Federal Court Case Tracker

volume 17

volume 17

 • 97217 civil procedure evidence law appeal procedure cassation procedure relevant evidence

  civil procedure evidence law appeal procedure cassation procedure relevant evidence     አንድ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት (ሰበር ሰሚ ችሎት )የሥር ፍ/ቤት ጉዳዮን አግባብነት ባላቸው ማስረጃዎች ሁሉ አጣርቶ እንዲወስን ብሎ አንድን ጉዳይ ሲመልስ ስለማስረጃ አቀራረብ በህጉ የተመለከቱትን ድንጋጌዎችን ሁሉ ባላገናዘበ መልኩ ማስረጃ ይቅረብ ማለት ስላለመሆኑ፡-   ለአንድ ጉዳይ አግባብነት ያላቸው  ማስረጃዎች  መቅረብ ያለባቸው ለህጉ የተዘረጋውን ሥርዓት ጠብቀው ሊሆን የሚገባ ስለመሆኑና ተገቢውን የማስረጃ አቀራረብ ሥርዓት ሳይጠብቅ የሚቀርብ ማስረጃ ግን ዋጋ ሊሰጠው የማይገባና ውድቅ ሊደረግ የሚገባ ስለመሆኑ፣   የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 137(3) እና 256   የሰ/መ/ ቁጥር 97217   መጋቢት 16 ቀን 2007 ዓ.ም.   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- አቶ ባካፋ አንለይ  -- ራሳቸው ቀረቡ፡፡   ተጠሪ፡- አቶ ቴዎድሮስ አንለይ  - ጠበቃ ጌትነት አየለ ቀረቡ፡፡ መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡  ፍ  ር ድ   ጉዳዩ ያለአግባብ የተያዘ የመኖሪያ ቤት ይለቀቅልኝ ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በምዕራብ ጎጃም አስተዳደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሁን ተጠሪ በአመልካች ላይ በመሠረተው ክስ መነሻነት ነው፡፡ የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡- በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 08 ክልል ውስጥ የሚገኘውን፣ በካርታ ቁጥር 10/00/93 የሚታወቀውንና በ660 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ሰፍሮ በስማቸው ተመዝግቦ ያለውን መኖሪያ ቤት ተከሳሽ ምንም መብት ሳይኖራቸው  ከህዳር ወር 1998 ዓ.ም ጀምሮ በመያዝ እየተጠቀሙበት እንደሚገኙ ገልፀው ቤቱ እንዲለቀቅላቸውና ያላግባብ ቤቱን ለተጠቀሙበት ጊዜ ደግሞ በወር ብር 2000.00(ሁለት ሺህ) ኪራይ ታስቦ እንዲከፈላቸው ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡   ተከሳሽ የሰጡት የመከላከያ መልስም፡- ከሳሽ ቦታውን የተመራበት ካርኒ አላቀረበም፡፡ ቤቱ በ1963 ዓ.ም የተሠራ ሲሆን ውሃና መብራት የገባው በወላጅ አባታችን በደጃዝማች አንለይ ኃይሌ ስም በመሆኑ ቤቱ የአባታችን ቤት...

 • 100079 criminal law/ criminal responsibility of artificial persons

  የህግ ሰውነት ያለው የንግድ ድርጅት በህግ በግልፅ በተደነገገ ጊዜ በዋና ወንጀል አድራጊነት ፣በአነሳሽነት ወይም  በአባሪነት ወንጀል ሊቀጣ የሚችል መሆኑ ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶች ህጉ በወንጀል የሚጠየቁ እንደሆነ በልዩ ሁኔታና በግልፅ ባልደነገገባቸው ወንጀሎች የወንጀል ተጠያቂነት እንደማይኖርባቸው በወንጀል ህጉ የተደነገገ ስለመሆኑ፡-     ህጋዊ ህልውና ያለው ድርጅት ወንጀል እንዳደረገ ተቆጥሮ የሚቀጣው በኃላፊዎቹ ወይም ከሰራተኞቹ አንዱ ከድርጅቱ ሥራ ጋር በተያያዘ ሁኔታ የድርጅቱን ጥቅም በህገ ወጥ መንገድ ለማራመድ በማሰብ ወይም የድርጅቱን ህጋዊ ግዴታ በመጣስ ወይም ድርጅቱን በመሳሪያነት አለአግባብ በመጠቀም በዋና ወንጀል አድራጊነት በአነሳሽነትና  በአባሪነት  ወንጀል  ሲያደርግ  መሆኑ  በወንጀል ህጉ በግልፅ የተደነገገ መርህ ስለመሆኑ።-       አንድ የንግድ ድርጅት የወንጀል ተግባር ከፈፀመና ጥፋተኛ መሆኑ በፍርድ ከተረጋገጠ ለወንጀሉ አድራጎት ኃላፊ የሚሆኑት ሠራተኞችና ኃላፊዎች በወንጀል ከመጠየቅ ነፃ የማይሆኑ ሥለመሆኑ፡-     የወንጀል ህግ አንቀፅ 34 የሰ/መ/ቁ 100079   መጋቢት 4 ቀን 2007 ዓ/ም   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- አቶ ዕቁባይ በርሀ ገ/እግዚአብሔር  - ጠበቃ ደሳለኝ መስፍን ቀረቡ ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ ገቢዎች ጉምሩክ ባለሥልጣን - ዐ/ህግ ወንድዬ ብርሃኑ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል    ፍ ር ድ   ጉዳዩ የቀረበው አመልካች የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 176025 ታህሳስ 19/2005 ዓ/ም የሰጠው ፍርድና የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመዝገብ ቁጥር 131320 ጥር 21 ቀን 2006 ዓ/ም የሰጠው ፍርድ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታርምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው ጉዳዩ ተጠሪ አመልካች የአንድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሥራ አስኪያጅ ሆኖ ሲሰራ ለግብር...

 • 100631 civil procedure legal status of associations legal personality standing

  civil procedure legal status of associations legal personality standing   በህግና በሚመለከተው መንግስት አካል እውቅና የተቋቋሙ ማህበራት የተቋቋሙበትን ዓላማ ለማሳካት፣የአባላታቸውን መብትና ጥቅም ለማስከበርፍ/ቤት፣ለግልግል ተቋም ወይም ለሌሎች የዳኝነት ሥልጣን ለተሰጣቸው አካላት የዳኝነት ጥያቄ የማቅረብ መብት ያላቸው ስለመሆኑ፣   የፍትሐ ብሔር ህግ ቁጥር 454(1) የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 35 አዋጅ ቁጥር 62/2001 አንቀፅ 55፣110   የሰ/መ/ቁ. 100631   ጥር 19 ቀን 2007 ዓ.ም   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመስል   አመልካች፡- ሮፓክ ነዋሪዎች  ልማት ማህበር   - ጠበቃ አቶ ማርሻል ፍቅረ ማርቆስ ቀረቡ ተጠሪ፡- ሮፓክ ኢንተርናሽናል ኃላፊነቱ የተወ.የግል ማህበር  -ጠበቃ አቶ ያለለት ተሾመ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡    ፍ ርድ   ጉዳዩ የቀረበው አመልካች የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 128626 ጥር 30 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት መዝገብ ቁጥር 98701 ሚያዝያ 22 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው፡፡ ጉዳዩ በመጀመሪያ የታየው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 197501 ነው፡፡ በስር ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ ጉዳዩ የግልገል ዳኛ እንዲሰየም ትእዛዝ ይስጥልኝ በሚል መንገድ የቀረበ የዳኝነት ጥያቄ ነው፡፡   1. የክርክሩ መነሻ አመልካች ለስር ፍርድ ቤት ያቀረበው ማመልከቻ ነው፡፡ ከሳሽ (አመልካች) ተከሳሽ(ተጠሪ) ከአባላቱ ጋር በተለያየ ጊዜ በተዋዋለው የመኖሪያ ቤት ግንባታ ውል ቤቶቹ ለሚሰሩበት መንደር የመሰረተ ልማት ግንባታና ልማት ስራ ለማከናወን...

 • 101079 property law/ rural land law/ Oromia region/ Execution of judgment

  በገጠር የእርሻ መሬት ላይ በተሠጠ ፍርድ  የፍርድ መቃወሚያ ሲቀርብ ፍርድ ተፈፅሟል ሊባል የሚችለው የፍርድ ባለመብቱ በይዞታው ላይ ህጋዊ ማረጋገጫ ሲያገኝ ስለመሆኑ፣ የሰ/መ/ቁ 101079   ጥር 22 ቀን 2007 ዓ/ም   ዳኞች:- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- የይልማና ዴንሳ ወረዳ አከባቢ ጥበቃ መሬት አስተዳደርና  አጠቃቀም ፅ/ቤት ከክልል ፍትህ ቢሮ አይናዲስ አሰጋህኝ - ቀረቡ ተጠሪ ፡- አቶ ውበት ገ/መድህን - የቀረበ የለም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡  ፍ ር ድ   ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ የገጠር የእርሻ መሬት የሚመለከት ሆኖ የተጀመረው በይልማና ዴንሳ ወረዳ ፍርድ ቤት ነው፡፡ የአሁን ተጠሪ በአቶ ልንገርህ ውበት ላይ የእርሻ መሬት ይዞታዬን ያላግባብ ይዞብኛል በማለት ክስ መስርተው ፍርድ ቤቱን የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ አከራካሪውን መሬት አቶ ልንገርህ ውበት ለአሁኑ ተጠሪ እንዲያስረክቡ በማለት ውሳኔ ሰጥቶ የአሁኑ ተጠሪ በዚሁ ፍርድ መሰረት እንዲፈጸምላቸው የአፈጻጸም ማመልከቻ አቅርበዋል፡፡በዚህ ሂደት የአሁኑ አመልካች አከራካሪውን ይዞታ ይዘው የነበሩት አቶ ልንገርህ ውበት የመንግስት ሰራተኛ ስለሆኑና አመልካችም የይዞታ ባለመብት  ስላልሆኑ ይዞታውን ሊረከቡ የሚችሉበት የሕግ አግባብ የለም፣ ውሳኔው የህዝብንና የመንግስት ጥቅም የሚነካ በመሆኑ ሊነሳ ይገባል በማለት አቤቱታውን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 መሰረት ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱም የአሁኑ ተጠሪ በአመልካች የፍርድ መቃወሚያ ላይ መልስ እንዲሰጡበት አድርጓል፡፡የአሁኑ ተጠሪ ለአመልካች የፍርድ መቃወሚያ አቤቱታ ላይ በሰጡት መልስም የአመልካች የፍርድ መቃወሚያ አቤቱታ አቀራረብ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 ስር የተመለከተውን አግባብ ያልተከተለ መሆኑን፣አቶ ልንገርህ ውበት የተባሉት ግለሰብ መሬቱን...

 • 101579 labor law dispute pension

  የአንድ ድርጅት የበላይ ኃላፊ ለሠራተኞች ለጡረተኞች የክፍያ ጭማሪን በተመለከተ በስሩ ለሚገኙ እንደየገቢያቸው መጠን እያስወሠኑና እያስፀደቁ የጭማሪ ክፍያ እንዲያደረጉ ያስተላለፈው ውሣኔ በሙሉ በስር በሚገኙት ድርጅቶች ላይ ተፈፃሚ ሊሆን የሚገባው ሥለመሆኑ፣

 • 101632 civil procedure interlocutory appeal attachment

  ሌሎች ሰዎች በሚከራከሩበት መዝገብ ለክርክሩ መነሻ ከሆነው ንብረት ውስጥ በአንደኛው ወገን ጠያቂነት የታገደን ንብረት ሌላ ሶስተኛ ወገን ለሌላ እዳ አፈፃፀም ንብረቱን ሥለምንፈልገው በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 158 መሰረት የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ይነሳልኝ ብሎ አቤቱታ አቅርቦ ዕግዱ ሊነሳ አይገባም ተብሎበሚሰጠው ብይን ላይ ይግባኝ በሚጠየቅበት ወቅት ከስረ ነገር ውሳኔ በፊት ይግባኝ የሚባልበት አይደለም ሊባልየማይቻል ስለመሆኑ፡-   የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 320(3)   የሰ/መ/ቁ.101632 መጋቢት 4 ቀን 2007 ዓ.ም. ዳኞች፡- መድሕን ኪሮስ   አልማው ወሌ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- አቢሲኒያ ባንክ አ.ማ. - ነገረ ፈጅ ብርሃኑ አሰፋ ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ዘይቱ ከማል - የቀረበ የለም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቶአል፡፡    ፍ ር ድ   በዚህ መዝገብ አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረበው ተጠሪ እና የተጠሪ ባለቤት ናቸው የተባሉት አቶ ኑሪ ከማል እንደቅደም ተከተላቸው ከሳሽ እና ተከሳሽ በመሆን ከፍቺ ጋር ተያይዞ ክርክር እያካሄዱ በነበረበት መዘገብ የአሁኑ አመልካች በተከሳሹ ግለሰብ ላይ በሌላ መዝገብ ላስፈረደው የብድር ዕዳ በንብረቱ ላይ አፈጻጸሙን መቀጠል ያስችለው ዘንድ ከፍቺ ክርክር ጋር ተያይዞ በተከሳሹ ስም ተመዝግቦ በሚታወቀው ቤት ላይ በከሳሽ ጠያቂነት የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ እንዲነሳለት በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 158 መሰረት ያቀረበውን አቤቱታ እና በአቤቱታው ላይ የተሰጠውን መልስ የመረመረው የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዕግዱ ሊነሳ አይገባም በማለት የሰጠው ብይን እና ብይኑ ጊዜያዊ አገልግሎት ያለው በመሆኑ ከስረ ነገሩ ፍርድ በፊት ይግባኝ የሚባልበት አይደለም በማለት ይግባኝ ሰሚው የፌዴራል ከፍተኛ  ፍርድ ቤት የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመባቸው በመሆኑ ሊታረሙ ይገባል በማለት ሲሆን አቤቱታው ተመርምሮ...

 • 101736 labor law dispute/ pension/ termination of contract of employment

  አንድ ሠራተኛ በህግ የተቀመጠው የጡረታ መዉጫ ዕድሜው ደርሶ በስራው ገበታ ላይ ቢቆይና በኋላ የስራ ውሉ ቢቋረጥ በአሰሪው ላይ የተለየ ግዴታ የሚጥል ስላለመሆኑና የማስጠንቀቂያ ጊዜ አልሰጠህም ተብሎ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ ክፈል ተብሎ ሊገደድ የማይችል ስለመሆኑ፣   አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 24(3)   አዋጅ ቁጥር 715/2003 አንቀፅ 17(1) የሰበር/መ/ቁ 101736   መጋቢት 18 ቀን 2007 ዓ/ም       ዳኞች፡-አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- ግዮን ኢንዱስትሪያልና ኮሜርሻል ኃ/የተ/የግል ማህበር ነገረ ፈጅ በዛዬ ሲያምረኝ ተጠሪ፡- አቶ አዲስ አለም ሀ/ኪሮስ ጠበቃ ውቤ አለነ አልቀረቡም መዝገቡ መርምረን ተከታዩን ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ርድ   ጉዳዩ ከአሠሪና ሰራተኛ የስራ ውል መቋረጥ ጋር የተያያዘ ሲሆን የተጀመረው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ነው። አመልካች በሥር የፌዴራል የመጀመሪያ እና ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሰጡ ውሳኔዎች መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመባቸው ስለሆነ ይታረምልኝ በማለት ያቀረበውን አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን የቀረበ ነው፡፡   የአሁኑ ተጠሪ በሥር ፍርድ ቤት በአመልካች ላይ ያቀረቡት ክስ አጭር ይዘት፡- በአመልካች ድርጅት ከመጋቢት 23/2005 ዓ/ም ጀምሮ በወር 2650 ብር እየተከፈላቸው በአሽከርካሪነት የስራ መደብ ሲሰሩ እንደ ነበር፣ አመልካች ያለ ምንም ጥፋትና ማስጠንቀቂያ የሥራ ውላቸውን ያቋረጡ በመሆኑ ስንበቱ ሕገ ወጥ ነው ተብሎ በሕግ የተፈቀዱ ልዩ ልዩ ክፍያዎች እንዲወስንላቸው ማመልከታቸውን የሚያሳይ ነው፡፡   አመልካች በሥር ፍርድ ቤት ያቀረበው መልስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረበ  ሲሆን በፍሬ ነገሩም ተጠሪ በጡረታ የተገለሉ በመሆኑ ስንብቱ ሕጋዊ ነው እንዲባልለት፤ የፕሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚ ስለሆነ የሥራ ስንብት ክፍያ የመጠየቅ መብት እንደሌላቸው የካሳ እና ወደ ሥራ ልመለስ ጥያቄ በይርጋ የታገደ ነው...

 • 101795 labor law dispute promotion of employee

  “ስለሠራተኛ ዕድገት አሰጣጥ ስርዓት” በሚል በአዋጁ የተገለፀው ሀረግ ሊተረጎም የሚገባው ከአንድ የሠራተኛ የስራ መደብ ወደ ሌላ የሠራተኛ የስራ መደብ የሚፈፀም የዕድገት አሰጣጥ ስርዓት በሚል መልኩ ስለመሆኑ፣   በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 142(1)(ሠ) የሰ/መ/ቁ. 101579   ህዳር 24 ቀን 2007 ዓ.ም.   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመስል አመልካቾች፡-   1.  አቶ ገ/መድህን አስፋው           13. አቶ ዓለማየሁ ተሾመ 2.  አቶ ተ/ፃዲቅ ደምሴ               14. አቶ ላቀው እርገጤ 3.  አቶ ዳኜ አየለ                   15. አቶ ተሾመ አግዴ 4.  አቶ ወ/ሚካኤል ዋቄ              16. አቶ አየለ ይግለጡ 5.  አቶ አምሃ ኃ/ስላሴ17. አቶ ይትባረክ ሰሜ                              ከጠበቃ 6.  አቶ አመሃ መላኩ ኃ/ማሪያም       18. ወ/ሮ ፀሐይ አእምሮ              መስፍን 7.  አቶ ደምሴ ድጋፌ              19.ወ/ሮብዙነሽ ማሞ                አለማየሁ 8.  አቶ ግዛው አስረስ               20. ወ/ሮ በቀለች ጐዳና              ጋር ቀረቡ 9.  አቶ ታደሰ ገ/መድህን21. አቶ ኃ/ማሪያም ገና 10. አቶ ወረደወርቅ ጥላሁን           22. አቶ ገብረ ተ/ኃይማኖት 11. አቶ ከበደ አወቀ                 23. አቶ ፍቃደስላሴ ርዳው 12. አቶ ይልማ ጨርቆስ              24. አቶ ሞገስ ኃ/መስቀል     ተጠሪ፡- ትንሳኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት ነ/ፈጅ ሳህለማሪያም ወዳጆ ቀረቡ፡፡   መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ር ድ   የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፍ/ብ/ይ/መ/ቁጥር 128430  ታህሳስ 7 ቀን 2006 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁ.96927 ግንቦት 05 ቀን 2006 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተሽሮ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት አመልካቾች የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው፡፡ ጉዳዩ የጡረታ ደመወዝ ማስተካከያ አስተዳደራዊ ውሳኔ ተግባራዊ ይሁንልን ጥያቄ የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው፡፡ በዚህ ፍርድ ቤት የአሁኑ አመልካቾች ከሳሾች ተጠሪ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት ተከሳሾች ነበሩ፡፡ የአመልካቾች የክስ ይዘትም፡- መንግስት ለመንግስት ሰራተኞች እና ጡረተኞች ህዳር 23 ቀን 2003 ዓ/ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባስተላለፈው ውሳኔ የደመወዝ ማስተካከያ ማድረጉን ተከትሎ የኢትዮጵያ ኦርተዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅድስ ሲኖዶስም በስሩ ላሉት ሰራተኞች የደመወዝ...

 • 102061 Bankruptcy law/ Priority of creditors/ employees

  አንድ የንግድ ድርጅት ሲከስር የዕዳ ክፍያን በተመለከተ የድርጅቱን ንብረቶች በመያዣነት ከያዛቸው ባንክ ይልቅ የከሰረው ድርጅት ሰራተኞች የቀዳሚነት መብት ያላቸው ስለመሆኑ፣   አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 167 አዋጅ ቁጥር 97/1990 እንደተሻሻለ የሰ/መ/ቁ. 102061 የካቲት 06 ቀን 2007 ዓ/ም አመልካች፡- የከሰረው ሆላንድ ካር ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጠበቃ ግርማ አለሙ ቀረቡ ተጠሪ፡- ዘመን ባንክ /አ.ማ/ ነገረ ፈጅ አቶ አዳም ሰገድ በላይ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡    ፍ ር ድ   ጉዳዩ የቀረበው አመልካች የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የመዝገብ ቁጥር 140316 ግንቦት 5 ቀን 2006 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔና የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመዝገብ   ቁጥር 101131 ግንቦት 28 ቀን 2006 ዓ/ም የሰጠው ትእዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው፡፡ ጉዳዩ የእግድ ትእዛዝ መነሳትን የሚመለከት ነው፡፡   1. የክርክሩ መነሻ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመዝገብ ቁጥር 200820 ተጠሪ የከሰረው የሆላንድ ካር ኃ/የተ/የግል ማህበር ንብረት ታግዶ እንዲቆይ የሰጠውን ትእዛዝ እንዲያነሳለት ጥያቄ አቅርቦ የስር ፍ/ቤት የእግድ ትእዛዝ የሚነሳበት ህጋዊ ምክንያት የለም በማለት ግንቦት 21 ቀን 2005 ዓ/ም የሰጠው ትእዛዝ ነው፡፡ አመልካች የስር ፍ/ቤት የሰጠው የእግድ ትእዛዝ ሲነሳና በመያዣነት የያዝኳቸውን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/1990 እንደተሻሻለው በተሰጠኝ ስልጣን መሠረት ንብረቶቹን በሀራጅ ለመሸጥ ለብድሩ መክፈያነት ላውል ይገባል በማለት ይግባኝ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርቧል፡፡ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ የስር ፍ/ቤት የዕግድ ትእዛዝ ተነስቶ ተጠሪ በመያዣነት የያዘውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር...

 • 102512 labor law dispute/ review of labor board decison by court/ error of law

  የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሠራተኛ ጉዳይ ወሣኝ ቦርድ የወሰነውን ጉዳይ በይግባኝ ሲያይ የህግ ስህተት መኖሩን እና አለመኖሩን ከማረጋገጥ ባለፈ የፍሬ ጉዳይ እና የማስረጃ ምዘናን በተመለከተ የማየት እና የማረም ስልጣን የሌለው ስለመሆኑ፣   አንድ አሠሪ የሠራተኛ ቅነሳ በሚል ምክንያት ሠራተኞችን ከሥራ ሲያሰናብት በአዋጁ የሠራተኛን ቅነሳ በተመለከተ የተቀመጡትን ድንጋጌዎች መሠረት ማድረግ ያለበት ስለመሆኑ፣   አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 28(2)(ሐ) ፣29፣140   የሰ/መ/ቁጥር 102512   ታህሳስ 10 ቀን 2007 ዓ.ም.   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል     አመልካቾች፡-   1.አቶ ብርሃኑ ቢኔ 2. አቶ ሞላ ደሴ 3. አቶ ተስፋዬ ሐበና 4. ወ/ሮ ጀማነሽ መንገሻ 5. አቶ ጉልትነህ ታደሰ 6. አቶ ወርቁ አይዴ 7. አቶ መኮንን ሙሉ 8. ወ/ሮ ክብነሽ ዋጤሮ 9. ወ/ሮ ታየች አሰፋ 10. አቶ አጫ አይሳሮ 11. ወ/ሮ ፀዳለ ቸችሮ 12. አቶ ሐይሌ አረጋዊ 13. አቶ ጠብቀው ሳንፎ 14. ወ/ሮ ለተብርሃን መኮንን 15. አቶ ዘሪሁን ደግፌ 16. አቶ በርሔ አሰፋ 17. ወ/ሮ አቦነሽ ሳካሎ 18. አቶ ዋህድ ካሳዬ 19. አቶ ግዛቸው ካሳ 20. አቶ አበራ ሐይሌ 21.አቶ ደምመላሽ ካሳዬ        ደመነ ቱኔ 22. ወ/ሮ መስከረም ካንኮ       የ34ቱም 23. አቶ ሙሉጌታ መቺሶ         ጠበቃ 24. አቶ ሱልጣን ሐሰን 25. አቶ ጌታሁን ሐይሌ 26. ወ/ሮ ዓለሚቱ ገብሬ 27. ወ/ሮ ባዩሽ በቀለ 28. አቶ ደሳለኝ ትንታግ 29. አቶ እንግዳ እሸቱ 30. ወ/ሮ ጀማነሽ መንገሻ 31. ወ/ሮ አየለች ባልቻ 32. አቶ መንበረ ጌታቸው 33. አቶ መተኪያ ፀጋዬ 34. አቶ አብዮት ጌታሁን ተጠሪ፡- የአርባ ምንጭ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካአ/ማ- ነ/ፈጅ ሹፋያን ሱልጣን ቀረቡ   መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡    ፍ ር ድ   ጉዳዩ የቀረበው አመልካቾች የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 139151 ግንቦት 25 ቀን 2006 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት...

 • 102652 family law/ divorce/ company shares/ partition of shares

  በጋብቻ ጊዜ የተፈራ የባልና ሚስት የጋራ የሆነ የአክስዮን ድርሻ በፍቺ ጊዜ በአይነት ሊከፋፈል የሚችል ስለመሆኑ፣   የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ  91 እና 92 የሰ/መ/ቁ.102652 መጋቢት 16 ቀን 2007 ዓ.ም. ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡-ወ/ሮ ሀቢባ መካ -ከጠበቃ ዘውዱ ተሾመ ጋር ቀረቡ ተጠሪዎች፡- 1.  አቶ ደሊል ሁሴን - ቀረቡ 2.  ኢትዮ የአሽከርካሪዎች እና መካኒኮች ማሰልጠኛ ማዕከል ኃ. የተወሰነ የግል ማህበር - ጠበቃ ስንታየሁ ብርሃኑ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ር ድ   ጉዳዩ የፍቺ ውሳኔን ተከትሎ በጋብቻ ውስጥ የተፈራ የአክሲዮን ድርሻ በተጋቢዎቹ መካከል የሚከፋልበትን ስርዓት አስመልክቶ የተነሳ የአፈጻጸም ክርክርን የሚመለከት ነው፡፡   የጉዳዩን አመጣጥ በተመለከተ የፍቺ ውሳኔን ተከትሎ በአመልካች እና በ1ኛ ተጠሪ መካከል በነበረው የንብረት ክፍፍል ክርክር በ2ኛ ተጠሪ ማህበር ውስጥ በ1ኛ ተጠሪ ስም ተመዝግቦ የሚገኘው 162 የአክሲዮን ድርሻ በጋብቻ ውስጥ የተፈራ የጋራ ንብረት መሆኑ ተረጋግጦ እኩል እንዲካፈሉ በስረ ነገሩ ውሳኔ የተሰጠ መሆኑን፣ይህንኑ ውሳኔ ለማስፈጸም አመልካች ባቀረቡት የአፈጸጸም ክስ ላይ የአሁኑ 2ኛ ተጠሪ የፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 418 ድንጋጌን ጠቅሶ መቃወሚያ አቅርቦ የነበረ መሆኑን፣ፍርድ ቤቱም መቃወሚያው ወደፊት የሚታይ ነው በማለት የጋራ ናቸው የተባሉትን ሌሎች ንብረቶች በተመለከተ አፈጻጸሙን መቀጠሉን፣ከዚህ በኃላ የአክሲዮን ድርሻውን በተመለከተ እንደ ፍርዱ እንዲፈጸምላቸው አመልካች አቤቱታ ማቅረባቸውን፣ፍርድ ቤቱም የአክሲዮን ድርሻው የሚገኝበት ማህበር ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ለአፈጻጸሙ ያመች ዘንድ በአፈጻጸም ጥያቄው ላይ ማህበሩ አስተያየት እንዲሰጥ ትዕዛዝ መስጠቱን ተከትሎ ከቀድሞ ተጋቢዎች መካከል  አንዳቸው ለሌላኛው ድርሻውን...

