Federal Court Case Tracker

volume 18

volume 18

 • 98014 Criminal procedure constitution Trying accused person in his absence Setting aside of judgment Right of persons accused

  Criminal procedure constitution Trying accused person in his absence Setting aside of judgment Right of persons accused Criminal procedure code art. 198, 200, 201 FDRE constitution art. 20 አንድ ሰው በሌለበት በወንጀል የተፈረደበት እንደሆነ ፍርድን ባወቀ በሠላሳ ቀናት ውሥጥ ፍርዱ ወድቅ እንዲደረግለት የማቅረብ መብቱን ሬጄሰትራሉ አቤቱታውን አልቀበልም በማለት ሊከለክለው የማይችል ስለመሆኑ፡- የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ.198፣200 እና 201 የኢፈ.ድ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 20   98014

 • 100290 Private international law Jurisdiction of courts Jurisdiction of federal courts

  Private international law Jurisdiction of courts Jurisdiction of federal courts Proclamation no. 25/1988 art. 11(2)a የግለሰብ ዓለምአቀፍ ህግን / private international law/ የሚመለከቱ ጉዳች ለማየት የስረ ነገር ስልጣን ያለው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 25/1988 /እንደተሻሻለ/ አንቀፅ 11/2/ /ሀ/    100290

 • 100426 Family law Minors Guardianship and tutorship Power of tutor Council of family

  Family law Minors Guardianship and tutorship Power of tutor Councilof family Cvil code art. 301 አንድ ሞግዚት አካለመጠን ያልደረሰን ልጅ በማስተዳደር ስልጣኑ ክርክር የሚደረግበት ጥቅም ከ300 ብር ያነሰ ካልሆነ በቀር ያለ ቤተዘመድ ምክር ጉባኤ ፈቃድ ምንም ግልግል መፈጸም የማይችል ስለመሆኑ፣ የፍ/ህ/ቁ. 301 100426

 • 100426 Family law Minors Guardianship and tutorship Power of tutor Councilof family

  Family law Minors Guardianship and tutorship Power of tutor council of family Civil code art. 301 አንድ ሞግዚት አካለመጠን ያልደረሰን ልጅ በማስተዳደር ስልጣኑ ክርክር የሚደረግበት ጥቅም ከ300 ብር ያነሰ ካልሆነ በቀር ያለ ቤተዘመድ ምክር ጉባኤ ፈቃድ ምንም ግልግል መፈጸም የማይችል ስለመሆኑ፣ የፍ/ህ/ቁ. 301 100426

 • 100621 Commercial law Share company Resolution adopted by meeting of shareholders Death of shareholder Period of limitation

  Commercial law Share company Resolution adopted by meeting of shareholders Death of shareholder Period of limitation Commercial code art. 416 Civil code art. 1845 በሞተ ሰው ሥም የተመዘገበን የአክስዮን ድርሻ ላይ ሟቹ እንደተገኘ ተቆጥሮ የሚተላለፍ ውሳኔ አግባብነት የሌለው ሥለመሆኑ እና ተፈፃሚነት ያለው በንግድ ህጉ የተቀመጠው የሦስት ወር ጊዜ ሳይሆን በፍ/ሕ/ቁ 1845 የተመለከተው የአስር ዓመት ይርጋ ስለመሆኑ የንግድ ህግ ቁ.416 የፍ/ሕ/ቁ.1845   100621

 • 100671 Contract law Sale of immovable property Sale of land Object of contract unlawful Void ab initio contract

  Contract law Sale of immovable property Sale of land Object of contract unlawful Void ab initio contract FDRE Constitution art. 40(3) Civil code art. 1716(1) ባዶ መሬትን ለማስተላለፍ የሚደረግ የሽያጭ ውል /የመሬት ግብይት ውል/ ፍሬ ነገሩ ሕገወጥ ሥለመሆኑና እና የዚህን አይነት ውል ከጅምሩ እንደሌለ ወይም እንዳልተደረገ የሚቆጠር ስለመሆኑ  የኢ.ፌ.ህገመንግስት አንቀፅ 40(3) የፍ/ሕ/ቁ.1716(1)   100671

 • 100673 Civil procedure Summon Summon to government organs

  Civil procedure Summon Summon to government organs Civil procedure code art. 70(a), 78(2), 96, 102   ለአንድ የመንግስት ተቋም የተላከ መጥሪያ መጥሪያው በአግባቡ ለሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ካልደረሰ በስተቀር መጥሪያው ለተቋሙ መዝገብ ቤት ገቢ በመሆኑ ብቻ መጥሪያው እንደደረሠ ተቆጥሮ ክርክሩ ተቋሙ በሌለበት ሊታይ የማይገባ ስለመሆኑ፣ የፍ/ሥ/ህ/ቁ 70/ሀ/፣78/2/፣96፣102 100673

 • 100860 Criminal procedure Constitution Human right Right of persons accused

  Criminal procedure Constitution Human right Right of persons accused Criminal procedure code art. 142(2) FDRE constitution art. 13(1), 13(2), 20(4) International convention on Civil and political rights art. 14(3)f ፍ/ቤቶች የተከሳሽን የመከላከል መብት የማክበርና የማስከበር ህገ-መንግስታዊ ኃላፊነትና ግዴታ ያለባቸው ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ህገ መንግስት አንቀፅ 13(1)፣13(2)፣20(4) የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 142(1) ዓለም አቀፍ የማህበራዊና ፖለቲካ መብቶች ሥምምነት አንቀፅ 14(3)(ረ)   100860

 • 101056 Criminal procedure Cassation procedure

  Criminal procedure Cassation procedure Criminal procedure code art. 196(1) የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 196(1) ለሰበር ሥርዓትም ተፈፃሚነት ሊኖረው የሚገባ ስለመሆኑ   101056

 • 101229 Extra contractual liability Strict liability Dangerous activities

  Extra contractual law Strictly liability Dangerous activities Civil code art. 2069(1) (2) and 2086(2) በአንድ ተቋም /መንግስታዊም ሆነ በባለስልጣን የተፈቀደለት/ ባለቤትነት የሚያካሄደው አደገኛ ተግባራት በሌላ ሰው ላይ ጉዳት ያደረሰ በሆነ ጊዜ ድርጅቱ ስራው በህግ የሚጠበቅበትን ደረጃ ያሟላ ስለመሆኑ እና በከፊልም ሆነ በሙሉ የተጎጂ ጥፋት መኖሩን እስካላስረዳ ድረስ ለደረሰው ጉዳት ኃላፊነት ያለበት ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 2069/1/ /2/ እና 2086/2/ 96943

 • 101345 Civil procedure Validity of Judgment Revision of judgement

  Civil procedure Validity of Judgment Revision of judgement Civil procedure code Art. 378, 372, 392   በመርህ ደረጃ በህግ አግባብ የተቋቋመ ፍ/ቤት የሠጠው ውሳኔ በህግ አግባብ በተቋቋመ የበላይ ፍ/ቤት በህጉ በተዘረጋው ስርዓት እስካልተለወጠ ድረስ የማይፈጸምበት ምክንያት የሌለ ስለመሆኑ፣  የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 378፣372፣392  101345

 • 101478 Civil procedure Ex-parte judgment Period of limitation

  Civil procedure Ex-parte judgment Period of limitation Civil procedure code art. 78(1) በሌለሁበት የተሰጠ ውሳኔ /ትእዛዝ/ ይነሳልኝ በማለት የቀረበ አቤቱታው ውሳኔው/ትእዛዙ ከተሰጠ በ30 ቀን ውስጥ በቃለ መሀላ ለሬጅስትራር የቀረበ ሆኖ እያለ አቤቱታው ለችሎት የቀረበው ከ30 ቀን በኋላ መሆኑ በህግ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ /ይርጋ/ አላሟላም ሊያስብል የማይችል ስለመሆኑ፣ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 78/1/ 101478

 • 101552 Family law Divorce Indemnities upon divorce

  Family law Divorce Indeminties upon divorce Federal family code art. Art. 81(2), 84 በጋብቻ ፍቺ ጊዜ ለፍችው ምንክያት የሆነው በደል ተፈጽሞባታል ተብሎ ለአንደኛው ወገን ካሣ የሚከፈለው እንዲከፍለው ዳኝነት ሲጠይቅና ካሣውም የሚወሰነው ለፍትህ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ብቻ ስለመሆኑ፣ የተሻሻለው የፌደራል የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 81/2/፣84 101552

 • 102543 Civil procedure Civil Jurisdiction of court Validity of judgment

  Civil procedure Civil Jurisdiction of court Validity of judgment Civil procedure code art. 9 and 231(b) የአንድ ክስ ዝርዝር ይዘቱ ሳይታይ እርስቱ ብቻ ታይቶ የፍርድ ቤት የሥረ ነገር ዳኝነት የሚወሰንበት የሕግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑ ስልጣን ሳይኖር የተሰጠ ውሳኔ ስርዓቱን ጠብቆ አቤቱታ እስከቀረበበት ድረስ ሊፀና የማይገባው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 9 እና 231(ለ) 102543

 • 102725 Commercial law Rent of government houses Transfer of rent right

  Commercial law Rent of government houses Transfer of rent right of business Government rent house Directive no 4/2004   በመመሪያ ቁጥር 4/2004 መሰረት በልዩ ሁኔታ በንግድ ቤት ተጠቃሚ ለመሆን ሊሟሉ ስለሚገባቸው ሁኔዎች   102725

 • 102778 Contract law Variation of contract Form of contract Invalidation of contract

  Contract law Variation of contract Form of contract Invalidation of contract Civil code art. 1684, 1722, 1678(c) በተዋዋይ ወገኖች የነበረን ውል አንዱ ለሌላኛው የውል መለዋወጥ ጥያቄውን ማቅረቡ  በፍሬ ነገር ደረጃ ሳይረጋገጥ ውሉ ተራዝሟል ሊባል የማያስችል ስለመሆኑ፡- የውሉ አጻጻፍ ፎርም ወይም ዓይነት በሕግ የታዘዘ ሆኖ እንደ ትዕዛዙ ባይፈጸም ፈራሽነትን የሚያስከትል ስለመሆኑ፡- የፍ/ብ/ሕ/ቁጥርየፍ/ሕ/ቁ 1684፣1722፣1678(ሐ))     102778

 • 102932 Law of succession Partition of inheritance property

  Law of succession Partition of inheritance property Civil code art. 1079 (1), 1096/1/, 1092, 1093 በአንድ የጋራ የሆነ የውርስ ንብረት ላይ አንደኛው ወራሽ ብቻውን ያወጣው ወጪ ካለ ወጪውን ሁሉም ወራሾች ሊጋሩት የሚገባ ስለመሆኑ፣ የጋራ የሆነ የውርስ ንብረትን በተመለከተ ወራሾች የሚስማሙ ከሆነ ክፍያው በስምምነታቸው መሠረት የሚፈጸም ስለመሆኑ፣  ወራሾች ንብረቱን ስለሚካፈሉበት ሁኔታ ካልተስማሙና ንብረቱ በአይነት ለወራሾች ለማካፈል የማይቻል ከሆነ ንብረቱ በሀራጅ ተሸጦ ሊከፋፈሉ የሚገባ ስለመሆኑ፣ የፍ/ህ/ቁ 1079/1/፣ 1086/1/፣1092፣1093 102932

