111216 law of succession/ liquidation of succession/ funeral expenses

የሟች ንብረት (የውርስ ሃብት) ወደ ወራሾች የሚተላለፈው በመጀመሪያ የሟች እዳ ከተከፈለ ብቻ ስለመሆኑ፤- ሟች ከሞተ በኋላ ለቀብር ማስፈፀሚያ የሚወጡ ወጪዎች ከውርሱ ክፍፍል በፊት መከፈል ያለባቸው ስለመሆኑ፡- የፍ/ሕ/ቁ.1014

 

የሰ/መ/ቁ.111216 ቀን የከቲት 15/2008 ዓ/ም

ዳኞች፡-አልማው ወሌ

 

ዓሊ መሀመድ

 

ተኽሊት ይመሰል

 

እንደሻው አዳነ ቀነዓ ቂጣታ

 

አመልካች፡- ወ/ሮ ኤልሳቤት አህመድ ተወካይ ፀሃይነሽ አህመድ ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ማፈኛ አባዩ ቀረቡ

መዝገቡ መርምረን ተከታዩን ፈርድ ሰጥተናል፡፡

 

 ፍ ር ድ

 

በዚህ ጉዳይ አከራከሪ የሆነው ጭብጥ የውርስ እና የሚስት ግማሽ ድርሻ ንብረት ክፍፍል ከመደረጉ በፊት ሟች ከተቀበሩበት ቀን ጀምሮ እስከ 80 ቀን ድረስ ያለውን ውጪ በእኩል ለመካፈል የተደረገው ስምምነት መሠሰረት ተደርጎ የስር ፍርድ ቤቶች የአሁኗ አመልከች የብር 153,040.00 ግማሽ ይክፈሉ በማለት የሰጡት ትእዛዝ በህጉ አግባብ ነው ወይስ አይደለም? የሚል ነው፡፡

 

አመልካች ውሉን እንዳልተስማሙበት የተከራከሩ ቢሆንም የስር ፍርድ ቤት የቀረበው ውል ሪፖርት እንደተቀበለ፤ በቀረበው ውል መሠረት ሟቹ ከተቀበሩበት ቀን ጀምሮ እስከ 80 ድረስ ያለው ወጪ ብር 153,540.00 እንደሆነ፤ በፍ/ህ/ቁ. 1014 መሠረት ወጪ ከውርስ ንብረት ክፍፍል በፊት የሚከፈል ስለመሆኑ በደንገጉን የግራ ቀኙ የውል ስምምነትም በዋናው መዝገብ ቁጥር 08093 ላይ ውሳኔ የተሰጠበት እንደሆነ ቤቶቹ የሚከፋፈሉት ከማንኛውም እዳ ነፃ ከሆኑ በኃላ ስለ ሚል፤ ወጪውም ሁለቱም ተከራከሪ ወገኖች እንደሚመለከት፤ የአፈፃፀም ከሳሽ (አመልካች) የወጪውን ግማሽ ብር 76,520.00 ከፍለው እንዲሁም እንደውላቸው የሴንተናል ሆቴል ቤት ግምት አንድ መቶ ሺህ ብር ከፍለው የቤት ቁጥር 1345 የሆነውን እንዲራከቡ ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡


አመልካች የዲጋ ወረዳ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 08412 በ21/08/2006 ዓ/ም የሰጠው ትዕዛዝ በመቃወም ሰምስረቅ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረቡት ይግባኝ ከተመረመረ በኃላ በአመልካች በኩል እዳው ከሆቴሉ ገቢ ተከፍሏል የሚል ክርክር እንደቀረበ ይሁንና ለክርክሩ መነሻ የሆነውን እዳ ብር 153,040.00 ከሆቴል ገቢ መከፈሉን እንዳልተረጋገጠ፣ ግራ ቀኙ ባደረጉት የውል ስምምነትም አውራሹ ከሞቱ በኃላ ከሞቱበት ቀን ጀምሮ እስከ 80 ቀናት ድረስ የወጣው ውጪ ሊካፈሉ መስማማታቸው እንደሚያሳይ በመግለጽ የስር ፍርድ ቤት ትዕዛዝ አጽንቷል፡፡

 

የአሁኗ አመልካች በዚህ ትዕዛዝ ቅር በመሰኘት ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረቡኩት አቤቱታ ውድቅ ተደርጓአል፡፡ የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንን ውሳኔ

/ትእዛዝ/ በመቃወም ለማስለወጥ ነው፡፡

 

የአመልካች አቤቱታ ተመርመሮ በሰበር እንዲታይ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሑፍ ክርክር ተለዋውጠዋል፡፡ አመልካች በሰበር አቤቱታቸው ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ዕዳ ከሟ የጋራ ሀብት የተከፈለ ወይም ሊከፈል የሚገባው በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች ብር 76,520.00 እንዲከፍሉ መወሰናቸው በአግባቡ አይደለም የሚል ክርክር ሲያቀረቡ፤ ተጠሪ በሰጡት መልስ ግራ ቀኙ ባደረጉት ስምምነት የሟች ዕዳዎች ተለይተው አመልካችም በግልጽ የተስማሙበት ስለመሆኑ፣ ወጪ የተደረገውም ለቀብር ብቻ ሳይሆን ሟች በህይወት በነበሩበት ጊዜ የነበረባቸው የብድር ዕዳዎች የሚመለከት በአመልከችም የታመነ ነው የስር ፍ/ቤት ትዕዛዝ የሚነቀፍ አይደለም የሚል ይዘት ያለው ክርክር አቅርበዋል፡፡ የመልስ መልስም ቀርቦ ከመዝገቡ ጋር ተያይዟል፡፡