 • 102711 contract law/ mortgage/ contract of loan/ calculation of interest

  -የማይንቀሳቀስ ንብረት የመያዣ ውልን በተመለከተ እዳው እንዲከፈል በተወሠነ ጊዜ ሳይከፈል የቀረ እንደሆነ ገንዘብ ጠያቂው የመያዣ መብት ያገኘበትን የማይንቀሳቀስ ንብረት ይወስዳል በሚል የተደረገ ውል ፈራሽ ስለመሆኑ፣   -የብድር ውልን በተመለከተ ተዋዋዬች ወለዱ በወር እንዲታሠብ የሚዋዋሉት ውል ፈራሽ ስለመሆኑና በህጉ መሠረት ወለድ ሊታሠብ የሚችለው በዓመት ሥለመሆኑ፣   የፍ/ህ/ቁ. 3060/1/፣  1711 እና 2479/1/ የሰ/መ/ቁ.102711 ህዳር 10 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመስል አመልካች፡- ፋንታዬ ፍሰሐ የቀረበ የለም ተጠሪ፡- አቶ ደጀኔ ማርዬ የቀረበ የለም መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ  ር ድ   ጉዳዩ በግለሰቦች መካከል በተደረገ የብድር ገንዘብ ውልን መሰረት አድርጐ የቀረበውን የቤት ልረከብ ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የጀመረው በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን  ከፍተኛ ፍርድ ቤት በላስታ ወረዳ ፍርድ ቤት የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው፡፡ ተጠሪ ከአሁኑ አመልካች ጋር ጥር 15 ቀን 2000 ዓ.ም ባደረጉት የብድር ውል በወር አምስት በመቶ ወለድ ሂሳብ የሚታሰብ ሁኖ ብር 8000.00 (ስምንት ሺህ ብር) ለአሁኑ አመልካች እንደአበደሯቸው፣ የብድሩ መመለሻ ጊዜም ጥር 14 ቀን 2001 ዓ.ም መሆኑን፣ በዚህ ጊዜ አመልካች የብድር ገንዘቡን ካልመለሱ በላስታ ወረዳ ላሊበላ ከተማ 01 ቀበሌ ልዩ ስሙ ሸብጽ ከተባለው ቦታ የሚገኘውንና በ200 ካ/ሜትር ስፋት ባለው ቦታ ላይ የሰፈረውን ቆርቆሮ ቤትና ባህርዛፍ ተክል አመልካች ለተጠሪ ሊያስረክቧቸው መስማማታቸውን በውሉ በተመለከተው የጊዜ ገደብና ወለድ ስሌት መሰረት በድምሩ ብር 9600.00 (ዘጠኝ ሺህ ስድስት መቶ ብር) አመልካች ያለመመለሳቸውን ዘርዝረው አመልካች በውሉ መሰረት ንብረቱን...

 • 103704 contract law/ rent/ government houses/ sub leting

  አንድ በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የሆነ ሰው ከመንግስት የተከራየውን ቤት ለሌላ ሰው አከራይቶ መጠቀምየሚችለው በመመሪያው የተመለከቱት ምክንያቶች ተጣምረው የተገኙ እንደሆነ ስለመሆኑ፡-   መመሪያ ቁጥር 3/2004 አንቀጽ 6 መመሪያ ቁጥር 4/2004 አንቀጽ 12   የሰ/መ/ቁ. 103704 ጥር 20/ቀን 2007ዓ.ም   ዳኞች፡- አልማው ወሌ ዓሊ መሀመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኸሊት ይመሰል   አመልካች፡- -------ቀረቡ ተጠሪ፡- --------ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡  ፍ  ር ድ ይህ ጉዳይ የተጀመረው በአዲስ አበባ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ ነበሩ፡፡ ተጠሪ ባቀረቡት ክስ በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ቤት.ቁ 1314 (ለ)የሆነውን የመንግስት ቤት አመልካች የተከራየውን ንግድ ቤት ለሶስት በመሸንሸን አንዱን በ8000 ብር አከራይቶኝ ሙዝ የመሸጥ ስራ እየሰራሁበት ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በመመሪያ ቁ.3/2004 መሰረት የከተማው ግብረ ሀይል ተጠሪ አንዱን ክፍል በመያዝ  ለአመልካች አንደኛውን ክፍል በመክፈል እንዲሰጠኝ ተወስኗል፤ ሆኖም የስር አንደኛ ተከሣሽ እኔ በሌለሁበት ዕቃዬን የታሽገውን ቤት በውስጡ ያለውን ንብረት ተጠሪ እንዲጠቀምበት አድርጓል ፤ንብረቴንም እየተጠቀመበት ነው፡፡ ቤቱንም ወደ መኖሪያ ቤት በመቀየር ይዟል ንብረቴን መረከብ እና የተቋረጠብኝ ገቢን ማስከፈል አልቻልኩም ስለዚህ የንብረት ግምት 4000 እና የተቋረጠ ገቢ ተከፍሎኝ የንግድ ቤቱን ያስረክቡኝ በማለት ጠይቋል፡፡ አመልካች ባቀረቡት መልስ ለተጠሪ ቤት ሸንሽኜ በ8000 አላከራየውም የሀሰት ክስ ነው፡፡ በመመሪያ ቁ.3/2004 መሰረት የኪራይ ውሉ ከእርሳቸው ጋር እንድቀጥል ጉዳዩን የሚመለከተው አካልም የተሳሳተ ግንዛቤ ውስጥ በመክተት ቢጠየቅም አመልካች ለማስፈጸም የተዋቀረውን ግብረሀይል ከቫይረሱ ጋራ መኖሬን የሚያስረዳ ማስረጃ...

 • 103781 Family law interdiction divorce

  በፍርድ የተከለለከለ ሰው የፍቺ ጥያቄ ስለሚያቀርብበት አግባብ   የሰ/መ/ቁ. 103781 ቀን መጋቢት 17/2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኸሊት ይመስል አመልካች ፡- ወ/ሮ አስካለ አሽኔ - ጠበቃ በርታ በቀለ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ታምራት ተስፋዬ - ጠበቃ አሸናፊ ቦሻ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡    ፍ ር ድ   ጉዳዩ የቀረበው አመልካች በመዝገብ ቁጥር 197469 ጥር 12 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔና የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 150493 ግንቦት 5 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው፡፡ ጉዳዩ የፍች ውሳኔን በመቃወም የቀረበ ጥያቄን የሚመለከት ነው፡፡ 1. የክርክሩ መነሻ ተጠሪ የአባቱ የአቶ ተስፋዬ ጉልማ አሳዳሪና ሞግዚት መሆኑን ገልፆ፣የአቶ ተስፋዬ ጉልማና አመልካች 1964 ዓ.ም ጀምሮ በጋብቻ ተሣስረው ኖረዋል፡፡በትዳራቸው ልጆች አላፈሩም ፡፡ አባቴና ሞግዚት አድራጊና በእድሜ በመግፋታቸው ምክንያት የአእምሮና የጤና መታወክ አጋጥሟቸዋል፡፡ ተጠሪ ባላቸውን ሊንከባከቡዋቸው አልቻለም በዚህ ምክንያት ሁለቱ ተለያይተው መኖር ከጀመሩ ረዥም ጊዜ ሆኋቸዋል ፡፡ ስለዚህ ሞግዚት አድራጊዬ ከተጠሪ /አመልካች /ጋር ያላቸው ጋብቻ በፍች እንዲፈርስ ውሣኔ ይሰጥልኝ በማለት አመልክቷል፡፡ የአሁን አመልካች /በሥር ተጠሪ/ለፍች የሚያበቃ ምክንያት የለንም በማለት ተከራክረዋል፡፡ የሥር ፍርድ ቤት አቶ ተስፋዬ ጉልማ  በአካል በተደጋጋሚ እያስቀረበ ካነጋገረ በኃላ በአቶ ተስፋዬ ጉልማና በአመልካች መካከል በፍች እንዲፈርስ ውሣኔ ሰጥቷል፡፡ አመልካች ይግባኝ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበዋል፡፡ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የአመልካችን ይግባኝ በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 337 መሠረት ሰርዞታል፡፡ 2. አመልካች ተጠሪ...

 • 104294 labor law dispute/ breach of duty by employee/ termination without notice

  አንድ ሠራተኛ የስራ ግዴታውን በአግባቡ ባለመወጣት በአሰሪው ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ላይ ጉዳት ያደረሰ ከሆነ የስራ ውሉን ያለማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ በቂ ምክንያት ሥለመሆኑ፣   አዋጅ ቁጥር 377/96 (1)(ሸ)፣ 12(2)(7) የሰ/መ/ቁ. 104294 ቀን 29/07/2007 ዓ/ም ዳኞች፡-  አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- ሐግቤስ ኃ/የተ/የግል/ማህበር - ነ/ፈጅ ፀጋዬ መካሻ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ በላይ ገ/ማሪያም - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡    ፍ ር ድ   ጉዳዩ የቀረበው በፌዴደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአመልካች የስንብት እርምጃ ህገ ወጥ ነው ተብሎ የተሰጠው ውሳኔ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመጽናቱ በውሳኔው ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት አመልካች ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው፡፡ ጉዳዩ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 “ን” መሰረት ያደረገ የግል የስራ ክርክር ሁኖ አንድ ሰራተኛ ከአሰሪው ንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል ተብሎ ከስራ ያለማስጠንቀቂያ የሚሰናበትበትን የህግ አግባብ ነው፡፡ በስር ፍርድ ቤት የቀረበው የተጠሪ ክስ አመልካች ተጠሪን በጨረታ እንዳይሳተፍ የተደረገውን ጥፋት ሳይፈጽም ይህንኑ ጥፋት ፈጽመሃል በሚል ምክንያት የስራ ውል አላግባብ ያቋረጠ በመሆኑ የተለያዩ ክፍያዎችን እንዲከፍል ይወሰንልኝ የሚል ነው፡፡ የአሁኑ  አመልካች በተከሳሽነቱ ቀርቦ በሰጠው መልስ የተጠሪ የስራ መዝርዝር በግልጽ የሚያሳየው የጨረታ ሰነድ አዘጋጅተው የጨረታውን ሂደት በመከታተል ሪፖርት ማቅረብ መሆኑን ፣ ተጠሪ ይህንኑ የስራ ግዴታ በመተላለፍ የጨረታ ሰነድ ሳያስገቡ በቀሩት የማሽን ጉልበት አመልካች ድርጅት ከጨረታ እንዲሰረዝ በመደረጉ ለተጠሪ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ቢሆንም አመልካች ድርጅት ተሳታፊ እንዲሆን በወሰነበት...

 • 104511 court jurisdiction/ jurisdiction of federal courts

  የክርክሩ አጠቃላይ ይዘት የዕቁብ ገንዘብ ይከፈለኝ ጥያቄን መሰረት አድርጐ የቀረበ በንግድ ህጉየተመለከቱትን አግባብነት ያላቸው ድንጋጌዎችን አተገባበር ለመመርመር የሚያስችልና ቼክ እንደተራ ማሰረጃነት ሆኖ በክርክር ወቅት በቀረበበት ጊዜ ጉዳዩ የፌደራል ነው ተብሎ የማይወሰድ ሥለመሆኑ፡-   አዋጅ ቁጥር 25/1988 የሰ/መ/ቁ 104511   መጋቢት 30 ቀን 2007   ዳኞች፡- አልማዉ ወሌ ዓሊ መሀመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡-1. ዳኜ ሀይሉ          ጠበቃ ታየ ቀረበ 2. በከልቻ መኮንን ተጠሪዎች፡-1. አለምሰገድ ሀብታሙ - የቀረበ የለም 2. ታሪኩ ተክሌ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ር ድ   ጉዳዩ የተጀመረዉ በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን ቡሌ ሆራ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካቾች ተከሳሽ ተጠሪዎች ከሳሾች ነበሩ፡፡ ተጠሪዎች ባቀረቡት ክስ 1ኛ አመልካች የዕቁብ ሰብሳቢ 2ኛ ተጠሪ ዳኛ እና ጸሀፊ፤ ተጠሪዎች አባል በመሆን1ኛ ተጠሪን በ01/01/2005 ብር 50000 ደርሶአቸዉ 2ኛ ተጠሪን 08/07/2005 ዓም ብር 60,000 ደርሷቸዉ ከቡሌ ሆራ አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክእንዲወስዱ ቼክ ተሰጥቷቸዉ ወደ ባንክ ሄደዉ በቂ  ገንዘብ  የለም በመባላቸዉ አመልካቾች በጋራ እና በተናጥል ይክፈሉንበማለት ጠይቋል፡፡አመልካቾች ባለመቅረባቸዉ በሌሉበት በማየት ተጠሪዎች የእቁቡ አባል መሆናቸዉን በማረጋገጥ በተጠቃሹ ቼክ ባንክ ቤት ሄደዉ ገንዘቡን በማጣታቸዉና አመልካቾችም የዕቁቡ ሀላፊዎች በመሆናቸዉ 110,000.00 ብር ለተጠሪዎች የመክፈል ሀላፊነት አለባቸዉ በማለት ወስኗል፡፡ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ጉዳዩን በማከራከር የስር ፍርድ ቤትን ዉሳኔ አጽንቶታል፡፡በመጨረሻም ጉዳዩን ያየዉ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ጉዳዩ የቼክ ክርክር በመሆኑ በአዋጅ ቁ. 25/1988 መሰረት የማየት ስልጣን የለኝም በማለት መዝገቡን ዘግቶታል፡፡   የአመልካቾች...

 • 105555 labor law dispute/ occupational accident

  አንድን ሰው ሠራተኛ ነው ለማለት በቅጥር ላይ የተመሰረተ የሥራ ግንኙነት መኖር፣ሠራተኛው አገልግሎት የመስጠት ግዴታ ያለበት መሆኑ፣ ሊሰጥ የሚገባውን አገልግሎትመቼ ሊያከናውን እንደሚገባና እንዴት ማከናወን እንደሚኖርበት አሰሪው የመቆጣጠር ስልጣን ያለው ስለመሆኑ መረጋገጥ ያለባቸው ስለመሆኑ፣   አንድን አደጋ በስራ ላይ የደረሰ ነው ለማለት ሠራተኛው ስራውን በማከናወን ላይ እያለ ወይም ከስራው ጋር ግንኙነት ባለው ሁኔታ ከራሱ ውጪ በሆነ ምክንያት ወይም በአካሉ በማንኛውም ክፍል ተፈጥሯዊ እንቅስቃሴ ላይ በድንገት የደረሰበት ጉዳት ስለመሆኑ፣   አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀፅ 2.4፣58.96፣97፣107፣110   የሰበር መ/ቁ 105555   መጋቢት 18 ቀን 2007 ዓ.ም   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ   ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- 1.መፍትሃ ሙሜ   2. ናቶሊ መሃመድ ነጂብ       የቀረበ የለም   3. ሐናን መሃመድ ነጂብ   ተጠሪ፡- አቶ ዑስማን ዓሊ - ጠበቃ ይማጅ ዮኒስ ቀረቡ   መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡    ፍ ር ድ   ጉዳዩ የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅን መሠረት ያደረገ ሁኖ የጉዳት ካሣ ክፍያን የሚመለከት ነው፡፡ ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካቾች ባቀረቡት የክስ ማመልከቻ የ1ኛ አመልካች ህጋዊ ባለቤት የሌሎች አመልካቾች ወላጅ አባት የሆኑት ሟች መሃመድ ነጂብ በተጠሪ በሠራተኛነት ተቀጥረው በማገልግል ላይ እያሉ የተጠሪ ንብረት የሆነውንና የሻንሲ ቁጥር JAAKP- 34HbB7P5165፣የሞተር ቁጥሩ 4HG1-865627 የሆነና የሰሌዳ ቁጥር ያልወጣለትን አይሱዙ ተሸከርካሪ ከድሬዳዋ አዲስ አበባ ለማድረስ በማሽከርከር ላይ እንዳሉ ተጠሪ በእሩምታ ጥይት ተተኮሶባቸው ሕይወታቸው በማለፉየጉዳት ካሳ 903.000.00(ዘጠኝ መቶ ሰለሳ ሺህ) ብር እንዲከፈላቸው ይወሰንላቸው ዘንድ በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በተጠሪ ላይ በመሠረቱት ክስ መነሻ ነው። የአሁኑ ተጠሪም በተከሣሽነት ቀርበው ከሟች ጋር የስራ ቅጥር ውል የሌላቸው መሆኑንና ሟቹ...

 • 105620 labor law dispute/ reduction of work force/ payments due

  ከስራ በቅነሳ ምክንያት ለሚሰናበት ሠራተኛ የስራ ስንብት ክፍያ የሚከፈል ስለመሆኑ፡-   አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 39(1)(ሐ)፣40(1)(3)፣28(2)(ሀ)(3) የሰ.መ.ቁ. 105620   ሚያዝያ 13 ቀን 2007 ዓ.ም   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካቾች፡-1. አቶ ሀብቴ ብርሃኔ   2. አቶ በየነ ለሜቻ   3. አቶ ግርማ አንጉራ   4. አቶ ጌትነት ዘውዴ               ጠበቃ አቶ ሣሙኤል ሽፈራው - ቀረቡ   5. አቶ ጥላሁን ተክለመድህን   6. አቶ ተመስገን ግርማ   ተጠሪ፡- አቶ ሙሉነህ ቡና ላኪ ትራንስፖርትና ትሪንዚት አገልግሎት - ጠበቃ ፈጠነ ደረሰ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።  ፍ ር ድ   ጉዳዩ የቀረበው አመልካቾች መዝገብ ቁጥር 140043 ሐምሌ 3 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልን በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው፡፡ ጉዳዩ የሥራ ስንብት የሁለት ወር ደመወዝ ይከፈለን በማለት የቀረበ ጥያቄ የሚመለከት ነው፡፡ ጉዳዩ በመጀመሪያ የታየው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው፡፡ በሥር ፍርድ ቤት አመልካቾች ከሳሽ ተጠሪ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡   1. የክርክሩ መነሻ አመልካቾች ያቀረቡት ክስ ነው፡፡ ከሳሾች ተከሳሽ በሹፌርነት ተመድባችሁ የምታሽከረክሩት መኪና ተሸጧል በሚል ምክንያት የሁለት ወር ማስጠንቀቂያ ከሰጠን በኃላ የሥራ ውላችን አቋርጧል፡፡ ተከሳሽ የሥራ ውሉን በቅነሳ ምክንያት ማቋረጥ ሲገባው አላግባብ የሥራ መደብ ተሰርዟል በማለት ያቋረጠው በመሆኑ በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ህግ መሠረት ሊከፍል የሚገባውን የሁለት ወር ደመወዝ የሥራ ስንብት ክፍያ ያልከፈለ በመሆኑ እንዲከፍል ውሣኔ ይስጥልን በማለት ክስ አቅርበዋል፡፡ ተጠሪ በሥር ፍርድ ቤት ተከሳሽ ሆኖ ቀርቦ ከሳሾች የሚያሽከረክሯቸው መኪኖች በመሸጣቸው የሥራ መደቡ ተሰርዟል፡፡ ስለዚህ ተከሳሾች የስራ ስንብት ክፍያ የምንከፍልበት ምክንያት የለም በማለት ተከራክሯል፡፡ 2. የሥር...

 • 105962 jurisdiction of court/ jurisdiction of federal courts

  በክልል በተነሳ ግምት በሌለው የመንገድ ይከፈትልኝ ጥያቄ ላይ ከተከራካሪ ወገኖች መሃል አንደኛው በፌዴራል መንግስት የተመዘገበ ማህበር ከሆነ ጉዳዩ በፌዴራል የፍ/ቤቶች ስልጣን ስር፣በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የስረ ነገርሥልጣን ስር የሚወድቅ ሲሆን የክልሉ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በውክልና ስልጣኑ ጉዳዩን የሚመለከት ስለመሆኑ፣   አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀፅ 5(2) እና 5(6)፣ አንቀፅ 14   በኦሮሚያ ክልል ህገ መንግስት አንቀጽ 64(3) እንዲሁም በክልሉ ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 141/2000 አንቀጽ 27(4)   የሰ/መ/ቁ 105962 ቀን የካቲት 19/2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመስል አመልካች፡- 1. ቢ.ኤም.ጂ ኃ.የተ.የግል ማህበር              ጠበቃ ሰለሞን እምሩ ቀረቡ፡፡ 2. ዜድ ኤ.ዲ.ኤስ ኃ.የተ.የግል ማህበር ተጠሪ፡- ፕሮፌሰር ባደግ በቀለ - ወኪል ተካልኝ በቀለ ቀረቡ፡ መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡  ፍ ርድ   ጉዳዩ ከመንገድ ይከፈትልን ጥያቄ ጋር ተያይዞ በኦሮሚያ ክልል የተነሳን ክርክር የሚመለከት ሲሆን ለዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት ጉዳዩ የቀረበው በአመልካቾችና በተጠሪ መካከል የተነሳውን ክርክር ለመዳኘት የስረ ነገር ስልጣን ያለውን ፍርድ ቤትን ለመለየት እና ስልጣን ሳይኖር ዳኝነት ተሰጥቶ ሲገኝ ውሳኔው ሊኖረው ስለሚኖረው ዋጋ ለመወሰን ይቻል ዘንድ ነው፡፡   ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካቾች ባሁኑ ተጠሪ ላይ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በኦሮሚያ ልዩ ዞን ሰበታ አዋስ ወረዳ ፍርድ ቤት በመሰረተው ክስ መነሻ ነው፡፡ የአመልካቾች ክስ ይዘትም፡- ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰበታ ከተማ ወስጥ አንደኛው  አመልካች 7939 ካ/ሜትር፣ ሁለተኛው አመልካች ደግሞ 8589 ካሬ ሜትር ቦታ ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዲስትሪ ልማት በኢንቨስትመንት መወሰዳቸውን፣ በዚህ ቦታ ላይ ለመውጫና መግቢያ የሚጠቀሙበትን መንገድ የአሁኑ ተጠሪ...

 • 106286 civil procedure/ contract law/ contract of arbitration/ exhaustion of arbitration remedies

    contract law contract of arbitration exhaustion of arbitration remedy   በአንድ መተዳደሪያ ደንብ በማህበር አባላትና በድርጅቱ  መካከል የሚነሱ አለመግባባቶች በመጀመሪያ በእርቅ መፈታት  አለባቸው የሚል ድንጋጌ ሲኖር ይኸው ሥርዓት ሳይፈፀም ወደ ፍርድ ቤት ክስ ማቅረብ አግባብነትየሌለው ስለመሆኑ   ተዋዋይ ወገኖች በመካከላቸው የሚነሳ አለመግባባትን በተመለከተ ጉዳያቸው ፍርድ ቤት ከመቅረቡ በፊት በሽምግልና እንዲታይ ሊሰማሙ ሥለመቻላቸው፣   የፍ/ሕ/ቁ. 1731(1)፣1732፣1736፣1738 የሰ/መ/ቁ 106286   መጋቢት 29 ቀን 2007 ዓ.ም   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- ቦሮ ትራቪል የግንባታ ሥራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር ነገረ ፈጅ ም/ስ አስኪያጅ ታከለ ንጉሴ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ኤፍሬም ሽብሩ - ቀረቡ   መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡    ፍ ርድ   የሰበር አቤቱታ ሊቀርብ የቻለው የሥር ፍርድ ቤቶች ግራ ቀኙ እያከራከረ ያለው ጉዳይ በመጀመሪያ ወደ ፍርድ ቤት ከመሄዱ በፊት በሽምግልና ዳኞች መታየት ነበረበት የሚለውን የአመልካች ክርክር ነጥብ ውድቅ በማድረግ ጉዳዩ በፍርድ ቤት እንዲታይ ብይን የመስጠታቸው አግባብነት አመልካች ከመተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 41(1) አንፃር መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ጭብጥ ለመመርመር ነው፡፡   ጉዳዩ የተጀመረው በቤንሻጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ነው፡፡ የአሁኑ ተጠሪ በአመልካች ድርጅት ያቀረቡት ክስ ከማህበሩ መሥራች አባልነት ያለአግባብ መሰረዛቸው እና የቼክ ፈራሚነታቸው ያለአግባብ እንደተነቀሉ የሚገልጽ ነው፡፡ የአሁኗ አመልካች ጉዳይ ከአሁኑ በፊት በፍርድ ያለቀ ነው፤ጉዳዩ ፍርድ ቤት ከመቅረቡ በፊት በሽምግልና ዳኞች መታየት አለበት የሚል ክርክር አቅርበዋል፡፡ የሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙ ክርክር ከመረመረ በኃላ ጉዳዩ በፍርድ ያለቀ ነው...

 • 107990 contract law/ donation/ Maintenance obligation/ invalidation of donation

  በግልፅ የሰፈረ የውል ቃል ባይኖርም ስጦታ ሰጪው በድህነት ላይ ወድቆ ሲገኝ ስጦታ ተቀባይ የመጦር ግዴታ ያለበት ስለመሆኑ፣ ሥጦታ ተቀባይ ይህን ግዴታውን ካልፈፀመ ደግሞ ስጦታ ሰጪ ውሉ እንዲሻር መጠየቅ ስለመቻሉ፣   የፍ/ሕ/ቁ. 2458(1)፣ 2464(1) የሰ/መ/ቁ. 107990   መጋቢት 14 ቀን 2007 ዓ/ም   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሀመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል     አመልካች፡- እማሆይ ወ/ገብርኤል የቀረቡ የለም (ተወካይ) ተጠሪ፡- ደረጀ ደሳለኝ - የቀረበ የለም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ር ድ   ጉዳዩ የተጀመረው በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ በጉራጌ ዞን አቤሸጌ ወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ተከሳሽ ነበሩ፡፡ አመልካች ባቀረቡት ክስ በ1997 ዓ/ም የባለቤቴ ልጅ ባል የሆነው ቄስ ሀይሎም ተስፋዬ ይዞታዬን ወሮ ይዞብኝ ተጠሪ ረዳት መስሎ ቀርቦኝ ቦታውን በትክክል በማላውቀው ቦታ ወስዶኝ ልጄ ነው ብለሽ ፈርሚልኝ ብሎ ከ1999 ዓ/ም ጀምሮ በመሬቴ ላይ ያመረተውን ድርሻዬንና 1.65 ሄክታር ይዞታየን ነጥቆኛል በመሆኑም ይመልስልኝ በማለት ጠየቁ፡፡ ተጠሪም በሰጠው መልስ አመልካች በ23/07/98 ዓ/ም  በተደረገ  የስጦታ ውል በፍ/ብ/ህ/ቁ/ 2443(1) እና በ881 መሠረት የተፈጸመ ስጦታ ነው በማለት ተከራክረዋል፡፡ ጉዳዩን ያየው የወረዳ ፍርድ ቤት የግራቀኙን በማከራከር አመልካች የስጦታ ውሉ  አልተመዘገበም በማለት ያቀረቡት ክርክር ውድቅ ነው፤ መሬቱን ወደውና ፈቅደው በስጦታ ውል ሰጡ እንጂ በማታለል መሆኑ አልተረጋገጠም፣ ስለዚህ ተጠሪ መሬቱን ሊለቁ አይገባም በማለት ወስኗል፡፡ በመቀጠልም ጉዳዩን ያየው ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ30/8/98 ለጉራጌ ዞን ፍትህ መምሪያ የቀረበው የስጦታ ውል እና የቀበሌ መስተዳደር የተጻጻፉት ደብደቤዎች ውሉ መመዝገቡን የሚይሳይ ካለመሆኑም በላይ በቀላጤ የሰው ንብረት ማስተላለፍ ስለማይቻል የስር...

 • 108539 law of succession/ property law/ rural land law/ Amhara region

  አንድ ሰው ከህግ ውጪ የገጠር እርሻ መሬት ለመውረስ የሚያስችል የወራሽነት ማስረጃ ስላወጣ ይሰረዝበት የሚል አቤቱታ በሚቀርብበት ጊዜ ፍ/ቤት ጭብጥ ይዞ ውሳኔ የሚሰጥበት ጉዳይ እንጂ የመሬት ክርክር ሲነሳ የሚታይ ነው ተብሎ ክሱን ውድቅ ማድረግ አግባብነት የሌለው ሥለመሆኑ፣   የአ/ብ/ክ/መንግስት የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም  አዋጅ ቁጥር 133/98   እና ደንብ ቁጥር 51/99   የሰ/መ/ቁጥር 108539   መጋቢት 30 ቀን 2007 ዓ.ም   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- አቶ አበባው አጥናፉ - ቀረቡ ተጠሪዎች፡- 1. ወ/ሮ የካባ ግዛው - ወኪል ተሻገር ካሤ - ቀረበ 2. አቶ ጌቴ ግዛው - ቀረቡ 3. ወ/ሮ ምሳዬ ግዛው - የቀረበ የለም፡፡ መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩን ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ር ድ   ጉዳዩ የገጠር እርሻ መሬት መብት በውርስ የሚተላለፍበትን አግባብ የሚመለከት ነው፡፡ ክርክሩ የጀመረው በመቄት ወረዳ ፍርድ ቤት የአሁኑ አመልካች  የአሁኑ ተጠሪዎች የሟች  እማሆይ እቴ አለማየሁ የገጠር መሬት ይዞታ ሕጋዊ ወራሽ መሆናቸውን የሚያረጋገጥ ማስረጃ በወረዳው ፍርድ ቤት ሰኔ 21 ቀን 2004 ዓ/ም መውሰዳቸው ከክልሉ የገጠር መሬት አስተዳደር ህግ ውጪ ነው በማለት ተጠሪዎች የወሰዱት ማስረጃ እንዲሰረዝ መስከረም 20 ቀን 2006 ዓ/ም ባቀረቡት አቤቱታ መነሻ ነው፡፡ አመልካች ለተጠሪዎች የገጠር መሬት ይዞታ ውርስ ማረጋገጫ ማስረጃ እንዲሰረዝ መሰረት ያደረጉት ምክንያት የሟች እማኋይ እቴ አለማየሁ የቤተሰብ አባልና የራሳቸው መሬት ይዞታ የሌላቸው ሁኖ እያለ ተጠሪዎች የሟቿ የመጀመሪያ ደረጃ ወራሾች በመሆናቸው ብቻ መሬቱን ሊወርሱ የሚችሉበት የሕግ አግባብ የለም የሚል ሲሆን ተጠሪዎች ወረዳ ፍርድ ቤት ቀርበው በሰጡት መልስ የሟች ልጆች ሁነው በሕጉ አግባብ የወራሽነት ማስረጃውን መውሰዳቸውን ፣ የአሁኑ አመልካች ደግሞ የሟቿ የቤተሰብ አባል ቢሆኑም እማሆይ እቴ...