 • 102994 Labor dispute Termination of contract of employment Termination without notice Leave payment Provident payment

      Labor dispute Termination of contract of employment Termination without notice Leave payment Provident payment      አንድ አሠሪ ሠራተኛው ህጋዊ የመብት ጥያቄ በማቅረቡ ምክንያት የስራ ውሉን ማቋረጥ ህገወጥ ተግባር ስለመሆኑ  አዋጅ ቁ.377/96 አንቀፅ 26(2)(ሐ)         የሰ/መ/ቁ.102994 ሚያዝያ 30 ቀን 2007 ዓ.ም     ዳኞች-፡- አልማው ወሌ ዓሊ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- ዳሽን ባንክ አክሲዮን ማህበር - ነ/ፈጅ ሰለሞን አያኖ - ቀረቡ፡፡ ተጠሪዎች፡-  1. አቶ ተፈሪ አሳልፈው       2. አቶ አየለ ገብረሃና              3.  አቶ በኃይሉ ዓለማየሁ ጠበቃ ሳህሉ ሀብቴ ጋር - ቀረቡ፡፡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡ ፍ ር ድ ጉዳዩ የአሠሪና ሠራተኛ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረውም በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሳሾች የነበሩት የአሁኖቹ ተጠሪዎች በአሁኑ አመልካች ላይ በ07/08/2005 ዓ.ም አዘጋጅተው ባቀረቡት ክስ ነው፡፡የክሳቸውም ይዘት ባጭሩ፡-ከሳሾች በተከሳሽ ድርጅት ተቀጥረው ቄራ አካባቢ በሚገኘው መጋዘን በመስራት ላይ እያሉ ከመጋዘኑ ግቢ ያልወጣን ንብረት “ለግል ጥቅማችሁ አውላችኃል” በማለት ከ13/07/2005 ዓ.ም ጀምሮ የስራ ውላቸውን ያቋረጠ መሆኑን፣ከሳሾቹ ንብረት ከመመዝገብ በስተቀር ንብረት የመያዝም ሆነ የመጠበቅ ኃላፊነት እና የስራ ድርሻ የሌላቸው መሆኑን፣ንብረት የመጠበቅ ኃላፊነት የተሰጠው ሠራተኛ በስሩ የሚገኘውን ንብረት ለአጠባበቅ ያመቸኛል በማለት ከመደበኛ ቦታ ውጭ በማስቀመጡ ድርጅቱ እርምጃ መውሰድ የሚገባው ጥፋተኛ ሆኖ በተገኘው ሠራተኛ ላይ ብቻ ሆኖ እያለ ከሳሾቹን ጭምር በማሰናበት የወሰደው እርምጃ የአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 27 (1) (መ) እና የድርጅቱን የሕብረት ስምምነት አንቀጽ 36 (1.3) የሚቃረን መሆኑን የሚገልጽ ሆኖ የስራ ስንብት እርምጃው ሕገወጥ ነው ተብሎ ድርጅቱ ውዝፍ ደመወዝ ከፍሎ ወደስራ እንዲመልሳቸው፣ይህ የሚታለፍ ከሆነም ሕገ ወጥ...

 • 103541 Contract law Consultancy service contract Form of contract

  Contract law Consultancy service contract Form of contract Civil code art. 1719, 2612(1), 1882 ማማከር የስራ ውል ልዩ ፎርም የሚያስፈልገው ሥለመሆኑ፡- የፍ/ሕ/ቁ 1719፣2612(1)፣1882   103541

 • 103717 Commercial law Law of cooperatives Business registration and licensing

  Commercial law Law of cooperatives Business registration and licensing Cooperative proclamation no. 147/1991 and 402/96 art. 6   የህብረት ሥራ ማህበራት በመሰረታዊነት ለትርፍ ተብሎ የሚቋቋሙ ሳይሆን የአባላቱን ፍላጕት በአነስተኛ ወጪ ለሟሟላት የሚቋቋሙ በመሆኑ ለትርፍ ስራ የሚሰሩ የንግድ ስራዎች የሚያስፈልጋቸውን የንግድ ፋቃድ እንዲያወጡ የሚገደድበት አግባብ የሌለ ሥለመሆኑ የኃብረት ሥራ ማህበራት አዋጅ ቁጥር 147/1991 ማሻሻያው አዋጅ ቁ. 402/96 አንቀጽ 6   103717

 • 103775 Criminal law Sentencing Sentencing guideline

  Criminal law Sentencing Sentencing guideline በወንጀል ጉዳይ መነሻ  ቅጣቱ በቅጣት መመሪያው ውስጥ  በተለያዩ እርከኖች የሚወድቅ ሆኖ በተገኘ ጊዜ ፍ/ቤቱ ዝቅተኛውን እርከን መምረጥ ያለበት ስለመሆኑ፣ የቅጣት መመሪያ 2/2006 አንቀጽ 19/11/   103775

 • 104220 Criminal procedure Constitution Human rights Rights of persons accused Summon of accused person Right to full access to evidence

  Criminal procedure Constitution Human rights Rights of persons accused Summon of accused person Right to full access to evidence FDRE constitution art. 20(4) Criminal procedure code art. 199(a), 123, 202(3) አንድ በወንጀል የተከሰሰ ተከሳሽ መጥሪያ ባስመዘገበው የመኖሪያ አድራሻ እንደደረሰው ሳይደረግ ወይም በዚሁ አድራሻ ተፈልጎ ሊገኝ አለመቻሉ ሳይረጋገጥ መጥሪያ በጋዜጣ እንዲወጣ አድርጎ ጉዳዩን በሌለበት ማየት የስነ ስርዓት ህጉን ያልተከተለ ስለመሆኑ፣ በወንጀል ጉዳይ የተከሰሱ ሰዎች የቀረበባቸውን ማንኛውም ማስረጃ የመመልከት፣ የቀረበባቸውን ምስክሮች የመለየት፣ ለመከላከል የሚያስችላቸውን ማስረጃ የማቅረብ ወይም የማስቀረብ እንዲሁም ምስክሮቻቸው ቀርበው እንዲሰሙላቸው የመጠየቅ መብት ያላቸው ስለመሆኑ፣  የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገመንግስት አንቀፅ 20/4/  የወ/መ/ሥ/ሥነሥርዓት አንቀፅ 199 /ሀ/ ፣ 123፣202/3/፣   104220

 • 104351 Civil service dispute Unlawful termination of contract of employment Back payment of salary Amhara region civil service proclamation

  Civil service dispute Unlawful termination of contract of employment Back payment of salary Amhara region civil service proclamation no. 171/2009 አንድ የመንግስት ሠራተኛ በአሠሪው የመንግስት መ/ቤት ጥፋት በሆነ ምክንያት የስራ ውሉ ተቋርጦ ቆይቶ በኋላ በፍርድ ሠራተኛው ወደ ስራው ሲመለስ ውሉ ተቋርጦ በቆየበት ጊዜ ያለው ደሞዝ ጭምር ሊከፈለው የሚገባ ስለመሆኑ፣    የተሻሻለው የአ/ብ/ክ/መ/የመግስት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 171/2002 አንቀጽ 81/2/፣87/1   የሰ/መ/ቁ.104351  ሰኔ 9 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወሌ ዓሊ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- ወ/ት ክምክም እማኛው - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- የደቡብ አቸፈር ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ጽ/ቤት - ዐ/ሕግ ዘላለም ተስፋዬ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡ ፍ  ር  ድ ጉዳዩ የስራ ቅጥር ውሉ የተሰረዘው አላግባብ ነው ተብሎ ወደ ስራው እንዲመለስ የተወሰነ የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኛ ውዝፍ ደመወዝ ክፍያ ጥያቄን የሚመለከት ክርክር ሲሆን የጉዳዩን አመጣጥ በተመለከተ፡-አመልካች በደቡብ አቸፈር ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ10/02/2004 ዓ.ም ተቀጥረው ሲያገለግሉ ከቆዩ በኃላ በቅጥር ውድድሩ ጊዜ ያቀረቡት የስራ ልምድ ማስረጃ ለተቀጠሩበት ፕሳ-3 የስራ ደረጃ የሚጠየቀውን አግባብነት ያለው የስምንት ዓመት የስራ ልምድ መስፈርት የሚያሟላ አይደለም በሚል የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ በ04/12/2004 ዓ.ም. የአመልካችን ቅጥር መሰረዙን፣አመልካች በዚህ የስረዛ ውሳኔ ቅር ተሰኝተው ለክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ የአስተዳደር ፍርድ ቤት ያቀረቡት ይግባኝ ተቀባይነት ማጣቱን፣ ይግባኙ ቀጥሎ የቀረበለት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ቅጥሩን የሰረዘው የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ መጥሪያ ደርሶት መልስ...

 • 104465 Labor dispute Unlawful termination of contract of employment

  Labor dispute Unlawful termination of contract of employment Proclamation no 377/96 art. 4/1/, 23, 26, 30, 31, 33, 39, 40/2/, 43/4/ሀ/, 35/1/, 38 የአንድ ድርጅት ሠራተኛ ለአሰሪው የስራ መልቀቂያ  አስገብቶ የስራ መልቀቂያው በአሰሪው ምክንያት በወቅቱ ሣይሠጠው ቆይቶ ሰራተኛው የስራ ግዴታውን እየተወጣና የስራ ግንኙነታቸው በተግባር ቀጥሎ ባለበት ሁኔታ ከረጅም ጊዜ በኋላ አሰሪው ሰራተኛው ቀደም ብሎ ያስገባውን የስራ መልቀቂያ መሰረት በማድረግ የስራ ውሉን ቢያቋርጥ የስራ ውሉ የተቋረጠው በህገወጥ መንገድ ነው ሊባል የሚችል ስለመሆኑ፣    አዋጁ ቁ.377/96 አንቀፅ 4/1/፣23፣26፣30፣31፣33፣39፣40/2/፣43/4/ሀ/፣ 35/1/ለ/፣38   የሰመ/ቁ/ር 104465 መጋቢት 30 ቀን 2007 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወሌ ዓሊ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- ወ/ሪት ሸዊት ኃይሉ - VC - ስላልሰራ ማረጋገጥ አልተቻለም፡፡ ተጠሪ፡- መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራዝ - ነ/ፈጅ ደረጀ ከበደ - ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡ ፍ  ር  ድ አዋጅ ቁጥር 377/96 “ን” መሰረት አድርጎ የቀረበ የአሠሪና ሠራተኛ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች ባሁኑ ተጠሪ ላይ በደጉዓ ተምቤን ወረዳ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው፡፡ የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡- በተጠሪ ድርጅት ውስጥ በካሼር የስራ መደብ  ላይ በወር ብር 1744.00 እየከፈላቸው ከሰኔ 27 ቀን 2004 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሀምሌ 25 ቀን 2005 ድረስ ቀጥሮ ሲያሰራቸው እንደቆዩና ከህግ ውጪ የስራ ውሉ ያለማስጠንቀቂያ በአሰሪው ድርጅት የተቋረጠ መሆኑን ገልጸው የተለያዩ ክፍያዎች እንዲከፈሏቸው ይወሰን ዘንድ ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ የአሁኑ ተጠሪ ለክሱ በሰጠው...

