የሕግ ክርክሮችን በሰበር ማየት /ማስተናገድ/ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግስት ለፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የተሰጠ ስልጣን (power) ስለመሆኑ በግልግል ዳኝነት (arbitration) የታየ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ተዋዋይ ወገኖች የይግባኝ መብትን ለማስቀረት የሚያደርጉት ስምምነት ጉዳዩን በሰበር ችሎት ከመታየት የማያግድ ስለመሆኑ (ከዚሀ ቀደም በሰበር ችሎት የተሰጠው የሕግ ትርጉም የተለወጠ ስለመሆኑ፡፡) የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 80/3 (ሀ), አዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2 (4), አዋጅ ቁጥር 25/88, የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 350(2) 351 እና 356