 • 75560 Jurisdiction of court/ Jurisdiction of Addis Ababa City court/ marriage certificate

  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍ/ቤቶች ጋብቻን በተመለከተ የባልነት ወይም የሚስትነት የምስክር ወረቀት ከመስጠት ባለፈ በማስረጃው ላይ ክርክር ከተነሳበት ወይም የጋብቻ መኖር አለመኖርን ለመወሠን የስረ ነገር ሥልጣን ያልተሠጣቸው ሥለመሆኑ፣   አዋጅ ቁጥር 408/1996 አንቀፅ 2   አዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀጽ 41/1/ /ሸ/ የሰ/መ/ቁ. 75560 ሐምሌ 26 ቀን 2004 ዓ.ም.   ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወሌ ዓሊ መሐመድ ነጋ ዱፊሳ አዳነ  ንጉሴ   አመልካች፡- ወ/ሮ ኪሮስ ገ/ማሪያም - ጠበቃ ዮሴፍ  አእምሮ ቀረቡ ተጠሪ፡-አቶ ገብረ ስላሴ ሃይሌ- ወኪል ወርቅነሽ መንግስቱ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ       ር       ድ   ጉዳዩ የባልነት ማስረጃን መሰረት ያደረገ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሁኑ አመልካች ባቀረቡት የመቃወም አቤቱታ መነሻ ነው፡፡አመልካች የመቃወም አቤቱታ ሊያቀርቡ የቻሉት የአሁኑ ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት የሟች ወ/ሮ ኪሮስ ውቤ ባል ነኝ በማለት በሐሰት የወሰዱት ማስረጃ ያላግባብ ነው በማለት የተወሰደው ማስረጃ እንዲሰረዝላቸው ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ የስር ፍርድ ቤትም ግራ ቀኙን ከአከራከረና የምስክሮች ቃል ከሰማ በኋላ በተጠሪና በሟች ወ/ሮ ኪሮስ ውቤ መካከል ጋብቻ ስለመፈፀሙ በትዳር ሁኔታ ተረጋግጧል በሚል ምክንያት የአመልካችን አቤቱታ ባለመቀበል ቀድሞ ተጠሪ የሟች ወ/ሮ ኪሮስ ውቤ ናቸው በማለት የሰጠውን ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 360(2) መሰረት በማጽናት ወስኗል፡፡ከዚህም በኋላ አመልካች የይግባኝ ቅሬታቸውን ለአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ተቀባይነት  አላገኙም፡፡ ጉዳዩን ለከተማው ሰበር ሰሚ ችሎት አቅርበውም ተቀባይነት አላገኙም፡፡የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው፡፡የአመልካች ሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም የባልነት ጉዳይ አከራካሪ በሆነበት...

 • 88275 family law/ divorce/ partition of property/ priority to purchase

  የባልና ሚስት ጋብቻ ፈርሶ የጋራ የሆነ ንብረት  ክፍፍል በሚፈፀምበት ጊዜ በፍ/ሕጉ ላይ የተቀመጡት በቅድሚያ የመግዛት መብት ድንጋጌዎች ተፈፃሚነት የሌላቸው ስለመሆኑ   የፍ/ሕ.ቁ. 1386፣1388፣1391፣1392፣1393፣(1)፣1397 የሰ/መ/ቁ.88275 ጥር 19 ቀን 2007.ዓ.ም   ዳኞች፡-አልማው ወሌ ዓሊ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- አቶ ኃይለሚካኤል ልኬ ሎሶ - የቀረበ የለም ተጠሪ ፡- 1. አቶ መኮነን በለጠ - ጠበቃ መለሰ ጦና ቀረቡ 2. ወ/ሮ አምሳለች ዘበን - አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡  ፍ ርድ   ጉዳዩ የቅድሚያ ግዥ መብት ጥያቄ የሚስተናገድበትን የሕግ አግባብ የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረውም በሐዋሳ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአፈፃጸም ከሳሽ የሆኑት የአሁኗ 2ኛ ተጠሪ በአሁኑ አመልካች ላይ በዋናው ፍርድ መሰረት እንዲፈፅምላቸው ባቀረቡት የአፈጻም ክስ መነሻ ነው፡፡ የአሁኑ አመልካችና 2ኛ ተጠሪ ባልና ሚስት የነበሩ ሲሆን ጋብቻው በፍርድ ቤት ውሳኔ ፈርሶ የጋብቻ ውጤት ከሆኑት ንብረቶች መካከል ለአሁኑ ክርክር መነሻ የሆነውን መኖሪያ ቤት በክልሉ የቤተሰብ ሕግ መሰረት የተቀመጡት የክፍፍል ስርዓቶችን መሰረት በማድረግ ቤቱ በግልጽ ጨረታ መሸጥ እንደአለበት ፍርድ ቤቱ ውሳኔ አሳርፎ የጨረታ ማስታወቂያ ወጥቶ የአሁኑ 1ኛ ተጠሪተወዳድረው የጨረታ አሸናፊ በመሆን የቤቱ ገዥነታቸው ከታወቀ  በኋላ የአሁኑ አመልካች ቤቱን የመልሶ መግዛት መብት እንደአላቸው ጠቅሰው ቤቱን እንዲያስቀሩ እንዲወሰንላቸው ለፍርድ ቤቱ አመልክተው የአሁኑ ተጠሪዎች ይህንኑ የአመልካችን ጥያቄ ተቃውመው የመልሶ መግዛት መብት ለአመልካች ሊሰጣቸው አይገባም የሚለውን መከራከሪያ ሁለቱም ተጠሪዎች ከማቅረባቸውም በተጨማሪ የአሁኗ 2ኛ ተጠሪ አመልካች አዲስ አበባ ውስጥ መንግስት በሰጣቸው ደረጃውን በጠበቀ ቤት እንደሚኖሩና...

 • 89676 criminal law/ evidence law/ fundamental principle of evidence law

  የማስረጃ ምዘና    መሰረታዊ      መርሆችን       መሰረት  ያላደረገ  ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለመሆኑ የሰ/መ/ቁ. 89676   ጥር 22 ቀን 2007 ዓ.ም   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሀመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመስል አመልካች፡- የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ - ዐ/ሕግ ምርምር ጥጋቡ ቀረቡ ተጠሪ፡- ሳሙኤል ፍቃዱ ኃይሌ - ቀረቡ መዝገቡን የተቀጠረው የቅጣት ውሳኔ ለመሰጠት ነው፡፡ በዚህም መሰረት መዝገቡን መርምረን ተከታዩን የቅጣት ውሳኔ ሰጥተናል፡፡    ቅ ጣ ት   1. አንድ ሰው በወንጀል ጥፋተኛ ሁኖ ከተገኘ ተገቢውን ቅጣት ማግኘት ያለበት ሲሆን ቅጣቱ የሚወሰነው ደግሞ ስራ ላይ በዋለው በፌዴራል ጠቅላይ  ፍ/ቤት የቅጣት አወሳሰን መመሪያ መሰረት ታይቶ ነው፡፡ ተጠሪ ጥፋተኛ የተባሉት የወንጀል ሕግ አንቀፅ 627/1/ ድንጋጌ የሚያስቀጣው ከአስራ አምሰት አመት እስከ ሃያ አምስት ለሚደርስ በሚችል ጽኑ እስራት ነው፡፡ 2. በመሰረቱ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ የወንጀል ህግ የአገሪቱን የወንጀል ህግ ግብ በአዋጅ ቁጥር 414/1996 አንቀፅ 1 ስር ሲደነግግ "የወንጀል  ህግ ግብ ወንጀል እንዳይፈፀም መከላከል ሲሆን ይህንን የሚያደርገው ስለወንጀሎችና ስለቅጣታቸው በቅድሚያ ማስጠንቀቂያ በመስጠት፣ ማስጠንቀቂያነቱ በቂ ባልሆነበት ጊዜ ወንጀል አድራጊዎቹ ተቀጥተው ሌላ ወንጀል ከመፈፀም እንዲቆጠቡና ለሌሎች ማስተማሪያ እንዲሆኑ ወይም እንዲታረሙ በማድረግ ወይም ተጨማሪ ወንጀሎች እንዳይፈፀሙ እርምጃዎች እንዲወሰድባቸው በማድረግ ነው" በማለት ያስቀምጣል ህጉ በአንቀፅ 87 ላይ ቅጣቶችና የጥንቃቄ እርምጃዎች ህጉ ሊደርስበት ያሰበውን ዓላማ ለማረጋገጥ በሚቻልበት ሁኔታ በህጉ መንፈስ መሰረት መፈፀም እንዳለባቸው በመርህ ደረጃ ይደነግጋል፡፡ ይኽው አንቀፅ ቅጣቶችና የጥንቃቄ እርምጃዎቹ ምን ጊዜም ሰብዓዊ ክብርን በሚጠብቅ መንገድ መፈፀም እንደሚኖርባቸው ያስገነዝባል፡፡ የወንጀል ህጉ አንቀፅ 88 ሲታይም የቅጣቶች እና...

 • 90121 Family law/ filliation/ DNA test/ Evidence law

  የDNA ምርመራ እንዲደረግ ትዕዛዝ መሰጠቱ አንደኛው ወገን አሉኝ የሚላቸውን የመከላከያ ማስረጃዎች የማሰማት መብት የማይከለክል ስለመሆኑ፣   የDNA ምርመራ እንዲረግ ፍ/ቤት ትዕዛዝ ስለሚሠጥበት አግባብ፣   የሰ/መ/ቁ.90121 ቀን 28/01/2007 ዓ/ም   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ሱልጣን አባተማም መኮንን ገ/ህይወት ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመለስ አመልካች፡- አቶ ………ጠበቃ ሀይልዬ ሰሀለ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ …………- ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል    ፍ ር ድ   በዚህ በመዝገብ የቀረበው ክርክር የአባትነት ይረጋገጥልኝ ጥያቄ የሚመለከት ነው፡፡ ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ጉዳይ የተጀመረው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሁን ተጠሪ ከሳሽ በመሆን በአመልካች ላይ ያቀረቡትን ክስ እናታቸው ወ/ሮ ….. ከአመልካች ጋር ከጥር ወር 1973 ዓ/ም እሰከ ህዳር ወር 1974 ዓ/ም ድረስ ጋብቻ ሳይኖር እንደባልና ሚስት አብሮው በመቂ ከተማ ድግዳቦራ ወረዳ ቀበሌ 02 የቤት ቁጥር 190 ወስጥ ሲኖሩ መቆያታቸውን ገልጸው በዚህ ግንኙነታቸው መሰረት ተጠሪ በጋንዲ ሆስፒታል ሚያዝያ 02 ቀን 1974 ዓ/ም የተወለዱ መሆናቸውን በመግለጽ አመልካች የተጠሪ አባት ነው ተብሎ እንዲወሰን የሚጠይቅ ነው የአሁን አመልካች በስር ፍርድ ቤት በሰጡት መልስ ልጅነት የሚረጋገጠው የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀፅ 154 እና 155 ላይ እንደተመለከተው የልደት ምስክር ወረቀት በማቅረብ መሆኑን፤ተጠሪ ያቀረቡትማስረጃ አለመኖሩ አመልካች መቂ  ከተማ  ኑረው እንደማያወቁ ተጠሪም አንድም ቀን እራሳቸውም ሆነ በሰው የአመልካች ልጅ መሆናቸው ጠይቀው እንደማያውቁ በመጥቀስ ክሱ ውድቅ ተደርጐ እንዲሰናበቱ አመልክተዋል፡፡   የስር ፍርድ ቤት የተጠሪ ሁለት ምስክሮች በማዳመጥ በሰጠው ውሳኔ በአሁን አመልካች እና የተጠሪ እናት እንደ ባልና ሚስት አብረው ይኖሩ ነበር በሚል ስላልተረጋገጠ የአመልካች...

 • 90713 civil procedure property law immovable property intervention by third party title deed

  civil procedure property law immovable property intervention by third party title deed     ቤትና ይዞታን በሚመለከት በሚደረግ ክርክር አንድ ጣልቃ ገብ አመልካች ክርክር በሚደረግበትቤትና ይዞታ ላይ ጣልቃ ገብቶ ለመከራከር መብት አለኝ በማለት መብቱን የሚያሳዩ ሰነዶችን አቅርቦ እያለ የባለይዞታነት ወይም የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር አላቀረብክም ተብሎ ከወዲሁ ጣልቃ ገብተህ ልትከራከር አትችልም ተብሎ አቤቱታውን ውድቅ ማድረግ አግባብነት የሌለው ሥለመሆኑ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 41  የሰ/መ/ቁ. 90713     መስከረም 29 ቀን 2007 ዓ.ም   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- ወ/ሮ አሚና ሰይድ ጠበቃ ይርሳው ጌትነት ቀረቡ ተጠሪዎች፡-1 ወ/ሮ ወለላ ንጋቱ - ጠበቃ ዘርፉ ካብትይመር ቀረቡ 2. የዲላ ከተማ ማዘጋጃ ቤት - ነ/ፈጅ ማዴቦ ዋንጐ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ር ድ   በዚህ መዝገብ አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት በፍትሐ ብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 41 መሰረት ያቀረቡትን የጣልቃ ገብነት ጥያቄ ውድቅ በማድረግ የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት ነው፡፡ የጉዳዩን አመጣጥ በተመለከተ ከሳሽ የነበሩት የአሁኗ 1ኛ ተጠሪ በዲላ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአሁኑ 2ኛ ተጠሪ ላይ ክስ መመስረታቸውን፣ የክሳቸው ይዘትም ከሳሽ ለኢንቨስትመንት ዓላማ ለማዋል በጨረታ ተወዳድረው እና አሸንፈው የገዙትን 602 ካሬ ሜትር የቦታ ይዞታ ተከሳሽ የተለያዩ ምክንያቶችን በመፍጠር ሊያስረክባቸው ፈቃደኛ ሳይሆን መቅረቱን የሚገልጽ ሆኖ ይህንኑ ቦታ ነጻ አድርጎ እንዲያስረክባቸው ይወሰን ዘንድ ዳኝነት የተጠየቀበት መሆኑን፣ተከሳሹም ርክክቡ የዘገየው የአሁኗ አመልካች በፈጠሩት ችግር ምክንያት መሆኑን እና በክሱ መሰረት ቦታውን ለማስረከብ ፈቃደኛ መሆኑን...

 • 90722 execution of judgement/ immovable property of judgment debtor/ absence of title deed

  በፍርድ ባለዕዳው ሥም የሚታወቅ ቤት ቤቱ በህጋዊ  መንገድ የተገነባና የፍርድ ባለዕዳው እስከሆነ ድረስ ካርታና ፕላን የሌለው መሆኑ እና ለሌላ ሶስተኛ ወገን ተሠጥቷል መባሉ ስጦታው ህጋዊ በሆነ መንገድ እስካልተከናወነ ድረስ ቤቱ ለፍርድ  አፈፃፀም እንዳይውል ሊያደረግው የሚችል ስላለመሆኑ፣ የፍ/ሕ/ቁ 276፣277 የሰ/መ/ቁ. 90722   ጥቅምት 11 ቀን 2007 ዓ.ም   ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ   አልማው ወሌ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- ወ/ሮ መዓዛ  መዝገቡ -  VC ሰላልሰራ መቅረባቸውን ማረጋገጥ አልተቻለም፡፡ ተጠሪ፡- አቶ መሰለ ገላነው - VC ሰላልሰራ መቅረባቸውን ማረጋገጥ አልተቻለም፡፡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቶአል፡፡    ፍ ር ድ   በዚህ መዝገብ አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት በስር የፍርድ ባለመብት (በአሁኑ ተጠሪ) እና በስር የፍርድ ባለዕዳ (የአሁኗ አመልካች የቀድሞ ባለቤት በአቶ ሰመረ ኃይሉ) መካከል በነበረው የአፈጻጸም ክርክር የአማራ /ብ/ክ/መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት በስር ሁለቱ ፍርድ ቤቶች የተሰጠውን ውሳኔ ሽሮ በፍርድ ባለዕዳው ስም የሚታወቀው ቤት ካርታ እና ፕላን የሌለው መሆኑ እና የቀድሞ ተጋቢዎች የፍቺ ውሳኔን ተከትሎ ቤቱን ለልጆቻችን ሰጥተናል በማለት በንብረት ክርክሩ መዝገብ ላይ ማስመዝገባቸው ቤቱ ለፍርድ አፈጻጸም እንዳይውል ሊያደርገው የሚችል ባለመሆኑ አፈጻጸሙ በቤቱ ላይ ሊቀጥል ይገባል በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት ነው፡፡ የጉዳዩን አመጣጥ በተመለከተ በስረ ነገሩ ክርክር ከሳሽ የነበሩት የአሁኑ ተጠሪ በስረ ነገሩ 1ኛ ተከሳሽ እና የአሁኗ አመልካች ባለቤት ከነበሩት ከአቶ ሠመረ ኃይሉ ጋር በ22/06/2000 ዓ.ም. ጋር አቋቁመውት በነበረው ውል መሰረት ባለመፈጸማቸው አቶ ሠመረ ኃይሉ ጉዳት አድርሰውብኛል በማለት ብር...

 • 92296 criminal law/ concurrent offences/ aggravating punishment/

  የወንጀል አድራጊው በአንድ ድርጊት ከአንድ ጊዜ በላይ አደራርቦ የህግ ድንጋጌዎችን የጣሠ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ የአካባቢ ሁኔታዎችን ሲመረምር በተለይም ወንጀለኛው አስቦና አቅዶ ህግ መጣሱን ወይም ግልጽ የሆነ መጥፎፀባይ ማሣየቱን ባመነ ጊዜ ቅጣቱን አክብዶ መወሠን ሥለመቻሉ፣   ተደራራቢ ወንጀሎች ተፈጽመው በተገኙ ጊዜ ፍርድ ቤቶች የድምር ውጤት የቅጣት አወሣሠን መርህን ተፈጻሚ ማድረግ ያለባቸው ሥለመሆኑ፣   በተደራራቢ ወንጀሎች የሚወሠነው ቅጣት ድምር ውጤት ከሃያ አምስት አመት ጽኑ እስራት ሊበልጥ የማይችል ሥለመሆኑ፣   የወ/ህ/ቁ. አንቀጽ 184/1/ለ/፣ 108/1/፣ 187/1/፣65 የሰ/መ/ቁ.92296 ህዳር 22 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካቾች፡- 1. አንዱዓለም አራጌ   2. ናትናኤል መኮንን     ጠበቆች አቶ ደርበው ተመስገንና አቶ አበበ ጉታ ቀረቡ   3. ክንፈሚካኤል ደበበ   ተጠሪ፡- የፌደራል ዓቃቤ ህግ አቶ ወንድምአገኝ ብርሃኑ ቀረቡ   መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡    ፍ ር ድ   ጉዳዩ የቀረበው አመልካቾች በየግላቸው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በወንጀል መዝገብ ቁጥር 112546 የሰጠው የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሳኔና፣ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወንጀል ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 83593 ጉዳዩን በይግባኝ ካየ በኋላ የሰጠው የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ሥህተት ያለበት ሥለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልን በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው፡፡ ጉዳዩ ተጠሪ አመልካቾች  የሽብርተኝነትና ከፍ ያለ የመክዳት ወንጀል ፈጽመዋል በማለት ያቀረበውን የወንጀል ክስና ክርክር የሚመለከት ነው፡፡ በሥር ፍርድ ቤት በቀረበው የወንጀል መዝገብ ቁጥር 112546 ተጠሪ ከሳሽ፣አንደኛው አመልካች አንደኛ ከሳሽ፣ሁለተኛው አመልካች ሁለተኛ ተከሳሽ እና ሶስተኛው  አመልካች አምስተኛ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡   1. ከሥር...

 • 92826 criminal law/ corruption/ breach of official duty

  የወንጀል ህጉ አንቀጽ 420 ድንጋጌ ተፈፃሚነት የሚኖረው የመወሰን ስልጣን በሌላቸው እና የሙያ አገልግሎት የመስጠት ኃላፊነት ያለባቸው በመንግስት ስራ ተመድበው ባሉበት ሁኔታ በመንግስት ንብረት ላይ የሥራ ኃላፊነት ወይም ግዴታቸውን ባልተወጡት ላይ ስለመሆኑ፣   የወ/ህ/አንቀጽ 420/1/ የሰ/መ/ቁ.92826 ጥር 05 ቀን 2007 ዓ/ም ዳኞች፡-አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- የደ/ብ/ብ/ሕ/ብ/ክልላዊ መንግስት ዐቃቤ ሕግ - የቀረበ የለም ተጠሪ፡-  ወ/ሮ ፀሐይ መጫሎ - ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ርድ   ጉዳዩ የወንጀል ጉዳይ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች የክልሉን የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽንን በመወከል በአሁኗ ተጠሪና በሌሎች ሁለት ሰዎች ላይ በካፋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሰረተው ክስ መነሻ ነው፡፡የአመልካች ክስ ይዘትም፡- ተጠሪና በስር ፍርድ ቤት 1ኛ ተከሳሽ የነበሩት አቶ ኢምቶ ወ/ማሪያም አቶ ዳዊት ደስታ የተባሉት ግለሰቦች ተገቢ ያልሆነ ብልጽግና ለራሳቸው ለማግኘት በማሰብ በዬቻ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ፅ/ቤት ውስጥ የስር 1ኛ ተከሳሸ የነበሩት አቶ ኢምቶ ወ/ማሪያም ዋና ገንዘብ ያዥ፣የአሁኗ ተጠሪ ደግሞ የክፍያ ኦፊሰር፣ቼክ አዘጋጅና ፈራሚ፣የስር ሶስተኛ ተከሳሽ የነበሩትና በብይን በነፃ የተሰናበቱት አቶ ዳዊት ደስታ ደግሞ የክፍያ ሰራተኛ እና ቼክ ፈራሚ በመሆን እየሰሩ የአሁኗ ተጠሪ ከኢትዩጵያ ንግድ ባንክ ቦንጋ ቅርንጫፍ ከሂሳብ ቁጥር GOV 787 ብር 100,000.00(አንድ መቶ ሺህ) ብር ወጪ ተደርጎ ለስር አንደኛ ተከሳሽ እንዲከፈል ቁጥሩ 0741998 የሆነውን ቼክ ሰኔ 30 ቀን 2004 ዓ.ም አዘጋጅተው ከስር ሶስተኛ ተከሳሽ ጋር ፈርማ በኃላፊ ሳይታዘዙ በመስጠታቸውና የስር 1ኛ ተከሳሽም ብር 100,000.00(አንድ መቶ ሺህ) ከተጠቃሹ...

 • 93234 criminal procedure/ amendment of charges/ interlocutory appeal

  በወንጀል ክስ ክርክር የክስ ይሻሻል ጥያቄ ቀርቦ ጥያቄው ውድቅ ከተደረገ ጥያቄው ውድቅ የተደረገበት ትእዛዝ በድጋሚ ለክርክር ሊቀርብ የሚችልበት ዕድል የሌለ በመሆኑና ትእዛዙ የመጨረሻ እንጂ ጊዜያዊ አገልግሎት እንዳለው ተቆጥሮ በስረ ነገሩ ከሚሰጠው ፍርድ ጋር ተጠቃሎ ይግባኝ የሚባልበት ነው ሊባል የሚችል ስላለመሆኑና በተሠጠው ትእዛዝ ላይ በስረ ነገሩ ከሚሰጠው ፍርድ በፊት ይግባኝ ሊቀርብበት የሚችል ስለመሆኑ፡-   የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 118፣184፣ የሰ/መ/ቁ. 93234 መስከረም 27 ቀን 2007 ዓ.ም.   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ሡልጣን አባተማም መኰንን ገ/ሕይወት ሙስጠፋ አህመድ ተፈሪ ገብሩ አመልካች፡- የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ዐቃቤ ሕግ - የቀረበ የለም፡፡   ተጠሪ፡- አቶ ኃይለኪሮስ ወልደብርሃን ካሕሳይ - የቀረበ የለም፡፡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡  ፍ ር ድ   በዚህ መዝገብ አመልካች አቤቱታ ያቀረበው በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በማዕከላዊ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአሁኑ ተጠሪ ላይ አቅርቧቸው በነበሩት ሁለት የሙስና ወንጀል ክሶች ጉዳዩ የከሳሽን ምስክሮች ለመስማት በተቀጠረበት ዕለት ምስክሮቹ እንዲሰሙ ከመደረጉ በፊት ተከሳሹ ከተከሰሱባቸው ሁለት የሙስና ወንጀሎች መካከል በሁለተኛው ክስ የተመለከተውን ወንጀል ያደረጉት ከሌላ ሰው ጋር በመተባበር ስለመሆኑ በሂደት የተደረሰበት መሆኑን ገልጾ የወንጀሉ ተካፋይ ነው የተባለውን ሌላኛውን ግለሰብ በክሱ በማካተት ክሱን አሻሽሎ ለማቅረብ እንዲፈቀድለት ያቀረበውን ጥያቄ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአብላጫ ድምጽ ውድቅ በማድረግ የሰጠው ብይን እና በብይኑ ቅር በመሰኘት አመልካች ያቀረበውን ቅሬታ የክልሉ የበላይ ፍርድ ቤቶች ባለመቀበል የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት ነው፡፡   የዞኑ...

 • 93239 civil procedure appointment of auditor compromise agreement finality of compromise agreement

  civil procedure  appointment of auditor   compromise agreement finality of compromise agreement ተከራካሪ ወገኖች ለፍ/ቤት የሒሳብ አጣሪ ይሾምልን የሚል አቤቱታ ሲያቀርቡ በሒሳብ አጣሪዎች ሪፖርት አለመስማማት ቢኖር እንኳ ጉዳዩ የንግድ ህጉንና የፍትሐብሔር ሥነ-ስርዓቱን መሠረት በማድረግ ውሣኔ በዛው በኩል እንደሚሠጥ በግልጽ ከተስማሙ ይህ ግልጽ ስምምነት ባለበት ሁኔታ የሒሳብ አጣሪዎች የስራ ክንውን ግድፈት አለበት በማለት ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት የሚያቀርቡበት ህጋዊ ምክንያት የሌለ ስለመሆኑ፣የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 277(1)(2) ፣የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 3312 የሰ/መ/ቁጥር 93239   ጥቅምት 25 ቀን 2007 ዓ.ም   ዳኞች፡-  አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኸሊት ይመሰል አመልካቾች ፡- የአቶ አበበ ክብረት ሚስትና ወራሾች እነ ወ/ሮ ብርሃኔ መኰንን 10 ሰዎች ጠበቃ አቶ አምሳሉ ባየ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ነጋ ቦንገር ዶ/ር ሸዋረጋ አስራት ቀረቡ   መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ር ድ   ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ክርክር የተጀመረው በሥር የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ  ፍርድ ቤት አመልካቾች ባቀረቡት አቤቱታ በኮ/መ/ቁ 06187 በ 13/07/2005ዓ.ም የተሰጠው ትዕዛዝ ነው፡፡አመልካቾች እና ተጠሪ የነበራቸውን ክርክር በስምምነት ለመጨረስ ያቀረቡት አቤቱታ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.277 መሠረት በፍ/ቤት የተመዘገበ መሆኑ መዝገቡ መዘጋቱን በሥር ፍ/ቤት መዝገብ የተገለጸ ሲሆን በስምምነቱ መሠረት የተሾሙት የሂሳብ አጣሪዎች ሪፖርት  ፍ/ቤት ቀርቦ እንዲጸድቅ በአሁኑ አመልካቾች ግንቦት 09 ቀን 2004ዓ.ም አቤቱታ ቀርቧል፡፡   የሥር ፍርድ ቤቱም የግራቀኙ የስምምነት ይዘት አጠር ባለመልኩ ከጠቀሰ በኃላ የግራ ቀኙ ጥያቄ ወይም ዳኝነት የተጠየቀበት ጉዳይ ሂሣብ አጣሪ ይሾምልን የሚል እንደነበር፤የሂሳብ አጣሪዎች ከተመረጡ በኃላ ሂሳቡ በምን...