 • 104521 Civil procedure Execution of judgment Family law partition of common property in kind Sale on public auction City master plan

  Civil procedure Execution of judgment Family law partition of common property in kind Sale on public auction Administrative law City master plan Civil procedure code art. 277(1), 325, 392 Family code of Amhara region art. 79/95 art. 73, 74, 101-103   እኩል እንከፋፈል በሚል በፍ/ቤት የፀደቀን የቦታና ቤት ስምምነት እኩል ለማካፈል የከተማ አስተዳደሩ የፕላን ስታንዳርድን አያሟላም በተባለ ጊዜ የባልና ሚስትን የጋራ ሀብት በሀራጅ ተሸጦ ይካፈሉ ብሎ መወሰን የግራ ቀኙን በቤቱ የመጠቀም ፍላጎት /ነጻነት የሚገደብ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ 277/1/,325,392 የአማ/ክልል የቤተሰብ ህግ አዋጅ 79/95 አንቀጽ 73,74 101-103   104521

 • 104862 Labor dispute Absence for 5 consecutive days Termination of contract of employment

  Labor dispute Absence for 5 consecutive days Termination of contract of employment Art. 27 of Proclamation no. 377/2004   አንድ ሰራተኛ በመደዳው ለአምስት የስራ ቀናት ካለበቂ ምክንያት ከስራ መቅረቱ የተረጋገጠ እስከሆነ ድረስ አሰሪው በዚሁ ምክንያት ሰራተኛውን ካለማስጠንቀቂያ ከስራ ያሰናበተው ስለመሆኑ በደብዳቤ ሳይገልፅ መቅረቱ የሥራ ውሉ በሕግ አግባብ አልተቋረጠም ወደሚል መደምደሚያ የሚያደርስ ስላለመሆኑ  አዋጅ ቁ.377/96 አንቀፅ 27(1) (ለ)  የሰ/መ/ቁ.104862 መጋቢት 3 ቀን 2007 ዓ. ዳኞች፡- መድሕን ኪሮስ አልማው ወሌ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመስል አመልካች፡-አቶ መልካሙ አረጋ - ቀረቡ ተጠሪ፡-ተስፋዬ ለገሠ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ - ጠበቃ ይትባረክ መኮንን ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቶአል፡፡ ፍ ር ድ ጉዳዩ የአሰሪና ሰራተኛ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረውም በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሳሽ የነበሩት የአሁኑ አመልካች በአሁኑ ተጠሪ ላይ በ09/12/2005 ዓ.ም አዘጋጅተው ባቀረቡት ክስ ነው፡፡ የክሳቸውም ይዘት ባጭሩ፡-ከሳሽ ከጥር 30 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ በወር ብር 8,076 ደመወዝ እና ብር 100 አበል እየተከፈላቸው በተከሳሽ ድርጅት ውስጥ በዶዘር ኦፕሬተርነት የስራ መደብ ተቀጥረው በመስራት ላይ እያሉ ተከሳሽ ከ01/11/2005 ዓ.ም ጀምሮ በእርሳቸው ምትክ ሌላ ሰራተኛ በመቅጠር የስራ ውላቸው በቃል ያቋረጠባቸው መሆኑን የሚገልጽ ሆኖ የስንብት እርምጃው ሕገወጥ ነው ተብሎ ሕገ ወጥ የስራ ስንብት የሚያስከትላቸውን ክፍያዎች እና ያልተጠቀሙበትን የዓመት ዕረፍት ክፍያ በድምሩ ብር 106,381.00 ተከሳሽ እንዲከፍላቸው ይወሰን ዘንድ ዳኝነት የተጠየቀበት ነው፡፡ ተከሳሽ ድርጅት በበኩሉ በ11/02/2006...

 • 104923 Criminal law Criminal procedure Fraudulent misrepresentation Constituent elements of a crime Sufficient and convincing evidence

  Criminal law Criminal procedure Fraudulent misrepresentation Constituent elements of a crime Sufficient and convincing evidence New criminal code art. 23(4), 32, 40, 57, 692(1) Criminal procedure code art. 141, 142, 149 በወንጀለኛ ህግ አንቀፅ 692(1) መሰረት የማታለል ተግባር ተፈፅሟል ለማለት መሟላት ስላለባቸው ሁኔታዎች አንድ ሰው ለወንጀል ድርጊት ኃላፊ ተብሎ ቅጣት ሊወሰንበት የሚገባው ወንጀሉ መሰራቱ ወይም መፈፀሙና ተሰራ ወይም ተፈፀመ የተባለው ወንጀል  ደግሞ በተከሳሹ መፈፀሙ በበቂና በአሳማኝ ሁኔታ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ የወንጀል ህግ አንቀፅ 23(4)፣32፣40፣57 እና 58(1) የወ/መ/ሥ/ሥ/ቁ/. 141፣142 እና 149   104923

 • 105092 Property law Rural land law Transfer of use right of rural farm land Non applicability of civil code in transfer of use right of rural farm land

  Property law Rural land law Transfer of use right of rural farm land Non applicability of civil code in transfer of use right of rural farm land Land proclamation no. 130.1999 art. 6 of Oromia regional state Federal Rural land administration proclamation no. 456/   በገጠር የእርሻ ይዞታ የመጠቀም መብትን ከባለይዞታው ጋር የስጋ ዝምድና ለሌለው ሰው ማስተላለፍ የማይቻል ስለመሆኑ የስጦታ አደራረግን አስመልክቶ በፍትሐ ብሔር የተመለከቱ ድንጋጌዎች በገጠር የእርሻ ይዞታ የመጠቀም፣የማስተላለፍ እና አስተዳደር ጋር ተያይዘው ለሚነሱ ክርክሮች ተፈፃሚነት የሌላቸው ስለመሆኑ፡- የኦሮሚያ ክልል የገጠር መሬት አስተዳደር አዋጅ ቁ. 130/1999 አንቀፅ 6 የፌድራል መንግስት የገጠር መሬት አስተዳደር አጠቃቀም አዋጅ.ቁ 456/19   105092

 • 105289 Criminal law Criminal conspiracy Aggravating circumstances Revised sentencing guideline

  Criminal law Criminal conspiracy Aggravating circumstances Revised sentencing guideline New criminal code art. 38(1) and 84(1)d አንድ ሰው የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመው ከሌላ ሰው ስምምነት በማድረግ ከሆነ እንደማክበጃ የሚወሰድ ስለመሆኑ የተሻሻለው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁ.2/2006 ከመውጣቱ በፊት በተፈፀመ ወንጀል ቅጣትን ለመወሰን ለተከሳሹ የሚጠቅመውን የቅጣት መመሪያ ተግባራዊ ማድረግ የሚገባ ስለመሆኑ ወ.ሕ/ቁ. 38(1) እና 84(1)(መ)   105289

 • 105406 Criminal law Concurrent (successive) crime Period of limitation

  Criminal law Concurrent (successive) crime Period of limitation New criminal law art. 219(2)   በተደጋጋሚ በተፈፀመ የወንጀል ድርጊት የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረው የመጨረሻው የወንጀል ድርጊት ከተፈፀመበት ቀን አንስቶ ስለመሆኑ የወንጀል ድርጊት ለረጅም ጊዜ ሲፈፀም የቆየ ከሆነ የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረው የወንጀል ድርጊቱ ካቆመበት ቀን ጀምሮ ስለመሆኑ ወንጀል ህግ ቁጥር 219(2)   105406

 • 105626 Civil procedure Death of parties to suit

  Civil procedure Death of parties to suit Art. 48, 49 and 50   የፍትሐ ብሔር ክርክር በሂደት ላይ እያለ ከሰሽ ወይም ተከሳሽ በሞት ሲለይ የክርክሩ አካሄድ በምን አኳኃን መመራት እንዳለበት ልንከተለው ስለሚገቡ ሁኔታዎች የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 48፣49 እና 50 105626

 • 105652 Donnation Undue influence invalidation Period of limitation

  Donation Undue influence invalidation Period of limitation Civil code art. 2441, 1845 በስጦታ ሰጪ ላይ በተደረገ የመንፈስ መጫን የተደረገ የስጦታ ውል ይፍረስልን ጥያቄ መቅረብ ያለበት ስጦታው በተደረገ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ስለመሆኑ አጠቃለይ የሥጦታ ውልን በመቃወም የይፍረስልን ጥያቄ መቅረብ ያለበት በአስር ዓመት ጊዜ ውስጥ ስለመሆኑ የፍ/ሕ/ቁ.2441፣በፍ/ብ/ሕግ ቁ.1845  105652

 • 105765 Contract law Legal service contract Legal service fee

  Contract law Legal service contract Legal service fee Proclamation no. 75/1994 art. 50, 51, 52 Civil procedure code art. 462 የጥብቅና ሙያ አገልግሎት ክፍያ ለመወሰን በልምድ የዳበረውና በአጠቃላይ ተቀባይነት ያገኘው የአከፋፈል መርህ ጉዳዩ የወሰደው ጊዜ፣ የሚጠይቀው ድካም፣ የጉዳዩ ውስብስብነት የክርክርን ግምት ታሳቢ በማድረግ ስለመሆኑ፣ የጥብቅና ሙያ አገልግሎት ክፍያ ያለምንም ገደብ ስምምነት የሚደረግበት አለመሆኑን ከስነ ህግ እና የፍርድቤቶች አሰራር የዳበረ ስለመሆኑ፣ የአብክመ የጥብቅና ስራ ፈቃድ አሰጣጥ ምዝገባ የጠበቆች ስነ-መግባር ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ ቁጥር 75/1994 አንቀፅ 50፣51፣52 የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 462   105765

 • 105834 Labor dispute Review of decision of discipline committee

  Labor dispute Review of decision of discipline committee Proclamation no. 377/2004 27(1)/g/ and art. 12/2/(7) በየመስሪያ ቤቱ የሚቋቋሙ የዲሲፕሊን ኮሚቴዎች በህግ አግባብ የሚቋቋሙና የሰራተኛው ጥቅም ያለአግባብ እንዳይጎዳ ተገቢው መጣራት ተደርጎ እርምጃ እንዲወሰድ እገዛ የሚያደርጉ ናቸው ተብሎ የሚታመን ስለሆነ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ውሳኔ ዋጋ ሊያጣ የሚገባው ተገቢው ማስረጃ ቀርቦ ህጋዊ ያለመሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ ስለመሆኑ፣    አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 27 ንዑስ አንቀፅ 1/ሸ/ እና አንቀፅ 12/2/(7)      ሰ/መ/ቁ. 105834   ሚያዚያ 28 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወሌ ዓሊ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ብሔራዊ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ጠበቃ እሸቴ ጓንጉል - ቀረቡ፡፡   ተጠሪ፡- ወ/ሮ እመቤት ኤርሚያስ - ቀ መዝገቡ መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡ ፍ ር ድ ጉዳዩ የቀረበው በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአመልካች የስንብት እርምጃ ሕገ ወጥ ነው ተብሎ የተሰጠው ውሳኔ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመጽናቱ በውሳኔው ላይ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት አመልካች ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው፡፡ ጉዳዩ የአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 “ን” መሰረት ያደረገ የግል የስራ ክርክር ሁኖ አንድ ሰራተኛ በስራ ላይ የዲስፕሊን ጥፋት ፈፅሟል ተብሎ ከስራ ያለማስጠንቀቂያ የሚሰናበትበትን የሕግ አግባብ የሚመለከት ነው፡፡ በስር ፍርድ ቤት የቀረበው የተጠሪ ክስ በአመልካች ማህበር ውስጥ በወር ብር 4,500.00 (አራት ሺህ አምስት መቶ) እየተከፈላቸው በሂሳብ ሰራተኝነት የስራ መደብ ከመስከረም 05 ቀን 1990 ዓ.ም ጀምሮ ሲያገለግሉ ቆይተው አመልካች ማህበር የዲስፕሊን...

