104061 contract/ suretyship/ validity of surety contract

አንድ የዋስትና ውል ዋሱ ግዴታ የገባበትን ኃላፊነት መጠን ወይም ልኩ ምንያህል እንደሆነ በዋስትና ውሉ ላይ በገንዘብ ካልተገለፀ በስተቀር ዋስትናው ፈራሽ ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ህ/ቁ-1922(3)

የሰ/መ/ቁ.104061

 

መስከረም 25ቀን 2008ዓ᎐ም

 

ዳኞች:-አልማዉ ወሌ

 

ረታ ቶሎሣ ሙስጠፋ አህመድ ቀነዓ ቂጣታ

ሌሊሴ ደሣለኝ

 

አመልካቾች፦ አቶ ፍቅሬ ግርማ ቀረቡ ተጠሪ፦    አቶ ደስታ ጫምሶ አልቀረቡም

መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።

 

 ፍ ር ድ

 

ጉዳዩ ከዋስትና ውል ጋር ተያይዞ የቀረበ ክርክርን የሚመለከት ሆኖ ክርክሩም የጀመረው ያአሁኑ አመልካች በኦሮሚያ ክልል አርሲ ነገሌ ወረዳ ፍ/ቤት የሰበር ክርክሩ ተከፋይ ያልሆነው አቶ አበበ ኤርጊቾ እና ሰበር ተጠሪ ላይ በመሠረተው ክስ መነሻነት ነው።የክሱ ፍሬ ነገርም ባጭሩ፦ግምቱ 20,000 ብር የሆነውን የኢጣሊያን ስሪት እህል ሚዛን 1ኛተከሳሽ በ 24/2/2001 ዓም በተደረገ ኪራይ ውል ወስዶ በኋላ ላይ እንዲመልስ ሲጠየቅ ለመመለስ ፊቃደኛ አልሆነም፣2ኛ ተከሳሽም በበኩሉ ሚዛኑን ለመመለስ ወይም መተካት የዋስትና ግዴታ ገብቷል፣ስለዚህ ተከሳሾቹ ተጠይቀው ሚዛኑን የማይመልሱ ከሆነ በገቡት ግዴታ መሠረት ግምቱን ይክፈሉኝ በሚል ዳኝነት የተጠየቀበት መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን 1ኛ ተከሳሽን በተመለከተ ክሱ ስነ-ስርዓቱን ጠብቆና ተሟልቶ አልቀረበም በሚል ምክንያት ተከሳሹ በወረዳ ፍ/ቤቱ ከክሱ ወጭ መደረጉን ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለ ሲሆን 2ኛ ተከሳሽ ግን ቀርቦ ለክሱ በሰጠው መልስ የገባው የዋስትና ግዴታ የሌለ መሆኑን፣የዋስትና ውል ነውተብሎ በቀረበው ሰነድ ላይ ያለውም ፊርማ የራሱ ያለመሆኑንና የዋስትና ውሉም ራሱ ለምን ያህል ገንዘብ ግዴታ እንደተገባ ስለማያሳይ በፍ/ብ/ህ/ቁ-1922(3) መሠረት ውሉ ፎርማሊቲን አያሟላም ተብሎ ክሱ ውድቅ እንዲደረግ በማለት ተከራክሯል።


ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ወረዳ ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና በዋስትና  ውሉ ላይ የተጠቀሱትን ምስክሮች ቃል ሰምቶ ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ ተጠሪ የዋስትና ዉሉን መፈረሙ በምስክሮች ቃል መረጋገጡን መገንዘቡን ካሰፈረ በኋላ ተጠሪ በዉሉ የተጠቀሰውን ሚዛን አይነት አዲስ ለአመልካች ይተካ ሲል ወስኗል። ባአሁኑ ተጠሪ የይግባኝ ቅሬታ መነሻነት ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው የምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍ/ ቤት በበኩሉ ግራ ቀኙን አስቀርቦ ካከራከረ በኋላ በዋስትና ውሉ ላይ ያለው ፊርማ የተጠሪ መሆን ያለመሆኑን ለማጣራት ሲባል ፊርማው በፎረንሲክ ተመርምሮ ውጤቱ እንዲቀርብ የሚል ትዕዛዝ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም የዋስትና ውሉ ፎቶ ኮፒ በመሆኑ ምርመራውን በዚህ ምክንያት ማካሄድ አልተቻለም የሚል ምላሽ ከተሰጠው በኋላ ጉዳዩን ባለበት ሁኔታ መርምሮ የስር ፍ/ቤቱን ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ- 348(1) መሠረት መልሶ አፅንቶታል። ተጠሪ አሁንም በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት የሰበር አቤቱታውን ለክልሉ ሰበር ችሎት አቅርቦና ችሎቱም በበኩሉ ግራ ቀኙ ቀርበው እንዲከራከሩ ካደረገ በኋላ ጉዳዩን መርምሮ የዋስትና ውሉ ዋሱ (ተጠሪ) ለምን ያህል ገንዘብ ግዴታ እንደገባ የማይገልፅ መሆኑን ጠቅሶና እንዲህ ከሆነ ደግሞ ውሉ በፍ/ብ/ህ/ቁ-1922(3) ስር የተመለከተውን የህግ መስፈርት ስለማያሟላ በዋሱ ላይ ግዴታ ሊጥል አይችልም በማለት የስር ፍ/ቤቶችን ውሳኔ ሽሯል።