 • 93772 extra-contractual liability/ contract law/ independent contractor/ waiver of liability

  የአንድ ግንባታ ባለቤት ግንባታውን ለሚያከናውነው የስራ ተቋራጭ ግንባታው ሲከናወን ለሚደርሱ ከውል ውጪ ኃላፊነቶች ወይም በህጉ የተጣለበትን ፍትሐ ብሄራዊ ግዴታዎች ለስራ ተቋራጩ በማስተላለፍ የሚያደርገው ስምምነት በህግ ጥበቃ የሚደረግለት ስለመሆኑ፡-   የፍ/ሕ/ቁ.2027(1)፣2130፣2132(1)፣2131(1)፣2035(1)፣2141 የሰ/መ/ቁ 93772   የካቲት 30 ቀን 2007 ዓ/ም   ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ   አልማው ወሌ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- አቶ ሁሴን አመዴ - ጠበቃ ጌታቸው ቅጣው ቀረቡ ተጠሪዎች፡- 1.ኢትዩ ቴሌኮም - ነ/ፈጅ ዘለቀ ሰይፉ ቀረቡ 2 ድርባን ሚድሮክ ሲሚንቶ ኃ/የተ/የግ/ማ…ጠበቃ ጋዲሳ ጉታ-ቀረበ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡  ፍ ር ድ   ጉዳዩ የኮንስትራክሽን ስራ በኮንትራክተር ሲሰራ ደረሰ ለተባለ የቴሌኮሚኒኬሽን ኬብል መበጠስ ጉዳት የጉዳት ካሳ ክፍያን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በአሁኑ 1ኛ ተጠሪ ከሳሽነት፣ በአሁኑ አመልካች ተከሳሽነት እና ለአሁኑ 2ኛ ተጠሪ ጣልቃ ገብነት በምስራቅ ጎጃም አስተዳደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው፡፡   የጉዳዩ አመጣጥ እና ይዘትም ባጭሩ የሚከተለው ነው፡፡   1ኛ ተጠሪ በስር ተከሳሽ ላይ ባቀረበው ክስ ተከሳሹ የአመልካች ንብረት በሆነው የአለም አቀፍ ግንኙነት በተሸከመ የኦፕቲካል ፋይበር ኬብል ላይ በሕግ የተጣለበትን ግዴታ በመጣስ ህዳር 30 ቀን 2002 ዓ/ም የብር 123,710.7234፣ ታህሳስ 20 ቀን 2002 ዓ/ም ደግሞ የብር 374,754.2334 ጉዳት የ2ኛ ተጠሪን ፋብሪካ አጥር ግንባታ ሲያከናውን አድርሷል በሚል በድምሩ ብር 498,465.10(አራት መቶ ዘጠና ስምንት ሺህ አራት መቶ ስልሳ  አምስት ብር ከአስር ሳንቲም) ከተለያዩ ወጪዎች ጋር እንዲከፍል ይወሰንለት ዘንድ ዳኝነት ጠይቋል፡፡ የአሁኑ አመልካችም የሲሚንቶ ፋብሪካ አጥር ግንባታውን ያከናወኑት ከአሁኑ 2ኛ...

 • 94278 commercial law/ company dissolution/ period of limitation/ successive events

  ክሱ የቀረበው በአንድ ተለይቶ በታወቀ ጊዜ ወይም ቀን የተፈጠረ ክስተትን መሠረት በማድረግ ሳይሆን በተለያየ ጊዜ  ተከስተዋል የተባሉ የተለያዩ ችግሮችን መሠረት አድርጐ ሲሆን የማህበር ይፍረስልኝ ጥያቄ ወይም ክስ በይርጋ ይታገዳል የሚባልበት ምክንያት   የሰ/መ/ቁ. 94278   ህዳር 11 ቀን 2007 ዓ.ም   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- አቶ ሐሰን መሐመድ ቀረቡ   ተጠሪ፡- ማጂ አግሮ ፎረስትሪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ ዶ/ር አሸናፊ ማሞ ቀረቡ   መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቶአል፡፡    ፍ  ር ድ   በስር ፍርድ ቤት ከሳሽ የነበሩት የአሁኑ አመልካች በዚህ መዝገብ አቤቱታ ያቀረቡት በተከሳሽነት ተሰይመው የነበሩት የማጂ አግሮ ፎረስትሪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ በማህበሩ የመመስረቻ ፅሁፍና የመተዳደሪያ ደንብ የተሰጣቸውን ተግባርና ኃላፊነት በአግባቡ ሊወጡ ባለመቻላቸው ምክንያት የማህበሩ ሕልውና አደጋ ላይ የወደቀ መሆኑን በምክንያትነት በመጥቀስ በንግድ ሕግ ቁጥር 218 እና 542 መሰረት ማህበሩ እንዲፈርስ ይወሰንልኝ በማለት ያቀረቡት ክስ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1835 መሰረት በአስር አመት ይርጋ የሚታገድ ነው በማለት ክሱ የቀረበለት በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግስት የማጂ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው እና በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በትዕዛዝ የፀናው ብይን መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት ነው፡፡ ከመዝገቡ ግልባጭ መገንዘብ እንደተቻለው ክሱ የቀረበለት የማጂ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከተከሳሽ የቀረበለትን የይርጋ መቃወሚያ በመቀበል የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር. 1835 ድንጋጌን ጠቅሶ ክሱ በአስር ዓመት ይርጋ የታገደ ነው በማለት ብይን የሰጠው የማህበሩ የመመሰረቻ ፅሁፍ ከተፈረመበት ከ19/06/1991 ዓ.ም ጀምሮ ማህበሩ እንዲፈርስ ክስ...

 • 94511 civil procedure non-appearance of parties Dismissal of case and its effect

  civil procedure non-appearance of parties Dismissal of case and its effect     በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 74(2) መሰረት ፍ/ቤቱ የተዘጋን የይግባኝ አቤቱታን እንደገና ስለሚያይበት አግባብ፣   የሰ/መ/ቁ. 94511 30/01/2007 ዓ.ም. ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ሡልጣን አባተማም መኮንን ገ/ሕይወት ሙስጠፋ አህመድ ተፈሪ ገብሩ አመልካቾች፡- 1.  ወ/ሮ ብዙ ሰንበታ      ቀረቡ 2.  ወ/ሮ ባይሴ ሰንበታ ተጠሪ፡- አቶ ታደሰ ሰንበታ - መብታቸው ታልፏል መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቱል፡፡    ፍ ር ድ   በዚህ መዝገብ አመልካቾች የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት ይግባኙ ሊሰማ  በተቀጠረበት ዕለት በቀጠሮው ሰዓት ለመድረስ ያልቻሉት ለጠበቃቸው የሰጡት የውክልና ስልጣን ማስረጃ በእጃቸው በመቅረቱ እና የሚመጡትም ከርቀት አካባቢ በመሆኑ ምክንያት መንገድ በመዘጋጋቱ በመሆኑ በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 73 መሰረት የተዘጋው የይግባኝ መዝገብ  በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 74(2) መሰረት ተከፍቶ እንዲታይላቸው ያቀረቡት አቤቱታ  በበቂ ምክንያት ላይ የተመሰረተ ባለመሆኑ ተቀባይነት የለውም በማለት በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ተሰጥቶ በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሰበር ችሎት በውሳኔ የጸናው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት ነው፡፡ የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ በዚህ ጉዳይ አመልካቾቹ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በነበራቸው ክርክር መዝገቡ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ አመልካቾቹ በዚያኑ ቀን በ4፡30 ሰዓት በፍርድ ቤቱ የደረሱ መሆናቸውን እና በሰዓቱ ለመድረስ ያልቻሉትም በመንገድ ስራ ምክንያት መንገድ በመዘጋጋቱ መሆኑን ገልጸው በሚከራከሩበት ሁኔታ አመልካቾቹ ያቀረቡት  ምክንያት በቂ ምክንያት የሚባል አይደለም በማለት የስር ፍርድ ቤቶች የአመልካቾቹን አቤቱታ ውድቅ የማድረጋቸውን አግባብነት "በቀዳሚው ቀነ ቀጠሮ ሳይቀርብ...

 • 94713 civil procedure counter claim procedure for counter claim

  civil procedure counter claim procedure for counter claim         የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ የፍትሐብሔር ሥነ- ስርዓት ህጉ በሚያዘው መሰረት ሥርዓቱን ጠብቆ ያልቀረበ ከሆነ ዳኝነት ሊሰጥበት የማይችል ስለመሆኑ፣     የፍ/ሥ/ሥ/ሕ.ቁ 234(1)፣(2)   የሰ/መ/ቁጥር 94713   መጋቢት 16 ቀን 2007 ዓ.ም   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል   አመልካቾች፡- 1. ህጻን ሲኢድ ዘውዴ   2. ህጻን ኑሩ ሁሴን ዘውዴ   ሞግዚት ወ/ሮ ሙሉ ሞሳ - ጠበቃ ሆነልኝ ዋለ -   3. ህጻን አዲሱ ዘውዴ       ቀረቡ   ተጠሪ፡-  1.ወ/ሮ ጥሩሰው ሞሳ        6. ሞሚና አግማስ     የ1ኛ፣2ኛ፣3ኛ፣5ኛ-8ኛ ጠበቃ 2. ሶፊያ አግማስ 7. ጥጋቡ አግማስ                   አዲስ መንግስት ቀረቡ፡፡ 3. ፋንታ አግማስ           8. በላይ አግማስ   4. አስጋርጅ አግማስ         9. አለሚቱ ታደሰ            ታልፏል፡፡   5.ብርቄአግማስ   መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ር ድ   ጉዳዩ ከውርስ ንብረት ግምት ክፍያ ጋር ተያይዞ የቀረበ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው ያሁኑ ተጠሪዎች በአሁኑ አመልካቾች ሞግዚት ላይ በአማራ ብሔራዊ ክልልዊ መንግስት በደብረ ታቦር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻነት ነው፡፡ የአሁኑ አመልካቾች ሞግዚት ተከሳሽ፣ አሁን ከተራ ቁጥር አንድ እስከ ስምንት የተጠቀሱት ተጠሪዎች ከሳሾች፣9ኛ ተጠሪ ደግሞ ጣልቃ ገብ ነበሩ፡፡   የክሱ ይዘትም፡-ከተጠሪዎች መካከል ከተራ ቁጥር ሁለት ጀምሮ ያሉት ከወላጅ አባታቸው ከሟች አቶ አግማስ አምባው ላይ በውርስ ያገኙትንና አዋሳኙ በክሱ ላይ የተጠቀሰውን በ369 ካ/ሜትር ያረፈውን ቤት ከሟች ባለቤት ከወ/ሮ ጥሩሰው ሞሳ ጋር እኩል ተካፍለው ከይዞታው ውስጥ 184.57 ካ/ሜ ከወ/ሮ ጥሩሰው ሞሳ ድርሻ ውጪ ያለው ግማሹን በወ/ሮ ሙሉ ሞሳ ተይዞ እንደሚገኝ፣ይህንኑ ቤትና ቦታ የወ/ሮ ሙሉ ሞሳ ባለቤት አቶ ዘውዱ አግማስ እንደስር ከሳሾችና ሌሎች የሟች ወራሾች ሁሉ የሟቹ ልጅ በመሆናቸው በቤቱ ላይ ወርሃዊ ኪራይ ክፍያ እየከፈሉ ይዘው ቆይተው አቶ ዘውዱ አግማስ በመስከረም ወር 2001 ዓ/ም ከዚህ አለም በሞት ከተለዩ በኋላ ወ/ሮ ሙሉ ሞሳ ቤቱን ያለ ክፍያ ይዘው የተቀመጡ መሆኑን ዘርዝረው ከጥቅምት ወር 2001 ዓ/ም ጀምሮ የቤቱን ጥቅም በተመሳሳይ ቤት በአካባቢው ያሉ ቤቶች  በሚያስገኙት ዋጋ መጠን እንዲከፍሉና ቤቱንም እንዲለቁ ይወሰንልን በማለት...

 • 94952 family law/ common property/ substantial improvement on private property

  ከጋብቻ በፊት በአንደኛው ተጋቢ ስም የነበረን የግል ንብረት በጋብቻ ወቅት በንብረቱ ላይ መሰረታዊ መሻሻል ቢደረግበትና ይሄው መሻሻል የተደረገው የባለንብረቱ የግል ገንዘብ መሆኑ እስካልተረጋገጠ ድረስ ህጉ ንብረቱ የጋራ ነው የሚል ግምት የሚወስድ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀፅ 63(1) የሰ/መ/ቁ. 94952   መስከረም 30 ቀን 2007 ዓ.ም.   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ሡልጣን አባተማም መኰንን ገ/ሕይወት ሙስጠፋ አህመድ ተፈሪ ገብሩ አመልካች፡- ወ/ሮ ዙሪያሽ ተገኝ - የቀረበ የለም፡፡   ተጠሪ፡- ወ/ሮ የሺ ውድዬ - ረ/ኢንስፔክተር ይመር ዮሴፍ ቀረቡ፡፡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቶአል፡፡  ፍ ር ድ   ጉዳዩ በሞት የተለየው ተጋቢ የግል ንብረት ነው የተባለን ቤት ከሌላኛዋ ተጋቢ  ለማስለቀቅ ከቀረበ ክስ ጋር ተያይዞ የተነሳ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረውም ከሳሽ የነበሩት የአሁኗ ተጠሪ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተከሳሽ በነበሩት በአሁኗ አመልካች ላይ በ08/02/2003 ዓ.ም. አዘጋጅተው ባቀረቡት ክስ ነው፡፡   የክሱይዘትም ባጭሩ፡-ከሳሽ የሟች ልጃቸው አቶታደሰ የሱፍ እናት እና ወራሽ መሆናቸውን፣ሟች እና ተከሳሽ በ17/09/1997 ዓ.ም. በባህላዊ ስርዓት ጋብቻ ፈጽመው አብረው ይኖሩ የነበረ መሆኑን፣በን/ስ/ላፍቶ ክፍለ ከተማ በቀበሌ 09/14 የሚገኘው ቁጥሩ አዲስ የሆነው መኖሪያ ቤት ከጋብቻው በፊት የተፈራ የአቶ ታደሰ የሱፍ የግል ሀብት ስለመሆኑ ጋብቻውን በፈጸሙበት ጊዜ ባደረጉት የጋብቻ ውል ማረጋገጣቸውን፣ይሁን እንጂ ጋብቻው በልጃቸው ሞት ምክንያት መፍረሱን ተከትሎ ተከሳሽ ቤቱን እና በክሱ የተጠቀሱ የቤት ቁሳቁሶችን ለከሳሽ እንዲያስረክቡ ተጠይቀው ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸውን የሚገልጽ ሆኖ ተከሳሽ የዋጋ ግምቱ ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ) የሆነውን ቤት እና የብር 10,000 (አስር ሺህ) የዋጋ ግምት ያላቸውን የቤት ቁሳቁሶች ለከሳሽ...

 • 95069 contract law/ non-performance/ reinstatement/ currency exchange

  ከውጪ አገር በዶላር የተላከ የውጭ ምንዛሬ ለተላከለት አላማ አልዋለም በሚል ገንዘቡ እንዲመለስ ክርክር ሲነሳ ገንዘቡ ሊመለስ የሚገባውዶላር በተላከበት ጊዜ በኢትዮጵያ ብር ተመንዝሮ በተሠጠው ተመን መሠረት ስለመሆኑ፣   የፍ/ሕ/ቁ 1705፣1749፣1750፣1771 የሰ/መ/ቁ. 95069   ህዳር 23 ቀን 2007 ዓ.ም   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- 1. ሴፍሜት አግሪ ቢዝነስ ኃ.የተ.የግ.ማህበር 2. አቶ ወንድምአንተነህ መሸሻ                  ጠበቃ ውቤ አለነ ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ኤልሳቤጥ ብረቱ ሱኬሱ ጠበቃ ወንድአወክ አየለ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡  ፍ  ር ድ   ጉዳዩ የገንዘብ ይመለስልኝ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የጀመረው የአሁኗ  ተጠሪ የአሁኑ አመልካቾችን እንደቅደምተከተላቸው 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች፣ ወ/ሮ ትግስት ድረስ የተባሉትን ግለሰብ ደግሞ 3ኛ ተከሳሽ በማድረግ መጋቢት 27 ቀን 2003 ዓ/ም በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው፡፡ የተጠሪ የክስ ይዘትም፡- 2ኛው ተከሳሽ 1ኛ ተከሳሽን በአሽሙር ማህበር በመመስረት የጥቁር ድንጋይ ማምረቻ እናቋቁም በማለት ተጠሪዋን ባግባቧቸው መሰረት በሚኖሩበት ከኬኒያ ናይሮቢ ከተማ ሆነው በተለያዩ ጊዜያት ማለትም ነሐሴ 06 ቀን 2001 ዓ.ም 10,000 የአሜሪካ ዶላር፣ ነሐሴ 07 ቀን 2001 ዓ/ም 70,000 የአሜሪካ ዶላር፣ ነሐሴ 11 ቀን 2001 ዓ.ም ደግሞ 67,000 የአሜሪካ ዶላር በ1ኛ አመልካች ስም ናይሮቢ ከተማ በሚገኘው ዲያመንድ ትረስት ባንክ አማካኝነት ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኘው በአቢሲኒያ ባንክ ቦሌ ቅርንጫፍ በኩል እንደላኩና ለእነዚህ በተለያዩ ጊዜያት ለተላኩት ገንዘቦች ደግሞ በተከታታይ 204 ዶላር፣ 1429 ዶላር፣ 1367 ዶላር ኮሚሽን እንደከፈሉባቸውና በአጠቃለይም 150,000 የአሜሪካን ዶላር ልከው 2ኛው አመልካችም ይህን ገንዘብ መቀበላቸውን በደረሰኝ ያረጋገጡላቸው መሆኑን...

 • 95072 contract law/ contract of sale/ warranty for defect

  አንድ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ለገዥ የሸጠ ሻጭ የገባው ውል እቃው ቢበላሽ ጥገና ለማድረግ እያለ ሆኖ እያለና ለድብቅ ጉድለቶች ኃላፊነት ሳይኖርበት ከውላቸው ውጭ እና ከህግ ውጭ እቃው ስላልሰራ እቃውን እንዲቀይር ወይም ገንዘቡን እንዲመልስ ሊደረግ የማይችል ስለመሆኑ፡- የፍ/ህ/ቁ 1731፣2266፣2288-2293፣2300 የሰ/መ/ቁ. 95072 ጥር 07 ቀን 2007 ዓ/ም   ጉዳዩ የማቀዝቀዣ(ፊሪጅ) ሽያጭን መሰረት አድርጎ የቀረበውን ክርክር የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኗ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው፡፡ የክሱ ይዘትም ከተጠሪ በብር 16,750.00 የገዙት ፊሪጅ አስፈላጊውን አገልግሎት መስጠት እንደማይችል እንደተረዱ ወደአመልካች ድርጅት አድርስው ድርጅቱ  እቃው እንደሚስተካከልላቸው ነግሯቸው እቃውን ተስተካክሏል በሚል ወደ ቤት ቢመልሱትም በተመሳሳይ ሁኔታ ለሁለተኛ ጊዜ ተበላሽቶ አገልግሎት መስጠት በማቆሙ እቃውን እንዲቀየርላቸው ድርጅቱን ቢጠየቁም ድርጅቱ ፈቃደኛ ያለመሆኑን ዘርዝረው አመልካች ድርጅት እቃውን እንዲቀይርላቸው ወይም የሽያጭ ገንዘቡን እንዲመልስላቸው ይወሰን ዘንድ ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስም ከተጠሪ ጋር የፊሪጅ ሽያጭ ውል መኖሩን ሳይክድ ማቀዝቀዣው ተጠግኖ እንዲሰራ ማድረጉን፣ ለአንድ አመት ደግሞ የጥገና ዋስትና ግዴታ ከመግባቱ ውጪ ፊሪጁን ለመቀየር ወይም የሽያጭ ገንዘቡን ለመመለስ ግዴታ ያለመግባቱንና ባለው የጥገና ዋስትና መሰረት ማቀዝቀዣውን ጠግኖ  አመልካች ለመውሰድ ፈቃደኛ ያለመሆናቸውን ገልፆ ክሱ ውድቅ ሊሆንይገባል በማለት ተከራክሯል፡፡ ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የአዳማ ወረዳ ፍርድ ቤትም ፊሪጁ መስራት አለመስራቱን በቦታው ላይ ተገኝቶ ከተመለከተ በኋላ ጉዳዩን መርምሮ ፍሪጁ መስራቱን መመልከቱን ገልፆ አመልካች...

 • 95267 Extra-contractual liability (tort)/strict liability/ collusion of cars

  ሁለት የሞተር ተሽከርካሪዎች ሲጋጩ እያንዳንዱ ተሽከርካሪ በየራሱ አንዱ ከአንዱ ላይ ጉዳት እንዳደረሱ  የሚቆጠረውና የእያንዳንዱ መኪና ባለሀብት ለአደጋው ኃላፊ የሚሆነው አደጋው የደረሠው ከአንደኛው መኪና አሽከርካሪ ስህተት መሆኑ በማስረጃ ያልተረጋገጠ እንደሆነ ብቻ ስለመሆኑ፡-   የፍ/ሕ/ቁ 2084 የሰ/መ/ቁ. 95267 ጥቅምት 28 ቀን 2007 ዓ.ም.   አመልካች፡-ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አክሲዮን ማህበር ነገረ ፈጅ ይነበብ ደርሰህ-ቀረቡ ተጠሪዎች፡- 1.   አቶ ካሣሁን ወንድሙ- ቀረቡ 2.  አቶ  ግርማ ታጳኖ- ከክርክሩ ውጭ ተደርገዋል 3. ኒያላ ኢንሹራንስ ኩባንያ አክሲዮን ማህበር- ነገረ ፈጅ ዮሴፍ ገብሬ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥ~ል፡፡    ፍ ር ድ   ክርክሩ በተጀመረበት የሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከሳሽ የነበረው የአሁኑ አመልካች በዚህ መዝገብ አቤቱታውን ያቀረበው በተሽከርካሪዎች ግጭት ምክንያት ጉዳት የደረሰበትን የደንበኛውን ተሽከርካሪ አስጠግኖ ወደ ነበረበት ለመመለስ ያወጣውን ወጪ ለማስተካት ያቀረበውን ክስ ውድቅ በማድረግ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት ነው፡፡   የጉዳዩን አመጣጥ በተመለከተ አመልካች ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ24/04/2004 ዓ.ም.አዘጋጅቶ ባቀረበው ክስ ንብረትነቱ የአሁኑ 1ኛ ተጠሪ ሆኖ በአሁኑ 2ኛ ተጠሪ በመሽከርከር ላይ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ 3-02598 ደ/ሕ. የሆነ ተሽከርካሪ በሾፌሩ ጥፋት  ንብረትነቱ የአድቫንስድ ኢንጂነርስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሆኖ በአመልካች የኢንሹራንስ ሽፋን የተሰጠውን የሰሌዳ ቁጥሩ 3-3277 የሆነ ተሽከርካሪ ገጭቶ ያደረሰበትን ጉዳት አስጠግኖ ወደ ነበረበት ለመመለስ አመልካች ያወጣውን ወጪ ብር 441,213.17 (አራት መቶ አርባ አንድ ሺህ ሁለት መቶ አስራ ሶስት ከአስራ ሰባት) 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች በአንድነትና በነጠላ...

 • 95440 criminal law/ retroactive law/ sentencing guideline

  አንድ በወንጀል የተከሰሰ ሰው ወንጀል የሰራው አዲሱ የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ከመውጣቱ በፊት ሲሆንና ቅጣቱ  በሚወሰንበት ጊዜ ወንጀሉን በፈፀመበት ጊዜ ከነበረው የቅጣት አወሳሰን ማንዋል ይልቅ አዲሱ የቅጣት አወሳሰን ማንዋል(መመሪያ) ቅጣቱን የሚያቀልለት ሲሆን ተፈፃሚ መደረግ የሚገባው አዲሱ የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ስለመሆኑ፡- የወ/ሕ/ቁ. አንቀፅ 88(4)፣6 የሰ/መ/ቁ.95440 ሰኔ 4 ቀን 2006 ዓ.ም. ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ረታ ቶሎሳ አዳነ ንጉሴ ሙስጠፋ አህመድ   አመልካች፡- አቶ ሰሚር ኢብራሂም ሂቡ ጉዳይ ተከታታይ ነኝ በማለት አቶ ኢብራሂም ሂቡ ቀረቡ ተጠሪ፡- የፌዴራል ዐ/ሕግ የቀረበ የለም   መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ር ድ   በዚህ መዝገብ አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት ተጠሪ ያቀረበባቸውን ሁለት የወንጀል ክሶች የተመለከተው የፌ/ከ/ፍ/ቤት የሰጠባቸው እና በፌ/ጠ/ፍ/ቤት ይ/ሰሚ ችሎት በውሳኔ የጸናው የጥፋተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት ነው፡፡   ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረባቸው ሁለት ክሶች ይዘት ባጭሩ፡- አመልካች የሚያዝበት ገንዘብ ሳይኖር ቼክ ለመስጠት አስቦ በአንደኛ ክስ በ28/09/2005 ዓ.ምእና በሁለተኛ ክስ በ30/09/2005 ዓ.ምበየክሶቹ ላይ በተመለከተው ጊዜ እና ቦታ የግል ተበዳይ ለሆኑት አቶ አሩቅ ሙሐባ አባድር ቁጥሮቻቸው በየክሶቹ ላይ የተመለከቱትን በአጠቃላይ ብር 520,000 የያዙ ከሕብረት ባንክ የሚመነዘሩ ሁለት ቼኮችን በመስጠቱ እና ሁለቱም ቼኮች እንደቅደም ተከተላቸው በ06/10/2005 ዓ.ም.እና በ05/10/2005 ዓ.ም. ለክፍያ ለባንኩ ሲቀርቡ በቂ ስንቅ የላቸውም ተብሎ ክፍያ ሳይፈጸምባቸው በመቅረቱ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የወንጀል ሕግ በአንቀጽ 693(1) ስር የተደነገገውን በመተላለፍ የሚያዝበት ገንዘብ ሳይኖር ቼክ የመስጠት ወንጀል አድርጓል ...

 • 95587 civil procedure agency death of principlal

  በሞተ ሰው ስም ቀደም ብሎ የተሰጠን ውክልና በመያዝ  የሚቀርብ ክስ ፣የሚደረግ ክርክር እና የሚሰጥ ውሣኔ እንዳልቀረበ እና ውሣኔም እንዳልተሰጠ የሚቆጠር ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2232(1)   የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 57   ሰ/መ/ቁ. 95587   ጥቅምት 28 ቀን 2007 ዓ.ም.   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመስል አመልካች፡- ወ/ሮ ሐዋ በከር አቶ ጀማል የሱፍ ቀረቡ   ተጠሪ፡- 1. አቶ ቶፊቅ መሀመድ        ጠበቃ አቶ ፋይሶ ከድር ቀረቡ 2. አቶ አብዱሰላም መሀመድ መዝገቡን መርምረን የሚከተለው ፍርድ ሰጥተናል፡፡    ፍ ር ድ   1. ጉዳዩ የቀረበው አመልካች በሐዋ በከር የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችሎት በመዝገብ ቁጥር 164559 ጥቅምት 18 ቀን 2006 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይወሰንልኝ በማለት የሐዋ በከር ጠበቃ ነኝ በማለት አቶ ራጅ ገመቹ በአመልካች ስም ፅፈውና ፈርመው ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው፡፡ ጉዳዩ በመጀመሪያ የታየው በሐሮማያ ወረዳ ፍርድ ቤት ነው፡፡ የአውዳይ ፍርድ ቤት ጥር 30 ቀን 2004 ዓ.ም በሀዋ በከር ስም የቀረበለት ክስ ላይ የተከሳሾችን ክርክርና ማስረጃ ሰምቶ ተከሳሾች በከሳሽ የይዞታ ቦታ ላይ ግንባታ በማከናወን ሁከቱ የፈጠሩበት ስለሆነ ሀከቱ እንዲወገድ በማለት በመዝገብ ቁጥር 24494 ታህሣሥ 15 ቀን 2005 ዓ.ም. ውሣኔ ሰጥቷል፡፡ 2. ተጠሪዎች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለምስራቅ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበዋል፡፡ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካችን (ሀዋ በከርን) በመልስ ሰጭነት በመሰየምና መልስ ሰጭ በወኪሏ በኩል መልሷንና ክርክሯን እንዳቀረበች በማስፈር የወረዳው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ በመዝገብ ቁጥር 34942 ግንቦት 19 ቀን 2005 ዓ.ም. በሰጠው ውሣኔ አፅንቶታል፡፡ ተጠሪዎች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት የሰበር አቤቱታ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበዋል፡፡ የክልሉ...