 • 105869Civil procedure Preliminary objections Hearing of evidence

  Civil procedure Preliminary objections Hearing of evidence Civil procedure code art. 244(1) and 245(1)   አንድን ክርክር በመጀመሪያ ደረጃ የሚመለከት ፍርድ ቤት በቀረበለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ አግባብነት ያላቸው ምስክሮች ሳይሰሙ ወይም አግባብነት ያላቸው ሰነዶች ሳይቀርቡ በመቃወሚያው ላይ ውሳኔ መስጠት የማይቻል በሚሆን ጊዜ ፍ/ቤቱ እነዚህ ማስረጃዎች እንዲቀርቡለት ትእዛዝ መስጠት የሚችል ስለመሆኑ፡- የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 244(1) እና 245(1) 105869

 • 105921 Labor dispute Unlawful termination of contract of employment

  Labor dispute Unlawful termination of contract of employment አንድ አሠሪ ሠራተኛው ህጋዊ የመብት ጥያቄ በማቅረቡ ምክንያት የስራ ውሉን ማቋረጥ ህገወጥ ተግባር ስለመሆኑ    አዋጅ ቁ.377/96 አንቀፅ 26(2)(ሐ) የሰ/መ/ቁ. 105921  ቀን 14/07/2007 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወሌ ዓሊ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመስል አመልካች፡- ፒተርድስ ፕሮዳክስት ማንፋክቸሪንግ (አ.ማ) አልቀረቡም ተጠሪች፡- 1. ወ/ሮ ይፍቱስራ ነጋሽ   2. ወ/ሮ ገነት ወንድሙ ጠበቃ ኤሊያስ አበበ ቀረቡ ጉዳዩን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል ፍ ር ድ ጉዳዩ የቀረበው አመልካች የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው፡፡ ጉዳዩ በመጀመሪያ የታየው በፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ነው፡፡ በስር ፍርድ ቤት አንደኛ ተጠሪ አንደኛ ከሳሽ ፤ በዚህ ክርክር ተሳታፊ ያልሆነችው ወ/ሪት መድሀኒት ሙቃ ሁለተኛ ከሳሽ ሁለተኛ ተጠሪ ሶስተኛ ከሳሽ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡  የክርክሩ መነሻ ተጠሪዎች ያቀረቡት ክስ ነው፡፡ ከሳሾች ተከሳሽን ለምንድን ነው ለእኛ የቦነስ ክፍያ የማይከፈለን በማለት በእረፍት ሰዓት በመጠየቃችን ከስራ አግዶ አቆይቶ ሚያዝያ 2 ቀን 2005 ዓ/ም በተፃፈ ደብዳቤ ከህግ ውጭ ያሰናበተን ስለሆነ የካሳ ክፍያ ፣ የማሰጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ ፣ ክፍያ የዘገየበት ክፍያና ወጭና ኪሳራ እንዲከፍል ይወስንልን በማለት ክስ አቅርበዋል፡፡ አመልካች በስር ፍርድ ቤት ተከሳሽ ሆኖ ቀርቦ ከሳሾች ህገ ወጥ የስራ አድማ እንዲያደርጉ ሌሎች ሠራተኞችን በማስተባበርና በመቀሰቀስ ፤ የአድማ ስራ በመሆንና ረብሻና ሁከት የመፍጠር ሙከራ ማድረጋቸው ተረጋግጦ ከስራ የተሰናበቱ በመሆኑ ስንብቱ ህግን መሰረት ያደረገ ነው በማለት ተከራክሯል፡፡...

 • 106147 Extra contractual liability vicarious liability Employer liability

  Extra contractual law vicarious liability Employer liability Civil code art. 2027-2136   በአንድ ንዑስ የስራ ተቋራጭ ውስጥ ተቀጥሮ የሚሠራ ሰራተኛ ለሚደርስበት ጉዳት ዋናው ሥራ ተቋራጭ ከውል ውጪ በኃላፊነት የሚጠየቅበት የህግ መሠረት የሌለ ስለመሆኑ፣  የፍ/ህ./ቁ 2027-2136   106147

 • 106450 Extra contractual liability Contributory negligence

  Extra contractual law Contributory negligence Civil code art. 2098(1) ለአንድ ጉዳት ወይም አደጋ መድረስ ጉዳት የደረሰበት ሰው አስተዋፅዋኦ ካለው የጉዳት አድራሹ ኃላፊነት በከፊል ስለመሆኑ፣ የፍ/ህ/ቁ 2098/1/፣ 2097/2/፣2095   106450

 • 106610 Labor dispute Payments termination of contract of employment

  Labor dispute Payments termination of contract of employment Proclamation no 377/96 art. 27/1/b, 25   አንድ አሰሪ ሰራተኛው ያቀረበውን የስራ መልቀቂያ ጥያቄ ተቀብሎ ሰራተኛውን ካሰናበተ በኋላ የተለያዩ የክፍያ ጥያቄዎች በሰራተኛው ሲቀርብለት ወደኋላ ተመልሶ የስራ ውል ማቋረጫ ምክንያት አግኝቻለሁ በማለት ሌላ ደብዳቤ በመጻፍ ለሰራተኛው የሚገባውን ክፍያ አልፈፅምም ማለት አግባብነት የሌለው ስለመሆኑ፣  አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 27/1/ለ/፣25    ሰ/መ/ቁ 106610 ግንቦት 14 ቀን 2007 ዳኞች - አልማው ወሌ ዓሊ መሀመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- አቶ ካብራክ ተኮላ - ጠበቃ ጋር ቀረበ ተጠሪ ፡-የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርት ሎጆስቲክስ -  ነ/ፈ ቀረበ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡ ፍ ር ድ ጉዳዩ የተጀመረው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ተከሳሽ ነበሩ፡፡ አመልካች ባቀረቡት ክስ በተጠሪ ድርጅት ከታህሳስ 26/2000 - ጥር 29/2005 ዓ.ም ድረስ ለ5 አመት ከ1 ወር ስሰራ ቆይቼ ስራዬን በራሴ ፍቃድ ብለቅም፤ የስንብት፤ ለዘገየበት እና አበል አልተከፈለኝም በማለት እንዲከፈላቸው ጠይቀዋል፡፡ ተጠሪም በሰጠው መልስ አመልካች ያለደሞዝ የወሰዱት እረፍት ከተጠናቀቀ ከህዳር 17/2005 ዓ/ም ጀምሮ ወደ ሥራ ያልገቡ መሆኑን በመረዳቱ ከህዳር 17 /2005 ዓ/ም ጀምሮ ውላቸው መቋረጡን ፤ እና 5 አመት ያልሞላቸው በመሆኑ ያለማስጠንቀቂያ ስለሆነ ስንብት አይገባቸውም፤ ይገባቸዋል ከተባለም የማስጠንቀቂያ ግዜ 1 ወር ደሞዝና የቦንድ መግዣ ተቀንሶ ሊከፈላቸው ይገባል በማለት ተከራክሯል፡፡ ጉዳዩን  ያየው ፍርድ ቤትም ተጠሪ የአመልካችን የስራ መልቀቅ ጥያቄ ከ29/6/2005 ጀምሮ ከተቀበለ እና ካሰናበታቸው በኋላ የስራ ውል ማቋረጫ ምክንያት...

 • 107002 Labor dispute Internal regulation and directive of organization Vacancy promotion

  Labor dispute Internal regulation and directive of organization Vacancy promotion በአንድ አሰሪ ድርጅት መተዳደሪያ ደንብና መመሪያ መሠረት በአንድ የሥራ መደብ ላይ የውጪ ሰው የሚቀጠረው መጀመሪያ ለቦታው የሚመጥን የውስጥ ሠራተኛ ካለ ለውስጥ ሠራተኛው እድል ከሰጠ ለኋላ ከሆነ አሠሪው ድርጅት ይኽን ደንብና መመሪያ ተላልፎ የውስጥ ዕድገት ማስታወቂያ ሣያወጣና ለሠራተኞች ዕድል ሳይሰጥ የውጪ ቅጥር ቢፈጸም ድርጊቱ ህገወጥ ተግባር ስለመሆኑና ቅጥሩ ሊሠረዝ የሚገባው ስለመሆኑ፣     የሰ/መ/ቁ. 107002 ግንቦት 14 ቀን 2007ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወሌ ዓሊ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኸሊት ይመሰል አመልካች፡- ሲስተር ትዕግስት ፈቃድ - ቀረቡ  ተጠሪ፡- የኤድስ መከላከያ ማህበራዊ አገልግሎት ድርጅት አልቀረበም ፍ ር ድ ጉዳዩ የቀረበው አመልካች የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 177544 መስከረም 22 ቀን 2007 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔና የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰበር ችሎት በመዝገብ ቁጥር 197235 ህዳር 17 ቀን 2007 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት ያቀረበችውን የሰበር አቤቱታ አጣራቶ ለመወሰን ነው፡፡ ጉዳዩ የሥራ መደብ ሊሰጠኝ ይገባል በማለት የቀረበን ጥያቄ የሚመለከት ነው፡፡ ጉዳዩ በመጀመሪያ የታየው በምዕራብ ኦሮሚያ አሠሪና ሠራተኛ ወሳኝ ቦርድ ነው፡፡ በአሠሪና ሠራተኛ ውሳኝ ቦርዱ አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል ፡፡ 1-      አመልካች በተከሳሽ (ተጠሪ) ድርጅት በአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በነርስ ካውንስለር ሰባተኛ ደረጃ ተቀጥሬ በመሥራት ላይ እያለሁኝ የቤተሰብ ችግር ስላጋጠመኝ በራሴ አቤቱታ አቅራቢነት በደረጃ ሶስት የነርስ ካውንስለር የሥራ መደብ ወደ ነቀምት...