 

የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም ጉዳዩን መርምረናል፡፡ እንደመረመርነውም የዚህ ችሎት ዕልበት የሚያስፈለገው ጭብጥ የስር ፍርድ ቤቶች አመልካች እና ተጠሪ ሟች ከተቀበሩበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 80 ቀን ተደረጉ የተባሉትን ወጪዎች እኩል ይክፈሉ በማለት ትዕዛዝ የመስጠታቸው አግባብነት በግራ ቀኙ ያደረጉት ስምምነት መሠረት ያደረገ ነው ወይስ አይደለም? የሚል ሁኖ አግኝተነዋል፡፡

 

ከስር ፍ/ቤት መዝገብ መረዳት የተቻለው ሟች ከተቀመሩበት ቀን ጀምሮ እስከ 80 ቀን ድረስ ያለውን ወጪ ብር 153,040 መሆኑን በ15/08/2004 ዓ/ም በተጻፈው ውል ቃለ ጉባኤ እንደተገለጸ፣ የህም ሁለቱን ወገኖች የሚመለከት ስለመሆኑ ነው፡፡ አመልካች ዕዳው ለሴንትራል ሆቴል ገቢ የተከፈለ ነው የሚል ክርክር ቢያቀርቡም የስር ፍ/ቤት በፍሬ ነገር ደረጃ በደረገው ማጣራት ዕዳው ከሆቴሉ ገቢ ስለ መከፈሉ የሚያረጋግጥ ነገር አለመቅረቡን በትዕዛዙ አስፍሯል፡፡ አመልካች እና ተጠሪ ሚያዝያ 15 ቀን 2008 ዓ/ም በሽማግሌዎች ፊት የፈረሙት ውል ላይ እንደተመለከተው የሟች ዕዳ ከግብአት ቀብር እስከ 80 ቀን በአጠቃላይ የሚመለከት እንዲሆነ፤ ሟች ከግለሰቦች የወሰዱት ዕዳም እንደሚያከቲት እና አጠቃላይ ወጪው 153,040.00 /አንድ


መቶ ሀምሳ ሦስት ከአርባ ብር/ እደሆነ ተገልጸዋል፡፡ ከዚህ መረዳት የሚቻለው የአሁኑ አመልካች እንዲጋሩት የተጠየቁት ዕዳ ለቀብር ስነ ስርዓት ማስፈጸሚያ የወጣውን ወጪ ብቻ ይሆን የሟች ዕዳዎች የሚያጠቃልል ስለመሆኑን ነው፡፡ የስር ፍርድ ቤት በውሳኔው /ትዕዛዙ/ እንደገለጸው በአመልካች እና ተጠሪ የተፈረመው ውል በመዝገብ ቁጥር 08093 ውሳኔ የተሰጠበት ለፍርድ አፈፃፀም መነሻ እንደሆነ ነው፡፡ አመልካች ከተጠሪ ጋር ውል አለማደረጋቸውን በህግ የተደገፈ ክርክር አላቀረቡም፡፡ ይህ ከሆነ ግራ ቀኙ ባደረጉት ግልጽ ስምምነት የውርስ ሀብት ክፍፍል ከመደረጉ በፊት የሟች ዕዳዎች ቅድሚያ እንደሚከፈሉ የተስማሙ መሆኑን መስራት በማድረግ የስር ፍርድ ቤቶች አመልካች ግማሹን ዕዳ አንዲከፍሉ መወሰናቸው በህጉ አግባብ ነው ከሚበል በቀር በጉዳዩ መሰረታዊ የህግ ስህተት በፈጸማቸውን አያሰይም፡፡

 

ሲጠቃለል አመልካች ከአውራሻቸው ያገኙት ሀብት ወደ ስማቸው ሊተላለፍ የሚችለው በቅድሚያ የሟች ዕዳ የሆነውን ግማሹ ማለትም 153,040.00 ሲካፈል ለሁለት 76,520.00 የመክፈል ግዴታቸው ከተወጡ በኃላ ነው፡፡ የስር ፍርድ ቤቶችም አመልካች ከተጠሪ ጋሪ በገቡት ውል መሠረት የሟች ዕዳ መሆኑን የተረጋገጠው ግማሹን ይክፈሉ በማለት መወሰናቸው በህጉ አግባብ ነው ብለናል፡፡ በዚህም ተከታዩን ወስነናል፡፡

 

 ው ሳ ኔ

 

1. የዲጋ ወረዳ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 08412 በ29/08/2006 ዓ/ም የሰጠው ትዕዛዝ የምስራቅ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 34524 በ10/11/2006 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ፤ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 186415 በ18/5/2007 ዓ/ም የሰጠው ትዕዛዝ ጸንቷል፡፡

2. አመልካች የሟች ዕዳ መሆኑን በገቡት ውል መሰረት ያረጋገጡት የብር 153,040.00 ግማሹን 76,520 /ሰባ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ሀያ/ እንዲከፍሉ መወሰኑ በህጉ አግባብ ነው ብለናል፡፡

3.  ወጪና ኪሳራ ይቻቻሉ መዝገቡ ተዘጋ ወደ መ/ቤት ተመለሰ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

 

ሩ/ለ