 • 95680 Oromia family law/ common property/ private property

  በኦሮሚያ የቤተሰብ ህግ መሠረት ባልና ሚስቱ በየግል ያገኟቸውን ንብረትም ሆነ ገንዘብ በግል ይዘው መቀጠል እንደሚችሉ  ሲደነገግ ይህ የግል የተባለው ንብረት የግል ሆኖ ሊቀጥል የሚችለው የግል ይባልልኝ ተብሎ በፍ/ቤት ሲፀድቅ ስለመሆኑ፣ የኦሮሚያ ክልል የቤተሰብ ህግ ቁ.69/1995 አንቀፅ 741ዐ፣አንቀፅ 74/2 የሰ/መ/ቁ. 95680   መስከረም 26 ቀን 2007 ዓ/ም   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- ወ/ሮ የሺ ተሾመ ተጠሪ፡- አቶ መስፍን ኃይሉ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥታል፡፡    ፍ ር ድ   ይህ ጉዳይ የተጀመረው በኦሮሚያ ክልል የሎሜ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁን አመልካች ከሣሽ ሲሆኑ የአሁን ተጠሪ ተከሣሽ ነበሩ አመልካች ባቀረቡት ክስ፡- ከተጠሪ ጋር የነበረው ጋብቻ የፈረሰ መሆኑን በመግለፅ በጋብቻ ውስጥ የተፈራ የጋራ ንብረት ያካፍለኝ በማለት በኤጄሬ ከተማ የሚገኝ በ198 ካ.ሜ.ላይ ያረፈ ቤትና ኩሺና፣ ዲናሞ ብቻውንና የወፍጮ ዲናሞ በንግድ ባንክ ያለ ገንዘብ በ369 ካ.ሜ. ላይ 90 ቆርቆሮ የተሠራ ቤት የሞተር ቤት 2 ክፍል በልማት የተከፈለ 80,000 ብር እና የተሸጠ የወፍጮ እና ጀኔሬተር ገንዘብ(13,000) ያካፍለኝ ብላለች በ198 ካ.ሜ.ላይ  ያረፈው ቤት በ1982 ከጋብቻ በፊት (በ17/02/82) የገዛሁትን ነው፡፡በ369 ካ.ሜ. ላይ ያለው ቤት 85 ቆርቆሮ እንጂ 90 አይደለም በመንገድ ሥራ የመኖሪያ ቤት ፈርሶ የተከፈለኝ 54,000 ባገኘሁት ካሣ ከአቶ መለሰ ጫካ ከተባለ ሰው ገንዘብ ተበድሬ የሰራሁት የግል ንብረት ነው፡፡ የካሣ ገንዘቡም ብር 80,000 ሣይሆን ብር 54,000 ነው፡፡ በናፍጣ የሚሠራ ሁለት ወፍጮና ጀኔሬተር 13,000 የተገዛ ቢሆንም 11,495.55 ተጨምሮበት በ24,495.85 ወደ ኤሌክትሪክ ተቀይሮ በሥራ ላይ የሚገኝ እንጂ በጥሬ...

 • 95751 extra-contractual liability/ insurance/ liability beyound insurance policy

  አንድ ኢንሹራንስ ኩባንያ በውል የመነጨውን ግዴታውን በወቅቱባለመወጣቱ ለተከሰተው ተጨማሪ ወጪ ተጠያቂ ሊሆን የሚችል ስለመሆኑ የን/ሕ/ቁ 665 የሰ/መ/ቁ. 95751 መስከረም 27 ቀን 2007 ዓ.ም    ፍ ርድ ይህ ጉዳይ የተጀመረው በኦሮሚያ ክልል የአዳማ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ አመልካች ተከሳሽ ሲሆኑ የአሁኑ 1ኛ ተጠሪ ከሳሽ 2ኛ ተጠሪ ጣልቃ ገብ ነበሩ፡፡ ከሳሽ በቀረቡት ክስ ባለቤቴ ሟች ወንደሰን ከፍያለው በተከሳሽ መኪና የታርጋ ቁጥሩ 323459 በሆነው ላይ በአሽከርካሪነት ተቀጥሮ በወር 1000 እየተከፈለው ሲሰራ በደረሰው የመኪና አደጋ ህይወቱ አልፏል በአዋጅ 377/96 አንቀጽ 110/1/ ለከሳሽ እና የሟች ልጅ ለሆነው (ዳግም ወንድወሰን) ጭምር በድርጅታችን 60,000 (ስልሣ ሺ) ይከፈለኝ በተጨማሪም የጠበቃ አበል 10% እና ውጪ ኪሣራ ይከፈለኝ በማለት ጠይቀዋል፡፡ አመልካችም በሰጡት መልስ ተጠቃሹ መኪና የኢንሹራንስ ሽፋን ያለው መሆኑን በመግለፅ ግሎባል ኢንሹራንስ ጣልቃ ገብቶ እንዲከራከር በጠየቁት መሠረት ይኸው አካል ወደ ክርክሩ በመግባት እስከ 60,000 ብር ድረስ ሽፋን መስጠቱን በመጥቀስ ከውላቸው ውጭ የመክፈል ኃላፊነት የሌለበት መሆኑን ገልፆ ተከራክሯል፡፡ ጉዳዩን ያየው የወረዳው ፍ/ቤት ግሎባል ኢንሹራንስ በሰጠው ሽፋን ልክ ይክፈል፡፡ በወቅቱ ባለመክፈሉ ምክንያት ለደረሰው ወጪና ኪሣራ እና የጠበቃ አበል ይክፈል በማለት ወሰነ፡፡ የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤትም ለደረሰው ጉዳት ይከፈል የተባለውን 60,000 በማጽናት የጠበቃ አበል፣ የወጪና ክሣራ አስመልክቶ ሊከፍል አይገባም በማለት አሻሽሎ አፀና በመጨረሻም 1ኛ ተጠሪ ለክልሉ ሰበር ሰሚ ቅሬታዋን በማቅረብ የሰበር ሰሚውም ሽፋን ከተሰጠው በላይ የአሁን 2ኛ ተጠሪ /ግሎባል/ ሊከፍል አይገባም ከሽፋኑ በላይ የሆነውን የአሁን አመልካች ተተክተው ሊከፍሉ ይገባል ሲል...

 • 95797 contract law/ administrative contract/ non performance/ interest

  -ከአስተዳደር ውሎች አለመፈፀም ጋር ተያይዞ የወለድ ጥያቄ ሊቀርብ የሚችለው የአስተዳደር መስሪያ ቤቱ በውሉ በተመለከተው መሠረት ከአስራ አምስት ቀን በኋላ ለተዋዋዩ ስለ ገንዘቡ አከፋፈል የሚያስፈልገውን የማረጋገጥ ሥራ ሳይፈጽም የቀረ እንደሆነ ወይም የአስተዳደር መስሪያ ቤቱ የሚፈለግበትን ገንዘብ የማረጋገጥ ሥራ በተፈፀመ በ3 ወር ውስጥ ሳይከፍል የቀረ እንደሆነ ስለመሆኑ፣   -ተቃራኒ የውል ቃል ቢኖርም እንኳን ከአስተዳደር መስሪያ ቤት ጋር የተዋዋለው ሰው መስሪያ ቤቱ ሳይከፍል  ለቆየበት  ገንዘብ ወለድ ወይም ኪሣራ ለመጠየቅ የሚችለው ሳይከፈል የቆየበት ጊዜ ከ6 ወር በላይ ሲሆን ወይም ውሉን ያደረገው የአስተዳደር መስሪያ ቤት ተዋዋዩን ለመጉዳት ብሎ ያደረገው ወይም ከባድ በሆነ ቸልተኝነትና ወይም ጥፋት ያደረገ ስለመሆኑ፣   የፍ/ህ/ቁ. 3196፣3197 የሰ/መ/ቁጥር. 95797   ጥር 20 ቀን 2007 ዓ.ም   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኸሊት ይመሰል አመልካች፡- ደበበ ድርሪሳ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ -ስራ አስኪያጆች ባለቤት ደበበ ድሪርሣ ቀረቡ ተጠሪ፡- የፈንታሌ ወረዳ ውሃ ማእድን ኢነርጂ ፅ/ቤት - የቀረበ የለም፡፡ መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ሰጥቷል፡፡    ፍ ርድ   ጉዳዩ ከንጹህ ውሃ ግንባታ ጋር ተያይዞ የተነሳውን የወለድ ክፍያ ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች ባሁኑ ተጠሪ እና በፈንታሌ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ጽ/ቤት ላይ በምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሰረተው ክስ መነሻ ነው፡፡ የክሱ ይዘትም አመልካች ከአሁኑ ተጠሪ ጋር በ17/08/2002 ዓ/ም በተደረገ የውል ስምምነት መሰረት የንጽህ ውሃ ግንባታ በፈንታሌ ወረዳ ከኒፋ ቀበሌ ውስጥ ለማከናወን ግዴታ ገብቶ በውሉ  መሰረት ስራው ተሰርቶና በባለሙያ ተለክቶ የ1ኛ የ2ኛ እና የ3ኛ ዙር የምስክር ወረቀት ተዘጋጅቶ ክፍያ የተፈፀመለት መሆኑን ከዚህ በኋላ የተሰራው ስራም ተለክቶ...

 • 96309 banking/ ATM/ damage to account

  አንድ የባንክ ደንበኛ ከባንኩ ጋር በገባው ውል መሰረት  የቁጠባ ሂሳቡን በኤ.ቲ.ኤ.ም ካርድ ሲያንቀሳቅስ ቆይቶ ነገር ግን በአጋጣሚ ካርዱ ቢጠፋ እና ይሄንኑ በፅሁፍ ለባንኩ ካሳወቀ ከዚያ በኋላ በሂሳቡ ላይ ለሚደርስ ጉድለት ባንኩ ኃላፊ ስለመሆኑ፡- አንድ የባንክ ደንበኛ ከባንኩ ጋር በገባው ውል መሰረት  የቁጠባ ሂሳቡን በኤ.ቲ.ኤ.ም ካርድ ሲያንቀሳቅስ ቆይቶ ነገር ግን በአጋጣሚ ካርዱ ቢጠፋ እና ይሄንኑ በፅሁፍ ለባንኩ ካሳወቀ ከዚያ በኋላ በሂሳቡ ላይ ለሚደርስ ጉድለት ባንኩ ኃላፊ ስለመሆኑ፡- ሰ/መ/ቁ 96309   መስከረም 27 ቀን 2006 ዓ.ም       ዳኞች፡- አልማው ወሌ ሡልጣን አባተማም መኮንን ገ/ህይወት ሙስጠፋ አህመድ ተፈሪ ገብሩ አመልካች፡- ዳሽን ባንክ አ/ማ - ነ/ፈጅ ሠለሞን አያኖ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ አበባየሁ ግርማ - ቀረቡ፡፡ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ወስነናል፡፡    ፍ ር ድ   የሰበር አቤቱታቸው የቀረበው የፌዴራሉ መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ. 189176 የካቲት 18 ቀን 2005 ዓ.ም በዋለው ችሎት የሰጠውን ውሳኔ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት በይግባኝ አይቶ በኮ/መ/ቁ/132422 ህዳር 23 ቀን 2006 ዓ.ም ማፅናቱን በመቃወም ነው፡፡ ጉዳዩም ባጭሩ እንደሚከተለው ነው፡፡   በሥር ከሳሽ የነበሩት የአሁን ተጠሪ የሥር ተከሳሽ በነበረው የአሁኑ አመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ በባንኩ ደንበኛ ሆነው በማጠራቀሚያ ሂሳብ ቁጥር 50100055 02016 ገንዘብ በባንኩ ተቀማጭ አድርገው የቁጠባ ሂሳቡን በኤ.ቲ.ኤም ካርድ ሲያንቀሳቅሱ ከቆዩ በኃላ  የኤቲ.ኤም ካርዱ ጥር 23 ቀን 2003 ዓ.ም የጠፋ በመሆኑ ለባንኩ ጥር 25/2003 ዓ.ም በፅሑፍ ያሳወቁ ቢሆንም ባንኩ ሂሳቡን መዝጋት እያለበት ባለመዝጋቱ ሪፖርት ከተደረገበት ከ25/5/2003 ዓ.ም እስከ 09/6/2003 ዓ.ም ድረስ ለማይታወቁ 3ኛ ወገኖች 40,300.00 (አርባ ሺህ ሶስት መቶ) ወጪ ሆኖ...

 • 96364 law of succession/ will/ Manner of revoking will

  አንድ ተናዛዥ ኑዛዜውን መሻር ሲፈልግ ሀሳቡን በማያሻማ አኳኋን በመግለጽ ከሻረ ኑዛዜዎች ዋጋ ያላቸው እንደሆኑ በሚያስፈልገው ፎርም አይነት ግልጽ አድርጐአልሻረውም ሊባል  የማይችል ስለመሆኑ፣ የፍ/ህ/ቁ. 898(1)፣ 899(1) የሰ/መ/ቁ. 96364   ጥቅምት 10 ቀን 2007 ዓ.ም.   ዳኞች፡-ተገኔ ጌታነህ   አልማው ወሌ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመስል አመልካች፡- እልፍነሽ ወርቁ ጠበቃ አሳምነው ቀረቡ ተጠሪ፡- ኤልሳቤጥ አስራት ጠበቃ መስፍን ጌታቸው ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሠጥቷል፡፡    ፍ ር ድ   ይህ ጉዳይ የተጀመረው በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁን አመልካች የመ/አመልካች፣ተጠሪ ደግሞ የመ/ተጠሪ ነበሩ የመ/አመልካች የነበሩት የአሁን  አመልካች ባቀረቡት የመቃወም አቤቱታ የመቃወም ተጠሪ ሟች ወ/ሮ አስረስ እሸቴ መስከረም 28/2000 ዓ.ም. ያደረጉትን ኑዛዜ ነሐሴ 23 ቀን 2003 ዓ.ም የሻሩት መሆኑን እያወቁ በተሻረው ኑዛዜ የወራሽነት ማስረጃ መውሰዳቸው ተገቢነት ስለሌለው ማስረጃው ይሻርልኝ በማለት ጠይቀዋል፤ተጠሪም በሰጡት መልስ ሟች መፃፍ እና መፈረም ይችላሉ መስከረም 28/2000 ዓ.ም ባደረጉት ኑዛዜም ላይ ስማቸውን ጽፈው የፈረሙ ሲሆን አመልካች የኑዛዜ መሻሪያ ብለው ያቀረቡት ሰነድ ላይ ግን የሟች ፊርማ ተብሎ የተቀመጠው የጣት ምልክት ሲሆን ከምልክቱ በላይ ግን የሟች ስም ተፅፏል፡፡ በመሆኑም መሻሪያ የተባለው ሰነድና መስከረም 28/2000 ዓ.ም. ያደረጉት ኑዛዜ ከፍተኛ ልዩነት አለው፡፡ ሟችም ለረዥም አመት ታመው ፓራላይዝ ሆነው የሚያደርጉትን አያውቁም ባጠቃላይ መሻሪያ ተብሎ የቀረበው ሰነድ የኑዛዜን ፎርማሊቲ የማያሟላና ህጉን ተከትሎ የተፈፀመ አይደለም፣ንብረቱንም ቢሆን ተጠሪ ወደ ስሜ አዙሬዋለሁ፣ ተቃወሞዋቸው ውድቅ ሊሆን ይገባል ሲሉ ተከራክረዋል፡፡   ጉዳዩን ያየው...

 • 96495 property law/ expansion of building by non-owner and its effect

  በአንድ ተቋም ውስጥ ተቀጥሮ ለሚሰራ ሠራተኛ አሰሪው ተቋም ለሰራተኛው ለመኖሪያ የሚሆን ክፍል ከሰጠው እና ሰራተኛው በአሰሪው ተቋም ፍቃድ ተጨማሪ ግንባታ በራሱ ወጪ ከገነባ እና አሰሪው ሰራተኛው እንዲወጣ ካስገደደው አሰሪው ተቋም ሰራተኛው ለተጨማሪ ግንባታ ያወጣውን ወጪ መክፈል ያለበት ወይም ሰራተኛው ተጨማሪውን ግንባታ አፍርሶ የመውሰድ መብት ያለው ስለመሆኑ፡- የፍ/ሕ/ቁ. 1446፣1454፣1455 የሰ/መ/ቁ. 96495 ቀን 05/06/2007 ዓ/ም ዳኞች፡-አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- ኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ድርጅት - ነገረ ፈጅ ወይንሽት እንድሪስ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ኃይሌ ብሩ - ተወካይ ዓመተ ኃይሌ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል    ፍ ር ድ   ጉዳዩ የቀረበው አመልካች በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 46873 በ30/08/2005 ዓ/ም የተሰጠው ፍርድ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሻሩ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት የቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው፡፡ ጉዳዩ በአመልካች ፈቃድ ተመስረተው ተጠሪ የገነቡት ቤት የሚኖረው ህጋዊ ውጤት የተመለከተ ነው፡፡ በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ተከሳሽ ሲሆኑ የአሁኑ ተጠሪ ያቀረቡት ክስ ባጭሩ፡- በአመልካች ተቀጥረው ሲሰሩ በ1967 ዓ/ም አንድ ክፍል መኖሪያ ቤት እንደተሰጣቸው በሒደት የቤተሰባቸው አባላት ቁጥር በመጨመሩ በራሳቸው  ወጪ ተጨማሪ ክፍል 2 መኝታ ፤ ሳሎን ፤ 2 ክፍል ኩሽና መስራታቸው በሰሩት ቤትም ከ1975 ዓ/ም ጀምሮ ለ 30 ዓመታት ሲጠቀሙ እንደነበር አሁን ግን አመልካች ቤቱን እንዲለቁ እያስገዳዳቸው በመሆኑ ድርጊቱ እንዲቆም ወይም ቤቱን የተሰራበት አርባ አምስት ሺህ ብር እንዲከፍላቸው ጠይቋል፡ የአሁኑ አመልካች በሰጠው መልስ ተጠሪ ቤቱን ያገኙት በስራ...

 • 96607 criminal law/ legality

  በማስረጃ በተረጋገጠ የወንጀል ፍሬ ነገር መፈፀሙ የተረጋገጠው የወንጀል ተጠያቂነትን በሚያስከትለው የህግ ድንጋጌ መሰረት የጥፋተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ መሠጠት ያለበት ስለመሆኑ፡-   የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል መንግስት የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 56/1995 አንቀጽ 98(2)(ሀ) የሰ/መ/ቁ. 96607   መስከረም 29 ቀን 2007 ዓ.ም.   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ተኽሊት ይመሰል   አመልካቾች፡- 1ኛ.አቶ ኤርሚያስ ካጢሶ   2ኛ. አቶ ዮሐንስ ላምቤቦ     ጠበቃ ፀጋዬ አሰፋ ቀረቡ   ተጠሪ፡- የከምባታ ጠምባሮ ዞን ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የቀረበ የለም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡  ፍ  ር ድ   በዚህ መዝገብ አመልካቾች የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት ገቢን አሳንሶ የማስታወቅ ወንጀል መፈጸማቸው በማስረጃ ተረጋግጧል በማለት በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠብን የጥፋተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት ነው፡፡   ክርክሩ በተጀመረበት በቀዲዳ ጋሜላ ወረዳ ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካቾቹ ላይ በ08/8/2005 ዓ.ም አዘጋጅቶ ባቀረበው ክስ ተከሳሾቹ በከምባታ ጠምባሮ ዞን በቀዲዳ ጋሜላ ወረዳ ጊዜ ደበኦ በተባለ ቀበሌ አሸዋ እና ድንጋይ ለማምረት ከመንግስት ጋር ውል አድርገው ስራውን እያከናወኑ በነበረበት ከ2004 ዓ.ም እስከ ህዳር ወር 2005 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ትክክለኛ የገቢ ግብር ላለመክፈል ሆን ብለው በማሰብ በኤንትሬ ገልባጭ መኪና በቢያጆ ከብር 300 እስከ ብር 360 ይሸጡ የነበረውን ነጭ ድንጋይ ከብር 40 እስከ ብር 100 የሸጡ አስመስለው፣እንዲሁም በፊያት ገልባጭ መኪና በቢያጆ ከብር 140 እስከ ብር 250 ይሸጡ የነበረውን ነጭ ድንጋይ ከብር 30 እስከ ብር 60 የሸጡ አስመስለው በመመዝገብ እና ገቢያቸውን በማሳነስ የመንግስትን እና የሕዝብን ጥቅም የሚጎዳ አድራጎት የፈጸሙ በመሆኑ...

 • 96628 law of succession/ property law/ estate of the deceased

  ሟች በህይወት እያለ ከይዞታ ቦታው ላይ ለሌላ ሠው ቤት እንዲሠራፈቅዶ ቢሰጠው ሟች በሚሞትበት ጊዜ በሟች ፈቃድ ቤት የሠራው የቤቱ ባለቤት እንደሚሆንና ከሌላው ቦታ ጋር ሆኖ የውርስ ክፍል የሚሆን ስላለመሆኑ፣ የፍ/ህ/ቁ. 826/2/፣1179/1/   የሰ/መ/ቁ. 96628   ህዳር 8 ቀን 2007 ዓ.ም.   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- 1. አሳመነው ከበደ   2. ወ/ሮ ፍቅርተ ከበደ            ጠበቃ አቶ ፍሰሀ አለማየሁ ቀረቡ፡፡   3. አቶ ምንተስኖት ከበደ - ቀረቡ   4. ተማሪ ቀንአየሁ ከበደ   5. ተማሪ ብሩክ ከበደ   ተጠሪ፡- አቶ ዳንኤል ከበደ- ጠበቃ አቶ በየነ ታደሰ ቀረቡ፡፡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡  ፍ ር ድ   ጉዳዩ የቀረበው አመልካቾች የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 38926 ግንቦት 21 ቀን 2005 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔና የፌዴራል የከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 137992 ጥር 14 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልን በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው፡፡ ጉዳዩ የውርስ ንብረት ጥያቄን የሚመለከት ነው፡፡ በሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ አመልካች አመልካችዎች  ተጠሪ በመሆን ተከራክረዋል፡፡   1. የክርክሩ መነሻ ተጠሪ ያቀረበው ማመልከቻ ነው፡፡ ተጠሪ ወላጅ አባቴ አቶ ከበደ ሰለሞን ጥቅምት 22 ቀን 2003 ዓ.ም በሞት ተለይቶ ወራሸነታችንን አረጋግጠናል፡፡ ስለዚህ ውርስ አጣሪ ተመድቦ ውርሱ እንዲጣራ ትዕዛዝ ይሰጥልኝ በማለት አመልክቷል፡፡ አመልካቾች ውርስ አጣሪ ቢመደብና የውርሱ ንብረት ተጣርቶ ቢቀርብ አንቃወምም በማለት መልስ ሰጥተዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም ውርስ አጣሪ ከመደበ በኋላ ውርሱ ሲጣራ ተጠሪ ሟች በ 24/11/1980 ዓ.ም በተፃፈ የስጦታ ውል በ210 ካሬ ሜትር ላይ ያረፉ አንድ ክፍል ቆርቆሮ በቆርቆሮ ቤት ሰጥቶኝ አባታችን በህይወት እያለ ቆርቆሮ ቤቱን በማፍረስ ሁለት ክፍል የጭቃ ቤት ሠርቼ እየኖርኩበት...

 • 96833 Pension law/ effect of extension of pension period

  አንድ የመንግስት ሠራተኛ የጡረታ ዕድሜው ከደረሠ በኋላ አሠሪው መ/ቤት ፈቃድና ከየትኛውም አካል ተቃውሞ  ሣይቀርብ የጡረታ ጊዜው ከተራዘመ ለተራዘመበት ጊዜ የሠራበት ለጡረታ ሊያዝ የሚገባው ሥለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 714/2003፣ አዋጅ ቁጥር 515/99 አንቀጽ 85፣89   የሰ/መ/ቁ.96833 ህዳር 08 ቀን 2007 ዓም   ዳኞች፡- አልማዉ ወሌ ዓሊ መሀመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል   አመልካች፡- የመንግሥት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጄንሲ - ቀረቡ /ነ-ፈጅ/ ተጠሪ፡- አቶ አስፋዉ ደነቀ - የቀረበ የለም፡፡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ርድ   ይህ ጉዳይ በማህበራዊ ዋስትና ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የተጀመረው ተጠሪ አቶ አስፋዉ ደነቀ የተራዘመዉ አገልግሎት ለጡረታ ተግባር እንዲያዝላቸዉ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ነዉ፡፡ ተጠሪ የሚጠይቁት ተጠቃሹ መስሪያ ቤት በወቅቱ በነበረበት የሰዉ እጥረት የጡረታ ጊዜዬን ለ5 ዓመታት እንዲራዘም በጻፈዉ ደብዳቤ ለማ/ዋ/ቅ/ጽ/ቤት ሲጻፍ ለእኔም ግልባጩ ደርሶኝ በተከፈተዉ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት የውሃ ጽ/ቤት ተጠባባቂ ኃላፊነት ተመድቤ በ6 ወረዳዎች ሰራሁ፣በድጋሜ የጡረታ ግዜ ለ5 ዓመታት እንዲራዘም ለክልሉ ሲቪል ሰርቪስ  ተጽፎ የስምምነቱ ደብዳቤ ለመ/ቤቱ ሲደርስ ግልባጩ ለክልሉ ማ/ዋ/ኤ/ጽ/ቤት ደርሷል፣ የዉሃ ሀብት ቢሮ ባዘጋጀዉ አዲስ መዋቅር የተደረገዉ ስምምነት 2 ዓመት ሲቀረኝ እርምጃ ወስዷል፣ስለዚህ ከየካቲት 1995 እስከ ጥር 30 ቀን 2003 ዓ/ም ድረስ የተራዘመዉ የ8 ዓመታት አገልግሎቴ እንዲያዝልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ አመልካችም በሰጠዉ መልስም፡- አቶ አስናቀ ደነቀ የትዉልድ ዘመናቸዉ ጥር 13 ቀን 1940 ዓ.ም ሲሆን በጡረታ መገለል የሚገባቸዉ ከየካቲት 01 ቀን 1995 ዓም ጀምሮ ነዉ፣አሰሪዉ መ/ቤቱ መረጃ እንዲልክ በ2/9/95 ዓ.ም ቢጠየቅም...

 • 96858 contract law/ rent/ rent increase

  አንድ ቤት የተከራየ ሠው የኪራይ ዘመኑ ሲያልቅ አከራዩ    ኪራዮን መጨመሩን ማስጠንቀቂያ ከሠጠውና ተከራዩም ዝም ብሎ ቤቱን መጠቀም ከቀጠለአዲሱን የኪራይ ተመን ተከራዩ እንደተቀበለው የሚቆጠር ስለመሆኑ፣     የፍ/ህ/ቁ.  1684፣ 2952/2/ ሰ/መ/ቁ.96858 ቀን 26/03/2007 ዓ/ም ዳኞች፡-  አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- ወ/ሮ አብቢልክሽ ገለታ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ዶ/ር ትግስት ቦርጋ - ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ር ድ   ጉዳዩ የኪራይ ገንዘብ ይከፈለኝ ጥያቄን መሰረት ያደረገ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሁኑ ተጠሪ በአሁኑ አመልካች ላይ በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው፡፡ የተጠሪ ክስ መጋቢት 10 ቀን 2004 ዓ/ም የተጻፈ ሆኖ ይዘቱም ህዳር 19 ቀን 2003 ዓ/ም በተደረገ የኪራይ ውል አመልካች /የስር ተከሳሽ/ የተጠሪ /የስር ከሳሽ/ የሆነውን ንብረት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ 522 የሆነ መኖሪያ ቤት በየወሩ ብር 2000.00 /ሁለት ሺህ ብር/ እየከፈሉ ለሶስት ወር ተጠቅመው ሊለቁና የተጠቀሙበትን የውሃና የመብራት ወጪ ከፍለው ቤቱን ለማስረከብ ግዴታ የገቡ መሆኑን ገልጸውና በግዴታው መሰረት ቤቱን ለማስረከብ ፈቃደኛ ያለመሆናቸውን፣ በዚህም ምክንያት ተጠሪ በህጋዊ ወኪላቸው በኩል ለአመልካች ታህሳስ 19 ቀን 2004 ዓ/ም ቤቱን አመልካች እንዲለቁ፣ የማይለቁ ከሆነ ደግሞ በየወሩ ብር 5000.00 /አምስት ሺህ ብር/ እንዲከፍሉ ማስጠንቀቂያ የሰጧቸው ቢሆንም ቤቱን ያልለቀቁላቸው መሆኑን ዘርዝረው  አመልካች ያለባቸውን የሁለት ወር ከአስር ቀናት ውዝፍ ኪራይ ብር 13,499.00 እንዲከፍሉና ቤቱን እንዲያስረክቧቸው፣ ቤቱን እስከሚያስረክቡ ድረስ ያለውን ኪራይም እንዲከፍሉ...

 • 97094 civil procedure Evidence law temporary injunction attachment of property before judgment priority of creditors

  civil procedure Evidence law temporary injunction attachment of property before judgment priority of creditors በተያዘ ወይም በተከበረ ንብረት ላይ መብት አለን ብለው ተቃውሞ የሚያቀርቡ ሠዎች በንብረቱ ላይ ያላቸውን የቀዳሚነት መብት ወይም ባለይዞታነት ለማረጋገጥ በጽሁፍ ማስረጃ ብቻ ሳይወሠኑ ሌላ ማስረጃም ሊያቀርቡ የሚችሉ ስለመሆኑ፣   የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ.418/3/ እና የፍ/ህ/ቁ 1193/1//2/   የሰ/መ/ቁ 97094 ቀን 08/03/2ዐዐ7 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- ወ/ሮ አስቴር አምባው - ቀረቡ ተጠሪዎች፡- 1. አቶ አበባው ክፍሌ የቀረበ የለም 2. ያሬድ አለማየሁ የቀረበ የለም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡  ፍ ር ድ   ይህ ጉዳይ የተጀመረው በከፋ ዞን የቦንጋ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁን አመልካች በስር ፍ/ቤት በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 418 በአፈፃፀሙ ጉዳይ ጣልቃ የገቡ ሲሆኑ 1ኛ ተጠሪ የአፈፃፀም ከሳሽ 2ኛ ተጠሪ የአፈፃፀም ተከሳሽ ነበሩ የአፈፃፀም ከሳሽ /የአሁንተጠሪ/ ለአፈፃፀም ይውሉ ዘንድ 1. የልብስ ስፌት ማሽን፣ ኮንትሮል ብፌ፣ የሴቶች ፀጉር ቤት ካስክ፣ ስሶት የፀጉር ማሽን፣ የፀጉር ቤት መስታወት፣ የመቀመጫ ወንበር፣ ባለ 21 ኢንች ቴሌቪዥን እና አራት የሶፋ ወንበሮች ተሽጦ እዳው ይከፈለኝ በማለት ጠይቀዋል፡፡ ፍ/ቤቱም የተጠቀሱት ንብረቶች ተገመተው እንዲቀርቡለት ትዕዛዝ በመስጠቱ ምክንያት የአሁን አመልካች ንብረቶች የግሌ ናቸው በማለት ሊፈፀም አይገባም በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁ. 418 መሰረት በመቅረቧ ፍ/ቤቱም አመልካች ተጠቃሹ ንብረቶች የራሳቸው ለመሆኑ ያቀረቡት የፅሁፍ ሰነድ የለም፣ በሰው ምስክር አስረዳለሁ ያሉትን ክርክር በስነ ስርዓት ህጉ 418/3/ መሰረት ተቀባይነት የለውም በማለት ጥያቄውን...