 • 107219 Criminal law Aggravating circumstances

  Criminal law Aggravating circumstances   አንድ የወንጀል ድርጊት ሊወድቅ የሚችልበት የህግ ድንጋጌ የተለያዩ የማክበጃ ነጥቦች በያዘ ጊዜ እና ተከሳሹ ጥፋተኛ በተባለበት አንቀጽ /ድንጋጌ/ ስር ያሉት ንዑስ ድንጋጌዎች የሚደነግጉት የቅጣት መጠን ተመሳሳይ በሆነ ጊዜ ፍርድ ቤቶች በዚያው የህግ ድንጋጌ ስር ድርጊቱ በይበልጥ ያሟላቸውን የማክበጃ ነጥቦች ወደ ያዘው ንዑስ ድንጋጌ መለወጥ የሚችሉ ስለመሆኑ፣     107219

 • 107442 Contract law Contract of consultancy service Discipline of advocates Legal service contract

  Contract law Legal service contract Discipline of advocates Proclamation no. 199/92 art. 30(2) Regulation no. 57/92 art. 30(2) የጥብቅና አገልግሎት የሚሠጥ ጠበቃ በደንበኛው የአገልግሎት ክፍያ ሲፈጸምለት ለተፈጸመው ክፍያ ደረሰኝ አለመስጠት የዲሲፕን ግድፈት ስለመሆኑ  አዋጅ 199/92 አንቀፅ 30/2/ ደንብ ቁጥር 57/92 አንቀፅ 8/1/   107442

 • 107840 Family law Rural land law Pecuniary effect of marriage Common property

  Family law Rural land law Pecuniary effect of marriage Common property Rural land proclamation no. 110/1999 art. 5(5) and 2(7) of southern Regional state   ባል እና ሚስቶች ሲጋቡ ለጎጆ መውጫ ተብሎ በቤተሰባቸው ፍቃድ የተሰጣቸው መሬት ሲገለገሉበት የቆዩ በሆነ ጊዜ ንብረቱ የጋራ ሀብት ሀኖ በፍቺ ጊዜ እኩል ሊካፈሉት የሚገባ ስለመሆኑ፣ የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ የመሬት አዋጅ ቁጥር 110/1999 አንቀጽ 5/5/,2/7/ 107840

 • 108106 Law of succession Rural land law Disinhersion

  Law of succession Rural land law Disinhersion Rural land proclamation no. 133/99 of Oromia region Rural land regulation no. 151/2005 of Oromia region   የውርስ የይዞታ መሬትን እኩል መብት ካላቸው ወራሾች መካከል አንደኛው አስቀድሞ ይዞ ወደ ልጁ ስም ማዞር የወራሾችን መብት መንጠቅ ስለመሆኑ፣ የኦሮሚያ የመሬት አዋጅ ቁጥር 130/99 ደንብ ቁጥር 151/2005  108106

 • 108785 Labor dispute Dependents’ benefit in case of death Period of limitation in labor dispute

  Labor dispute Dependents’ benefit in case of death Period of limitation in labor dispute Proclamation no. 377/2004 art (1)     ሰራተኛው በስራ ላይ በደረሰበት የሞት አደጋ ምክንያት የሰራተኛው ባለቤትና ሌሎች ጥገኞች የሚያቀርቡት የካሣ ክፍያ ጥያቄ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ መቅረብ ያለበት ስለመሆኑ  አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 162 ንዑስ አንቀፅ 1   የሰ/መ/ቁ 108785 ሀምሌ 21 ቀን 2ዐዐ7 ዓ.ም ዳኞች  ፡- አልማው ወሌ ዓሊ መሐመድ ተኸሊት ይመስል እንደሻው አዳነ ቀነአ ቂጣታ አመልካች ፡- ዩሴፍ ተክሌ ህንፃ ሥራ ተቋራጭ ጠበቃ ብሥራት መኮንን  ቀረቡ ተጠሪ ፡-   ወ/ሮ ወርቅነሽ ጌታቸው በራሳቸው  እና ሞግዚት በሆነችላቸው  እነ ሕፃን ረዲኤት ታምራት ከጠበቃ አቶ ፋንቱ አስፋው ጋር ቀረቡ፡፡ መዝገቡን መርምረን  የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል ፡፡ ፍርድ 1.    ጉዳዩ የቀረበው አመልካች የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሠጠው ውሣኔ መሠረታዊ  የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው፡፡ ጉዳዩ በሥራ ላይ በሚደርስ ጉዳት ለሚስትና በሌሎች ጥገኞች የሚከፈል የካሣ ገንዘብ ጥያቄ የይርጋ የጊዜ ገደብ የሚመለከት ነው ተጠሪ ባለቤቷ የሁለት ልጆች አባት የሆነው ታምራት ሀይሌ አሠሪው በመደበው መኪና ከሌሎች ሠራተኞች ጋር ሲጓጓዝ መኪናው ተገልብጦ ሚያዝያ 23 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም ህይወቱ ያለመሆኑን ገልፆ በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሠረት ለእርሷና ለህፃናቱ ካሣ እንዲከፈላቸው ውሣኔ እንዲሰጥላት ጥር 25 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም ጠይቃለች ፡፡ 2.    አመልካች በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 162 ንሁስ አንቀፅ 4 የተደነገገው የስድስት ወር የይርጋ የጊዜ ገደብ አልፏል በማለት መቃወሚያ አቅርቧል ፡፡ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች ያቀረበውን መቃወሚያ በመቀበል ክሱ በይርጋ ቀሪ ይሆናል በማለት ብይን ሰጥቷል ፡፡ ተጠሪ ይግባኝ...

 • 108933 Labor dispute Termination of contract of employment without notice Failure to discharge duties based job specification

  Labor dispute Termination of contract of employment without notice Failure to discharge duties based job specification Proclamation no. 377/2004 Art. 13(2) እና (7)     አንድ ሰራተኛ በስራ መዘርዝሩ በግልጽ የተሰጠውን /የተቀመጠለትን/ ግዴታዎቹን አለመወጣቱ የስራ ውሉን ያለማስጠንቀቂያ ሊያቋርጥ የሚችል ስለመሆኑ፡-  አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 13(2) እና (7)   የሰ/መ/ቁ 108933 ሐምሌ 30 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወሌ ዓሊ መሐመድ ተኽሊት ይመሰል እንዳሻው አዳነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- ሠላም ቦሌ ሸማቾች ኃ.የተ.የህብረት ስራ ማህበር - የቀረበ የለም ከተባለ በኃላ ጠበቃ መለሰ ግርማይ - ቀረቡ ተጠሪ፡-  አቶ እሸቱ አደፍርስ  - ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡ ፍ  ር  ድ ጉዳዩ የግል ስራ ክርክር ሲሆን የተጀመረውም ተጠሪ በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአመልካች ላይ ሰኔ 02 ቀን 2006 ዓ/ም ባቀረቡት ክስ መነሻ ነው፡፡ የክሱም ይዘት ባጭሩ፡-ተጠሪ በአመልካች ድርጅት ውስጥ ከ7/00/2003 ዓ/ም ጀምሮ በጉልበት ሰራተኝት የስራ መደብ ተቀጥረው በወር ብር 770.00 እየተከፈላቸው በመስራት ላይ እንዳሉ የአሁኑ አመልካች ከስራ መደባቸው ውጪ የሆነ ስራ ተጠሪ እንዲሰሩ በማድረጉ ተጠሪ የአመልካችን ትዕዛዝ ከስራ መዘርዝራቸው ውጪ ነው በሚል በመቃወማቸው ምክንያት ከስራ ያሰናበታቸው መሆኑን ዘርዝረው ስንብቱ ሕገ ወጥ ነው ተብሎ የተለያዩ ክፍያዎች እንዲከፈሏቸው ይወሰን ዘንድ ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ የአሁኑ አመልካቸ ለክሱ በሰጠው መልስም ተጠሪ የታዘዙት ከስራ መደባቸው ጋር ተያያዥነት ያለውንና በስራ መዘርዝሩ በተጠቀሰው አግባብ መሆኑን እንዲሁም በተደጋጋሚ በቅርብ አለቃቸው ሲታዘዙ ትዕዛዙን የማይቀበሉ መሆኑን ጠቅሶ ስንብቱ...

 • 109055 Labor dispute Cost of litigation Civil procedure code

  Labor dispute Cost of litigation Civil procedure code art. 463, 464(1) Proclamation no. 377/2004 art. 161  አንድ ሰራተኛ ለአሠሪው በሥራ ክርክር ምክንያት ያወጣውን ወጭና ኪሳራ የመክፈል ግዴታ የሚጣልበት በክርክሩ ተረች በመሆኑ ምክንያት ብቻ ሳይሆን ሠራተኛው በአሠሪው ላይ ያቀረበው ክስ ሀሰተኛና በተጭበረበረ ማስረጃ ላይ የተመሰረተ ሆኖ ሲገኝ ብቻ ስለመሆኑ  የፍትሐ ብሔር ሥነ ስርዓት ህግ ቁጥር 463 ፣465 (1) አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 161    የሰ/መ/ቁ.109055 ሐምሌ 29 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወሌ ዓሊ መሀመድ ተኽሊት ይመሰል አዳነ እንደሻው ቀነአ ቂጤታ አመልካች ፡- አቶ ጌትነት ከበደ - ቀረቡ   ተጠሪዎች ፡-  ሃያት ሜድካል ከሌጅ  አልቀረቡም፡፡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡ ፍ  ር  ድ 1.    ጉዳዩ የቀረበው የአመልካች የጠበቃ አበልና ወጭና ኪሳራ ብር 6000/ስድስት ሺ ብር/እንዲከፍል የተሰጠው ውሳኔ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ አጣርቶ ለመወሰን ነው፡፡ ጉዳዩን እንደመረመርነው አመልካች የስራ ውሉ ከህግ አግባብ ውጭ ተቋርጧል የሚል ክስ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቅርቦ፣ተጠሪ የአመልካች የስራ ውል የተቋረጠው የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ በሚደነግገው መሰረት መሆኑን ገልጾ በመከራከሩ፣ የስር ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ ተጠሪ የአመልካችን የስራ ውል ያቋረጠው በህግ አግባብ ነው በማለት አመልካች /ከሳሽ/ ለተጠሪ ለተከሳሽ የጠበቃ አበል ብር 5000 / አምስት ሺ ብር/ እና ኪሳራ ብር 1000 /አንድ ሺ ብር/ በድምሩ ብር 6000 /ስድስት ሺ ብር/ ይክፈል ማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ 2.    አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ ይግባኝ አቅርቧል፡፡ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሽ...

 • 109697 Law of succession Rural land law Rural land proclamation no. 133/98 of Amhara region

  Law of succession Rural land law Rural land proclamation no. 133/98 of Amhara region Rural land regulation no.51/99 art. 11(7)a of Amhara region ለክርክር ምክንያት በሆነው መሬት ወራሽ መሆኑን በማስረጃ ያረጋገጠ ሰው ከአውራሹ ተነጥሎ ለጊዜው ውጭ ሀገር ሄዶ መመለሱ በሕጉ “ለቤተሰብ አባል” የተቀመጠውን ትርጉም አላሟላም በሚል በቤተሰብ አባልነት መሬቱን ሊወርስ አይገባም ማለት ተገቢነት የሌለው ስለመሆኑ፣ የአ/ብ/ክ/መ አዋጅ ቁጥር 133/98 ፣ደንብ ቁጥር 51/99 አንቀጽ 11/7/ሀ/ 109697

 • 109731 Family law Divorce Divorce based on mutual agreement Power of court

  Family law Divorce Divorce based on mutual agreement Power of court Federal family code art. 76(1) አንድ ጋብቻ በተጋቢዎቹ ስምምነት ፈርሶአል ሊባል የሚችለው የፍቺ ስምምነቱ ተደርጎአል በተባለበት ቀን ሳይሆን የፍቺ ስምምነቱ ለፍርድ ቤት ቀርቦ ተቀባይነት ባገኘበት እና በጸደቀበት ጊዜ ስለመሆኑ፡- የተሸሻለው የፌድራል የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀፅ 76(1) 109731

 • 109776 Property law Rural land law Inheritance of rural land use right Conditions for inheriting rural land use right

