብት ካላቋቋመ በቀር ከሌሎች የፍርድ ባለገንዘቦች ጋር ደረጃቸው(መብታቸው) እኩል መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት ባስፈረዱት የገንዘብ መጠን መቶኛ ስሌት በፍርድ ቤት ትዕዛዝ የታገደውን ገንዘብ እንዲከፍሉ ማድረጉ የህግ መሰረት ያለው ስለመሆኑ፣ የፍ/ስ/ስህ/ቁ 403 የፍ/ህ/ቁ 3043፣3044፣3045፣2825 Download Cassation Decision

 • 97372 tax law/ custom duties/ comliant/ tax appeal commission/ jurisdiction

  ከጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ጋር በሚሰጡ አስተዳደራዊ ውሳኔዎች ቅር የተሰኘ ሰው ለባለስልጣኑ አቤቱታ አጣሪ ቡድን ከዛም ለግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ በየደረጃው ሳያቀርብ በቀጥታ ጉዳዩ በመደበኛ ፍ/ቤት እንዲታይለት የሚጠይቅበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀፅ 89(2) እና ንዑስ አንቀፅ 3(ሐ)፣ አንቀፅ 89(2)(3)(ሐ) ፣(5) እና (6) Download Cassation Decision

 • 97409 tax law/ constitution/ tax authority

  በሕጉ አግባብ ስልጣን ባለው አካል ያልተከፈለ ቀረጥና ታክ እንደተከፈለ የሚቆጠርበት የሕግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑ፣ ---ቀረጥና ታክሱን የማስከፈል ስልጣን በህገ መንግስቱ ተለይቶ የተቀመጠ ስለመሆኑ፣ የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 96(1) አዋጅ ቁጥር 578/2ዐዐዐ አንቀጽ 6(8)፣9 እና 1ዐ፣ ከአዋጅ ቁጥር 622/2ዐዐ1 አንቀጽ 2(6)፣(2(11)፣2(17) እና 91 ፣15(1)፣ 82 (1ሀ))((ለ)) Download Cassation Decision

 • 97464 property law/ land law/ urban land/ jurisdiction/ constitution/

  ጉዳዩ ከይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት እና ከሰነዶች ጋር የተያያዘ በመሆኑ ብቻ በፍርድ ሊወሰን የሚችል አይደለም ሊባል ስላለመቻሉ፤ እንዲሁም የይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ካርታ ወይም ሌሎች ሰነዶች ተወስደውብኛል ተብሎ ክስ በሚቀርብበት ጊዜ የተወሰዱበት አግባብ ህጋዊ መሆን አለመሆኑ በፍርድ ቤት ሊጣራ የሚችል ጉዳይ ስለመሆኑ፣ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 37(1)፣ የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.4 Download Cassation Decision

 • 97512 labor dispute/ occupational accident/ insurance coverage/ liability exceeding insurance coverage

  የመድን ዋስትና የገባ የመንግስት የልማት ድርጅት በአንድ ሰራተኛው ላይ ለደረሰ የአካል ጉዳት ተጠያቂ የማይሆነው የተገባው የመድህን ሽፋን በአዋጁ የተጠበቀውን መጠን የሚሸፈን ከሆነ ብቻ ስለመሆኑ፣ በአዋጁ ስሌት ለአነሰ መጠን ያህል የመድህን ሽፋን አሰሪው ተጠያቂ ስለመሆኑ፣ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 109(1)፣ አንቀጽ 109(3) ,134(1) Download Cassation Decision

 • 97555 civil procedure/ appearance of parties/ non appearance of plaintiff/

  ክስ በሚሰማበት ወቅት የቀረ ከሳሽ ፍ/ቤቱን በበቂ ሁኔታ የቀረበትን እክል ካስረዳ ፍ/ቤቱ መዝገቡ እንዲንቀሳቀስ ሊያደርግ የሚገባ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 74(2) Download Cassation Decision

 • 98052 labor dispute/ contract of employment/ probation/ termination of contract of employment

  በአሰሪና ሰራተኛ መካከል በሚደርግ የቅጥር ውሉ ላይ በግልፅ የሙከራ ጊዜ እንዲኖር ካልተስማሙ በስተቀር አሰሪው የሙከራ ጊዜ ነው ብሎ በሚያስበው ጊዜ ውስጥ የሰራተኛውን የስራ ውል ያለማስጠንቀቂያ ሊያቋርጥ የማይችል ስለመሆኑ፡- አዋጅ 377/1996 አንቀፅ 11(3) Download Cassation Decision