 • 97132 evidence law/ expert opinion/ ownership of gun

  ለክርክሩ መነሻ የሆነ ሽጉጥ (የጦር መሳሪያ) የንምራ ቁጥር አከራካሪ በሆነበት ወይም የመጀመሪያው ንምራ ቁጥር በሌላ ተተክቷል የሚል ክርክር በተነሳ ጊዜ በመሳሪያው ላይ ያለው ንምራ ቁጥር ኦሪጅናል ነው? ወይስ በሂደት የተተካ ቁጥር ነው? የሚለውን አግባብነት ባለው አካል ሞያዊ አስተያየት/expert opinion/ አጣርቶ መወሰን አስፈላጊ ስለመሆኑ፣   የሰ/መ/ቁ.97132 መጋቢት 30 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመስል አመልካች፡- አቶ መሀመድ ከማል ሀምዛ ቀረቡ   ተጠሪዎች ፡-1ኛ የከሚሴ ከተማ ወረዳ ፖሊስ           ተወካይ አይኔ አዲስ አሰጋኸኝ ቀረቡ 2ኛ የከሚሴ ከተማ ወረዳ ሚሊሻ ጽ/ቤት መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩን ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ርድ   ጉዳዩ በኢግዚቢት ተይዞ ነበር በተባለው እስታር ማክሮቭ ሽጉጥ አመላለስ ጋር በተያያዘ የቀረበ ሲሆን በሥር የደ/ሥ/ፈ/ወረዳ ፍርድ ቤት የአሁኑ አመልካች በተጠሪዎች ያቀረቡት ክስ ውድቅ የተደረገባቸው በመሆኑ በሰበር ተጣርቶ እንዲወሰን የቀረበ ነው፡፡ አመልካች በሥር ወረዳ ፍርድ ቤት በአሁኑ ተጠሪዎች ያቀረቡት ክስ አጭር ይዘት፡- ቁጥሩ 635 የሆነው እስታር ማክሮቭ ሽጉጥ ከ8 መሰል ጥይቶች ጋር ህገ ወጥ መሣሪያ ይዘሃል ተብሎ በፖሊስ ተጠይቀው መሣሪያውም በኢግዚቢት ተይዞ ምርመራ ከተጠናቀቀ በኋላ ሽጉጡ ፈቃድ ያለው የግላቸው መሆኑ ቢከራከሩም የሥር ፍርድ ቤት ሳይቀበል ጥፋተኛ ያላቸው መሆኑን፤ ለአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት አግኝቶ በነፃ እንደተለቀቁ፣ በኢግዚቢት የተያዘው ሽጉጥ በፍትሐብሄር መጠየቅ እንደሚችሉ ሰበር ሰሚ ችሎቱ መብታቸው የጠበቀላቸው በመሆኑ፣ በኢግዚቪት ተያዘ የተባለውን ሽጉጥ ላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ አለመስጠቱን፤ ተጠሪዎች በአንድነትና በነጠላ ኃላፊዎች በመሆናቸው ሽጉጡ ከመሰል ጥይቱ በዓይነት እንዲመልሱ፤ በዓይነት ማስረከብ የማይችሉ ከሆነም...

 • 97203 criminal law/ participation in the commission of crime/ individuation of guilt

  ከአንድ በላይ ሰዎች በወንጀል ተሳታፊ በሚሆኑበት ጊዜ ለወንጀሉ ድርጊት ኃላፊ ናቸው የተባሉት ወንጀለኞች የእያንዳንዳቸውን ተሳትፎ ህጉ ባስቀመጠው የማስረጃ መለኪያ መሰረት መለየት ያለበት ስለመሆኑ- የወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ 141፣ የወ/ህ/ቁ. 40 የሰ/መ/ቁ 97203     ዳኞች፡-አልማው ወሌ ሡልጣን አባተማም መኮንን ገ/ሕይወት ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል መስከረም 30 ቀን 2007   አመልካች፡- 1.አቶ ታምራት ደምሴ 2.አቶ በሪሁን ደምሴ       የቀረበ የለም 3.አቶ ታደለ ሽቱ ተጠሪ፡- የቤንሻንጉል ጉምዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፍትህ ቢሮ ዐቃቤ ሕግ - የቀረበ የለም፡፡ መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ  ር ድ   ጉዳዩ የወንጀል ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በመተከል ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው፡፡ በዚህ ፍ/ቤት የአሁኑ ተጠሪ በአሁኑ አመልካቾች እና አቶ አለኽኝ ጋሻው በተባሉት ግለሰብ ላይ የመሰረተው ክስ:- በ1996 ዓ.ም በወጣው የኢ.ፌ.ዲ.ሪፐብሊክ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1)(ሀ) እና 539/1/ሀ/ ስር የተመለከተውን በመተላለፍ ታህሳስ 29 ቀን 2002 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 3፡00 በሚሆንበት ጊዜ ግልገል በለስ ከተማ ከወ/ሮ አለምፀሐይ ጌታሁን ሻይ ቤት አረቄ እየጠጡ በፈጠሩት ፀብ ለምንድን ነው የሰደብከን? በማለት የአሁኑ 1ኛ፣2ኛ አመልካቾች እና የስር 3ኛ ተከሳሽ የነበሩት አቶ አለኸኝ ሟች ኤርሚያስ ኃይሉን ሊደበድቡት ሲሉ በገላጋይ ከቤት ከወጡ በኋላ ከስር ሶስተኛ ተከሳሽ ጋር በመሆን ተከታትለው በመሄድ ኤርሚያስ ኃይሉን በአንድ ላይ ተባብረው በዱላና በድንጋይ ግንባሩንና መላ ሰውነቱን ደብድበው በግፍ ገድለዋል የሚል ነው፡፡አመልካቾች ክሱ ተነቦላቸው እንዲረዱት ከተደረገ በኋላ ስለእምነት ክህደት ቃል ሲጠየቁ በክሱ ላይ ተቃውሞ የሌላቸው መሆኑን ገልፀው የድርጊቱ አፈጻጸሙን በተመለከተም ክደዋል፡፡ ተጠሪ በበኩሉ አሉኝ ያላቸውን ማስረጃዎችን ያሰማ ሲሆን የስር ፍ/ቤትም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃዎችን መርምሮ አመልካቾች ድርጊቱን መፈፀማቸው በበቂ ሁኔታ...

 • 97332 civil procedure execution of judgement sale by auction defect in auction

  የፍርድ ባለዕዳ ንብረት የሆነ ለፍርድ ማስፈፀሚያ ተብሎ በጨረታ ከተሸጠ በኋላ በሐራጅ ላይ ጉድለት አለ፣የጨረታ ሽያጩ ይሰረዝ የሚል አቤቱታ በሚቀርብበት ጊዜ ሽያጩ ሊሰረዝ ይገባዋል? ወይስ አይገባውም? በሚለው ላይ መከራከር ያለባቸው የፍርድ ባለዕዳና ባለገንዘብ ብቻ ሳይሆኑ ንብረቱን በሐራጅ አሸንፎ የገዛው 3ኛ ወገንም ጭምር ስለመሆኑ፡   የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 32፣39፣40፣79 እና 370(3)   የሰ/መ/ቁጥር 97332   መጋቢት 30 ቀን 2007 ዓ/ም   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- አቶ አይመረ በላይ - ጠበቃ ሙሉአለም ዘውዴ ቀረቡ ተጠሪ፡- 1. መሪጌታ ኮነ ንጋቱ - ጠበቃ ተሾመ መኮንን ቀረቡ 2. አቶ አንዷለም አሻግሬ - ታልፏል   መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ር ድ   ጉዳዩ አንድ በፍርድ ቤት የተደረገ የጨረታ ሽያጭ ውድቅ የሚሆንበትን አግባብ የሚመለከት ነው፡፡ የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካች የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁጥር 14450 በሆነው ህዳር 4 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እንዲነሳላቸው አመልካች ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት በማጣቱ ነው፡፡   የክርክሩ አመጣጥ ሲታይም የአሁን1ኛ ተጠሪ ለአሁኑ 2ኛ ተጠሪ በነበረባቸውና በወረዳው ፍርድ ቤት በተወሰነው የብር 15,000.00 ዋና ገንዘብ፣ የዚሁ ገንዘብ ወለድና የተለያዩ ወጪዎች ዕዳ መክፈያ እንዲሆን በአሁን አመልካች ስም ይታወቅ የነበረው በአዴት ከተማ ቀበሌ 02 ክልል ውስጥ የሚገኘው ቤት በምስራቅ መንገድ፣ በምእራብ 16 ቁጥር፣ በሰሜን 15 ቁጥር፣ በደቡብ 19 ቁጥር በሚያዋስኑት መካከል የሚገኝ ቤት ባለሙያ ተገምቶ በአከባቢ ማስታወቂያ ጨረታ እንዲወጣ ተደርጎ የአሁኑ አመልካች የሃራጁ አሸናፊ ሁነው ከተሸጠ በኋላ የ1ኛ ተጠሪ  እዳ ለ2ኛ ተጠሪ እንዲከፈል፣ የተረፈው ገንዘብ ደግሞ ለአሁኑ 1ኛ ተጠሪ እንዲቀመጥላቸው የወረዳው ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሲሰጥ የአሁኑ 1ኛ...

 • 97683 unlawful enrichment/ government houses/ liability of government

  የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ያልተወረሰ ቤትን በህገወጥ  መንገድ በመያዝ የተጠቀመበት ከሆነ የኪራይ ገንዘብና ያለአግባብ የበለፀገበትን ያህል ሊከፍል የሚገባ ስለመሆኑ፡-   ያለአግባብ በመንግስት ተይዞ ለቆየ ቤት የታጣ ጥቅም አይከፈልም ሊባል የማይችል ስለመሆኑ፡-   የፍ/ሕ/ቁ 2162   አዋጅ ቁጥር 193/92 አንቀፅ 7(3) አዋጅ ቁጥር 192/92 አንቀፅ 3 የሰ/መ/ቁ. 97683   መጋቢት 18 ቀን 2007 ዓ.ም   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሀመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኸሊት ይመሰል አመልካች፡- አክበር አሊ ካምሩዲን ኩባንያ ተጠሪዎች ፡- 1) የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ 2) የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ የቀጠና 4 ጽ/ቤት   3) በመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ የአ/አ ቅ/ጽ ቤት   መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ር ድ   ጉዳዩ የተጀመረው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች ከሳሽ ተጠሪዎች ተከሳሽ ነበሩ፡፡ አመልካች ባቀረቡት ክስ 1ኛ ተጠሪ የቤት ቁ.868 እና 872 ሁከት በመፍጠር በመያዝ 2ኛ ተጠሪ በቤት ውስጥ የነበሩትን ልዩ ልዩ ዕቃዎች እና ሰነዶች በ3ኛ ተጠሪ መጋዘን የተቀመጠ ሲሆን 2ኛ ተጠሪ ዕቃውን እንዲመልስ ቢጠየቅ ለመመለስ ፍቃደኛ አልሆነም በተጨማሪም 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች የአመልካችን ቤት ለተለያዩ ግለሰቦች እያከራዩ ብር 149,294,00 (አንድ መቶ አርባ ዘጠኝ ሺ ሁለት መቶ ዘጠና አራት ብር) ተጠቅመውበታል፡፡ አመልካች ቤቱን ስረከብ 5000 ብር ወጪ አድርጌያለሁ ፡፡1ኛ እና 2ኛ ተጠሪ ቤቱን አከራይተው አለአግባብ የበለጸጉበትን እና ቤቱን ለማሳደስ ያወጣሁትን ወጪ በድምሩ 154,294,00 (አንድ መቶ ሀምሳ አራት ሺ ሁለት መቶ ዘጠና አራት ብር) የስር 4ኛ፣5ኛ ፣6ኛ ተከሳሾች ጭምር የአሁን ተጠሪዎች የአመልካችን ንብረት ይመልሱ ፣ካልሆነ ግምቱን ብር 124,786.(አንድ መቶ ሀያ አራት ሺ ሰባት መቶ ሰማንያ ስድስት ብር) እንዲከፍሉኝ ባጠቃላይ ተጠሪዎች 279,080.00(ሁለት መቶ ሰባ...

 • 97948 law of succession/ government houses/ justiceable matters

  አንድ የቀበሌ ቤትን ተከራይቶ የነበረ ሠው ከዚህ አለም በሞት ሲለይ ወራሾቹ ወይም ቤተሠቦቹ የተከራይነት መብቱ ይተላለፍልን ብለው በሚጠይቁበት ጊዜ ከሕግ አኳያ ዳኝነት የሚሠጥበት እንጂ በፍርድ ቤት የሚያልቅ ጉዳይ አይደለም ብሎ ጥያቄውን  አለመቀበል አግባብነት የሌለው ስለመሆኑ፣ የኢ.ፌ.ዲ.ሪፕብሊክ ህገ መንግስት አንቀጽ 37 የፍ/ህ/ቁ. 826/2/ እህ 2928 የሰ/መ/ቁ. 97948   ታህሳስ 21 ቀን 2007 ዓ/ም   ዳኞች፡-አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡-ወ/ሪት ሄለን ተክሌ - ቀረቡ ተጠሪ፡-ወ/ሮ ዘይድ አብርሃ - የቀረበ የለም መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ር ድ   ጉዳዩ የውርስ ንብረት ይጣራልኝ ጥያቄን የሚመለከት ነው፡፡ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች የሟች አባታቸው የአቶ ተክሌ ነጋሽ የውርስ ንብረት እንዲጣራላቸው ባቀረቡት አቤቱታ መነሻ ነው፡፡ የውርስ አጣሪው በፍርድ ቤቱ ተቋቁሞ የማጣራት ስራውን ከአጠናቀቀ በኋላ ሪፖርቱ ለፍርድ ቤቱ ቀርቦ ግራ ቀኙ አስተያየት ከሰጡበት በኋላ የውርስ አጣሪው ሪፖርት ተሻሽሎ በስር ፍርድ ቤት ፀድቋል፡፡በዚህ ውሳኔ የአሁኗ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የሥር ፍርድ ቤትን ውሳኔ አፅንቶታል፡፡የአሁኑ የሠበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው፡፡የአመልካች የሠበር አቤቱታ መሰረታዊ  ይዘትም፡- አመልካች ሶፋውን ከእነ ሙሉ ጠረጴዛ የግል ንብረቴ ነው በማለት ጠይቀው እያለ በንብረቱ ላይ የግል ወይም የጋራ ነው ተብሎ ዳኝነት ሳይሰጥበት መታለፉ እና የቀበሌ ቤት የተከራይነት መብትን በተመለከተም አመልካች በወራሽነታቸው የሚገባቸው ስለመሆኑ በፍርድ ቤት መወሰን ሲገባው በቤቱ አካራይ የሚወሰን ነው ተብሎ መታለፉ ያላግባብ ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ...

 • 98263 Execution of judgment/ agreement between judgment creditor and debtor/ registration of agreement

  በፍርድ ውሣኔ በተሰጠበት ጉዳይ አፈፃፀምን ለማስቀረት በፍርድ ባለመብት እና በፍርድ ባለ ዕዳ የሚደረግ የእርቅ ውል በፍርድ ቤት ቀርቦ  ካልፀደቀ በቀር አፈፃፀምን ሊያስቀር የሚችል ስላለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 276፣277 የሰ/መ/ቁ. 98263 ጥር ዐ6 ቀን 2ዐዐ7 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመስል አመልካች፡- ወ/ሮ እናናይቱ ይሳ - አልቀረቡም   ተጠሪ፡- ወ/ሮ ሀሲና ሁሴን ወራሽ መክያ ከንዙ - ቀረቡ   መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡    ፍ ር ድ   ጉዳዩ የቀረበው አመልካች የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችሎት በመዝገብ ቁጥር 34482 የካቲት 13 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም በሰጠው ትዕዛዝ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 356ዐ8 የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት የደረሰበት መደምደሚያ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት ያቀረበችውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው፡፡ ጉዳዩ በአፈፃፀም ክርክር የሚመለከት ነው፡፡ አፈፃፀሙ በመጀመሪያ የታየው በፎገራ ወረዳ ፍርድ ቤት ነው፡፡ በወረዳው ፍርድ ቤት ተጠሪ የአፈፃፀም ከሳሽ አመልካች የአፈፃፀም ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡   1. የክርክሩ መነሻ ተጠሪ አመልካች በመዝገብ ቁጥር 11394 በተሰጠው ፍርድ መሰረት በመሬቱ ላይ የገነባቸውን ንብረት በማንሳት ቦታውን እንድታስረከብ ይወሰንልኝ የሚል የአፈፃፀም ክስ ለወረዳው ፍርድ ቤት በማቅረቧ ነው፡፡ አመልካች በተከሳሽነት ቀርባ፤ የፍርድ ባለመብት ከነበረችው ከሟች ወ/ሮ ሀሲና ሁሴን ጋር የካቲት 28 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም የዕርቅ ውል ተዋውለናል፡፡ በዕርቁም የፍርድ ባለዕዳ ለፍርድ ባለ መብት ብር 6ዐዐዐ /ስድስት ሺ ብር/ ለመከፈልና ቦታውንና ቤቱን ባለበት ሁኔታ ይዥ ለመቆየት ተስማምተናል፡፡ የዕርቅ ውሉን...

 • 98283 criminal law/ criminal responsibility of judges/ corruption

  ከዳኝነት ስራ ጋር ያልተያያዙ እና የአስተዳደር ስራ ሲያከናውኑ የሚፈፀሙ የወንጀል ጥፋቶች ዳኛውን ከተጠያቂነት የማያስቀሩ ስለመሆኑ፣ የወ/ህ/ቁ. 402(1) እና (2) በትግራይ ክልል ዳኞች እና ሬጂስትራሮችን ለማስተዳደር ተሻሽሎ የወጣው ደንብ ቁጥር 1/2003 የሰ/መ/ቁ. 98283   መስከረም 26 ቀን 2007 ዓ.ም   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   መኮንን ገ/ህይወት ሙስጠፋ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ተኸሊት ይመስል አመልካች፡- አቶ ሐጐስ ገ/ሄር መኮንን   ተጠሪ፡- የትግራይ ክልል የስነ/ፀ/ሙ/ኮ - ዐ/ሕግ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ወስነናል፡፡  ፍ ርድ   የአሁኑ አመልካች በወንጀል ህጉ አንቀጽ 407(2) የተመለከተውን በመተላለፍ የማይገባውን ብልፅግና ለራሱ ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ በትግራይ ክልል በደቡብ ዞን አሰላ ወረዳ ፍ/ቤት ዳኛ ሆኖ ሲሰራ ሥልጣኑን አላግባብ በመጠቀም የመንግስት የአበል አከፋፈል ሥርዓት በመጣስ ለራሱና ለሥራ ባልደረቦች ሊከፈል የማይገባውን ብር 7653.4 እንዲከፈል በማድረጉ በፈፀመው በሥልጣን ያለአግባብ መጠቀም ወንጀል ተከሷል ሲል የአሁን ተጠሪ  ክስ አቅርቦበታል፡፡   ጉዳዩን በቅድሚያ የተመለከተው የአላማጣ ማዕከላዊ ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ከሰማ በኋላ አመልካች በተዘዋዋሪ ችሎት ስም ከሥራ ቦታዬ ወደ ቀበሌዎች ሄጃለው በማለት በተሞክሮ ልውውጥ ስም፤ በመሀበራዊ ፍ/ቤትና የመሬት ዳኞች ሥልጠና ስም አበል አላግባብ መውሰዱ ፤ዳኞች ስልጠና ሰጥተዋል በማለት በፔሮል ወደ ቀበሌ እንደወጡ አሰመስሎ አበል መክፈሉ ፤ የሂሳብ መደብ በማይፈቅድበት ሁኔታ በራሱ ስም አበል ወጪ በማድረግ የፅሕፈት መሣሪያ መግዛት እና ከፋይናንስ ደንብ እና መመሪያ ውጭ ስለመስራቱ በራሱ በዝርዝር የተመለከተውን እና የቀረበበትን የሰውም ሆነ የሰነድ ማስረጃ ማስተባበል ባለመቻሉ እንደ ክሱ አቀራረብ ጥፋተኛ ነው በማለት የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶችን ተቀብሎ በ1(አንድ) ዓመት ፅኑ እስራት እና በብር 2000...

 • 98358 contract law/ shipping contract/ non-performance/ period of limitation

  የባህር ላይ የእቃ ማጓጓዝ ውልን በተመለከተ የዕቃው ርክክብ ከተፈፀመበት ወይም የማስረከቡ ጉዳይ ሳይፈፀም ቀርቶ እንደሆነ እቃውን ማስረከብ ከሚገባበት ቀን አንስቶ በአንድ አመት ውስጥ ክስካልቀረበ በይርጋ የሚታገድ ስለመሆኑ፡-   የባህር ህግ ቁጥር 203፤180፤162 የሰ/መ/ቁ. 98358   ጥር 05 ቀን 2007 ዓ.ም   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ -ነገረ ፈጅ ኃይሉ ተሰማ ቀረቡ   ተጠሪ፡- የኢትዩጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ጠበቃ ማረን ወንዴ - ቀረቡ   መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ       ር       ድ   ጉዳዩ የመድን ውልን መሠረት አድርጎ የቀረበውን የገንዘብ ይተካልኝ ጥያቄ የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች በአሁኑ ተጠሪ ላይ በፌዴራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረተው ክስ መነሻ ነው፡፡የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡- የአሁኑ አመልካች ለደንበኛው ለነፃ ኃላፊነቱ የተ.የግል ማህበር ከቱርክ ሀገር ለሚያስመጣቸው 246 ጥቅል ብረቶች ከተጫኑበት ሀገር ተጓጉዞ እስኪመጣ ድረስ ለሚያጋጥም ጉዳት በፖሊሲ ውል ቁጥር 01/ኤም አር ኦኤ/00001/07 የባህር ላይ የጉዞ መድን ሽፋን መስጠቱን፣ተጠሪ የመድን ሽፋን የተሰጣቸውን 246 ጥቅል ብረቶችን ተረክቦ ሆውማ ቤሊ ቪ.ኢኤስቲአር53  በሚባለው  መርከብ ከሊአጋ ኢዝሚር ቱርክ አጓጉዞ ጅቡቲ ለማድረስ በባህር እቃ መጫኛ ሰነድ ቁጥር 305/ኤስሲ ግዴታ መግባቱን፣ተጠሪ ጅቡቲ ለማድረስ ግዴታ ከገባባቸው 246 ጥቅል ብረቶች ውስጥ እቃው ጅቡቲ ወደብ ደርሶ ሲራገፍ 11(አስራ አንድ) ጥቅል ብረቶች መጥፋታቸውን፣ ከተጓጓዘው 246 ጥቅል ብረቶች ውስጥ የአመልካች ደንበኛ በ11/04/2004 ዓ/ም 226 ጥቅል አዲስ አበባ ላይ በእቃ መረከቢያ ሰነድ ቁጥር 10431 መረከቡን፣ቀሪው 20 ጥቅል ብረት ውስጥ 9 ጥቅል ደግሞ ዘግይቶ በ05/06/2004...

 • 98541 Diplomatic immunity/ jurisdiction of court/ labor law dispute/ Ethiopian employees of UN organizations

  የዲፕሎማቲክ ግንኙነቶችን ስምምነት ልምድን ለማክበር ሲባል የውጭ ዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖችና ኢትዮጲያዊያን ሠራተኞቻቸው የሚያደርጉት የቅጥር ግንኙነት ላይ የአሠሪና ሠራተኛ ሕግ ተፈፃሚ የማይሆን ስለመሆኑ፡-   የተባበሩት መንግስታት አካል የሆነ ድርጅት የተባበሩት መንግስታት ጥቅምና የተለየ ከለላን በተመለከተ በተደነገገ ሥምምነት በማንኛውም የመንግስት ፍ/ቤቶች ተከሶ መቅረብ የሌለበት ሥለመሆኑ፡-   አፈፃፀም በፍርድ ቤት የተሰጠ ውሳኔ ትርጉም እንዲኖረው በማድረግ ውጤት ያለውና በተገቢው መንገድ መፈፀም ያለበት መሆኑ የሚታወቅ ቢሆንም ለማንኛውም ጉዳዮች ይሰራል ተብሎ ድምዳሜ ላይ መድረስ የማይቻል ስለመሆኑ፡-   አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 3/3(ሀ) የተባበሩት መንግስታት ቻርተር አንቀፅ 105 ከተባበሩት መንግስት ጥቅምና የተለየ ከለላን በተመለከተ የተደነገገው ሥምምነት አንቀፅ 2/2/ እና 3   የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 212 የሰ/መ/ቁ/ 98541   ህዳር 10 ቀን 2007 ዓ.ም   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሡልጣን አባተማም መስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- አቶ አለማየሁ ኦላና - ቀረቡ   ተጠሪ፡-የተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት (UNDP) ታልፏል ፡፡   መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ርድ   ይህ የሰበር ጉዳይ የቀረበው አመልካች በተጠሪ ላይ የአሠሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/1996 ድንጋጌዎችን መሰረት አድርገው ያቀረቡት ክስ ተጠሪ በሌለበት ታይቶ በክርክሩ ከተረጋገጠበት የፍሬ ነገር ጉዳዮች በመነሳት የአሁኑ አመልካች የተለያዩ ክፍያዎች በተጠሪ እንዲከፍሏቸው በወረዳው ፍርድ ቤት በተወሰነው መሰረት የአፈጻጸም መዝገብ ከፍተው ክርክሩ በመታየት ላይ እያለ ተጠሪ የመከሰስ መብት የለውም ተብሎ የአፈጻጸም መዝገቡ በሁሉም የበታች ፍርድ ቤቶች መዘጋቱ ተገቢ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ተብሎ ነው፡፡   የአሁን አመልካች ተጠሪ ከህግ ውጪ ከስራ አሰናብቶኛል በማለት ካሳና የተለያዩ ክፍያዎች እንዲከፍሏቸው ይወሰን ዘንድ በያበሎ ወረዳ ፍርድ ቤት በአሁኑ...

 • 99375 court jurisdiction/ jurisdiction of federal courts/ Addis Ababa city court

  የአዲስ አበባ መስተዳደር አስፈፃሚ አካላት በሌላ ሰው ንብረት ላይ ጉዳት አድርሰዋል ካሳ ይክፈሉ ተብሎ የሚቀርብ ክስን በተመለከተ የማየት የስረ-ነገር ስልጣን ያላቸውየፌዴራል  ፍ/ቤቶች ስለመሆናቸው፡-   አዋጅ ቁጥር 361/1995፣ አዋጅ ቁጥር 408/1996   አዋጅ ቁጥር 25/88   የሰ/መ/ቁ.99375 መጋቢት 15 ቀን 2007 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማዉ ወሌ   ዓሊ መሀመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- አምባቸዉ አለሙ - ጠበቃ ፋሲል ቀረበ ተጠሪዎች፡-1ኛ የካ/ክ/ከ/ወ/01/አስተደር - የቀረበ የለም 2ኛ አቶ አሸናፊ መንገሻ   3ኛ አቶ ኦገስት አድነዉ   4ኛ አቶ አድማሱ አንጀሎ   መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ  ር ድ   ጉዳዩ የተጀመረዉ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ተከሳሾች ነበሩ፡፡ አመልካች ባቀረቡት ክስ በተለምዶ ፈረንሳይ ለጋሲዩን ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ በግምት 5 ሄክታር የተጎዳ መሬት በ 1985 ዓ/ም ተረክቤ የተለያዩ የዉጭ እና የሀገር ዉስጥ ዛፎች አልምቼ ዙሪያዉን በግንብና በሽቦ አጥር በመከለል፤ በርካታ የንብ፤ እንስሳት እርባታ፤ የእንግዳ መቀበያ እና መዝናኛ ቤቶች የሚገኙበትን የተሟላ መናፈሻ አቋቁሜ እያለሁ ተጠሪዎች እኔ በማላዉቀዉ ሁኔታ በመምጣት መናፈሻዉን በዉስጡ የነበሩትን ንብረቶችን አዉድመውብኛል ፤ግምቱንና የተቋረጠ ገቢ ብር 30,822,160.00(ሰላሳ ሚሊዩን ስምንት መቶ ሃያ ሁለት ሺህ አንድ መቶ ስልሳ ብር) ከፍለዉኝ ድርጅቱን እንዲያስረክቡኝ ሲል ጠይቋል፡፡   1ኛ ተጠሪ በሰጠዉ መልስ አመልካች ይዞታዉን በህጋዊ መንገድ አልተረከበም፣  በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1195 እና በደንብ ቁ.14/96 መሰረት ያቀረበዉ ማስረጃ የለም፣ ወደመ የተባለዉም ንብረት ስለመኖሩም አልተረጋገጠም፣ አመልካች ይዞታን አለቅም የሚል ሲሆን ተጠሪ በህግ በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት ያከናወነው ተግባር በመሆኑ ሊከስ መብት የለዉም፣ ፍርድ ቤቱም ጉዳዩን የማየት ስልጣን የለዉም በማለት ተከራክሯል፡፡...