 

አመልካችም ይሄንኑ በክልሉ ስበር ሰሚ ችሎት የተሰጠውን ውሳኔ በመቃወም የሰበር አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን መሠረታዊ ይዘቱም ባጭሩ፣ለዋስትና ውሉ መነሻ የሆነው ግዴታ ዓይነትም የእቃ ኪራይ እንጅ ብድር ውልን የሚመለከት ካለመሆኑ በላይ ተጠሪም እራሱ በዋስትና ውሉ መሠረት የገባው ግዴታ በፍ/ብ/ህ/ቁ-2727 እና 2738 ስር እንደተመለከተው ሚዛኑን እራሱን በአይነት ለመተካት ወይም ለመመለስ ከመሆኑ አንፃር በውሉ ላይ የገንዘብ መጠን መጥቀስ የግድ አይደለም የሚል ይዘት ያለው ሲሆን አቤቱታውም ተመርምሮ ወደ ሰበር  ሰሚ ችሎት በመመራቱ ተጠሪም ቀርቦ ግራ ቀኙ በፅሑፍ እንዲከራከሩ ተደርጓል።

 

የጉዳዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተውን የሚመስል ሲሆን እኛም በበኩላችን በክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ ላይ መሠረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት መሆን ያለመሆኑን በጭብጥነት ይዘን ጉዳዩን መርምረናል። መዝገቡን እንደመረመርነውም ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ሚዛን ከአመልካች የተከራየሁ ግለሰብ (ዋና ባለእዳ) በውሉ መሠረት መልሶ ለአመልካች አለማስረከቡ ክርክር የቀረበበት ጉዳይ አይደለም።ተጠሪም በበኩሉ በዋስትና ውሉ ላይ ተመሳሳዩን ሚዛን በዓይነት ለመተካት በሚል የዋስትና ግዴታ እንደገባ ተደርጎ በውሉ ላይ መስፈሩን የክርክሩ ሂደት ያሳያል።ሆኖም ግን የዋስትና ውሉ አፃፃፍ ወይም ይዘት ምንም ይሁን ምን ዋሱ ግዴታ የገባበትን የኅላፊነት መጠን ወይም ልኩ ምን ያህል እንደሆነ በዋስትና ውሉ ላይ በገንዘብ ካልተገለፀ በስተቀር ዋስትናው ፈራሽ እንደሚሆን ከፍ/ብ/ህ/ቁ-1922(3) ድንጋጌ ይዘት መገንዘብ   ይቻላል።


በተያዘው ጉዳይም ተጠሪ ተመሳሳዩን ሚዛን በዓይነት ለመተካት በሚል የዋስትና ውሉን የፈረመ ቢሆንም የግዴታው መጠን ግን እስከ ምን ያህል እንደሆነ በገንዘብ ተገልፆ በውሉ ላይ አልተመለከተም። ይህ የዋስትና ግዴታ አድማስ ደግሞ ለምን ያህል እንደሆነ በውሉ ላይ በገንዘብ ካልተገለፀ የዋስትና ውሉ ዋጋ ስለማይኖረው ወይም ፈራሽ ስለሚሆን አመልካች የገንዘቡ መጠን መገለፅ የግድ አይደለም በማለት ያቀረበው ክርክር የህግ መሠረት ስለሌለው አልተቀበልነውም።

 

በሌላ   ትና   መሠ ሆነ   ራይን   ግዴታ ይሁን ወም ሌላ ው ቁም ነገበዚህ ጉራ ቀን እያከራከረ ያው ግዴታ (ኪራ) ራሱ ሳይሆን የእሱ ተቀፅላ (accessory) የሆነው የዋስትና ውል ኖ የቀረው ጉይ የትና ሉ ከነ ደግሞ በተግባት ያው የህጉ   ///-  1920  ዎች   እንጂ   ሰበር አዉ የ ///2727 2738 ዩ አባብ። ሲል የክሰበሚ ችበግኙ መል የተመው የትና ዩ አግብነት ያን የ///-1922(3) ድጋጌን መስርት ማያሟላና ነ ተሪ ላይ ግዴታ ሊጥል ይችም በኃላፊፃ በማድግ መወሰኑ ህጉን በትክሠረት ያደረው ከሚል በተቀር ሌላ ል የሚቻል ኑ ተከን ወ

 

 ው ሳ ኔ

 

1. የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት በመቁ-175321 በ 23/10/2006 ዓ᎐ም የሰጠዉ ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ-348(1) መሠረት ፀንቷል።

2.  የአመልካች ሰበር አቤቱታ ተቀባይነት የለውም ብለናል።

3. የሰበር ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል። መዝገቡ ተዘግቷል፣ወደ መ/ቤት ይመለስ።


 

ወ/ከ


የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