  Property law Rural land law Inheritance of rural land use right Conditions for inheriting rural land use right Proclamation no. 456/97 art 2(5) Land proclamation no. 130/99 art. 2(13) and 16 of Oromia region የገጠር መሬት ወራሽነትን በሚመለከት በአንድ ወቅት በቤተሰብ አባልት መመዝገብ ብቻውን የሟችን የእርሻ መሬት በቀዳሚነት የመውረስ መብትን የማያጎናጽፍ ስለመሆኑ በውርስ ለማግኘት ወራሹ አርሶ አድርና ከእርሻ መሬቱ ከሚገኘው ገቢ የሚተዳደር የቤተሰብ አባል መሆን ያለበት ስለመሆኑ፣ አዋጅ 456/97 አንቀፅ 2 ንዑስ አንቀፅ 5  የኦሮሚያ የመሬት አዋጁ 130/99 አንቀፅ 2 ንዑስ አንቀፅ 13 እና 16/   109776

 • 109829 Property law Rural land law Donation of use right of rural land Registration of donation of use right of rural land

  Property law Rural land law Donation of use right of rural land Registration of donation of use right of rural land Land proclamation no. 130.1999 of Oromia regional state ከቤተሰባዊ ቅርርብ የተነሳ ውለታ ላደረገ ሰው አንደኛው ወገን ካለው መሬት ውርስ ቆርሶ በስጦታ መልክ እንዲጠቀም ሰጥቶት በሁለቱ መካከል አለመግባባት ቢፈጠር በሥጦታ ተቀባዩ ወገን በመሬቱ የመብት ክርክር ቢያነሳ የመሬት ይዞታ ስጦታው ሊፀና የሚችለው የክልል የመሬት አዋጅ በሚፈቅደው መሠረት ሥልጣን ባለው አካል ዘንድ ቀርቦ የስጦታ ውሉ መመዝገቡ ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡ /የኦሮሚያ ክልል የመሬት አዋጅ ቁጥር 130/99   109829

 • 110022 Law of succession Certificate of inheritance Liquidation of succession

  Law of succession Certificate of inheritance Liquidation of succession Civil code art. 996(1) ፍ/ቤቶች የወራሽነት ማስረጃ ወይም የምስክር ወረቀት ብቻ አንዲሰጡ ማመልከቻ ሲቀርብላቸው ውርስ እንዲጣራ የሚሰጡት ትእዛዝ የማይገባና አላስፈላጊ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሕ/ 996/1/ 110022

 • 110969 Criminal procedure Bail Appeal by prosecutor

  Criminal procedure Bail Appeal by prosecutor Criminal procedure code art. 75(1)   የወንጀለኛ ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 75 (1) ዋስትናን በመፍቀድ በሚሰጥ ትዕዛዝ ላይ ዐቃቤ ሕግ ይግባኝ እንዳያቀርብ ሕጉ ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ ከልክሏል በሚል አግባብ መተርጎም የሌለበት ስለመሆኑ ዋስትናን በመፍቀድ በተሰጠ ትዕዛዝ ላይ ከሳሽ /ዐቃቤ ህግ/ ይግባኝ የማቅረብ መብት ያለው ስለመሆኑ   110969

 • 111006 Criminal law Sentencing guideline Admission of guilt Extenuating circumstance

  Criminal law Sentencing guideline Admission of guilt Extenuating circumstance New criminal code art. 106(1) and 109(1) ደረጃ እና እርከን ላልወጣላቸው ወንጀሎች ቅጣት ስሌት ሲሠራ በወንጀል ህጉ ጠቅላላ ክፍል ስር ያሉት አንቀጽ 106/1/ እና 109/1/ ድንጋጌዎች ከግንዛቤ ውስጥ መግባት ያለባቸው ስለመሆኑ፣ አንድ በወንጀል ተከሶ ጥፋተኛ የተባለ ሰው ወንጀሉን ስለመፈጸሙ ሙሉ በሙሉ ባላመነበት ሁኔታ በከፊል ማመኑ ብቻ ራሱን ችሎ እንደ አንድ የቅጣት ማቅለያ ሊወሰድለት የማይችል ስለመሆኑ፣ የወ/ህ/ቁ 82/ ሠ   111006

 • 111599 Civil procedure Pleading Denial to be specific damage

  Civil procedure Pleading Denial to be specific damage   በካሳ ጉዳይ ካሳ የጠየቀው ወገን ገንዘቡን በማስረጃ ባላረጋገጠበት ሁኔታ ሌላኛው ተከሳሽ ወገን ዝም በማለቱ ብቻ እንዳመነ ተቆጥሮ የሚሰጥ ውሣኔ ተገቢ ያለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 83 111599

 • 111742 Criminal procedure Plea of guilt Cautionary Procedure to followed by court in case of plea of guilt

  Criminal procedure Plea of guilt Cautionary Procedure to followed by court in case of plea of guilt Criminal procedure code art. 132(1) and (3) ፍርድ ቤቶች በተከሳሽ ላይ በዕምነት ክህደት ላይ በመመስረት የጥፋተኝነት ውሳኔን ከመወሰናቸው በፊት ቃሉ ከወንጀሉ ዝርዝር እና ከተከሰሱበት የህግ ድንጋጌዎች አነጋገር አንጻር ወንጀሉን ማድረጉን ሙሉ በሙሉ አምኗል የሚያስብል እና ቃሉ የእምነት ክህደትን ቃል የሚያቀቋቁም መሆኑን ማረጋገጥ የሚገባቸው ስለመሆኑ፣ የወ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ. 132/1/ እና /3/   111742

 • 111839 Labor dispute Termination of contract of employment without notice Negligence

  Labor dispute Termination of contract of employment without notice Negligence Proclamation no. 377/96 አንቀፅ 13/3/፣27/1/g/  አንድ በሹፌርነት የተቀጠረ ሠራተኛ አሰሪው ጋር በተያያዘ ሁኔታ ጥንቃቄ ማድረግ ከሚገባው ነገር አንዱ መኪናውን የሚያሽከረክርበት አግባብ ከአካባቢው አየር ሁኔታና ከመልከዓ ምድሩ ጋር ባገናዘበ መልኩ መሆን ያለበት ስለመሆኑና ይህንን ሳያደርግ ቀርቶ አደጋና ጉዳት ቢደርስ ከባድ ቸልተኝነት እንዳደረሰ ተቆጥሮ የስራ ውሉ ያለማስጠንቀቂያ ሊቋረጥ የሚችል ስለመሆኑ፣   አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 13/3/፣27/1/ሸ/    የሰ/መ/ቁ. 111839 ግንቦት 28 ቀን 2ዐዐ7 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወሌ ዓሊ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- ፒ.ኤስ አይ ኢትዩጵያ - ጠበቃ አላምነህ ስንሻው ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ እሸቱ ካሳ - የቀረበ የለም፡፡  መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡ ፍ ር ድ ጉዳዩ የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅን መሠረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ሐምሌ  24 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም በተፃፈ ክስ በአመልካች ድርጅት በሹፌርነት ተቀጥረው እየሠሩ ባለበት ሁኔታ ያላግባብ ከስራ መሰናበታቸውን ገልፀው ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሏቸው ወደ ስራ እንዲመለሱ ይወሰንላቸው ዘንድ ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ የአሁኑ አመልካችም በተከሣሽነቱ ቀርቦ በሰጠው መልስ ተጠሪ የድርጅቱን መኪና ባግባቡ የመንዳት ኃላፊነታቸውን ባለመወጣት ግንቦት 05 ቀን 2006 ዓ.ም ሰው ገጭቶ ጉዳት ማድረሱንና ከዚህ በኋላም ሰኔ 08 ቀን 2006 ዓ/ም ከደሴ ወደ መቐሌ በሚሄድበት ጊዜ በግድየለሽነት በማሸከርከር በመኪናው ላይ ጉዳት ከማድረሱም በላይ በተሽከርካሪው ውስጥ በነበሩት የድርጅቱ ሰራተኞች ላይ ቀላል የመቁሰል አደጋ ማድረሱንና ይህም በክፍሉ የትራፊክ ፖሊስ መረጋገጡንና አመልካችም ተገቢውን ኮሚቴ አቋቁሞ በማጣራት...

 • 112032 Custom Duties law Constitution Criminal law Retro-activity of law

  Custom Duties law Constitution Criminal law Retro-activity of law Custom duties proclamation no. 22(2) New criminal code art 6 FDRE constitution art. 22(2) አንድ ተከሻሽ የጉሙሩክ አዋጅን በመተላለፍ በፈፀመው ድርጊት ጥፋቱ የመጨረሻ ውሳኔ አስከላገኘ ድረስ  ሥራ ላይ ከነበረው የጉሙሩክ አዋጅ ይልቅ አዲሱ የጉሙሩክ አዋጅ ለተከሳሽ ቅጣትን የሚያቀል በሚሆን ጊዜ ፍርድ ቤቱ ለተከሳሹ  የተሻለው ህግ ተፈፃሚ እንዲሆን ማድረግ ያለበት ስለመሆኑ የኢፌድሬ ህገመንግስት  አንቀጽ 22 /2/ ፣የወ/ህ/ቁ/ 6  የጉሙሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2001፣ አዲሱ የጉሙሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2007    112032

 • 112091 Electoral law Law of political parties Candidates of political parties

  Electoral law Law of political parties Candidates of political parties Proclamation no. 532/1999 art. 46(4)b Proclamation no. 632/2002 art. 7 አንድ የፖለቲካ ድርጅት የሌላ የፖለቲካ ድርጅት አባል የሆኑ ሰዎችን አባልነታቸው ህጋዊ በሆነ መልኩ ሳይቋረጥ ወይም ቀሪ ሳይሆን እጩ ተወዳዳሪ አድርጎ ማቅረብ የማይችል ስለመሆኑ፣ አንድ ሰው በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ የሁለት የፖለቲካ ድርጅት አባል መሆን የማይችል ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 532/199 አንቀፅ 46፣102/4//ለ/፣አዋጅ ቁጥር 632/2002 አንቀፅ 7   112091

 • 35946 Civil procedure Third party intervention Effect of hearing of witnesses before third party intervention

  Civil procedure Third party intervention  Effect of hearing of witnesses before third party intervention በክርክር ሂደት ተቃዋሚ ወገን መጠራት ያለበት ምስክር ከመሰማቱ በፊት  ስለመሆኑ 35946

 • 36848 civil procedure. Decision be based on Fact and law

  civil procedure Decision be based on Fact and law ማንኛውም ክርክር ሊወሰን የሚገባው በቀረበው  ማስረጃ እና በህጉ መሰረት ብቻ ስለመሆኑ   36848

 • 82725 Contract law Agency Conflict of interest Period of limitation

  Contract law Agency Conflict of interest Period of limitation Civil code art. 2187 ተወካይ የጥቅም ግጭት ባለበት አኳኋዋን የፈጸመውን ተግባር ለማፍረስ ወካዬ ይኸው ድርጊት መፈጸሙን ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ በሚታሰብ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ አቤቱታውን ማቅረብ ያለበት ስለመሆኑ፣ የፍ/ሕ/ቁ 2187   82725

 • 90529 Law of unlawful enrichment Gain from the work or property of another

  Law of unlawful enrichment Gain from the work or property of another Civil code art. 2162   በሌላ ሰው የስራ ድካም ወይም የሌላ ሰው ሃብት በሆነ ነገር በመገልገል በቂ ባልሆነ ምክንያት ጥቅም ያገኘ ሰው አለአግባብ ጥቅም ባገኘበት መጠን ለባለሃብቱ ወይም ጉልበቱ ለደከመው ሰው ይህ አድራጎት ባደረሰበት ጉዳት መጠን ኪሳራ መክፈል የሚገባው ስለመሆኑ የፍ/ሕ/ቁ.2162   90529