 • 99679 arbitration/ recusal of arbitrator

  በአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት የግልግል ተቋም ውስጥ አንድን ጉዳይ በግልግል እንዲያይ የተቀመጠ የግልግል ዳኛ ከተከራካሪ ወገኖች በአንዱ እንዲነሳ አቤቱታ በሚቀርብበት ጊዜ ይነሳ የተባለው ዳኛ ልነሳ አይገባም ብሎ ጥያቄውን ካነሳው ወገን ጋር ሊከራከር የማይገባው ሥለመሆኑና ልነሳ አይገባም እያለ በሚከራከርበት ሆኔታም ጉዳዩን ገለልተኛ ሆኖ ያየዋል ተብሎ ሥለማይገመት መነሳት ያለበት ሥለመሆኑ፣   አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 9 እና 10 የፍ/ህ/ቁ.3342/ 3340/2/ የግልግል ተቋሙ የተሻሻለ ደንብ አንቀጽ 13 እና 15 የሰ/መ/ቁ 99679 ታህሳስ 24 ቀን 2007 ዓ.ም.   ዳኞች፡- አልማው ወሌ ዓሊ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- የኢትዮጵያ ኤርፓርቶች ድርጅት - ጠበቃ አቶ ሚካኤል ጉንታ ቀረቡ፡፡ ተጠሪ፡- አቶ በየነ ወልደገብርኤል - ጠበቃ ኃይሉ ብርሃኑ ጋር ቀረቡ፡፡ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡    ፍ ር ድ   ጉዳዩ የቀረበው አመልካች የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 96130 ጥር 6 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ መሠረታዊ የሕግ ሰህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት አመልካች ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው፡፡ ጉዳዩ የግልግል ጉባኤ ዳኛና ሰብሳቢ ሆኖ የተሰየመ ሰው ጉዳይን ከማየት ይነሳልኝ በሚል መንገድ በቀረበ ጥያቄ የተሰጠን ውሣኔ በመቃወም የቀረበ ነው፡፡ 1. ጉዳዩ የተጀመረው ለአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤትና የዘርፍ ማህበራት የግልግል ተቋም አመልካች ባቀረበው ጥያቄ ነው፡፡ በግልግል ተቋሙ መልስ ሰጭ የሆነው አመልካችና የይገባኛል ጥያቄ አቅራቢ የሆነው ጂኦሜትሪ ሉዊጅ ቫርኔሮ  አምፕራስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በመካከላቸው የተፈጠረው አለመግባባት በግልግል ዳኞች እንዲቀርብ በመስማማታቸው የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤትና የማህበራት ዘርፍ...

 • 99689 higher education/ award of diploma

  አንድ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ላስተማራቸው ተማሪዎች ጊዜያዊ ዲፕሎማ ከሠጠ በኋላ ዋናው ዲፕሎማ ሳይሠጣቸው የማስተማር ፈቃዱ ቢነጠቅ እንኳ ፈቃዱን ተነጥቄያለሁ፣  ዋናውን ዲፕሎማ ልሰጥ አልችልም የማለት መብት የሌለው ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 650/2001፣ ደንብ ቁጥር 199/2003   የሰ/መ/ቁ. 99689   ታህሳስ 24 ቀን 2007 ዓ/ም   ዳኞች፡-አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡-ዶ/ር መኮንን ንዋይ የአዲስ አበባ ዴንታል ሳይንስና ኮሌጅ ባለቤትና   ዲን   - ጠበቃ ግርማ ኃይሌ ቀረቡ     ተጠሪ፡- 1. መንግስቱ ጋሞ 2. አቶ እንዳለ አለማየሁ 3. አቶ ኢሳያስ አበራ 4. አቶካሊድ አባስ 5.ወ/ሮ መሰረት መላኩ              ሌሎች አልቀረቡም 6. አቶ አዲስአለም አለማየሁ 7. አቶ ታዬ አዱኛ……….ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡  ፍ ርድ   ጉዳዩ ኦርጂናል ዲፕሎማ ይሰጠኝ ጥያቄ የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪዎች በአሁኑ አመልካች ላይ በፌዴራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው፡፡የተጠሪዎች የክስ ይዘትም፡-አመልካች በ1999 ዓ/ም አዲስ አበባ ዴንታል ሳይንስ ኮሌጅውስጥ ለማስተማር ተቀብሎ ለሶስት አመታት የጥርስ ህክምና ትምህርት አስተምሮ በ2002 ዓ/ም ካስመረቀ በኋላ ትራንስክርቢትና ጊዚያዊ ዲፕሎማ የሰጣቸው ቢሆንም ኦርጂናል ዲፕሎማውን ለመስጠት ፈቃደኛ ያለመሆናቸውን ገልጸው ይህንኑ  ማስረጃ እንዲሰጧቸው ይወሰን ዘንድ ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጡት መልስም ተጠሪዎች ትምህርቱን ጨርሰው ጊዜያዊ ዲፕሎማ መውሰዳቸውንአምነው ዋናውን ዲፕሎማ ለመስጠት ኮሌጁ ዝግጅት ላይ እንዳለ የመንግስት ክልከላና የፈቃድ ስረዛ በማጋጠሙ የተነሳ ማህተምም ሆነ ፊርማ የሚፈርም ባለስልጣን ባለመኖሩ ለተጠሪዎች ኦርጂናል ዲፕሎማ እንዳልተሰጠና በፍርድ ቤት ቢወሰንም ሊፈጸም የማይችል መሆኑን ገልጸው ክሱ ውድቅ ሊሆን ይገባል በማለት ተከራክረዋል፡፡ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማና ተገቢ ነው...

 • 99717 jurisdiction of court/ jurisdiction of federal courts

  የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መምህራን ትምህርት ለመማር ከአሰሪያቸው ተቋም ጋር የሚያደርጉትን ውል አፈፃጸምና ከውሉ ጋር ተያያዥ ባላቸው ጉዳዮች ላይ የሚነሱ ክርክሮችን ለማየት ስልጣኑ ያላቸው የፌደራል ፍርድ ቤቶች ስለመሆናቸው፣   የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 79(1)   የፌድራል የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 515//1919 አንቀፅ 75(5)(6) የሰ/መ/ቁ. 99717   ጥር 20 ቀን 2007 ዓ/ም   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሀመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመስል አመልካች ፡- አቶ ሲሳይ ይማነ - ቀረቡ   ተጠሪ፡- አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ነገረ ፈጅ አቶ መስፍን ጌታቸው - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል ፡፡  ፍ ር ድ   ጉዳዩ የቀረበው አመልካች የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመዝገብ ቁጥር 41105 ህዳር 30 ቀን 2006 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔና የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ  ቁጥር 143053 ጥር 13 ቀን 2006 ዓ/ም የሰጠው ትእዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው፡፡ ጉዳዩ የዳኝነት ስልጣን ጥያቄን የሚመለከት ነው፡፡ በስር ፍ/ቤት አመልካች ከሳሽ ተጠሪ  ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ 1. የክርክሩ መነሻ አመልካች ያቀረበው ክስ ነው፡፡ አመልካች  /ከሳሽ/  ከተከሳሽ ጋር የአካዳሚክ ሰራተኛ የነበረ መሆኑን ገልፆ፣ ግንቦት 9 ቀን 2001 ዓ/ም ከሳሽና ተከሳሽ ባደረጉት ስምምነት መሰረት በሌክቸረርነት አገልግያለሁ፣ ከሳሽ የማስተርስ ድግሪ ትምህርት በመማር ውጭ ሃገር ሄጄ ተመልሻለሁ፡፡ ከዚያም የዶክትሬት  ድግሪ ትምህርት ለመከታተል ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ተከሳሽ ከነሀሴ 19 ቀን 2001 ዓ/ም ጀምሮ ለሶስት ዓመታት የሚታሰብ ፍቃድ ሰጥቶኝ የዶክተሬት ትምህርቴን በመከታተል ላይ እገኛለሁ ትምህርት ፍቃድ የተሰጠኝ ሀምሌ 4 ቀን 2001 ዓ/ም...

 • 99743 execution of judgment/ counter-claim/ set-off

  የፍርድ ባለመብት ፍርዱን እንዲፈፀምለት ሲጠይቅ የፍርድ ባለዕዳው የፍርድ ባለመብቱ ተነፃፃሪ የሆነ ግዴታውን እንዲወጣ ትዕዛዝ ይሠጥልኝ በማለት ጥያቄ ለማቅረብ የሚችለው በአንድ ፍርድ ቤት ውስጥ ሁለቱም ተከራካሪ ወገኖች የፍርድ ባለመብት መሆናቸው ተረጋግጦ ውሳኔ ተሰጥቶበት እንደሆነ ብቻ ስለመሆኑ፡-   አንድ የፍርድ ባለእዳ እንደ ፍርዱ እንዲፈጽም ሲጠየቅ ፍርድ ያላረፈበትን ቅድመ ሁኔታ በማቅረብ በአፈፃፃም ሊከራከር ሥላለመቻሉ፣   የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 398፣ 378 የ/ሰ/መ/ቁ 99743   መጋቢት 17 ቀን 2007 ዓ.ም   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- ንብ ኢንሹራንስ (አ.ማ) - ነገረ ፈጅ ተስፋሁን ሽብሩ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ራዲካል ኢንጅነሪንግ ኃላ/የተ/የግል ማህበር - አልቀረበም፡፡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል  ፍ ርድ   ጉዳዩ የቀረበው አመልካች የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 147896 መጋቢት 22 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው የአፈፃፀም ትዕዛዝና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችሎት በመዝገብ ቁጥር 99409 ሚያዝያ 3 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው፡፡ ጉዳዩ ፍርድ አፈፃፀም የሚመለከት ነው፡፡   1. የክርክሩ መነሻ ተጠሪ ያቀረበው የአፈፃፀም ክስ ነው፡፡ ተጠሪ አመልካች ወጪና ኪሣራን ጨምሮ አመልካች በፍርድ የተወሰነበትን ብር 589880/ አምስት መቶ ሰማኒያ ዘጠኝ ሺ ስምንት መቶ ሰማኒያ ብር / እንዲከፍል የአፈፃፀም ትዕዛዝ ይሰጥልኝ በማለት ለሥር ፍርድ ቤት የአፈፃፀም ክስ አቅርቧል፡፡ የሥር ፍርድ ቤት አመልካች በፍርዱ መሠረት የማይፈፀምበትን ምክንያት ቀርቦ እንዲያስረዳ ትዕዛዝ ሰጥቶ አመልካች የፍርድ   ባለመብት /ተጠሪ/ የሚከናወን ቅሪት ለመሸጥ የሚያስፈልግ ሊብሬና ውክልና...

 • 101020 labor law dispute salary

  በሠራተኛው የሚጠየቅ የውዝፍ ደመወዝ ክፍያ ጥያቄ በአሠሪው የይርጋ መቃወሚያ ካልቀረበበት በስተቀር ተከፋይ ስለመሆኑ።- የሰ/መ/ቁ. 101020 መስከረም 29 ቀን 2007 ዓ.ም   ዳኞች፡- አልማው ወሌ ሱልጣን አባተማም መኰንን ገ/ህይወት ሙስጠፋ አህመድ ተኸሊት ይመስል   አመልካች፡- አቶ ዳዊት ገ/ማርያም - የቀረበ የለም፡፡ ተጠሪ፡- አቶ ሣህለማርያም ደግፌ - የቀረበ የለም፡፡ መዝገቡ ተመርምሯል፡፡    ፍ ር ድ   የሰበር አቤቱታው የሶማሌ ክልል መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ.05-0- 60/06 መጋቢት 19 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም በሰጠው ውሣኔ መሠረታዊ የህግ ስህተት ተፈፅሟል ይታረምልን የሚል ሲሆን፤ይግባኝ ባይ በጠበቃቸው በኩል ግንቦት 18 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት ሦስት ገጽ ቅሬታ፡- በሥር ፍርድ ቤት ከሳሽ የአሁኑ የሰበር አመልካች በተጠሪ ላይ በ17/10/2005 ዓ.ም በተፃፈ ክስ ከተጠሪ ጋር በ3ዐ/09/2004 ዓ.ም በተዋዋሉት የሥራ ቅጥር ውል መሠረት አመልካች ሲሰሩ የቆዩ ቢሆንም ተጠሪ ክፍያ ባለመፈፀማቸው እና አመልካችን ከሥራ አላግባብ በማሰናበታቸው ተጠሪ ውዝፍ ደመወዝ፣ ካሣ እና ሌሎች ጥቅማ ጥቅም ለአመልካች እንዲከፍሉ ይወሰንላቸው ዘንድ ጠይቀዋል፡፡ ተጠሪ ለቀረበባቸው ክስ ከአመልካች ጋር የሥራ ቅጥር ውል የለንም ከማለት አልፈው በፍሬ ነገር ክርክሩ መልስ ባለመስጠታቸው ክሱ የቀረበለት የጅጅጋ ወረዳ ፍርድ ቤት በግራ ቀኙ መካከል የሥራ ቅጥር ውል አለ ተጠሪ ውዝፍ ደመወዝ ብር 42,000 /አርባ ሁለት ሺህ/ አመልካች ይክፈሉ ሲል ወስኗል፡፡ ተጠሪ በውሣኔው ቅር በመሰኘት ለፋፈን ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ የጠየቁት ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙ አከራክሮና ማስረጃ ሰምቶ የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔን በማፅናት ጥር 26 ቀን 2006 ዓ.ም በዋለው ችሎት ወስኗል፡፡ የአሁኑ ተጠሪ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት...

 • 101040 labor law dispute payment instead of annual leave

  የዓመት ዕረፍት ክፍያ አስፈላጊው የገቢ ግብር ተቀንሶ ለሠራተኛው ሊከፈለውየሚገባ ስለመሆኑ:-አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 27(ሐ)፣36፣37   የገቢ ግብር አዋጅ 286/94 እና ደንብ ቁጥር 78/94 አንቀፅ 3 የሰ/መ/ቁ. 101040   መስከረም 27 ቀን 2007 ዓ.ም.   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ሡልጣን አባተማም መኮንን ገ/ሕይወት ሙስጠፋ አህመድ ተፈሪ ገብሩ አመልካች፡- አቶ አየለ መንግሥቱ   ተጠሪ፡- የኢትዮጲያ እህል ንግድ ድርጅት   መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሠጥቷል፡፡    ፍ ር ድ   ይህ ጉዳይ የተጀመረው በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ነገሌ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁን አመልካች ከሣሽ ሲሆን    ተጠሪ  ተከሣሽ  ነበሩ አመልካች                     ባቀረበው ክስ  ተጠሪ  ያለምንም ምክንያት ያለማስጠንቀቂያ ከሥራ ስላሰናበተኝ የአገልግሎት ካሣና ጉዳት ፣የስድስት ወር ደሞዝ፣ የአመት ዕረፍት ክፍያ እና የሥራ ልምድ ጨምሮ 51,778 ብር እንዲከፈለኝ በማለት ጠይቋል፡፡ ተጠሪም በሰጠው መልስ አመልካች የመጋዘን ኃላፊ ሆነው ሲሰሩ 41.01 ኩንታል በቆሎ በጆንያ መሐከል ተደብቆ በፅዳት ሠራተኛ በኩል ተደረሶበት ይህንንም ያደረጉት ለራሳቸው ጥቅም ለማዋል በማሰብ ነው፣በድርጊቱም ተጠይቀው በቀን ሰራተኛ ሲጫን ተዛብቶ ይሆናል በማለት ተናግሯል፡፡ ይሁንና ይህ ተግባራቸው ያለቅድሚያ ማስጠንቀቂያ የሚያሰናብት ነው በማለት ተከራክሯል፡- ጉዳዩ የቀረበለት ፍ/ቤትም ተገኘ የተባለው በቆሎ ማን እንደደበቀው በግልፅ ባልተረጋገጠበት ያለማስጠንቀቂያ መሰናበቱ ህገ ወጥ ነው በመሆኑም በአዋጅ ቁ. 377/96 አንቀፅ 36፣37 ሣያሟላ እርምጃ መወሰዱ አግባብ ስላልሆነ በአዋጅ አንቀጽ 43(1) መሰረት ካሳና ደሞዝ ጋር ተያይዘው የሚመጡትን ክፍያዎች ጨምሮ በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 40(1-3) ባጠቃላይ 49,998.50 ይከፈለው ሲል ወሰነ ጉዳዩ በይግባኝ የቀረበለትም የከፍተኛው ፍ/ቤት በፍ/ህ/ስ/ስ/ቁ.337 ሰርዞታል፡፡ የክልሉም የሰበር ሰሚ ችሎት ጉዳዩን በማየት ጠፋ የተባለው በቆሎ በመጋዘን ውስጥ...

 • 101396 labor law dispute Independent contractor scope of labor proclamation

  አንድ ባለሙያ በአሠሪው ቁጥጥር ሳይሆን በራሱ የሙያ ኃላፊነት የሙያ አገልግሎት ለመስጠት ከአንድ አሠሪ ጋር ውል ሲኖረው ጉዳዩ የሚገዛው በአሠሪና ሠራተኛ ህግ ስላለመሆኑ፣ -ከአንድ ባለሙያ ጋር የሙያ ግልጋሎት ውል ያለው አሠሪ ውሉን በማናቸውም ጊዜ ማፍረስ ሥለመቻሉ፣ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 3 ንዑስ አንቀስ /1//2/ የፍ/ህ/ቁ. 2140፣2646/1/፣ 2638/1/   የሰ/መ/ቁ. 101396   ታህሳስ 21 ቀን 2007 ዓ.ም   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኸሊት ይመሰል አመልካች፡- አዲስ አጠቃላይ ሆስፒታል ጠበቃ አብደላ ዓሊ ቀረቡ ተጠሪ፡- ዶ/ር ምስራቅ ጥላሁን ጠበቃ አቶ ስመኘው አራጌ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል    ፍ ር ድ   ጉዳዩ የቀረበው አመልካች የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 42275 ሐምሌ 9 ቀን 2005 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔና የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 135997 ግንቦት 18 ቀን 2006ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው፡፡ ጉዳዩ የሥራ ውል ከሕግ ውጭ በአሠሪው ተቋርጣል በማለት ያቀረቡትን ጥያቄየሚመለከት ነው፡፡ 1. የክርክሩ መነሻ ተጠሪ ያቀረበው የክስ ማመልከቻ ነው፡፡ተጠሪ በአመልካች ድርጅት ውስጥ በወር ብር 8000,/ስምንት ሺ ብር/ እየተከፈለው በራዲያሎጅስት ሙያ ከጥር 1 ቀን 2000ዓ.ም ጀምሮ ሲያገለግሉ የቆዩ መሆኑን ገልፀው፤አሰሪው አመልካች ከሕግ አግባብ ውጭ ያቋረጠ ስለሆነ በአዋጅ ቁጥር 377/96 ድንጋጌዎች መሠረት የተለያዩ ክፍያዎች እንዲከፍል ውሣኔ ይሰጥልኝ በማለት አመልክተዋል፡፡ አመልካች ተከሣሽ ሆኖ ቀርቦ ከከሳሽ/ተጠሪ/ጋር የሥራ ቅጥር ውል ግንኙነት የለንም፡፡ከሳሽ ጋር ያለን ግንኙነት፣ከሳሽ በትርፍ ሠዓታቸው...

 • 101890 labor law dispute termnination of contract of apprentice

  አንድ አሠሪ ለሙከራ የቀጠረውን ሠራተኛ በቀጠረው በ46ኛው ቀን ለስራው ብቁ አይደለም ብሎ የስንብት ደብዳቤ ቢጽፍለት ድርጊቱ ህገ ወጥ ነው ሊባል የማይችል ስለመሆኑ፣   አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 11(2)፣(3) የሰ/መ/ቁ. 101890 ጥቅምት 24 ቀን 2007 ዓ.ም.   አመልካች፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ- ጠበቃ አውላቸው  ደሣለኝ ቀረቡ፡፡ ተጠሪ፡- ወ/ት ፍጹም ኃይሉ - የቀረበ የለም፡፡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥተናል፡፡  ፍ ር ድ   በዚህ ጉዳይ የቀረበው ክርክር የሥራ ውሉ ማቋረጡን የሚመለከት ነው፡፡ ለዚህ ሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ተጠሪ ያቀረቡት ክስ ነው፡፡ የተጠሪ የዳኝነት ጥያቄ አመልካች ከግንቦት 3ዐ ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ በዕቃ ግምጃ ቤት ተቆጣጣሪነት በቋሚ ደመወዝ ብር 2,639 የቀጠራቸው መሆኑና ያለማስጠንቀቂያ በ12/11/2005 የተፃፈ የቅጥር ውል ማቋረጫ ደብዳቤ በ15/11/2005 እንዲሰጣቸው በሕገወጥ መንገድ ከሥራ ሰለአሰናበታቸው የተለያዩ ክፍያዎች ተከፍሏቸው ወደ ሥራ እንዲመለሱ እንዲወሰን የሚል ነበር፡፡ የአሁኗ ተጠሪ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ በትብብር በሚሰራ ድርጅት ተቀጥረው ሲሰሩ ስለነበር የተቀጠሩት በቋሚነት ነው በማለት ያቀረቡት ክርክር ከቀረበው ማስረጃ አንፃር ተገቢነት የለውም በማለት የታለፈ ሲሆን በግራ ቀኙ የነበረው የሥራ ውል ግንኙነት በ29/09/2005 ዓ.ም በተፃፈው ደብዳቤ ከግንቦት 7 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ ለ45 ቀናት የሙከራ ቅጥር ተቀጥረው ሲሰሩ እንደነበር መሠረት በማድረግ ታልፏል፡፡ አመልካች በሥር ፍርድ ቤት በተደረገው ክርክር ተጠሪ ሊመደቡበት ላቀደው የዕቃ ግምጃ ቤት የስራ መደብ ተስማሚ መሆናቸውን ለመመዘን ለ45 ቀናት የሙከራ ግዜ ተቀጥረው ለታቀደው ሥራ ተስማሚ ያለመሆናቸውን በማረጋገጥ ሕጉ በሚፈቅደው አግባብ የሥራ ውል ማቋረጡን ገልጿል፡፡ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የግራ ቀኙ ክርክር እና ማስረጃ በማገናዘብ...

 • 101913 labor law dispute priority of payment to employees

  ከአሠሪና ሠራተኛ ክርክር ጋር በተነሳ ማንኛውም የሠራተኛ ክፍያ ጥያቄ ከማናቸውም የክፍያ ወይም የዕዳ ጥያቄ ቅድሚያ የሚኖረው ለሠራተኛ እንጂ ለስራ መሪዎች ስላለመሆኑ፣   አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 2(2)(ሐ) (3)፣167 የሰ/መ/ቁ.101913 የካቲት 17 ቀን 2007 ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- አቶ መላከ ሙሉጌታ - ጠበቃ ሙሉጌታ ወንድምአገኘሁ ቀረቡ፡፡ ተጠሪ፡- አቶ አበበ አቡራ - አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡    ፍ ር ድ   ጉዳዩ የቀረበው አመልካች የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 11115 ታህሳስ 21 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝና ታህሳስ 28 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ እንደዚሁም የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 139436 ሰኔ 6 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠውየአፈፃፀም ውሣኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው፡፡ ጉዳዩ በአፈፃፀም ሂደት የቀዳሚነት መብት ጥያቄን የሚመለከት ነው፡፡   1. የፍርድ ባለዕዳ የሆነው ዲማክዶ መስማት የተሳናቸው የተባለ ድርጅት በመክሰስ አመልካችና ተጠሪ የፍርድ ባለመብት ሆነዋል፡፡ ተጠሪ የድርጅቱ የሥራ መሪ ስለነበረ በፍትሐብሔር ሕጉ መሠረት የፍትሐብሔር ክስ አቅርቦ የፍርድ ባለመብት ሆኗል፡፡ የፍርድ ባለዕዳውንም ንብረት አስቀድሞ በማስከበር በአፈፃፀም እንዲሸጥ አድርጓል፡፡ አመልካች በፍርድ ባለዕዳው ላይ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 መሠረት ክስ አቅርቦ የፍርድ ባለመብት ሆኗል፡፡ አመልካች በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 167 መሠረትየቀዳሚነት መብት ያለኝ ስለሆነ በቅድሚያ ለእኔ ሊከፈለኝ ይገባል የሚል ጥያቄ አንስቷል፡፡ የሥር ፍርድ ቤት አመልካችም ሆነ ተጠሪ የፍርድ ባለዕዳው ሠራተኞች...

 • 103209 labor law dispute body injury by employee-teacher on student termination of contract of employment

  አንድ ተማሪ በአካሉ ላይ ጉዳት እንዳይደርስበት የመጠበቅ ህገመንግስታዊ መብት ያለው ስለመሆኑ፡-   አንድ አስተማሪ የሚያስተምራቸውን ተማሪዎች በአግባቡ የመቆጣጠርና የመከታተል ህጋዊ ግዴታ ያለበት ስለመሆኑና ይህንን ግዴታውን ተላልፎ ተማሪን ቢደበድብ ያለማስጠንቀቂያ የስራ ውሉን ሊያቋርጥ የሚችል በቂ ምክንያት ስለመሆኑ፡   የኢ.ፌ.ዲ.ሬ ህገ መንግስት በአንቀፅ 16 የፍ/ሕ/ቁ 2124 እና 2125 አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 27(1)(ቀ) ፣አንቀፅ 14(2)(ሀ) የሰ/መ/ቁ 103209   የካቲት 16 ቀን 2007 ዓ.ም   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል     አመልካች፡- አትላስ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት - ጠበቃ መልካም ዓለማየሁ ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሪት መስታወት ስመኝ - ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ር ድ   ጉዳዩ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 መሰረት የቀረበውን የግል የሥራ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመሰረቱት ክስ ነው፡፡ ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረቡት ክስም፡- ከአመልካች ጋር በሕግ አግባብ ያደረጉት የስራ ቅጥር ውል ከሕግ ውጪ የተቋረጠባቸው መሆኑን ገልፀው የተለያዩ ክፍያዎች እንዲከፍሏቸው ይወሰን ዘንድ ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጠው መከላከያ መልስም፡- ተጠሪ ከስራ የተነሰናበቱት በአመልካች ንብረት ያላግባብ በመገልገላቸው ከስራ ባልደረባቸው ጋር በክፍል ውስጥ ግጭት በመፍጠራቸው ማስንጠቀቂያ እየተሰጣቸው ከስራ ገበታቸው ያለበቂ ምክንያት በመቅረታቸው እና ተጠሪ በሚያስተምሯቸው የክፍል ተማሪዎች ላይ የመግረፍና የማስደንገጥ ተግባር እየፈፀሙ በተማሪዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የስነ ልቦና ችግር በማድረሳቸው ምክንያት ነው በማለት ስንብቱ ሕጋዊ ነው ሲል ተከራክሯል፡፡ የስር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና የአመልካችን ምስክሮችን ከሰማ በኋላ ጉዳዩን...

 • 95638 labor law dispute jurisdiction of court

  በስራ ክርክር የተከራካሪ ወገኖች ማንነት የፍርድ ቤቶችን ስልጣን (የክልል ወይም የፌዴራል)ብሎ ለመወሰን እንደወሳኝ  መለኪያ ሊወሰድ የማይገባ ስለመሆኑ፤   የአሰሪው እርምጃ ህገ ወጥነት የተረጋገጠ እንደሆነ  የክፍያ መጠኑ ሊሰላ የሚገባው አዋጁ ባስቀመጠው ስሌትና በማስረጃ በተረጋገጠ የደመወዝ መጠን መሆን ያለበት ስለመሆኑ፣   አዋጅቁጥር377/1996አንቀፅ 35(1(ለ))፣39(1(ለ))፣40(1)(2)፣43(4(ሀ)፣68፣71 የሰ/መ/ቁጥር 95638   መስከረም 29 ቀን 2007 ዓ/ም   ዳኞች፡-አልማው ወሌ ሡልጣን አባተማም መኮንን ገ/ሕይወት ሙስጠፋ አህመድ ተፈሪ ገብሩ አመልካች፡-ኢስት ሲሜንት አክሲዩን ማህበር - ጠበቃ ዓለሙ ደነቀው - ቀረቡ ተጠሪ፡-አቶ ዘላለም ታደሰ  - ጠበቃ ገናናው ተሾመ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ  ር ድ   ጉዳዩ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 መሰረት የቀረበውን የግል የስራ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረበት ፍርድ ቤት የሂደቡ አቦቴ ወረዳ ፍርድ ቤት ነው፡፡በዚህ ፍርድ ቤት ከሳሽ የአሁኑ ተጠሪ ሁኖ የክሱ ይዘትም፡-በተጠሪ ድርጅት በአስተዳደር ኃላፊነት እና ጉዳይ አስፈፃሚነት አምስት አመት ከዘጠኝ ወር ብር 6,410.90 በወር እየተከፈላቸው ማገልገላቸውንና የስራ ውሉ ከሕግ ውጪ መቋረጡን ገልጸው ልዩ ልዩ ክፍያዎች እንዲከፈላቸው ይወሰን ዘንድ ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡የአሁኑ አመልካች ተከሳሽ የነበረ ቢሆንም መጥሪያ ደርሶታል፣ግን አልቀረበም ተብሎ በሌለበት ጉዳዩእንዲታይ ተደርጓል፡፡የሥር ፍርድ ቤትም ጉዳዩን መርምሮ የአሁኑ አመልካች ለክሱ ኃላፊ ነው ተብሎ ለከሳሽ ብር 277,294.00 ( ሁለት መቶ ሰባ ሰባት ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና አራት) ብር እንዲከፈል ወሰኗል፡፡   የአሁኑ አመልካች በሌለሁበት ታይቶ የተወሰነው ውሳኔ ተነስቶ ባለሁበት ይታይልኝ በማለት ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን ከዚሁ ጋር በተጨማሪ ከሳሹ የአሰሪ ወገን...

