አንድ ሰው በፈጸመው ወንጀል ምክንያት በማረሚያ ቤት በመሆኑ በሕፃናት ልጆቹ ላይ የሚደርሰውን ቁሳዊም ሆነ ኅሊናዊ ጫና ለማስቀረት ሲባል እንዲሁም ሕጻናቱ የወላጆቻቸውን እንክብካቤ እና ድጋፍ አግኝተው እንዲያድጉ ለማድረግ ሲባል፤ ፍ/ቤቶችም የሕጻናት ደኅንነት በቅድሚያ የማረጋገጥ ሕገመንግስታዊ ግዴታ ያለባቸው በመሆኑ በወንጀለኛው ላይ የተወሰነውን ቅጣት በመገደብ ህፃናቱ ተገቢውን የወላጅ እንክብካቤ እንዲያገኙ ለማድረግ ያስችል ዘንድ በወንጀል ህጉ ቅጣት ለማገድ የተቀመጡትን ሁኔታዎች በማረጋገጥ የተወሰነውን ቅጣት እንዳይፈጸም ማገድ የሚገባ ስለመሆኑ
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገመንግሥት አንቀጽ 36/2፤የወንጀል ህግ አንቀጽ 192፣194፤የዓለም አቀፉ የህፃናት መብቶ፤ች ስምምነት የጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ ቁጥር 44/25 እንደ ኤሮፓውያን አቆጣጠር 1989 የወጣው አንቀጽ 7 (1)፤ የህፃናት መብቶች ኮንቬንሽን አንቀጽ 18