 • 94481 Commercial law Partnership Written agreement of partnership Sharing of profit and loss from real activities

  Commercial law Partnership Written agreement of partnership Sharing of profit and loss from real activities Commercial code art. 211, 229, 269(1) የሽርክና ማህበር በህግ አግባብ ተቋቁሞ እየሠራነው ለማለት በጽሁፍ ውል መደረጉ እንደተጠበቀ ሆኖ በተግባራዊ እንቅስቃሴ ተዋዋይ ወገኖች በጋራና በተናጥል በመተባበር በመስራት ከጥቅሙም ይሁን ከእዳው በጋራ ሲጋሩ እንደነበር መረጋገጥ ያለበት ሥለመሆኑ፣ አንድ የሽርክና ማህበር በህጉ አግባብ ተቋቁመ ለማለት የሚቻለው ተዋዋይ ወገኖች ተነጻጻሪ ሣይሆን ተደጋጋፊ የሆነ ግብ ይዘው መዋጮ በማውጣት አብረው በመስራትና በመተባበር ትርፍና ኪሣራም በህጉ አግባብ እየተጋሩ ኢኮኖሚያዊ  ተግባር ማከናወናቸው ሲረጋገጥ ብቻ ስለመሆኑ፣ የንግድ ህግ ቁጥር 211፣229፣269/1/   94481

 • 94811 Family law Pecuniary effect of marriage Common property

  Family law Pecuniary effect of marriage Common property ጋብቻ ፀንቶ በነበረበት ጊዜ ባንደኛው ተጋቢ ተገዝቶ ነገር ግን ስመሀብቱ ከ3ኛ ወገን ሻጭ ሳይዛወር የቀረ መሆኑ ንብረቱ የተጋቢዎች የጋራ ሀብትነው ከመባል የሚያስቀረው ስላልመሆኑ፣ 94811

 • 95157 Tax law Tax evasion Tax evasion whistle blower reward

  Tax law Tax evasion Tax evasion whistle blower reward Proclamation no. 286/94 art. 84(1)   ገቢውን በሚደብቅ ፣አሳንሶ በሚያሳውቅ፣ በሚያጭበረብር ወይም በማናቸውም መንገድ ግብር ሳይከፍል በሚቀር ግብር ከፋይ ላይ በተጨባጭ መረጃ በመደገፍ ሪፖርት ያቀረበ ሰው ከተደበቀው ግብር እስከ 20% ድረስ ግብሩ ሲሰበሰብ ማግኘት የሚገባው ስለመሆኑ፡- አዋጅ ቁ. 286/94 አንቀፅ 84(1) 95157    

 • 95921 Criminal procedure Constitution Human right Right of persons accused Right to full access to evidence

  Criminal procedure Constitution Human right Right of persons accused Right to full access to evidence FDRE constitution art. 20(4), 9(4), 13(1) (2) International convention on Civil and political rights art art. 14(3)b    

 • 96588 Civil procedure Execution of judgment Sale by public auction Rights of buyer on public sale

  Civil procedure Execution of judgment Sale by public auction Rights of buyer on public sale Civil procedure code art. 429, 441 and 447 በሃራጅ ጨረታ ያሸነፈ አንድ አካል ያሸነፈውን ንብረት በስሙ ካዘወረና ካስተላለፈ በኋላ የሃራጅ ሽያጩ ሙሉ በሙሉ ከተፈፀመለት በኋላ፣ ንብረቱ በሃራጅ ከተሸጠበት ዋጋ ላይ እንዲቀነስለት የሚያቀርበው ጥያቄ ተገቢነት የሌለው ስለመሆኑ፡- የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.429፣441 እና 447   96588

 • 96814 Civil procedure Execution of judgment Power of execution bench

  Civil procedure Execution of judgment Power of execution bench Civil procedure code art. 372, 378 የአፈፃፀም ችሎቶች ስለፍርድ አፈፃፀም የተዘረጉትን ሥርዓቶች በመከተል እንደ ፍርዱ ከመፈፀም በቀር የአንድ ፍርድ ይዘትን በመመልከት የፍርዱን ይዘት አድማስ በማጥበብም ሆነ በማስፋት ረገድ ፍርድን የመተርጎም ሥልጣን የሌላቸው ሥለመሆኑ፡- የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 372፣378   96814

 • 96853 Family law Irregular union Condition for existence of irregular union

  Family law Irregular union Condition for existence of irregular union Federal Family Code art. 97, 98, 99 and 106(2) ጋብቻ ሳይኖር እንደባልና ሚስት ለሚኖሩ ሰዎች የሚፈለገው ማስረጃ ወንዱና ሴትየዋ የተጋቡ ሰዎችን ሁኔታ ሲያሳዩና ቤተዘመዶቻቸውና ማህበረሠቡ እንደተጋቢ ሰዎች የሚኖሩ ናቸው ብለው የሚገምቷቸው መሆን ያለባቸው ስለመሆኑ፣  በአንድ ወንድና ሴት መካከል ለተወሰነ ጊዜ የፍቅር ግንኙነት መኖሩ ብቻ እንደባልና ሚስት የሚኖሩ ናቸው ሊያስብል የማይችል ስለመሆኑ ፣ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀፅ 97፣98፣99 እና 106/2/ 96853

 • 96943 Civil procedure Intervention by third party Interest of third party in the dispute

  Civil procedure Intervention by third party Interest of third party in the dispute አንድ ተከራካሪ ወገን ሌላ ተከራካሪ ግለሰብ ወደ ክርክር እንዲገባ በህጉ አግባብ መጠየቁ ተገቢ ቢሆንም ጉዳዩ መታየት ያለበት ከግለሰቡ መብት አንፃር ብቻ ሳይሆን ከፍትሐ ብሔር ሥነ- ሥርዓት ህጉ ዓላማና ግብ አንፃር ጭምር ስለመሆኑ፣ 96943

 • 96990 Commercial law Partnership Conditions for existence of partnership

  Commercial law Partnership Conditions for existence of partnership Commercial code art. 5, 10(1), 210(1), 211 and 229(2) ሽርክና ውል ስምምነት አለ ለማለት መሟላት ሥለሚገባቸው መስፈርቶች የንግድ ህግ 5፣10(1)፣210(1)፣211፣215 እና 229(2) 96990

 • 97009 Constitution Jurisdiction of courts Power of courts Justiceable matters Religious institutions

  Constitution Jurisdiction of courts Power of courts Justiceable matters Religious institutions FDRE constitution art. 11 and 37 የአንድ የእምነት ተቋም አስተዳደራዊ ስራዎችን ለማከናወን የተሰጠ ሹመትና የሽረት ጉዳይ ከሀይማኖት ተቋሙ መሰረታዊና ተፈጥሯዊ ባህሪ ተነጥለው ለብቻቸው ሊታዩና ሊወሰኑ የማይችሉ በመሆናቸው በፍርድ ሊወሰኑ የማይገባቸው ስለመሆኑ፣ የኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገመንግስት አንቀፅ 11 እና 37   97009

 • 97021 Contract law Contract of arbitration

  Contract law Contract of arbitration Civil code art. 2325, 3326-3346 ተዋዋይ ወገኖች በመካከላቸው የሚፈጠርን አለመግባባት በዘመድ ዳኛ የመጨረስ ስምምነት ማድረግ የሚችሉ ስለመሆኑ፡- የዘመድ ዳኛ አለመግባባቶችን አይቶ የመወሰን ስልጣን የሚመነጨው ተገልጋዮቹ በግልፅ እና በማያሻማ ሁኔታ በሚሰጡት ሥምምነት ላይ ብቻ ስለመሆኑ፡- የፍ/ሕ/ቁ 3325፣3326-3346   97021

 • 97083 Civil procedure Jurisdiction of court Jurisdiction of Federal courts

  Civil procedure constitution Jurisdiction of court Jurisdiction of Federal courts Proclamation no. 696/2002 art. 6(2) (2) (4) Proclamation no. 25/88 5(2) FDRE constitution art. 80(2) አንድ በፌደራል መንግስት የተመዘገበ የንግድ ድርጅት በክልል ቅርንጫፍ ከፍቶ የንግድ ሥራ መሰራቱና ቅርንጫፍ በክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ፅ/ቤት መመዝገቡ በፌደራል መንግስት የተቋቋመ የንግድ ድርጅት በመሆኑ ላይ የሚያሳድረው ለውጥ የሌለ ሥለመሆኑና ድርጅቱ ተካፋይ የሆነበትንም ክርክር በዳኝነት አይቶ ለመወሰን ሥልጣኑ የፌደራል ፍርድ ቤቶች ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 686/2002 አንቀፅ 6/2/ /3/ /4/ ፣ አንቀፅ 5/2/ አዋጅ ቁጥር 25/1988/6/ የኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገ መንግሥት አንቀፅ 80/2/ /4/   97083

 • 97291 Criminal law Sentencing Sentencing shall be according to law

  Criminal law Sentencing Sentencing shall be according to law   አንድ ፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ ከተሰጠበት የህግ ድንጋጌ ስር ከተቀመጠው የቅጣት አማራጭ ውጪ የሚሰጠው የቅጣት ውሳኔ የሕግ መሰረት የሌለው ስለመሆኑ፣   97291

 • 97829 Property law Administrative law Urban land lease law Addis Ababa city Administration Period of grace for construction

  Property law Administrative law Urban land lease law Addis Ababa city Administration Period of grace for construction Urban land lease regulation no. 48/2004 art. 11(1) Urban land lease directive no. 11/2004 art. 14(3), 37(6)b, 38(8) ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቦታ በሊዝ ለገዛ ሰው ቦታውን ለግንባታ ምቹ አድርጎ ማስረከብ ያለበት ስለመሆኑና በወቅቱ ካላስረከበ ካስረከበበት ጊዜ ጀምሮ የሁለት አመት የችሮታ ጊዜ ለገዥው ሊሰጠው የሚገባ ስለመሆኑ፣ መመሪያ ቁጥር 11/2004 አንቀፅ 14/3/ ፣ 37/6/ለ/ ፣ 38/8/ ደንብ ቁጥር 48/2004 አንቀፅ 11/1/ ፣ አንቀፅ 12/2/   97829

 • 98029 Family law Contract of marriage Interpretation of contract of marriage

  Family law Contract of marriage Interpretation of contract of marriage አንድ ወንድና ሴት ሲጋቡ በጋብቻ ውላቸው ንብረትን በተመለከተ ካደረጉት ስምምነት ላይ “ከወለደች የግል የለባትም” ፣ “ ሀብትሽ ሀብቴ ነው “ ተብሎ የተፈጸመው የውል ሀረግ ካለና ልጅ ከወለዱ ከጋብቻ በፊት የነበራቸውን የግል ንብረት የጋራ ለማድረግ እንደተስማሙ የሚቆጠር ስለመሆኑ፣ 98029

