ስለ ስራ ክርክር- የስራ ክርክር ችሎቶች ሰልጣን - የAሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ስልጣን /የሰራተኞች ቅነሳ ጉዳይ በሚመለከት የሚነሳ የስራ ክርክር ለማየት/ -የAሰሪና ሰራተኛ Aዋጅ ቁ.42/85 Aንቀጽ 138/1/፣ 147
1. የAሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ የመዳኘት ስልጣን የተሰጠው የወል የስራ ክርክር ጉዳዮችን የሚመለከቱ ክርክሮችን ሲሆን የስራ ክርክር ችሎቶች ደግሞ የግል የስራ ክርክሮችን Eንዲዳኙ ስልጣን ተሰጥቷቸዋል፡፡
2. ህጉ የስራ ክርክር ጉዳዮችን የወል ወይም የግል ብሎ ለመለየት የተከራካሪ ሰራተኞችን ቁጥር Eንደ መስፈርት መውሰድ Eንዳለበት Aያመላክትም፡፡
3. ከAጠቃላይ የህጉ መንፈስ Eና ድንጋጌዎች በመነሳት Aንድ የስራ ክርክር ጉዳይ የወል ነው የሚባለው ጉዳዩ በጋራ የሆነ የሠራተኞች መብትና ጥቅም ላይ Aሉታዊ ሆነ Aዎንታዊ ውጤት የሚያስከትል ሆኖ ሲገኝ ብቻ ሲሆን Aንድን የስራ ክርክር ጉዳይ የግል የሥራ ክርክር ጉዳይ የሚያደርገው ደግሞ ጉዳዩ ከግል Aልፎ በጋራ መብት ላይ የሚያመጣው ለውጥ የሌለ Eንደሆነ ነው፡፡
4. የሰራተኛ ቅነሳ ጉዳይ የጋራ በሆነ የሰራተኞች መብትና ጥቅም ላይ Aሉታዊ ተጽEኖ ያለው በመሆኑ የወል የስራ ክርክር ጉዳይ ነው፡፡ ጉዳዩን የማየት ስልጣንም የAሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ነው፡፡
5. የAሰሪና ሰራተኛ ፍ/ቤት ቦርዱ የህግ ስህተት ፈጽሟል ብሎ ሲያምን ጉዳዩን ከመመሪያ ጋር ወደ ቦርዱ ከመመለስ Aልፎ የቦርዱ ውሳኔ መሻር Aይችልም፡፡
'