በሌላ አገር ህግ እና በኢትዮጵያ የቤተሰብ ህግ መካከል እንደባልና ሚስት አብረው በመኖር ግንኙነት ውስጥ የተፈራ ንብረት የጋራ እንዲሆን ለመወሰን በሁለቱም ህጎች መካከል ግጭት መኖር ያለመኖሩን የሌላኛው አገር ህግ እንዲቀርብ በማድረግ መወሰን የሚገባው ስለመሆኑ በዓለም አቀፍ የግለሰብ ህግ /Private International law/ መሠረት በዘርፉ እውቀት ያለ ወይም ምሁር /Scholar/ የሰጠውን አስተያየት በማስረጃነት ሲቀርብ የቀረበውን አስተያየት እንደማንኛውም ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን አስተያየቱ የቀረበለት ፍርድ ቤት ስለመሆኑ የኢ.ፊ.ድ.ሪ ቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 5፤102 /1/