 • 98347 Civil procedure Execution of judgment Validity of judgment

  Civil procedure Execution of judgment Power of execution bench Validity of judgment until changed by appeal or otherwise   ለአፈፃፀም መነሻ የሆነን ፍርድ ይግባኝ  በመጠየቅ ሳያሽሩ ወይም ሳያሻሽሉ በዋናው ጉዳይ ሊነሱ የሚገባቸውን የክርክር ነጥቦች በአፈፃፀም በተያዘው መዝገብ የክርክር መሰረት ማድረግ ተገቢ ስላለመሆኑ   98347

 • 98593 Civil procedure code Costs of litigation Appeal

  Civil procedure code Costs of litigation Appeal Cvil procedure codea art. 466 በወጪና ኪሳራ ጉዳይ በተሰጠ ውሳኔ ላይ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁ. 466 98593

 • 99071 Property law Administrative law Power of court Title deed of immovable property

  Property law Administrative law Power of court Title deed of immovable property Civil code art. 1196 FDRE constitution art. 32 ፍርድ ቤቶች በአስተዳደር ክፍል የተሰጠ የቤት ካርታ የተሰጠበት ወይም የተሻረበት ስርዓት እና አስተዳደራዊ ውሳኔው ህግና መመሪያ ያገናዘበ መሆን አለመሆኑን በማጣራት ውሳኔ የመስጠት ሥልጣን ያላቸው ስለመሆኑ፣ የፍ/ህ/ቁ 1196፣የ.ኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 32   99071

 • 99634 Contract law Contract of sale Invalidation of contract Reinstatement Unlawful enrichment

  Contract law Contract of sale Invalidation of contract Reinstatement Unlawful enrichment Civil code art. 1818 Civil procedure code art. 392(2) አንድ የሽያጭ ውል በፍርድ ፈራሽ ነው ተብሎ ተዋዋዮች ወደነበሩበት እንዲመለሱ ከተወሰነ ንብረት የመመለስ ግዴታ ያለበት ሰው ንብረቱን ለውጦ ወይም በዚህ ላይ ወጪ አውጥቶ ከሆነ ከዚህ መለዋወጥ ወይም ወጪ የተነሳ ያለውን መብት በተመለከተ አለአግባብ መበልጸግ በሚለው የህጉ ክፍል መሠረት የመጠየቅ መብት ያለው ስለመሆኑ፣ የፍ/ህ/ቁ 1818፣የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 392/1/   99634

 • 99642 Civil procedure Attachment before judgment Temporary Injunction Security

  Civil procedure Attachment before judgement Temporary Injunction Security Civil procedure code art. 151   ለክርክሩ መነሻ የሆኑ እና በተከሳሽ እጅ የሚገኙ ንብረቶች እንዳይሸጡ፣ እንዳይለወጡና በማንኛውም መንገድ ለ3ኛ ወገን እንዳይተላለፍ በታገዱበት ሁኔታና ተከሳሽ በንብረቶች ላይ ጉዳት እንደሚያደርስ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ተከሳሽን ተጨማሪ ዋስ አቅርብ ማለት አግባብነት የሌለውና የስነ ርዓት ህጉን ዓላማ ያላገናዘበ ስለመሆኑ፣  ፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 151  99642

 • 99954 Family code Filiation Paternal filiation Contestation of filiation

  Family code Filiation Paternal filiation Contestation of filiation Federal family code art. 167 Civil code art. 682, 741 አንድ ልጅ ሲወለድ ከልጇ እናት ጋር በጋብቻ ተሳስሮ የነበረው ሠው በህጉ ግምት መሠረት የልጁ አባት ስለመሆኑና ይህን የህጉን ግምት ማስተባበል የሚችለው እሡ ወይም በህግ የተፈቀደላቸው ሰዎች አባት አለመሆኑ እንዲወሰን የመካድ ክስ በማቅረብ ስለመሆኑ፣ የፍ/ህ/ቁ. 682፣741፣ የፌደራል የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 167 99954

 • 105997 Labor dispute Transfer of employees Collective agreement

  Labor dispute Transfer of employees Collective agreement  አንድ ሠራተኛ መብትና ጥቅሙን ሳይነካ ከአንድ የሥራ ቦታ ወደ ሌላ የሥራ ቦታ ወይም የስራ መደብ በማዛወር ማሠራት የአሰሪው አስተዳደራዊ ሥልጣን ነው ሲባል ዝውውሩ ያለህጋዊ ምክንያትና በህብረት ስምምነቱ ከሠፈረው አሰራር ውጪ ይከናወናል ተብሎ ሊተረጎም የማይገባው ስለመሆኑ፣  የሰ/መ/ቁ 105997 ሚያዚያ 26 ቀን 2ዐዐ7 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወሌ ዓሊ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡- ወ/ሪት ሉሊት አያሌው ማሞ - ቀረቡ  ተጠሪ፡-  የኢትዩጵያ መድን ድርጅት - ነ/ፈጅ ማህሌት ዓለሙ - ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡ ፍርድ ጉዳዩ ከሰራተኛ የስራ መደብና ቦታ ዝውውር ጋር ተያይዞ የተነሳውን ክርክር የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች ባሁኑ ተጠሪ ላይ በፌዴራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው፡፡ የአመልካች የክስ ይዘትም፡- የተጠሪ ድርጅት አመልካች የኢንዲስትሪ ሰላም አላግባብ ንትርክ እየፈጠሩ መረባሻቸውን ሳያረጋግጥ በ26/08/2005 ዓ/ም በፃፈው የአመልካችን የግል ታሪክ በሚያጎድፍ ደብዳቤ ከኦዲት ወደ ማርኬቲንግ ክፍል ያላግባብ በማዘዋወር እርምጃ መውሰዱን ጠቅሰው የተወሰደው እርምጃ እንዲነሳና ወደ ኦዲት ክፍል እንዲመለሱ እንዲሁም የዝውውሩ ደብዳቤ እንዲሰረዝላቸው ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡  የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስም፡- አመልካች ከኦዲት ሰራተኞች ጋር ባላቸው አለመግባባት የተነሳ የኢንዲስትሪ እና የስራ ቦታ ሰላም ለመጠበቅ ሲባል የአመልካች የስራ ደረጃ እና ደመወዝ ሳይነካ ዝውውሩ መፈፀሙንና ክሱ ከተመሰረተ በኋላም የአመልካችን ደመወዝ ብር 10,759.00 ማድረጉን ገልፆ ክሱ ውድቅ ሊሆን ይገባል በማለት ተከራክሯል፡፡ ጉዳዩ በዚህ መልክ የቀረበለት...

 • 110615 labor law dispute/ termination of contract of employment/ brawl at work place

  Labor dispute Termination of contract of employment without notice Brawl at work place Proclamation no 377/2004 art. 32/1/a, 13/2/ and 27   የሰ/መ/ቁ. 110615 ግንቦት 28 ቀን 2007 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወሌ ዓሊ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኸሊት ይመስል አመልካች፡- ኃብተሚካኤል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማሕበር -    ሥራ አስኪያጅ አቶ ተካልኝ ሁንዴ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ታመነ ታደሰ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል ፍ ር ድ ጉዳዩ የቀረበው አመልካች የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 22279 ሐምሌ 10 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔና የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት በመዝገብ ቁጥር 187457 የካቲት 9 ቀን 2007 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ሥህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው፡፡ጉዳዩ በመጀመሪያ የታየው የሰበታ ሀዋሳ ወረዳ ፍርድ ቤት ነው፡፡ በወረዳው ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሕግ አግባብ ውጭ የሥራ ውሌ ተቋርጧል በማለት ከሳሽ ተጠሪ ተከሳሽ አመልካች ሆነው ተከራክረዋል፡፡ 1.   ከሳሽ (ተጠሪ) ከተከሳሽ (አመልካች )ድርጅት ጋር በሠራተኝነት ተቀጥሮ ሲሰራ ተከሳሽ ከሕግ አግባብ ውጭ የሥራ ውሉን ያቋረጠው መሆኑን ገልፆ በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ መሠረት የተለያዩ ክፍያዎችን ተከሳሽ እንዲከፍል ይወሰንልኝ በማለት ክስ አቅርቧል፡፡አመልካች በተከሳሽነት ቀርቦ ከሳሽ በጥቅምት 2 ቀን 2006 ዓ.ም አደም ገረመው ከሚባል ሠራተኛ ጋር በመደባደብ በሥራ ቦታ ሁከት የፈጠረ መሆኑንና ህዳር 25 ቀን 2006 ዓ.ም የድርጅቱን ሥራ አስኪያጅ አልታዘዝም ከማለቱም በላይ “ዝም በል አንተ አሽሻም...

 • 33945 civil procedure Judgment on only requested remedy

  civil procedure Judgment on remedy civil procedure code art. 182(2) ዳኝነት ባልተጠየቀበት ጉዳይ የሚሰጥ ፍርድ አግባብነት የሌለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 182(2)  33945

 • labor law dispute/ termination of contract of employment 108789

  Labor dispute Termination of contract of employment without notice Execution of instruction of employer Proclamation no. 377/2004 Art. 13/1/2/ and /7/ and 27/1/ g/     የሰ/መ/ቁ.108789  ሚያዝያ 13 ቀን 2007 ዓ. ዳኞች-፡-አልማው ወሌ ዓሊ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽሊት ይመሰል አመልካች፡-ሴንቸሪ ጄኔራል ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር - ጠበቃ አሰፋ ዓሊ ቀረቡ ተጠሪ፡-አቶ ገስጥ ንጉሴ - ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቶአል፡፡ ፍ ር ድ ጉዳዩ የአሰሪና ሰራተኛ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረውም በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሳሽ የነበሩት የአሁኑ ተጠሪ በአሁኑ አመልካች ላይ በ11/09/2006 ዓ.ም አዘጋጅተው ባቀረቡት ክስ ነው፡፡ የክሳቸውም ይዘት ባጭሩ፡-ከሳሽ ከ09/03/2006 ዓ.ም ጀምሮ በአሽከርካሪነት የስራ መደብ ላይ በወር ያልተጣራ ብር 1,900 (አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ) ደመወዝ እየተከፈላቸው በተከሳሽ ድርጅት ውስጥ በመስራት ላይ እያሉ ተከሳሽ ድርጅት ካለአንዳች ምክንያት በ19/07/2006 ዓ.ም ከስራ ካገዳቸው በኃላ በ24/08/2006 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ ከስራ ያሰናበታቸው መሆኑን የሚገልጽ ሆኖ የስራ ስንብት እርምጃው ሕገወጥ ነው ተብሎ ሕገ ወጥ የስራ ስንብት የሚያስከትላቸውን እና ተዛማጅ ክፍያዎችን በድምሩ ብር 21,850 (ሃያ አንድ ሺህ ስምንት መቶ ሃምሳ) ድርጅቱ እንዲከፍላቸው ይወሰን ዘንድ ዳኝነት የተጠየቀበት ነው፡፡ ተከሳሽ ድርጅት በበኩሉ በ26/09/2006 ዓ.ም. በሰጠው መልስ የከሳሽ የስራ ውል እንዲቋረጥ የተደረገው ከሳሽ ስራቸውን ለመስራት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው፣አሮጌ ተሽከርካሪ አላሽከረክርም በማለታቸው፣ከድርጅቱ ሰራተኞች ጋር ለመስራት ባለመቻላቸው፣በዚህም ምክንያት የድርጅቱ ሰራተኞች በከሳሽ...