169077 contract law-rent-non performance-damage calculation

አንድ ውል እንደ ውሉ ባለመፈፀሙ ለደረሰ ጉዳት ኪሳራ የመክፈል ኃላፊነት ያለበት ተዋዋይ ወገን ሊከፍል የሚገባውን የኪሳራ መጠን ለመወሰን በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው የውል ዓይነት፣የነበራቸውን ግንኙነት እንዲሁም ቀድሞ የሚታወቁ ሁኔታዎች ሁሉ ግምት ውስጥ ሊገቡ የሚገባቸው ስለመሆኑ

አንድ የኪራይ ውል እንደ ውሉ ባለመፈፀሙ ምክንያት የደረሰ ኪሳራ የሚቆረጠው በኪራይ ውል ስሌት ተመን መሰረት ሲሆን የኪራዩን ገንዘብ ልክ ለመወሰን አግባብነት የሚኖረው ማስረጃ የማዘጋጃ ቤት ባለስልጣናት የሚወሰኑት ታሪፍ በመሆኑ ለተመሳሳይ ቤት የሚታወቅ ታሪፍ ቢኖር በመጠየቅ እንዲሁም ታሪፍ ከሌለ የቦታዎቹን ልማድ በመከተል ሊወሰን የሚገባ ስለመሆኑ

በፍ/ብ/ህ/ቁ 1771፣1799፣1801፣2950(2)