 • 98079 contract law/ sale of immovable property/ form/ custormary practices/ government responsibility

  የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ በተመለከተ መንግስት ካለበት ኃላፊነት የተነሳ በተዋዋይ ወገኖች መካከል ውል እንዲዋዋሉ እና መዝገብ እንዲያደራጁ የተወሰነ አካልን ባላደረገበት ጊዜና ቦታ በአካባቢው የሚፈፀሙ ልማዳዊ አሰራሮችን ህጋዊ መሰረት የላቸውም ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣ ከፍ/ሕ/ቁ. 3364 Download Cassation Decision

 • 98099 labor dispute/ public pension/ termination of contract of employment/ jurisdiction/

  የጡረታ እድሜያችን ሳይደርስ በጡረታ እንድንወጣ ተደርጐ የስራ ውላችን ከህግ ወጪ ተቋርጧል በማለት የሚቀርብ ክስን መደበኛ ፍ/ቤት ስንብቱ በህግ አግባብ የተደረገ መሆን አለመሆኑን የማጣራትና የመመርመር ስልጣን ያለው ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 23-27 ተእና 30፣40 አዋጅ ቁጥር 714/2003 አንቀጽ 19 Download Cassation Decision

 • 98552 family law/ maintainance obligation/ calculation of maintainance

  የቀለብ ገንዘብ መጠን ስለሚወሰንበት አግባብ፣ የተሻሻለው የፌዴራል የቤተሰብ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 197 አንቀጽ 2 Download Cassation Decision

 • 98647 criminal law/ arbitratry action

  ከውል ግንኙነት ጋር በተያያዘ በህገ ወጥ መንገድ መብትን ማስከበር የወንጀል ተጠያቂነትን የሚያስከትል ስለመሆኑ፣ የወ/ህ/አንቀፅ 436(ለ) Download Cassation Decision

 • 98724 labor dispute/ termination of contract of employment/ payments due/ late paymen

  ከስራ ውል መቋረጥ ጋር ተያይዞ በአሰሪው ቁጥጥር ውጪ በሆነ ምክንያት ካልሆነ በቀር በሰባት የስራ ቀናት ውስጥ አሰሪው ለሰራተኛው መክፈል የሚገባውን ሒሳብ ካልከፈለ ክፍያ ለዘገየበት ጊዜ ለሰራተኛው እስከ ሶስት ወር የሚደርስ ደሞዙን ያህል አሰሪው እንዲከፍለው ሰራተኛው ጉዳዩን ለማየት ስልጣን ላለው ፍ/ቤት በመጠየቅ ሊያስወስን የሚችል ስለመሆኑ- አዋጅ ቁ.377/ 1996 አንቀፅ 38 Download Cassation Decision

 • 99026 labor dispute/ occupational accident/ sick leave

  አንድ ሰራተኛ በስራ ላይ እያለ በሚደርስበት የጤንነት ችግር ምክንያት አሰሪው የአንድ ወር የህመም ፍቃድ ሰጥቶት ነገር ግን በተሠጠው ጊዜ ውስጥ ከህመሙ ማገገም ካልቻለ ተጨማሪ የህመም ፍቃድ ከግማሽ ደመወዙ ጋር እንዲያገኝ ሊደረግ የሚችል ስለመሆኑ፡- አዋጅ ቁ.377/96 አንቀፅ 85(1)፣86(2) Download Cassation Decision

 • 99367 civil service/ police/

  አንድ ሰው የፖሊስ ቅጥር ፎርም የሚል ስያሜ የያዘ ሰነድ ስለሞላ ወይም በቅጥር ፎርሙ በሕጉ አግባብ የሚገኙት ማዕረጎች ተሰጥተውት የጥቅማ ጥቅሙ ተጋሪ መሆኑ ብቻ ጉዳዩን በፖሊስ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት እንዲዳኝ ማድረግ ተገቢ ስላለመሆኑ፡- አዋጅ ቁ.720/2004 አንቀፅ 2(1) የፌዴራል ፖሊስ አባላት መተዳደሪያ የሚኒስተሮች ምክር ቤት ደንብ ቁ.268/2005 አንቀፅ 3፣4፣5፣6(1) እና 7 Download Cassation Decision