 • 100712 criminal procedure/ RTD procedure/ right to defense

  የRTD ችሎት መከላከያ የማቅረብ መብትን የማያስነፍግ ስለመሆኑ     ዳኞች፡-አልማው ወሌ ዓሊ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል   አመልካች፡- አቶ ሽብሩ ጌቱ ሴንጫ - ጠበቃ ወይሸት ከበደ ቀረቡ፡፡ ተጠሪ፡- የፌዴራል አቃቤ ሕግ - የቀረበ የለም፡፡ የሰ/መ/ቁ 100712 መጋቢት 28 ቀን 2007 ዓ/ም መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ር ድ   ጉዳዩ የወንጀል ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ በመሰረተው ክስ መነሻ ነው፡፡ የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡- በ1996 ዓ/ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዲ.ሪፐብሊክ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 669(2)ን በመተላለፍ የማይገባውን ብልፅግና ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ በ18/02/06 ዓ/ም በግምት ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ሲሆን በኮ/ቀ/ክ/ከ/ወረዳ 02 ልዩ ቦታው ካራቆሬ ደጋማን የፕላስቲክ ውጤቶች ማምረቻ ድርጅት ውስጥ በስራ አስኪያጅነት ተቀጥሮ እየሰራ ባለበት የግል ተበዳይ አማረ አብርሃም የድርጅቱ ባለቤት የሆኑትን ንብረት አንድ መቶ ሃምሳ ከረጢት የጫማ ጥሬ እቃ ፕላስቲክ የአንድ ከረጢት ግምት ብር 1100.00 (አንድ ሺህ አንድ መቶ ብር) የጠቅላላው ግምት ብር 165,000.00 (አንድ መቶ ስልሳ አምስት ብር) የሚያወጣውን ወስዶ ለስር 2ኛ ተከሳሽ አቶ ደረጀ ፍቃዱ የሸጠና የተያዘ በመሆኑ ከባድ የስርቆት ወንጀል ፈጽሟል የሚል ነው፡፡ አመልካችም ፍርድ ቤት ቀርቦ የአቃቤ ሕግ የክስ ቻርጅ ተነቦለት እንዲረዳው ከተደረገ በሁዋላ እምነት ክህደት ቃሉን ሲጠየቅ የወንጀል ድርጊቱን ያለመፈፀሙን በመግለጹ አቃቤ ሕግ አሉኝ የሚላቸውን ማስረጃዎች  አቅርቦ አሰምቷል፡፡ ከዚህም በኋላ ፍርድ ቤቱ አመልካች ድርጊቱን ስለመፈፀሙ በአቃቤ ማስረጃዎች የተነገረበት መሆኑን ተገንዝቦ የአመልካችን የመከላከያ ማስረጃ ማሰማት መብቱን በአመልካች ፍላጎት ማለፉን ጠቅሶ አመልካችን በአቃቤ ሕግ በኩል ተጠቅሶ በቀረበበት አንቀጽ ስር ጥፋተኛ አድርጎ ቅጣቱንም...

 • 103448 criminal law/ sentencing/ sentencing guideline

  በወንጀል የቅጣት አወሳሰን ጊዜ የቅጣት መነሻ ለማግኘት ቀላልየእስራት ቅጣትን ወደ ፅኑ እስራት መለወጥ የሚያሥፈልገውወንጀለኛው ጥፋተኛ የተባለው በሁለት ወይም ከዚያ በላይ በሆኑወንጀሎች ሲሆንና አንዱ ወንጀል በቀላል እስራት ሌላው ደግሞ በፅኑእስራት የሚያስቀጣ በሆነ ጊዜ ብቻ ስለመሆኑ፡-የተሻሻለው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁ.2/2006የወ/ሕ/አንቀፅ 184(1(ለ)) የሰ/መ/ቁ/103448 የካቲት 16 ቀን 2007 ዓ.ም. ዳኞች:-አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- አቶ አገኘሁ አስፋው የቀረበ የለም   ተጠሪ፡- የፌዴራል አቃቤ ሕግ - ወይን ገ/እግኢአብሄር  ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡  ፍ ር ድ   ጉዳዩ በሰው ሕይወትና አካል ላይ በቸልለተኝት ጉዳት ማድረስን የሚመለከት የወንጀል ክርክር ሲሆን ክርክሩ የጀመረው የአሁኑ አመልካች ባሁኑ ተጠሪ ላይ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሰረተው ክስ መነሻ ነው፡፡ የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ የመሰረተው በአምስት ምድብ የተከፈለ ክስ ነው፡፡   1ኛክስ፡-በ1996 ዓ.ም የወንጀል ሕግ አንቀጽ 543(3) እና የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ ቁጥር 208/2003 አንቀጽ 13(ሀ) የተመለከተዉን በመተላለፍ አመልካቹ አሽከርካሪ በመሆኑ የሌላን ሰዉ የሕይወት ደህንነት የመጠበቅ የሙያ ግዴታ እያለባቸው በ03/06/2005 ዓ.ም ከቀኑ በግምት 9፡40 ሲሆን በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከ/ወረዳ 01 ልዩ ቦታዉ ቻይና ካምፕ መታጠፊያ አካባቢ የሠሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-15006 ኦ/ሮ የሆነ ተሸከርካሪ ይዞ ከአየር ጤና ወደ ሳሪስ አቦ አቅጣጫ እያሽከረከረ ሲጓዝ ከተሸከርካሪ መንገድ ዉጭ በመዉጣት በእግረኛ መንገድ ላይ ስትጓዝ የነበረችዉን ህጻን ሕይወት ዳዲ የተባለችዉን በሚያሽከረክረዉ መኪና የፊት አካል ገጭቶ በመግደሉ በቸልተኝነት ሰዉ መግደል ወንጀል ፈጽሟል የሚል ነዉ፡፡...

 • 103452 criminal procedure/ preliminary objection/ amendment of charge

  አንድ በወንጀል ተጠርጥሮ የተከሰሰ ሰው ቅጣት በሚያከብድ የህግድንጋጌ ስለተከሰስኩ ክሱ ይሻሻልልኝ በማለት ተቃውሞ ካቀረበማስረጃ ከተሰማ በኋላ ፍ/ቤቱ የሚወስነው እንጂ ከጅምሩ ማስረጃሳይሰማ አቋም የሚወሰድበት እና ክሱ ይሻሻል ተብሎ የሚታዘዝስላለመሆኑ፣ የሰ/መ/ቁ 103452 ቀን ጥር 19/2007 ዓ.ም ዳኞች፡-  አቶ አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኸሊት ይመሰል አመልካች፡- አቶ ጥዑም ተኬ ገብራይ ጠበቃ ሀብታሙ ንጉሴ ቀረቡ   ተጠሪ፡- የፌዴራል ሥነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን የዐቃቤ ሕግ የድሬደዋ ምድብ ዋልተንጉስ ፍቅሬ - ቀረቡ   መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩን ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ርድ   ጉዳዩ የወንጀል ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረውም በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድሬደዋ ምድብ ችሎት ነው ፡፡ ተጠሪ በአሁኑ አመልካች ያቀረበው ክስ የኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 408(2) የተመለከተውን በመተላለፍ ከግል ተበዳይ አቶ ንጉሴ ለማ ብር ሁለት ሺህ (2,000.00) ጉቦ ሲቀበል እጅ ከፍንጅ ተይዟል የሚል ይዘት ያለው ነው፡፡   አመልካች በአሁኑ ተጠሪ የተመሰረተበት የወንጀል ክስ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርቦ የተከራከረ ሲሆን ተጠሪም የበኩሉን መልስ ሰጥቷል፡፡ አመልካች በሥር ፍርድ ቤት ያቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ መሠረታዊ ይዘት በጉቦ መልክ ተቀብለው የተባለው  የገንዘብ መጠን ትንሽ መሆኑ፤የሥልጣን ደረጃውም በአዋጅ ቁጥር 433/97 አንቀፅ 2(5) እንደማይካተት በመግለፅ ክሱ በወ/ሕ/ቁ 408(1) ሥር እንዲቀርብ ዐቃቤ ሕግ ክሱን እንዲያሻሽል እንዲታዘዝለት አመልክቷል ፡፡ ተጠሪ በበኩሉ በሰጠው መልስ አመልካች ስራ አስኪያጅ መሆኑን ፤በአዋጅ ቁጥር 668/2002 መሠረት የመንግስት የልማት ድርጀት ስራ አስኪያጆች የመንግስት ባለ  ስልጣን በሚል ሥር ያካተታቸው በመሆኑ መቃወሚያው ውድቅ እንዲሆን...

 • 104715 criminal law/ concurrence of offenses/ notional concurrence/ senetincing

  አንድ ወንጀል ከመስራት ሃሳብ የሚመነጩ የተለያዩ ድርጊቶች አንድወንጀል ከመስራት ሃሳብ የሚመነጩ ናቸው በማለት ተጠቃለው እንደአንድ ወንጀል እንዲተገበሩ ማድረግ የህጉን አግባብ የተከተለስላለመሆኑ፡-በፅኑ እስራትና በቀላል እስራት የሚያስቀጡ ወንጀሎች ተደራርበውሲገኙ የቀላል እስራት ወደ ፅኑ እስራት እንደሚለወጥ፤ስሌቱምየሁለት ዓመት ቀላል እስራት እንደ አንድ ዓመት ፅኑ እስራትየሚቆጠር ስለመሆኑ፡-የወ/ሕ/ቁ/ 184 (1)(ለ) የሰ/መ/ቁ. 104715   መጋቢት 02 ቀን 2007 ዓ.ም   ዳኞች፡- መድሕን ኪሮስ   አልማው ወሌ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡-   እንደሻው ይልማ ዳዲ - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ አቶ ያሬድ አየለ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡    ፍ ርድ   ጉዳዩ የጀመረው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ነው፡፡ ጉዳዩ የወንጀል ክርክር የሚመለከት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪ በአመልካች ላይ ሁለት ክሶች አቅርበዋል፡፡ አንደኛው ክስ አመልካች የወ/ሕ/ቁ 692(1) የተመለከተውን በመተላለፍ ጉዳይ ፈፃሚ ነኝ የፍቺ የምስክር ወረቀት ላሰራልህ በማለት የግል ተበዳይ ወንድወሰን አራጋው እህት ለሆነችው ፍቅርተ አራጋው እና ባለቤቷ በማታለል በሁለት ጊዜ ክፍያ አርባ ሺህ ብር ከወሰደ በኃላ ለልደታ ክፍለ ከተማ ውልና ጋብቻ መዝገብ የተሰጠ በማስመሰል ሀሰተኛ የፍቺ የምስክር ወረቀት የሰጠመሆኑን፤ 2ኛ ክስ ደግሞ የወ/ሕ/ቁ 385(1)(ሀ) የተመለከተውን በመተላለፍ በሀሰት የተዘጋጀ የፍቺ ምስክር ወረቀት በማዘጋጀት ለግል ተበዳይ የሰጠ በመሆኑ፤በምስክር ወረቀቶች ላይ በሚደረግ ወንጀል መከሰሱን የሚያሳይ ነው፡፡ የሥር ፍርድ ቤትም የአመልካች የእምነት ክህደት ቃል በሕጉ አግባብ ከመዘገበ በኃላ አመልካች ክዶ በመከራከሩ የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች ቃል አዳምጧል፡፡ አመልካች...

 • 92141 criminal law/ evidence law/ expert opinion/ traffic police

  አንድ የትራፊክ ባለሙያ የሚሰጠው ሙያዊ አስተያየት የማስረጃ ዋጋየማይሰጠው አስተያየቱ ተገቢውን የሙያ ደንብ ተከትሎ ያልተሰጠናያልቀረበ፣በጊዜውና በቦታው ከነበሩት የአይን ምስክሮች ቃል ጋርተነፃፅሮ ሲታይ በመሰረታዊ ነጥቦች ላይ ልዩነት ያለበት መሆኑሲረጋገጥ እንጂ በጭፍጫፊ ነጥቦች ላይ ልዩነት ተከስቷል ተብሎሊሆን እንደማይገባ፣የልዩ አዋቂዎች ምስክሮች ቃላቸውን ገለልተኛ ሆነው መስጠት እንደአለባቸውና ቃላቸው ያለበቂ ምክንያት ልዩ አዋቂ ያልሆኑ ሰዎችበሚሰጡት የምስክሮች ቃል ውድቅ መሆን የሌለበት መሆኑንተቀባይነት ያላቸው የማስረጃ ህግ ደንቦች የሚያስገነዝቡ ስለመሆኑየወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 141፣142፣194የወንጀል ህግ ቁጥር 24፣59፣239(2)፣57፣543(2) የሰ/መ/ቁ. 92141 መስከረም 3ዐ ቀን 2ዐዐ7 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ሱልጣን አባተማም መኮንን ገ/ሕይወት ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመስል አመልካች፡- የደ/ብ/ብ/ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትፍትሕ ቢሮ አቃቤ ሕግ ተጠሪ፡- አቶ አለማየሁ አስፋው መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡    ፍ ር ድ   ጉዳዩ ወንጀል ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች በአሁኑ ተጠሪ ላይ በጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሰረተው ክስ መነሻ ነው፡፡ የክሱ ይዘትም፡- ተጠሪ በ1996 ዓ.ም በወጣው የወንጀል ሕግ አንቀፅ 543/2/ ስር የተመለከተውን በመተላለፍ በሾፌርነት ሙያቸው የሌላውን ሰው ሕይወትና ደህንነት የመጠበቅ ግዴታ እያለባቸው መጋቢት ዐ2 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም ከቀኑ 5፣3ዐ ሲሆን ንብረትነቱ የድርባ ደፈርሻ የመንገድ ስራ ተቋራጭ የሆነውን፤ የሰሌዳ ቁጥሩ   3- 25709 ኦሮ የሆነውን ቶዮታ ሃይሉክስ መኪና ከአዲስ አበባ ከተማ ወደ አርባ ምንጭ መሰመር በከፍተኛ ፍጥነት እና የራሳቸውን መስመር በመልቀቅ በማሽከርከር ላይ እያሉ በምዕራብ አባያ ወረዳ ብርብር ከተማ የሰሌዳ ቁጥሩ 2-ደ/ሕ...

 • 93577 criminal procedure/ criminal trial in absentia

  በወንጀል የተከሰሰ ሰው ጉዳዩን በሌለበት ለማየት ፍ/ቤቱ በመጀመሪያለተከሣሹ ህጉ ያስቀመጠውን ጥብቅ መስፈርት በተከተለ መልኩበአግባቡ ጥሪ ሊያደርግለት የሚገባ ስለመሆኑ፣የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ቁጥር 161(1)(2) እና 162 የሰ/መ/ቁ. 93577   ህዳር 22 ቀን 2007 ዓ.ም.   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመስል አመልካች፡- አቶ ዘውዴ ተስፋይ ስመኝ ጉዳይ ተከታታይ ቀረቡ ተጠሪ፡- የትግራይ ክልል ፍትህ ቢሮ ዐቃቤ ህግ የቀረበ የለም መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ር ድ   ጉዳዩ የተጀመረው በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ደግሞ ተከሳሽ ነበር፡፡ተጠሪ በአመልካች እና በስር ፍርድ ቤት አንደኛ ተከሳሽ በነበረው ካሳየ ጌጡ ያቀረበው ክስ ከባድ የሰው ግድያ ወንጀል ነው፡፡ ለዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት አቤቱታ መነሻ የሆነው የአሁኑ ተጠሪ ጉዳዩ የተሰማው በሌለበት በመሆኑ ከመጥሪያ አደራረስ ጋር የተያያዘ ክርክር በማቅረቡ ነው፡፡ ዓቃቤ ህግ በስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጠሪ እና 1ኛ ተከሳሽ በነበረው ካሳየ ጌጡ ያቀረበው ክስ የወ/ሕ/ቁ.32(1)(ሀ) እና 539(1)(ሀ) የተመለከተውን በመተላለፍ ሰው ለመግደል አስበው በ19/10/1997 ዓ.ም. ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ትግራይ ክልል አላማጣ ወረዳ ቀበሌ ማረዋ ሟች ሰመሀኝ አረቂ በክላሽ ኮፕ መሳሪያ አንድ ጥይት በመተኮስ ገድለዋል የሚል ነው፡፡ አመልካች ጉዳዩ ሊሰማ በተያዘው ቀጠሮ ባለመቅረቡ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.161(1) በሚያዘው መሰረት በመኖሪያ አካባቢው በተለጠፈ መጥሪያ ጥሪ ቢደረግለትም ባለመቅረቡ በሌለበት ክርክሩን ቀጥሎ የዓቃቤ ህግ ምስክሮች ከተሰሙ በኃላ የሥር ፍርድ ቤት ዐቃቤ ህግ እንደ ክሱ አቀራረብ አስረድቷል በማለት አመልካች ጥፋተኛ ነው በማለት ወስኗል፡፡ ቅጣት በተመለከተም...

 • 96168 criminal law/ sentencing/ extenuating circumstances/ evidence law/ sentencing guideline

  በወንጀል ጉዳይ ጥፋተኛ የተባለ ሠው በቅጣት ማቅለያነትእንዲያዝለት ያቀረበውን ምክንያት በማስረጃ ማስደገፍ እንዲችል በቂጊዜ ባልተሠጠበት ሁኔታ በማስረጃ የተደገፈ አይደለም በሚልየማቅለያ ምክንያቱን ውድቅ በማድረግ የሚሠጥ የቅጣት ውሣኔበወንጀል ህጉ እና በቅጣት አወሳሠን መመሪያው ሥለ ቅጣትአወሣሠን የተቀመጡትን ድንጋጌዎች መሠረት ያደረገ ነው ለማለትየሚቻል ስላለመሆኑ፣የወ/መ/ሥ/ሥርዓት 149/3//4/ የሰ/መ/ቁ.96168 ህዳር 9 ቀን 2007 ዓ.ም. ዳኞች፡-አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- አቶ አርአያ ኪዳነ ቤተሰብ ነኝ በማለት መምህር ፍሰሐ ገ/መስቀል ቀረቡ ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዐ/ሕግ - የቀረበ የለም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ር ድ   በዚህ መዝገብ አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት ተጠሪ ያቀረበባቸውን የኮንትሮባንድ የወንጀል ክስ የተመለከተው የምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠባቸው እና በኦሮሚያ ብ/ክ/መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የጸናው የጥፋተኝነት እና የተሻሻለው የቅጣት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት ነው፡፡   ተጠሪ በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ተከሳሽ በነበሩት የአሁኑ አመልካች እና የዕቃዎቹ ባለቤት ናቸው ተብለው በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 141 መሰረት በብይን በተሰናበቱት 2ኛተከሳሽ ላይበ07/06/2005 ዓ.ም.አዘጋጅቶ ያቀረበው ክስ ይዘት ባጭሩ፡-ተከሳሾቹ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(3) እና በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2001 በአንቀጽ 91(2) ስር የተደነገገውን በመተላለፍ የጉምሩክ ስነ ስርዓት ያልተፈጸመባቸውን የቀረጥ እና የታክስ መጠናቸው ብር 136,657 የሆነ እና ንብረትነታቸው የ2ኛ ተከሳሽ የሆኑ የተለያዩ...

 • 96310 criminal procedure/ confession by accused/ effect of confession on co-accuseds

  አንድ ተጠርጣሪ ወይም ተከሳሽ በምርመራ ሒደትም ሆነ ክሱንለሚሠማው ፍ/ቤት የሚሠጠው የእምነት ቃል ውጤት በራሱ በቃልሠጪው ላይ ተወስኖ የሚቀር ከመሆኑ ውጪ ወንጀሉንአልፈፀምኩም ብሎ በሚከራከር ሌላ ተከሣሽ ላይ ህጋዊ ውጤትሊያስከትል የማይችል ሥለመሆኑ፣የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ሥነ-ሥርዓት ቁጥር 27፣35 እና 134   ዳኞች፡-አልማው ወሌ ዓሊ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል የሰ/መ/ቁጥር 96310 ህዳር 26 ቀን 2007 ዓ.ም.   አመልካች፡-አቶ ጉዲና ለማ ገዛኸኝ - አባት ነኝ በማለት አቶ ለማ ገዛኸኝ ከጠበቃ ልዑል አያለው ጋር ቀረቡ ተጠሪ፡- የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት የስ/ፀ/ሙስና ኮሚሽን ዐ/ሕግ - የቀረበ የለም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡  ፍ ር ድ   በዚህ መዝገብ አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት ተጠሪ ያቀረበባቸውን በስራ ተግባር ላይ የሚፈጸም የመውሰድና የመሰወር ከባድ የሙስና የወንጀል ክስ የተመለከተው በቤንች ማጂ ዞን የቤንች አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠባቸው እና በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ እና ሰበር ችሎቶች በትዕዛዝ የጸናው የጥፋተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት ነው፡፡   ተጠሪ በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ተከሳሽ በነበሩት የአሁኑ አመልካች እና በሌሎች አምስት ሰዎች ላይ ያቀረበው አንደኛ ክስ ይዘት ባጭሩ፡-ተከሳሾቹ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1) (ሀ) (ለ)፣33 እና413(2) ስር የተደነገገውን በመተላለፍ በሚዛን አማን ሆስፒታል  ውስጥ 1ኛ ተከሳሽ የዋናው መድኃኒት ቤት ጠባቂ፤2ኛ ተከሳሽ የመድኃኒት ማሰራጫ ክፍል ባለሙያ እንዲሁም 3ኛ ተከሳሽ የግዢና የፋይናንስ የስራ ሂደት ባለቤት ሆነው በመስራት ላይ በነበሩበት ጊዜ በወንጀሉ ስራና በሚሰጠው ውጤት በመስማማት 1ኛ ተከሳሽ ይሰራበት ወደነበረው የመድኃኒት መጋዘን በ13/03/2005 ዓ.ም. ገቢ የተደረጉትን ሁለት...

 • 96378 criminal procedure/ appeal/ application of appeal decision on co-accuseds

  ከስር ተከሳሾች መካከል ፍ/ቤት የሠጠው ውሣኔ ለአንዱየሚጠቅምበሆነ ጊዜና ይግባኝ ባዩ ጋር ተከሠውጥፋተኛ ተብለው የተቀጡሠዎች ይግባኝ ቢያቀርቡ ኖሮ በይግባኝ ሠሚው ፍቤት ውሣኔሊጠቅሙ ይችሉ የነበረ መሆኑ ከተረጋገጠ ይግባኝ ሠሚዉ ፍ/ቤትየሠጠው ውሣኔ ይግባኝ ላላቀረቡት ተከሳሾች ጭምር ተፈፃሚነትሊኖረው የሚገባ ሥለመሆኑ፣የወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 196/1/ /ሀ/ /ለ/ የሰ/መ/ቁ.96378 ህዳር 25 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡-አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- ሀቢብ ጀማል   ተጠሪ፡- የደ/ብ/ብ/ሕ/ብ/ክ/መንግስት ዐ/ሕግ -   አቤቱታ አቅራቢዎች፡- 1.ረዳት ሳጅን መሐመድ እንድሪስ      ጉዳዩን ተከታታዮች ተስፋዬ 2. አብዱ ኡመር                                   አለሙ እና ወሰላ ከድር 3. ደግፌ አለሙ                     ቀረቡ   መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ር ድ   ጉዳዩ የወንጀል ክርክርን የሚመለከት ሲሆን መዝገቡ የተከፈተው በሀቢብ ጀማል አመልካችነት ሁኖ ከተጠሪ ጋር ክርክሩ ተካሂዶ ይህ ችሎት ጥቅምት 28 ቀን 2007 ዓ/ም በዋለው ችሎት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ የአሁኑ የሠበር አቤቱታ የቀረበው ጥቅምት 28 ቀን 2007 ዓ/ም በዚህ ችሎት የተሰጠው ውሳኔ በስር ፍርድ ቤት ከሀቢብ ጀማል ጋር ተከሳሽ የነበሩትን የአሁኑ አቤቱታ አቅራቢዎችንም የሚጠቅም በመሆኑ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 196 ድንጋጌ መሰረት የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሳኔ ተግባራዊ ሊሆን ይገባል በማለት ህዳር 02 ቀን 2007 ዓ/ም ማመልከቻ ስለአቀረቡ ነው፡፡ ይህ ችሎትም ይህንኑ የአቤቱታ አቅራቢዎችን ጥያቄ ለማስተናገድ ይቻለው ዘንድ ተጠሪ አስተያየት እንዲሰጥበት ያደረገ ሲሆን ተጠሪ ህዳር 19 ቀን 2007 ዓ/ም ባቀረበው አስተያየት አቤቱታ አቅራቢዎቹ ጥቅምት 28 ቀን 2007 ዓ/ም በተሰጠው የጥፋተኝነት ውሳኔ ተጠቃሚ መሆን ያለባቸው መሆኑን የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 196 ከአስቀመጠው ድንጋጌ የሚገነዘበው መሆኑን ዘርዝሮ አቤቱታ አቅራቢዎች አቶ ሀቢብ ጀማል ጥፋተኛ በተባሉበት በወንጀል ሕጉ አንቀፅ...

 • 99883 criminal procedure/ jurisdiction of court/ federal court jurisdiction/ consolidation of charges

  በአንድ ተከሳሽ ላይ ከቀረቡት ከአንድ በላይ ከሆኑት ክሶች መካከልከፊሎች የሚወድቁት በፊዴራል ፍ/ቤት የስረ ነገር ስልጣን ስርከፊሎቹ ደግሞ በክልል ፍርድ ቤት የስረ- ነገር ስልጣን ስር በሆነጊዜናበወንጀል ህግ ሥነ-ስርዓቱ የክስ አቀራረብ መርህ መሰረትበቀጥታም ሆነ በውክልና በፌደራል ፍ/ቤት ቀርበው እንዲታዩከተደረገ በሚሰጠው ውሳኔ ላይ የይግባኝ እና የሰበር ሥርዓታቸውበመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲቀርቡ እንደተደረገው ሁሉየፌደራልፍ/ቤቶችን የይግባኝ እና የሰበር ሥርዓት ተከትለውና ተጠቃለውመታየትያለባቸው ስለመሆኑ።- ወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 109(3)፣116(2)አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀፅ 4(4)፣15(1) የሰ/መ/ቁ/ 99883   ጥር 19 ቀን 2007 ዓ.ም.   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- አቶገ/ሥላሴ ገብሩ - ጠበቃ ገ/እግዚአብሔር ተስፋዬ ቀረቡ፣ ጠበቃ ሐና ዲግራንዲ ከመቀሌ በV.C. ቀረቡ፡፡   ተጠሪ፡- የትግራይ ብ/ክ/መንግስት ፍትሕ ቢሮ - ዐ/ሕግ ገ/እግዚአብሔር ተወልደብርሃን ከመቀለ በV.C. ቀረቡ፡፡   መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ር ድ   በዚህ መዝገብ እና ቁጥራቸው 98349 እና 98350 በሆኑት በዛሬው ዕለት በዚሁ ችሎት ውሳኔ በተሰጠባቸው ሌሎች ሁለት መዝገቦች ለቀረበው የሰበር ክርክር ምክንያት የሆነው ጉዳይ የተጀመረው ተጠሪ በ19/08/2003 ዓ.ም በተጻፈ የክስ ማመልከቻ በትግራይ ክልል  በመቀሌ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ተከሳሽ በነበሩት የአሁኑ አመልካች እና 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች በነበሩት ሌሎች ሁለት ተከሳሾች ላይ ስድስት የወንጀል ክሶችን በማቅረቡ ሲሆን ይዘታቸውም በአጭሩ፡-   1. በአንደኛ ክስ ሶስቱም ተከሳሾች በገቢ ግብር አዋጅቁጥር 286/1994 በአንቀጽ 96 ስር የተደነገገውን በመተላለፍ በተለያየ የንግድ ስራ ዘርፍ ተሰማርተው ይሰሩ በነበረበት ጊዜ...